mezmurat

Description
yaaaa
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

3 years, 3 months ago

#አዘክሪ

አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን

ከአንቺ መወለዱን - - - አዘክሪ
በቤተልሔም - - - አዘክሪ
በጨርቅ መጠቅለሉን - - - አዘክሪ
መኝታው ግርግም - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
አዝ= = = = =
በዚያ በብርድ ወራት - - -አዘክሪ
የገበሩለትን - - - አዘክሪ
የአድግና የላህም - - - አዘክሪ
እስትንፋሳቸውን - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
አዝ= = = = =
በግብጽ በረሃ - - - አዘክሪ
መሰደድሽን - - - አዘክሪ
የአሸዋውን ግለት - - - አዘክሪ
ረሃብና ጥሙን - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
አዝ= = = = =
በመቃብሩ ዘንድ - - - አዘክሪ
ባለቀሽው እንባ - - - አዘክሪ
አሳስቢ ድንግል ሆይ - - - አዘክሪ
ገነት እንድገባ - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን

@MEZMURA

3 years, 3 months ago

#አክሊለ ፅጌ

አክሊለ ፅጌ ማርያም አክሊለ ፅጌ
አክሊለ ፅጌ ማርያም አክሊለ ፅጌ

ስሟ ማርያም ነው አክሊለ ፅጌ
የጌታ እናት "
እናት አባቷ "
ያወጡላት "
ከምድር ማር "
ከሰማይ ያም "
ብለው ሰየሟት "
ድንግል ማርያምን "
አዝ......
የስሟ ጣህም አክሊለ ፅጌ
ከማር ይበልጣል "
እንደሷ ያለ "
ከየት ይገኛል "
የፍቅር መዝገብ "
ነቅህ የሌለባት "
ለክብሯ ወደር "
ማን አግኝቶላት "
አዝ......
የከበረ ዘውድ አክሊለ ፅጌ
የወርቅ ሙዳይ "
የሽቱ ብልቃጥ "
የነፍሴ ሲሳይ "
ከጥፋት ውሀ "
ኖህ የዳነብሽ "
የሰላም መርከብ "
ቤቱ አንቺ ነሽ "
አዝ......
በቤተ መቅደስ አክሊለ ፅጌ
ስትኖር ተመርጣ "
ምግቧን ይዞላት "
ፋኑኤል መጣ "
አስራ አምስት ዓመት "
ሲሆናት ድንግል "
በገብርኤል ብስራት "
ተፀነሰ ቃል "

@MEZMURA

3 years, 3 months ago

#ገሊላ_እትዊ

እመቤቴ እሰከ መቼ
በባዕደ ሀገር ትኖርያለሽ /2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሐገርሽ ገሊላ ግቢ/2/

ገሊላ እትዊ/4/ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ
ሰደቱ ይበቃሽል ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቱልብሉ ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነገሮሽል ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰርገላ ገሊላ እትዊ
ዑራኤል የምራሻል ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

የዝናቡን ጌታ ገሊላ እትዊ
እናቱ ሁነሽ ሳለ ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰው አደሩ ገሊላ እትዊ
ውሃ ጥም ፅንቶብሽ ገሊላ እትዊ
አፈሽ ደርቁ ዋል ገሊላ እትዊ
ይብቃል እናቴ ገሊላ እትዊ
ርሀብ ጥማትሽ ገሊላ እትዊ
ሂጅ ወደ ገሊላ ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመድችሽ ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

የሰማዕታት ገሊላ እትዊ
የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ
ባርክሽ ሰጠሽቸው ገሊላ እትዊ
መክራን ሰድት ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደገን ገሊላ እትዊ
የአንቺው ብርክት ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

ገፃሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ ገሊላ እትዊ
እግዚትነ ማርያም ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ ገሊላ እትዊ
መክራ ስቃይ ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ /2/
ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/

@MEZMURA

3 years, 3 months ago

#እግዚአብሔር እኛን ይወደናል

እግዚአብሔር እኛን ይወደናል
መላዕክቱን ለኛ ልኮልናል
እንዲረዱን እንዲጠብቁን/2/
መላዕክቱ እንዲታደጉን/2/
አዝ.............
መንገደኛ መስሎ መላኩ ሲራራ
በሐሞት መስሎ በዚያ በተራራ
የጦቢትን አይኑን ያበራ/2/
ሩፋኤል ነው ለኛ የሚራራ/2/
አዝ........
ጦቢያና ጦቢት ይናገሩ
የመላዕኩን ታአምር ይዘርዝሩ
ይናገሩ ይገለጥ ክብሩ /2/
የታወሩ ሁሉ እንዲበሩ /2/
አዝ.............
ወለተ ራጉኤል ተናገሪ
የጫጉላ ቤትሽን ታሪክ አውሪ
ተናገሪ ለህዝብ አብስሪ /2/
ታምራቱን ምንም ሳፈሪ /2/
አዝ...........
ሰባቱ ባሎችሽ መሞታቸው
የሚያሳዝነ ነበር ታሪካቸው
ሩፋኤልም ደረሰልሽ/2/
ጎጆሽንም ባረከልሽ/2/
አዝ...........
እንግዲህ ተደሰች እልል በይ
አስማንዲዮስ ወቷል ከአንቺ ላይ
ህይወትሽን ሩፋኤል ዋጀው/2/
ሰላምሽን ለአለም አወጀው /2/
አዝ...........
ጦቢያም ይናገር በተራው
ያደረገለትን አለኝተው
ወዲያው ደሞ አባት ሆነው/2/
ሽማግሌ ሆኖ ዳረው /2/
አዝ.............
እኔም ልናገር በተራዬ
ቀሎልኛልና መከራዬ
ሩፋኤል ነው እናት አባቴ/2/
እለዋለሁ ወንድም እህቴ/2/
አዝ.......
እኔም ልናገር በተራዬ
ያደረገልኝን አለኝታዬ
ህይወቴን ሁሉ ቀይሮታል/2/
ልቦናዬ ፍቅሩ ማርኮታል/2/

@MEZMURA

3 years, 3 months ago

#ሁሉም ነገር ሆነ

ሁሉም ነገር ሆነ በግሸን ማርያም
በደብረ ከርቤ በጊሸን ማርያም
በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ሆነ

መስቀሌን በመስቀል - በግሸን ማርያም
እንዳለ በቃሉ - በግሸን ማርያም
በግሸን አደረ - በግሸን ማርያም
ግማደ መስቀሉ - በግሸን ማርያም
ክርስቲያኖች ሁሉ - በግሸን ማርያም
እንጓዝ ከደጅዋ - በግሸን ማርያም
ትኖራለችና -በግሸን ማርያም
ድንግል ከነልጅዋ - በግሸን ማርያም
አዝ= = = = =
በገነት መስሎ - በግሸን ማርያም
ጌታ ያስቀመጠው - በግሸን ማርያም
ዙሪያሽ ገደል ሁኖ - በግሸን ማርያም
አንድ መግቢያ ያለሽ - በግሸን ማርያም
ግሸን ደብረ ከርቤ - በግሸን ማርያም
የታቦር ተራራ - በግሸን ማርያም
ሁነሽ የተመረጥሽ - በግሸን ማርያም
የመስቀል ማደሪያ - በግሸን ማርያም
አዝ= = = = =
እንማፀናለን - በግሸን ማርያም
ከደጅሽ ላይ ሆነን - በግሸን ማርያም
ባንቺ አማላጅነት - በግሸን ማርያም
ጌታ እንዲለመነን - በግሸን ማርያም

@MEZMURA

3 years, 3 months ago

#ማር ሊቀ ሰማዕት

ማር ሊቀ ሰማዕት ገባሬ መንክር
ጊዮርጊስ ኃያል(፪)

የዱድያኖስ አምላክ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ያንን ደራጎን - - ጊዮርጊስ ኃያል
አምላክ እንዳልሆነ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ገድለህ አሳየኸን - - ጊዮርጊስ ኃያል
የቤሩት ኮከብ ነህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
የልዳ ፀሐይ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ለባሴ ሞገስ ነህ መክብበ ሰማዕት(፪)
አዝ= = = = =
መከራና ስቃይ - - ጊዮርጊስ ኃያል
እያጸኑብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ትናገር ነበረ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ስለ አምላክህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሥጋህን ፈጭተው - - ጊዮርጊስ ኃያል
ይድራስ ሲበትኑት - - ጊዮርጊስ ኃያል
ዳግመኛ አስነሳህ አምላከ ምሕረት(፪)
አዝ= = = = =
አንገትህ ሲታረድ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ምድር ተናወጠች - - ጊዮርጊስ ኃያል
ወተትና ውሃ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ደምም አፈለቀ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰብዐ ነገሥታት - - ጊዮርጊስ ኃያል
እስኪደነቁብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰባት አክሊላትን ጌታ አቀዳጀህ(፪)
አዝ= = = = =
የዚህን ዓለም ጣዕም - - ጊዮርጊስ ኃያል
ንቀኸው ጥቅሙን - - ጊዮርጊስ ኃያል
በፍቅር ተቀበልክ - - ጊዮርጊስ ኃያል
መራራ ሞትን - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰማይና ምድር - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሳርና ቅጠሉ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰማዕተ ክርስቶስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሉ(፪)

@MEZMURA

3 years, 3 months ago

#እናቴ እመቤቴ

እናቴ እመቤቴ/ የማትጠፊው ከአፌ/2/
በረከቴ አንቺ ነሽ/ የመስቀል ስር ትርፌ /2/
አምላኬ ሸልሞኝ ለዘላለም ያዝኩሽ
ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ

በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ፀዳሉ
የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ
ተወዳጁ ልጅሽ ፀጋውን ያብዛልኝ
እድሜዬ እስኪ ፈፀም ለክብርሽ እንድቀኝ

/አዝ====

ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና
ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና
እኖራለሁ ገና ንኢ ንኢ ስልሽ
ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፌ የማልነጥልሽ

/አዝ =====

ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ
ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰአሊ ለነ እያልኩሽ
አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ
የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ

/አዝ=====

መች በስጋ ጥበብ ሰው ለአንቺ ይቀኛል
ከአምላክ ከአልተላከ ከፊትሽ ይቆማል
አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ
በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ስላሴ

/አዝ=====

ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም
ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም
እኔን በእደ ፍቅርሽ የምትባርኪ
ኦ ምልዕይተ ፀጋ ድንግል ሰላም ለኪ

@MEZMURA

3 years, 3 months ago

#ሰውነቴ
ሰውነቴ በአንተ ፍቅር ተጠምዳለች
ውለታህን እያሰበች ታለቅሳለች
መከራው ተረሳ ትካዜም ቀረልኝ
ገብረመንፈስ ቅዱስ ፈጥነህ ደርሰህልኝ

ደጅህን ለመርገጥ መንገድ ስጀምር
ተፈቶ አየዋለው የልቤ ችግር
ወዳጅ እና አባቴ ሚስጥሬ ተስፋዬ
ቀና እንድል አረከኝ በነፍስ በስጋዬ

/አዝ=====

በሚመጥን ፊደል በሚያምሩ ቃላት
ነፍሴ ትጠማለች ስምክን ለመጥራት
እንባዬ ይፈሳል አንደበት ያጥረኛል
ውለታህን ሳስብ ልቤ ይቀልጥብኛል

/አዝ =====

ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረህይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ

/አዝ =====

ስለቴን ስሰማኝ ሲጠብቀኝ ምልጃህ
ሳጉረመርምብህ ትታገሰኛለህ
የጭንቄ ማረፊያ የህመሜ ፈውስህ
አርከ እግዚአብሔር ገብረመንፈስ ቅዱስህ

/አዝ =====

ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረህይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ

@MEZMURA

3 years, 5 months ago

✞ ​ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ /2/ ሆኦ ልጆች ሁሉ ሆ
የኛማ ጌታ ሆኦ የዓለም ፈጣሪ ሆ
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ
በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባረቀው ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ያዕቆብ ዮሐንስሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ
ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ

ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ
ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ

በተዋህዶ ሆ ወልድ የከበረው ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደማርያም ነው ሆ
ቡሄ በሉ ሆ ቡሄ በሉ ሆ
የአዳም ልጆች ሆ ብርሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ

አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ከአጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አክስቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ

የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ
ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ

ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ ያላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ ያዙ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ
ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ

አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ
የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ
ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ

ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ

ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ
በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችንይድረስ ሆ

ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና

እንዲሁ እንዳላችሁ በምነት አይለያችሁ በምነት
ላመቱ በሰላም በምነት ያድርሳችሁ በምነት
ክርስቶስ በቀኙ በምነት ያቁማችሁ በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርጋችሁ በምነት
እንዲሁ እንዳለን በምነት አይለየን በምነት
ለዓመቱ በሰላም በምነት ያድርሰን በምነት
አማኑኤል በቀኙ በምነት ያቁመን በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርገን በምነት

የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት/2/ ይግባ በረከት/2/
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት /3/

@MEZMURA

3 years, 6 months ago

#ገብርኤል ስለው ሰምቶ

ገብርኤል/2/ ሰለው ሰምቶ መጣ ወደኔ ፈጥኖ
ሰንሰለቴን በጠሰው የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ

ገብርኤል ስጋዬ ሳይረግፍ በአናብስቹ ጥፍር
ገብርኤል ታድጎኛል ምልጃው የመላኩ ፍቅር
ገብርኤል በረሐብ ለነደዱ አናብስት ሲጥሉኝ
ገብርኤል አንተ አለኸኝና ክንፎችህ ከለሉኝ

አዝ_______________

ገብርኤል ከአፎቱ ሲመዘዝ የጠላቴሰይፍ
ገብርኤል አጽንቶ ይዞኛል ፍሬዬ ሳይረግፍ
ገብርኤል አደገድጋለሁ አለኝና ፍቅሩ
ገብርኤል በእሳት ክንፉ ታጥራል የደጄ ድንበሩ

አዝ_______________

ገብርኤል በሰይፍ ተመትራል የክፉዎች ብክነት
ገብርኤል ሐብሉ ተበጣጥሷል ያመጡት ሰንሰለት
ገብርኤል ከቅድሱ ድንጋይ ሕይወት ከሚያፈልቀው
ገብርኤል እንዳልለይ ረዳኝ ክብሬን ከፍ አረገው

አዝ_______________

ገብርኤል አለው ልዩ ስልጣን በአምላክ የተሰጠው
ገብርኤል ይመጣል ወደኛ እሳቹን ሊያጠፋው
ገብርኤል እኛም እናምናለን ሰምተናል አይተናል
ገብርኤል የመላክት አለቃ ከአምላክ ያማልዳል

አዝ_______________

ገብርኤል ስጋዬ ሳይረግፍ በአናብስቹ ጥፍር
ገብርኤል ታድጎኛል ምልጃው የመላኩ ፍቅር
ገብርኤል በረሃብ ለነደዱ አናብስት ሲጥሉኝ
ገብርኤል አንተ አለኸኝና ክንፎችህከለሉኝ

@MEZMURA

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago