የተማሪዎች መወያያ

Description
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

7 месяцев назад
«ዳሩ ካልተከበረ መሃሉ ዳር ይሆናል!» ይላሉ …

«ዳሩ ካልተከበረ መሃሉ ዳር ይሆናል!» ይላሉ አበው።
ባለፈ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ስለ ኒቃብ ወቅቱን፣ ቦታውንና ተጨባጩን ያላገናዘበ ለጠላት ዱላ የሚያቀብል አክሳሪ ንግግር ሲናገር የጮኽነው ለዚህ ነበር።
አንዳንድ ጭፍን ተከታዮቹ ግን ጥፋቱን አምነው እንዲያርም ከማድረግ ይልቅ ጉዳዩን ወደ መንሃጅና ብሔር እየወሸቁ አለባብሰውት አለፉ፤ እርሱም ነፍስያው አሸንፋው ተገቢውን እርምት ሳይሰጥ አለፈ።

«ኒቃብ አውልቀው መማር ይችላሉ!» የሚል አረንጓደ መብራት አበሩላቸው፤ ይሄው ከኒቃብ አልፈው ጂልባብ ለብሳ የምታስተምረውን መምህር ፈትሕያን አለባበስሽ አርዓያነት የጎደለው ነው ብለው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋታል።

እኔ'ምለው፦ ገላን ሸፍኖ ማስተማር ነው ወይንስ ተገላልጦ ማስተማር ለተማሪዎች አርዓያነት የጎደለው አለባበስ የሚባለው?
በእናንተ እይታ ሐፍረተ ገላቸውን ለመግለጥ ሩብ ጉዳይ የቀረው አለባበስ ለብሰው የሚያስተምሩ መምህራን ለተማሪዎች መልካም አርዓያ ናቸው ማለት ነው?

የመልካም አርዓያነት ምንነት የተምታታባችሁ ደነዝ አስተዳደሮች ናችሁ። የተገለበጠ አዕምሮ ነው ያላችሁ!

ለማንኛውም ካሚልን የዘራኸው ስላፈራ ና ና አጭደህ ምርትህን አንሳ በሉት።
የኒቃብን በር ሲከፍትላቸው ወደ ጂልባብ በራሳቸው ጊዜ ወረዱ። አሁንም ዝም ሲባሉ ከላይ ጣል የሚደረገውን ሒጃብ ከልክለው መገላለጥን ግድ ያደርጉልሃል።
ምንም እንኳ አንተ ባታምንበትምና ቤተሰብህ ላይ የምትተገብረው ባይሆንም፤ መጀመሪያውኑ በኒቃብ ጉዳይ በሩን ዘግተኸው በነበር አነሰ ቢባል ጂልባብ የመልበስን ጉዳይ ሳንከራከርበት በሙሉ ድምፅ እናስከብር ነበር። ይሄው ዳሩን ሳታስከብረው ቀረህና መሃሉን ዳር አደረግከው። ያኔ ስንቃወመው ስትወቅሱን የነበራችሁ ሁሉ ኑና እናንተም ደስታችሁን ከኡስታዛችሁ ጋር ተጋሩ።

አላሁ-ል-ሙስተዓን ገና ብዙ እናያለን!

7 месяцев назад

12ኛ ክፍል ያለፋችሁ ወንድምና እህቶች በቅድሚያ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ የዩኒቨርስቲና የፊልድ ምርጫ እስከ ጥቅምት 14 ድረስ ማስተካከል እንደምትችሉ ተነግሯል።

ዩኒቨርስቲ ለዲናችሁ የሚመች ምረጡ። ፊልድ ደግሞ በብዛት ወደ ቴክኖሎጂ ነክ ፊልዶች አዘንብሉ።
በቴክኖሎጂው እድገት ሳቢያ አውቶሜት እየተደረጉ ወዳሉ የትኛውም ፊልዶች አትግቡ።

ለበለጠ መረጃ "The future of jobs 2023" በሚል ርዕስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም (World Economic Forum - WEF) አሁን ባለፈ ሜይ 2023 ላይ ያወጣውን ባለ 296 ገፅ አመታዊ ሪፖርት ተመልከቱ።
https://t.me/MuradTadesse/32350

ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። ምንና ከምን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፊልዶች ከገበያው እየወጡ ነው?
እነማንስ ከገበያው የመውጣት ስጋት ተጋርጦባቸዋል?
እነማንስ ይበልጥ ተፈላጊ እየሆኑ ነው? እነማንስ ገበያውን እየተቀላቀሉ ነው ስለሚለው ጥቆማ ይሰጣችኋል።
በነገራችን ላይ የዘንድሮውን ሪፖርቱን ብቻ ሳይሆን በተለይም ከ2019 ጀምሮ ያሉ ሪፖርቶቹን ብትመለከቱ በየአመቱ ሪኮመንድ የሚያደርጋቸውንና የማያደርጋቸውን መታዘብ ትችላላችሁ።

በተረፈ አሁን እነዚህ ቀነ ገደብ ስላላቸው እንጂ ላላፋችሁትም ሆነ ኢቭን አልፋችሁ እንኳ ማለፍ በራሱ በቂ ስላለመሆኑና መሰል ጥቆማዎችን በሌላ ጊዜ በሰፊው እናወራለን።

7 месяцев назад

አንብቡት
||
t.me/MuradTadesse

7 месяцев, 1 неделя назад
ኢንተርናሽናል ፎረም ላይ ኢትየጵያን ወክሎ እየተሳተፈ …

ኢንተርናሽናል ፎረም ላይ ኢትየጵያን ወክሎ እየተሳተፈ የሚገኘው ወንድማቼን ዶክተር መስኡድ አላህ ከፍ ያድርግህ። ወንድሞችህን በመድረኩ እንዳስታወስካቸው አላህ ያስታውስህ ጀግናዬ

7 месяцев, 1 неделя назад
የትዊተር (ኤክስ) አካውንት ያላችሁ፤ ቶሎ ወደ …

የትዊተር (ኤክስ) አካውንት ያላችሁ፤ ቶሎ ወደ ትዊተር በዚህ ሊንክ ግቡና እስራኤል የሚለውን ምረጡ። ሊንኩ ይሄው፦ https://twitter.com/stats_feed/status/1712914872994845064 በአስቸኳይ ለሌሎችም ሼር አድርጉት። የዓለም አቀፍ ሪፈረንደም ጥያቄ ነው። ጥያቄው፦ «ጥፋተኛው ማነው?» ነው የሚለው። እስራኤል ናት። 22 ደቂቀ ብቻ ነው የቀረው፤ አፍጥኑት። ደቂቃው ሳያልቅ…

7 месяцев, 1 неделя назад

የትዊተር (ኤክስ) አካውንት ያላችሁ፤ ቶሎ ወደ ትዊተር በዚህ ሊንክ ግቡና እስራኤል የሚለውን ምረጡ።

ሊንኩ ይሄው፦ https://twitter.com/stats_feed/status/1712914872994845064

በአስቸኳይ ለሌሎችም ሼር አድርጉት።

የዓለም አቀፍ ሪፈረንደም ጥያቄ ነው።

ጥያቄው፦ «ጥፋተኛው ማነው?» ነው የሚለው። እስራኤል ናት።

22 ደቂቀ ብቻ ነው የቀረው፤ አፍጥኑት።

ደቂቃው ሳያልቅ በተለያዩ ገጾች ሼር አድርጉት።

ከአንድ በላይ አካውንት ያለው ካለ በሁሉም ይምረጥ።

||
ለተለያዩ መረጃዎች ይህን ቻነል መቀላቀል ትችላላችሁ።
↓↓
t.me/MuradTadesse

7 месяцев, 1 неделя назад

አላህ ይጠብቀን!

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

"አሚን" በል! … ድገመው (አሚኑን) ፣ ደጋግመው!
አረ በቃህ… ከምን ይጠብቀን እንዳልኩ ሳታውቅ ፤ ዝም ብለህ "አሚን" ትላለህ እንዴ ሞኞ?! ለማንኛውም እኔ "ይጠብቀን" ያልኩት ከጅህልና (ከአለማወቅ) አደጋ ነው ።

ጅህልና መከራ ነው ፤ መከራንም ያባብሳል ። ጅህልና ጨረማ ነው ፤ ብርሀንን የሚያጠፋ ጨለማ ። የአለማወቅ ጥቅም አለመጨነቅ ብቻ ነው ። (በአግባቡ) አለመጨነቅ ደግሞ ከንቱነት ነው ። እናም… በአለማወቅና በአለመጨነቅ ሰበብ የተጫነህን ከንቱነት ለመቀነስ ያለህ እድል ፤ እውቀትህን መጨመር ብቻ ነው ። እድልህን ተጠቅመህ ከከንቱነት ለመውጣት ሞክር ።

ይበቃናል

በጅህልናችን የምንኮራበት ጊዜ መብቃት አለበት ። ለማወቅ አለመጣጣር ነው በአለማወቅ መኩራት ። ሳንሸማቀቅ ተሸክመነው መዞራችን ፣ ሳይሸምመን በኮንፊደንስ የግል ሀብታችን ማድረጋችን ነው ፤ መኩራራታችን ።

አረ እንፈር ፣ እውቀታችንን እየጨመረን አለማወቃችንን ለመደበቅ እንሞክር ። ይህን ተከትሎ የሚመጣው ሌላኛው ኩራት ደግሞ በትንሽ እውቀት መኩራት ነው ። ምንም ብናውቅ ከማናውቀው አንፃር ከትንሽ አያልፍም ።
وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا
{ከሩሕም ይጠይቁሃል፡፡ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡} አልኢስራእ 85

በጅህልናችን አንኩራ ፤ እንወቅ ። በማወቃችንም አንኩራ ፤ ተጨማሪ እንወቅ ።

በተያያዘ…

አንዳንድ ሰው ሱረቱንናስን ሲቀራ "ቁል አዑዙ ቢረቢናስ (በሰዎች ጌታ እጠበቃለሁ በል! …) ብሎ ይጀምርና "ሚነል ነቲ ወናስ" (ከጋኔንና ከሰው (ወስዋሶች)) በሚለው ቦታ "ሚነል ነቲ ወናስ" ማለትም ፡· ከጀነትና ከሰው (በአላህ እጠበቃለሁ) ይላል ፤ ሳያውቀው ። ያላወቀ አለቀ ፣ ደቀቀ ፣ … ያወቀ ፣ ተጠነቀቀ ፣ ተጠበቀ … በሉ እንወቅ!

እንቃረብ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

**አላህ ይጠብቀን**!
7 месяцев, 1 неделя назад

ኒቃብ AAU ይፈቀዳል እንዴ ?!

ይህንን ጥያቄ አንዳንድ እህቶች እየጠየቃችሁ እንደሆነ አስተውያለሁ :: በመጀመሪያ ደረጃ ይፈቀዳል እንዴ ብላችሁ አትጠይቁ :: ምክንያቱም ማንም አካል የመፍቀድ መብት ስለሌለው :: ኒቃብ ልበሱ የሚለው ትዕዛዝ መለኮታዊ ትዕዛዝ ስለሆነ ማለት ነው :: የሚከለክል አለ እንዴ ካልን ደግሞ በአሁን ሰዓት ባለን መረጃ ደፍሮ የሚከለክል አካል የለም :: አልፎ አልፎ ጥበቃ ሲቀየር ባለማወቅ በር ላይ ሊያስቸግሩ ይችላሉ :: ከከለከሏችሁና ከአቅማችሁ በላይ ከሆነ ደግሞ ለካምፓስ አሚሮች አሳውቁ :: በአላህ ፈቃድ በአጭር ጊዜ መፍትሔ ያደርጉላችሗል ::

ኒቃብ መብታችሁ : የሀይማኖታችሁ ምልክት እና ውበታችሁ ነውና ልበሱ አስለብሱ ::

©aaumsu

7 месяцев, 1 неделя назад

የተዘያው በትውልድ ላይ ቀልድ ነው። የፖለቲካ ብሽሽቅ፤ በቀል የሚመስል ... እንኳን መጭውን ትውልድ የተማረውን ጭምር «ትምህርት ምን ያደርጋል» የሚል እሳቤ የመጠርና በጅምላ የማደደብ አካሄድ ነው። 97% ወደቀ ያለፈው 3% ብቻ ነው ሲባል «ለምን» ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ በጅምላ ተማሪን መስደብና ማሸማቀቅ ከዚህ በላይ ትውልድ ገደላ ከየት ይምጣ? ፈተና ለተማሩት ትምህርት መለኪያ እንጅ ያልተማሩትን በመፈተን…

7 месяцев, 1 неделя назад

የተዘያው በትውልድ ላይ ቀልድ ነው። የፖለቲካ ብሽሽቅ፤ በቀል የሚመስል ... እንኳን መጭውን ትውልድ የተማረውን ጭምር «ትምህርት ምን ያደርጋል» የሚል እሳቤ የመጠርና በጅምላ የማደደብ አካሄድ ነው። 97% ወደቀ ያለፈው 3% ብቻ ነው ሲባል «ለምን» ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ በጅምላ ተማሪን መስደብና ማሸማቀቅ ከዚህ በላይ ትውልድ ገደላ ከየት ይምጣ?

ፈተና ለተማሩት ትምህርት መለኪያ እንጅ ያልተማሩትን በመፈተን የፈታኙን እውቀት ማሳያና መመፃደቂያ አይደለም። እስከሁን በነበረው ካሌኩረም ስሁት እንኳ ቢሆን ያንን ካሌኩረም ሊመጥን የሚችል ፈተና በመውጣት ለመጭው ትውልድ ደግሞ አዲስ ስርዓት በመዘርጋት በሂደት ሊስተካከል የሚችል እንጅ በአንዴ ሁሉንም እየጣሉ በአመት አንዴ መግለጫ መስጠት የግል ጉረኝነትን እንጅ ዘርፉን የሚምጥን ስራ እየተሰራ እንዳለሆነ ግልፅ ማሳያ ነው።

በየትኛውም አለም የትምህርት ጉዳይ ሲርየስ ነው። ማንም ሰው በትምህርት ቤት ያለፈ ባግራውንድ እንዲኖረው የማይሰራ መንግስት የለም። ሰው የሚማረው ለመቀጠር አይደለም። በሚሰማራበት ዘርፍ በጥራትም በምርትም ውጤታማ ሁኖ ሀገሩንና ህዝቡን እንዲያገለግል ነው።

እኛ ሀገር በትምህርት ላይ መጥፎ ልምድ እየተወሰደ ነው። ያልተማሩ ሀብታሞች እንደስኬት እየታዩ አለመማር የተሻለ እንደሆነ እየተሰበከ ነው። «እከሌ ተምሮ ያልተማረ ቀጠረው» አይነት መጥፎ ልምምድ። ሰው ሲማር ለመቀጠር ብሎ መሆን የለበትም። የመጀመሪውን የህየወት ፈተና የሚወድቀው ለመቀጠር መማር የጀመረ እለት ነው።

ያልተማሩ ሀብታሞች «የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው» ላይ ናቸው። መለኪያቸው ቁስ ቁስ ብቻ የሆኑ ሰዎች ጉሊት ሲቀመጡ ሸክላ ፈጭተው ብርበሬ ብለው ይሸጣሉ። መርካቶ ሲገቡ የተበላሸ ምርት ላይ የኤክስፓይርድ ቀን አራዝመው መርዝ ሽጠው በሰዎች ሞት እነርሱ ይኖራሉ። ሞራል የለማ። ግብረገብነት የለማ። ምክንያታዊነት የለማ። ከፍ ያለ ሀብት ላይ ሲደርሱ የመሳሪያ ንግድ ላይ ይሰማሩ ወይም ድሀ በብራቸው አፈናቅለው ፎቅ ይገነባሉ። ከፍ ሲልም ኢትዮጵያ ላይ የሰበሰበትን ብር ዱባይ ሄደው ቤት ይገዛሉ።

የተማሩ ሀብታሞች በስደት የሰሩበት ሀገር ላይ ሁለት ቤት በሚገዛላቸው ገንዘብ ሀገራቸው ላይ አንድ ቤት ይገዛሉ። ሀገር ለእነርሱ ትርጉም ስላለው። ያልተማሩ ሀብታሞች ለብር ብለው ሀገር ሲያፈርሱ፤ የተማሩ ድሀዎች እራሳቸውን እያቀለጡ ሀገር ነው የሚለውጡ።

በእያንዳንዱ ጦርነት ጀርባ ያልተማሩ ነጋዴች እንዳሉ ለማዎቅ ፈተና መቀመጥ አይጠበቅብህም። ጥራ ብለህ ...
ከሰው በላይ ለቀለሀ ዋጋ የሚጨነቁ ስንቶችን አይተናል።

ወዳጄ ሱዳን ላይ ሀገር ያፈረሱት ሁለቱም መሪዎች ከ4ኛ ክፍል በላይ አልሄዱም። በግመልና መሳሪያ ንግድ ፉክክር ውስጥ የነበሩ በተለያዩ የአለማችን ክፍል ውድ ውድ ቤቶችን የገዙ የጦር ጀኔራሎች ናቸው ሀገር ያፈረሱት።

እናም ትውልዱን ትምህርት ምን ያደርጋል እንዲል የሚሰራው ስራ ኤርትራን እንጅ እኛን አይጠቅመንም። ከዩንቨርስቲ ጋር የተለያዬችው አስመራ 50 አመት በቆመችበት የቆመችው አስመራ ለእኛ ምሳሌ የምትሆን አይደለችም። ተስፋ የቆረጠ ተማሪ ወታደር የመሆን እድል አለው ተብሎ ከሆነም የተማረ ወታደር በስንት ጠዓሙ?

እናም ለምን እንብል። ፕሮፌሰሩ ያየዙትን የትውልድ ቅስም የመስበር አካሄድ እንቃወም።

አዱኛው ሙጬ

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago