★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 3 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 8 months ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago
***አዎን መንኛለው!
ለበረከት አይሉት አጉል ምንኩስና
ከመጣመር ሽሽት ጠልቶ ቅድስና::
እንዳይረግሙኝ መናኝ ስዎችን የምፆም
እንዳልፅድቅም በዳይ ከድቼ የምቆም::
--------- ----------- --------
ቃሌን ሳጥፍ ለአመል ለምዶብኝ ሳይለቀኝ
አጉአጉል ሽሽቴ በሌለው ሲያስቀኝ
ካለ ከሚዘልቀው ደርሶ ስያላቅቀኝ......
ተባራሪ ሆንኩኝ ባሌለ አባሮሽ
ዛሬዬን ቢሸፈን የትላንቴ ግርዶሽ::
አንቺም ተውሽኝ አሉ የቀረሁኝ መስሎሽ
እንደኔው መሸሹ ከመጠበቅ ቀሎሽ
ጠልቼሽ አይደለም...... እመኚኝ ግዴለም
ለምዶብኝ ነው ጉዞ የብቻነት ዐለም::
ለምዶብኝ ነው ነገር ከቶኝ ከኩነኔ
ምን ይሉት ተአምር ነው ኃጢአትን ማግበስበስ ገብቶ ከምናኔ?*
✍#Lewi JOIN AND SHARE**@ktibebalem@ktibebalem@ktibebalem
ያገባኛል ሁሉም........
አይደለም ደባብሶሽ ሊነካሽ ያሰበ
ይጎትታል እኔን አንቺን የሳበ
የነካሽ ነካካኝ ያለፈ በጎንሽ
ሲሸረፋ ሸረፈኝ ጠርዝሽ ምናምንሽ
ወላ በእንባሽ ውስጥ ስቃዬን ታዝቤ
ከስምሸ ጋር ታየኝ አብሮ ያለ ስሜ
ወጥተሽ ሳለ ያኔ ድሮ ከሚባል ጥንት
ከገዛ ራሴ የጎኔ ላይ አጥንት
አዋዝቶ ባይገለኝ ያዝላል መሄድሽ
ባይረዝም፣ ቢረዝም ተላላ መንገድሽ።
JOIN AND SHARE
@ktibebalem
@ktibebalem
@ktibebalem
አምላኬ
ጓዳዬ ባይስተካከል
አዳፋ ጨርቄ ባይነጣም
የጭንቄ ለሊት ቢረዝም
ዙሪያዬን ሽንቁር ባላጣም
አውቃለሁ ላያልፍ አልመጣም
ትከሻ አበጀህልኝ
ፈተና ባይቀልልኝም
ላታስችል አልሰጠኸኝም!
አውቃለሁ ላይነጋ አልመሸም
መሻቴን ዛሬ ባላገኝ
በእምነት ጠባቂህ አርገኝ?
✍️ሊና አርጋው
JOIN AND SHARE
@ktibebalem
@ktibebalem
@ktibebalem
አለሜ
ሰው አንዳለህ ሰማው......
ሰው አላት ይሉሀል?
አብሮ መክረም ሁሉ
(አብሮ መዝለቅ ሁሉ)
መኖር ይመስልሀል?
እእ
ከእልፍኝ ቢሾሙት
አባወራ ሁሉ ጎጆ አያደምቅም
መዳፍ ሁሉ አይነዝርም
እቅፍ ሁሉ አይሞቅም
ፍቅር ካልተቸረ
ጣት ይኮሰኩሳል
ካካል ቢርመሰመስ
ነፍስ አይተረክክም
ከናፍር ቢቀመስ
ልብ ያልታከለበት
የልብ አያደርስም
አንሶላ ቢገፉት
ተው ስሜን አያጥፉት
መሄድህን እንጂ
መሄዴን አትመን
ምን ቀናት ቢርቁ
በፍቅር ስሌት ላይ...
ከመኖር አይደለም
......ከልብ ነው ሀቁ!
✍️ሊና አርጋው
JOIN AND SHARE
@ktibebalem
@ktibebalem
@ktibebalem
ስካለብ ያልታየኝ ጊዜ ጣለኝ አጉል
አይበሩት ሲያበረኝ፣ አይፈጥኑት ስቸኩል፡፡
ችኩልኩል፣ ችኩልኩል ጥድፍድፍ ያለ ወግ
አስር ጊዜ መስጠት የሌለሽን ማዕረግ፡፡
ላልነካኝ እጣትሽ ኪዳን ከቀለበት
ቃሌን መጠባበቅ ቃልሽ በሌለበት
ዱካሽን መፈለግ እግርሽ ባልዞረበት፡፡
መልኬንም ሳትለዪው፣ ሳታቂኝ ሳይገድሽ
እንዴት? በየት በኩል ሳልቀጥርሽ ማርፈድሽ?
እንደምንድን? እንዴት? በየትኛው ስሌት?
ከቃልሽ ቀድሜ ሳትጠሪኝ አቤት
እንዴት?
እንዴት?
እንዴት?
ምኑን ብታውቂበት? ምኑን ብትሰሪ?
በየትኛው ተዓምር ነው መጥተሽ የምትቀሪ?
እየሌለሽ ያለሽ፣ ኖረሽ የማትኖሪ
አወይ ልቤ ሞኙ!
የአየር ላይ ሰላምታሽ ተካብዶ ቢገርመው
ባልነበር አንድምታ የተተረጎመው
መሳቅሽ መሽኮርመም ደርሶ እየመሰለው፡፡
እኔ…..
የተገላበጠኝ መሆን ከአለመሆን
አሁንም ማስበው እንዲህ ስመሳቀል እያየሽኝ ይሆን?
**✍️****#Lewi
@Lee_wrld777
SHARE AND JOIN@Ktibebalem
@Ktibebalem
@Ktibebalem
*(አይሽ፣ አይሽና……. )
‹ዐይኗ ነው› እላለሁ
ያዘዘብኝ መፍዙዝ
‹ዐይኗ ነው› እላለሁ
ያደረገኝ ድንዙዝ፡፡
አልታዘዝ አለኝ……
የአካሌ ግማሹ
እንደ አዲስ ሰራሽኝ
የአምላክ ታናሹ፡፡
(ዘፋኟ እንዳለች…….. )
ለዚያውም አጉድለሽ፣
ምላሽ ሰጪ አካል
ነፍገሽ እንደ ቀላል
ይቅርታውስ ዘበት አፍሽ መሳቅ ያቃል፡፡
(አይሽ፣ አይሽና…….. )
መሳቅ ብቻ ማወቅ
ነውር ሆኖ ያልታየው
አሳዘነኝ አፍሽ ይቅርታ ነበረ የፍርድ ቀን ዋስሽ፡፡
(አይሽ፣ አይሽና…….. )
ባላይሽ እላለሁ……..
አይቶ ከመቃጠል በትንሽ ለመርገብ ምን ተረፈኝ አልፎ ደርሶ ከመንገብገብ . . .
(አይሽ፣ አይሽና…… )
*✍️*#Lewi@Lee_wrld777 SHARE AND JOIN***@Ktibebalem@Ktibebalem@Ktibebalem
#ግማሽ ***ጨረቃ
ከጨረቃ በታች.....
ወጥነት የሳተ ብጥስጣሽ ደመና
አርጅቶ እንዳፈጀ አሮጌ ጎዳና
የሻገተ ነገር ጊዜው ያለፈበት
ያለማማር ወጉ ውበት ያልሻረበት.....
ከሱ ማዶ አጀብ
እዛ እና እዚህ ኮከብ
ማየት ሲያደካክም ያንቺን ነገር ማሰብ።
የሌለሽን አንቺ በፍለጋ ሂሳብ
ከሩቅ እንደ መሳብ
ማውጣት፣ ማውረድ ለጉድ
ከጊዜ መካለብ፣ በሰኞ እና በእሁድ።
ላልበጠስ ውጥር ፣
ላይለይልኝ ነገር ብዳከር ለዘመን
አይቀየር፣ አይሻር ብደበቅ ከማመን
ግማሽ ጨረቃ ነው ትዝታሽ በተመን።
የተሳነው መሙላት፣ ያልሆነለት መጉደል
ጎኑን የደፈረው የጨለማ ገደል
መራቅ ያላጠፋው መቅረብ የመሰለ
ልዳብሰው ስሻ እንደመሄድ ያለ
የቀረበኝ ስለው የራቀኝ ከዘመን
ግማሽ ጨረቃ ነው ትዝታሽ ሲተመን።
✍️#Lewi@Lee_wrld777 SHARE AND JOIN***@Ktibebalem@Ktibebalem@Ktibebalem
ቃል እዳ ነው!!
በሚሰስት አይን
በሚያፈቅር ልሳን
የእድሜ ገደባችን
ውሉ እስከሚረሳን
ምለን ተማምለን
ብትን ገላቸንን
በአንድ ስናበጂ
ለእድሜህ አላልከኝም!
ለእድሜዬ አላልኩህም
ለዘአለም እንጂ::
ቃል እዳ ነው!
ዝንፍ የሌለው መስቀል
ከመዳፍህ ስዬ
መልኬ እስኪጠፋኝ
መልክህን መስዬ
የጉንጭህን ወለል
ዳብሼ እየሳምኩት
የት ድረስ ነበረ
እወድሀለው ያልኩት?
ቃል እዳ ነው!
(ተጉዘሀል ብዬ)
(መንገድ ቀናህ ብዬ)
አላዋውሰውም
የቃልኪዳን ጣቴን
ቀለበት ቢሰበር
ዘላለም ልወድህ
ኪዳኔ አልነበር?
ለምን "እስከ" ኩርፊያህ ?
ለምን "እስከ" ጥፋት ?
ለምን "እስከ" በደል ????
ዘላለም በሚሉት
እሩ……………ቅ መሀላ ውስጥ
"እስከ" የለም አይደል ??
.
.
.
.
ቃል እዳ ነው !!
✍ሊና አርጋው
13/08/2016
SHARE AND JOIN
አስራ ሁለት ተኩል .. ልርሳህ በየት በኩል .. ፡ ፡ ካቻምና ናፍቀኸኝ ካቻምና ናፍቄህ ከመነጋገሪያው ከስልኩ ጠብቄህ ነፍሴን ልታጠፋት በፍቅር ጨዋታ አስራ ሁለት ተኩል አልከኝ እዛች ቦታ.. . . አስራ ሁለት ተኩል .. ልርሳህ በየት በኩል .. ፡ ፡ በፈዘዘ ማታ .. ከቀጠርከኝ ቦታ .. ስትከንፍ ደርሰህ ... ስከንፍ ደርሼ እኔን ተደግፈህ ... አንተን ተንተርሼ ከጠቆረው ሰማይ ... አይናችንን ሰፍተን…
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 3 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 8 months ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago