የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 1 month ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 4 months, 2 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 6 months, 2 weeks ago
#ለኢንትራንስ ፈተና ወደ ግቢ ለምትገቡ እህቶች የተላለፈ የጥንቃቄ መልእክት።
1⃣ዶርም ስትይዢ በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እህቶች ጋር ያዢ።
2⃣ጋጠወጥ ከሆኑና እይታን ከሚሹ መጥፎ ጓደኞች ራስሽን አርቂ።
3⃣በማንኛውም ሰኣት ግቢ ላይ ለብቻሽ አትንቀሳቀሺ።
4⃣ዶርም ውስጥ ለብቻሽ አትሁኚ/አትተኚ/አታንብቢ።
5⃣ሂጃብሽን ጠብቂ፤ስርአት ያለውን አለባበስ ብቻ ልበሺ።
6⃣የሴቶች ተብሎ በሚከለለው የዶርም አከባቢም ቢሆን ብቻሽን አትሁኚ።
7⃣ከመሸ በኋላ በተቻለ አቅም ከዶርምሽ አትውጪ።
8⃣ሰላትሽንም ቢሆን ዶርምሽ ውስጥ ስገጂ።
9⃣"አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቅ" የሚውን አዝካር አዘውትሪ።
?አላህ ከክፉዎች ተንኮል እንዲጠብቅሽ ዱዐ አድርጊ።
?እነዚህን ቅድመ ጥንቃቄዎች በመተግበር ራስሽን ከፆታዊ ጥቃት ከአላህ ጋር ጠብቂ!!
#Share
#ሼር
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
በሚቀጥለው ወር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ትምህርት ማጠናቀቂያ ወይም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና አስመልክቶ ሙስሊም ተማሪዎች ምን አይነት ዝግጅት እና ምን አይነት ግዜ ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን አምና ተፈታኝ ሆኘ ካሳለፍኩትኝ ሁኔታ አንጻር የተወሰኑ ጥቆማዎችን ለተፈታኞ አደርስ ዘነድ የሞነጫጨርኳት…
ፈጅር እንደተሰገደ እንድትሰባሰቡ ወደታዘዛችሁበት ትምህርትቤት በመሄድ በተዘጋጀው የየትምህርትቤታችሁ ባስ ላይ ከመጀመርያ ዙር ቀለል ያለ ፍተሻ በኋላ ገብታችሁ ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ጉዞ ትጀምራላችሁ፡፡ መፈተኛ ግቢ እንደደረሳችሁ የያዛችሁት እቃ እንደ እቃችሁ ብዛት ጠንከር ላለ ፍተሻ ይበተናል፡፡(በዚህ ፍተሻ ሰዐት ቤታችሁ ጥንቅቅ አድርጋ እናታችሁ ያስተካከላችው ልብስ ከፍተሻ በኋላ እንዳልነበረ ሆኖ ሻንጣችሁ ሊጠባችሁ ስለሚችል እቃ አለማብዛቱ ይመከራል)፡፡ ግቢ ከገባችሁ በኋላ በመጀመርያ ወደተመደባችሁበት ብሎክ በመሄድ ከብሎካችሁ ስር ከሚገኛው ዶርሚተሪ ዶርም ውስጥ በሚገኘው አልጋ ልክ እየመደበ ለአንዳችሁ የዶርም ቁልፍ ይሰጣል፡፡(በአንዳንድ ግቢዎች ላይ እንደተፈታኙ ፍላጎት የዶርም ምደባ ስለሚደረግ ለማንኛውም ግዜያችሁን በአግባቡ ሊያስጠቅም የሚችል ጓደኛ ጋር ቀድማችሁ በመነጋገር ቀደም ብላችሁ በመገኘት ከዶርሚተሪ ቁልፍ በመቀበል የራሳችሁን ዶርም ለመያዝ ብትሞክሩ የተሻለ ነው፡፡) ከፈተናው አንድ ቀን ቀደም ብሎ በምትፈተኑበት አዳራሽ በሱፐር ቫይዘሮች ቀለል ያለ ኦረንቴሽን ይሰጣል፡፡ ፈተና እስኪያልቅ ድረስ በየእለቱ ሁለት ፈተና (ጠዋት አንደ ከከሰዐት አንድ) ይሰጣል፡፡ ከፈተና በፊት በሚደረገው ሁሉም ፍተሻ የሴት እና የወንድ ፍተሻ የተለየ ስለሆነ ኒቃብ የምታደርጉ ተማሪዎች ሳትደናገጡ ዩኒፎርማችሁን እንደለበሳችሁ ከነኒቃባችሁ በመቅረብ ፈተና መፈተን የምትችሉ ሲሆን ( ሆነ ብለው ከፈተና እንዳርቋችሁ በመጀመርያ ግቢ ላይ በሚኖራችሁ ፍተሸ ስትማሩ እንደነበራችሁት በማስክ እና በሂጃባችሁ ብትሸፈኑ እላለሁ) የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ እስከነጅልባባችሁ ያስፈትኗችኋል፡፡ ከፈተና 30 ደቂቃ በፊት መገኘት እና ፈተና ከተጀመረ ኋላ እስከ 45 ደቂቃ ድረስ መቀመጥ ግዴታ ስለሆነ በግዜ መገኘት ትእግስት አድርጋችሁ መቆያታችሁን አትዘንጉ፡፡ ወደ መፈተኛ ክፍል ስትገቡ ADMISSION CARD ፣ ማንነጽን የሚገልጽ መታወቂያ ፣ እስራስ ፣ ላጲስ እና መቅረጫ ውጭ (የእጅ ሰዐትም ቢሆን) ይዛችሁ አለመግባታችሁን አረጋግጡ፡፡
ምግብ ከዩኒቨርሲቲው የምትመገቡ ምሳ ከ5፡30 እስከ 7፡00 ፣ እራት ከምሽቱ 12፡30 እስከ 2፡00 እንዲሁም ቁርስ ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 2፡00 ድረስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በሰዐታችሁ ተገኝታችሁ መመገባችሁን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ምግቡ በአብዛኛው ተመሳሳይ ሊሆን ቢችልም የሚታማ አይነት ምግብ ስላልሆነ ብትመገቡት አትጎዱም ይልቅ ወስፋታችሁ ይከፈት ዘንድ ከታች የዘረዘርኩላችሁን ደረቅ ምግቦች ብትጠቀሙ አሪፍ ነው፡፡ ካፌ ከፍላችሁ ተጠቃሚ የምትሆኑ ከሆነ ደግሞ ምግብ ሊያልቅ ስለሚችል ከሁሉም በፊት ቀደም ብላችሁ በመገኘት ምግብ ማዘዝ ይኖርባችኋል፡፡
ከሁሉም በላይ መረሳት የሌለበት ነገር ቢኖር የሰላት ወቅት ሲሆን በዩኒቨርሲቲዎች አከባቢ መሳጂዶች ላይኖሩ ስለሚችል ዲስኮ(ደቂቃ ብቻ የሚቆጥር መዘነጫ ያልሆነ የእጅ ሰዐት) መያዝ እና የሰላት አውቃቶችን እና የቂብላ አቅጣጫን ግቢ ከመግባታችሁ በፊት ማረጋገጥ ተመራጭ ነው፡፡ ለፈጅር ሰላት ለመነሳት ብቸኛው መፍትሄ በግዜ መተኛት ስለሆነ ከአልባሌ መዝናኛ ቦታዎች ራስን ማራቁ ይመረጣል፡፡ የተፈታኙ ብዛት ከፍተኛ በሆነበት ዩኒቨርሲቲ ብዛት ያለው ጀማዐ ሊከለከል ስለሚችል ለደህንነታችሁ ሲባል እናንተ ብሎክ ጋር ካሉ ተማሪዎች ጋር ብቻ ባዶ በሆኑ ዶርሞች ወይም ከዶርም አጠገብ በሚኖረው ግሪን ኤሪያ ላይ ብትሰግዱ የተሻለ ነው፡፡
ዶርም ውስጥ ሁሉም ተማሪ የየግሉ ሎከር ስለሚኖረው ተመሳሳይ መክፈቻ በመይገኝለት የጋን ቁልፍ መቆለፍ የሌለበት ጉዳይ ነው፡፡
ተማሪዎች ሰብሰብ ብለው ከሚያመሹባቸው ቦታዎች ራስን ማራቁ ከደህንነት በተጨማሪ በአቻ ግፊት ምክንያት ከሚመጡ ፈሳዶች ይከላከላል፡፡ በተረፈ በሚኖራችሁ ትርፍ ግዜ መጽሀፍ ማንበብ ከድብርት ሙድ ውስጥ ያወጣችኋል፡፡
በፈተና የመጭሻ ቀን በየቦታው የቡድን ጸቦች ስለሚኖሩ ከዶርም አካባቢ ራቅ በማለት ራሳችሁን የምትጠብቁበት ቦታ ብትሆኑ እና በየትኛውም አይነት ጸብ እጃችሁን ከማስገባት መቆጠብ ይኖርባችኋል፡፡
ካልተመደባችሁበት ብሎክ እና ወንዶች ወደሴቶች ዶርም ሴቶች ወደወንዶች ዶርም መሄድ ካለማወቅ ከሚፈጠሩ ምናልባትም ቅጣታቸው ከፍ ያለ ሊሆን ከሚችሉ ስህተቶች ውስጥ ነው፡፡
ለማንኛውም ፈታኝ ፣ ጥበቃ ፣ የስራ ሀላፊ በተለይ ለማንኛውም ከጸጥታ አካላት ለሚመጣ ትእዛዝ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይኖርባችኋል፡፡
ዳቦ ፣ ነጠላ ጫማ እና ፈሳሽ ምግቦች ሱቅ ላይ ስለሚገኙ ባትሸከሙ…
*
ልትይዟቸው የሚገቡ …
1 ታጣፊ የኪስ መስገጃ እና በመጠኑ አነስ ያለ ቁርዐን(ብዙ ተፈታኝ የሚዘነጋቸው)
2 በትርፍ ግዜ ሊነበቡ የሚችሉ አጠር አጠር ያሉ አዝና እና አስተማሪ መጽሀፍት(ሁለት መጽሀፍ በቂ ነው)
3 የ ATM ማሽን ያሉባቸው ቦታዎች በጸጥታ እና በንብረት ጥበቃ ጉዳይ ዝግ ሊሆኑ ስለሚችሉ ለዝርፊያ የሜጋልጣችሁን ቢበዛ እስከ 1000 ብር ካሽ
4 የምትመገቡት ምግብ መላመዱ ሊከብዳችሁ እና እንደ ቤት ላይሆን ስለሚችል ከቤት የተዘጋጁ ደረቅ ምግቦችን እና የታሸጉ ምግቦችን(ለውዝ ቅቤ ፣ ማርቤላ) መያዝ
5 ፍተሸ ሰአት እንዳትቸገሩ ከዪኒፎርም ውጭ ሁለት ተቀያሪ ልብስ ብቻ መያዝ
6 ማንነትን ሊገልጽ የሚችል መታወቂያ (የትምህርት ቤት ፣ የቀበሌ ፣ ብሄራዊ መታወቂያ)
7 የሻንጣ ጋን ቁልፍ(ትንሿን ብቻ)
8 ለፍተሸ ምቹ የሆነ ንብረታችሁን በሙሉ በትክክል ሊይዝ የሚገባ ሻንጣ ወይም ቦርሳ
9 የሰላት እና ሌሎች ግዜያችሁን አብቃቅታችሁ ለመጠቀም ዲስኮ ሰዐት መያዝ
10 ለሴቶች የወር አበባ መቆጣጠሪያ(ሞዴስ)
11 የታዘዘላችሁ መድሀኒት ካለ እስከነማዘዣ ወረቀቱ ይዛችሁ መገኘት
ባትይዟቸው የሚመረጡ እና እንዳትይዟቸው የሚከለከሉ
1 በጠንካራ ማይካ ወይም ፕላስቲክ ፣ በጠርሙስ እና በብረት የታሸጉ ማንኛውም አይነት ነገሮች
2 እንደ በሶያሉ ዱቄት ይዘት ያላቸው ምግብ ነክ ነገሮች ጋር አደገኛ እጾች ስለሚገቡ የጸጥታአካላት ሊያስጥሏችሁ ይችላሉ
3 ጥቅል ሶፍት(ግቢ ውስጥ ባሉ ሱቆች ውስጥ ስለሚገኝ ባትይዙ)
4 ከስክስ ሰፍቲ የወንድም የሴትም ጫማ
አላህ ከናንተ ጋር ይሁን፡፡
ጽሁፉን በከፊልም ሙሉውንም ሀሳባችሁንም አድርጋችሁ ለተማሪዎች ማጋራት ትችላላችሁ።
ወንድማችሁ ASD
12ኛ ክፍል ያለፋችሁ ወንድምና እህቶች በቅድሚያ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ የዩኒቨርስቲና የፊልድ ምርጫ እስከ ጥቅምት 14 ድረስ ማስተካከል እንደምትችሉ ተነግሯል።
ዩኒቨርስቲ ለዲናችሁ የሚመች ምረጡ። ፊልድ ደግሞ በብዛት ወደ ቴክኖሎጂ ነክ ፊልዶች አዘንብሉ።
በቴክኖሎጂው እድገት ሳቢያ አውቶሜት እየተደረጉ ወዳሉ የትኛውም ፊልዶች አትግቡ።
ለበለጠ መረጃ "The future of jobs 2023" በሚል ርዕስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም (World Economic Forum - WEF) አሁን ባለፈ ሜይ 2023 ላይ ያወጣውን ባለ 296 ገፅ አመታዊ ሪፖርት ተመልከቱ።
https://t.me/MuradTadesse/32350
ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። ምንና ከምን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፊልዶች ከገበያው እየወጡ ነው?
እነማንስ ከገበያው የመውጣት ስጋት ተጋርጦባቸዋል?
እነማንስ ይበልጥ ተፈላጊ እየሆኑ ነው? እነማንስ ገበያውን እየተቀላቀሉ ነው ስለሚለው ጥቆማ ይሰጣችኋል።
በነገራችን ላይ የዘንድሮውን ሪፖርቱን ብቻ ሳይሆን በተለይም ከ2019 ጀምሮ ያሉ ሪፖርቶቹን ብትመለከቱ በየአመቱ ሪኮመንድ የሚያደርጋቸውንና የማያደርጋቸውን መታዘብ ትችላላችሁ።
በተረፈ አሁን እነዚህ ቀነ ገደብ ስላላቸው እንጂ ላላፋችሁትም ሆነ ኢቭን አልፋችሁ እንኳ ማለፍ በራሱ በቂ ስላለመሆኑና መሰል ጥቆማዎችን በሌላ ጊዜ በሰፊው እናወራለን።
አንብቡት‼
||
t.me/MuradTadesse
የትዊተር (ኤክስ) አካውንት ያላችሁ፤ ቶሎ ወደ ትዊተር በዚህ ሊንክ ግቡና እስራኤል የሚለውን ምረጡ።
ሊንኩ ይሄው፦ https://twitter.com/stats_feed/status/1712914872994845064
በአስቸኳይ ለሌሎችም ሼር አድርጉት።
የዓለም አቀፍ ሪፈረንደም ጥያቄ ነው።
ጥያቄው፦ «ጥፋተኛው ማነው?» ነው የሚለው። እስራኤል ናት።
22 ደቂቀ ብቻ ነው የቀረው፤ አፍጥኑት።
ደቂቃው ሳያልቅ በተለያዩ ገጾች ሼር አድርጉት።
ከአንድ በላይ አካውንት ያለው ካለ በሁሉም ይምረጥ።
||
ለተለያዩ መረጃዎች ይህን ቻነል መቀላቀል ትችላላችሁ።
↓↓
t.me/MuradTadesse
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 1 month ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 4 months, 2 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 6 months, 2 weeks ago