የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc
2⃣ آیگرام پلاس نسخه 4.2.1
دانلود از کافه بازار:
https://cafebazaar.ir/app/org.telegram.igram.plus/
3⃣ آیگرام سوم نسخه 4.2.1
የዛሬ ሐሙስ ታሕሳስ 9/2012 ዐበይት ዜናዎች
1) የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የወላይታን ክልልነት ጥያቄ ለማፈን የመከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ወደ ዞኑ እየገባ ይገኛል ብሏል ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ፡፡ በዞኑ ግጭት ቢፈጠር ተጠያቂው መንግሥት ይሆናል፡፡ ወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ለደቡብ ክልል ካቀረበ ነገ ዐመት ይሞለዋል፡፡ እናም ሕገ መንግሥቱ ባለመከበሩ መንግሥት ለወላይታ ክልልነት ባስቸኳይ ዕውቅና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ በተያያዘ፣ ዛሬ በሶዶ ከተማ የባጃጅ ሹፌሮች ጥያቄውን በመደገፍ ሰልፍ አድርገዋል፡፡
2) የቻይናዋ ሃንዥ ግዛት ልዑካን ቡድን ወደ መቀሌ እንዳይጎዝ መከልከሉን የትግራይ መገናኛ ብዙኻን ዘግቧል፡፡ ቡድኑ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የተመለሰው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው ተብሏል፡፡ የክልሉ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አብርሃም ተከስተ ወደ አዲስ አበባ ሂደው ከቡድኑ ጋር የማዕድን፣ ቱሪዝምና ግብርና የትብብር ስምምነቶችን ፈርመዋል፡፡ የትኛው የመንግስት አካል እንደከለከለ ግን ገና አለመታወቁን ሃላፊው ተናግረዋል- ብሏል ዘገባው፡፡
3) በዚምባብዌ የኢትዮጵያ ኢምባሲ 19 ኢትዮጽያዊያንን ዛሬ ከዛምቢያ እስር አስፈትቶ ወደ ሀገራቸው እንደሚመልስ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በፌስቡክ ገጹ ካሰራጨው መረጃ ተመልክተናል። እስረኞቹ የሚፈቱት ለዛምቢያ ጭምር የተወከለው የሐራሬው ኢምባሲ ከዛምቢያው ፕሬዝዳንት ጋር ባደረገው ስምምነት ነው። ኢምባሲው ሌሎች 25 እስረኞችን ለማስፈታት ጥረት ላይ ነው ተብሏል፡፡
4) ኢትዮጵያ ነገ የመጀመሪያዋን ሳተላይት ታመጥቃለች፡፡ ሳተላይቷ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማለዳ 12፡21 ላይ ወደ ሕዋ የምትመጥቀው ከቻይና ሳተላይት ጣቢያ መሆኑን የመንግስት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡
ቦይንግ ኩባንያ በመጨረሻ የ 737 MAX አውሮፕላኖችን "ለግዜው" ማምረት አቁሟል!
ቦይንግ ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ባጋጠሙ ሁለት አደጋዎች ከ300 ሰዎች በላይ ህይወት የቀጠፈውን አውሮፕላን በያዝነው የፈረንጆች አመት መጨረሻ ላይ ወደ በረራ ለመመለስ ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ የበረራ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች በፍጥነት በመመለሱ ስላልተስማሙ ኩባንያው ከመጪው ወር ጀምሩ ምርቱን እንደሚያቆም አስታውቋል ።
“መጪው ምርጫ ሁከትን ሊያቀጣጥል ይችላል” - ክራይስስ ግሩፕ #Election2020
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘንድሮ ይደረጋል የተባለዉ ምርጫ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየውን ክፍፍል ሊያሰፋው እና ሁከትንም የበለጠ ሊያቀጣጥል እንደሚችል ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተሰኘው ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም አስጠነቀቀ። በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ከተባባሰ የኢትዮጵያ መንግስት መጪውን ምርጫ የሚያካሄድበትን ጊዜ እንዲያዘገይ ተቋሙ መክሯል።
ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ይህን ያለው የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 6 ባወጣው ዳሰሳ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ቀውስ አምጪ ሁነቶችን በመተንተን የሚታወቀው ይሄው ተቋም በኢትዮጵያ በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎችየሚታዩትን ሁከቶች የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል ተንብዩዋል።
(Deutsche Welle)
በሰርጋቸው ድግስ እዳ ጭንቀት የገቡት ሁለት ናይጀርያውያን ጥንዶች እራሳቸውን አጥፍተው ሞቱ ።
ከሁለት ሳምንት በፊት ጋብቻቸውን የፈፀሙት ናይጀርውያን ጥንዶች ለሰርጋቸው ድግስ ብዙ ብር በመበደራቸውና በዚህም ጭንቀት ውስጥ በመግባታቸው ስርጋቸው ባለፈ በሶስተኛ ቀን እራሳቸውን አጥፍተው ሞተው እንደተገኙ በናይጀርያ ተነባቢ የሆነው ቶማስማርሴሎ ብሎግ አስነብቧል።
3 ቢልየን ዶላር የሚያክል ገንዘብ እንዴት ለኢትዮጵያ ተፈቀደ ብዩ ራሴን ስጠይቅ እና ምክንያቱስ ምንድነው ብዩ አስቤ አንዳንድ የዜና ምንጮችን ስመለከት ከስር ያለውን ነገር አነበብኩ.....
✔መንግሥት ከዐለም የገንዘብ ድርጅት 3 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘው የገንዘብ ምንዛሬ ተመኑን በገበያ እንዲወሰን ተስማምቶ እንደሆነ ዋዜማ ሰምታለች፡፡ ሀገር በቀሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሚተገበርባቸው ቀጣዮቹ 3 ዐመታት የጥቁር ገበያ ምንዛሬ አገልግሎት ሕጋዊ ፍቃድ ባላቸው የግል ወኪሎች እንዲከናወን ይደርጋል፡፡ መንግሽት የገበያ አሠራሩንም ይቀይራል፡፡
ይህ ምን ማለት ነው የምትሉ ካላችሁ ....
በኢትዮጵያ የምንዛሬ ተመን በየእለቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሚያወጣው ዋጋ ግብይት የሚፈጸምበት ሲሆን ፣ ብሄራዊ ባንክ ካወጣው ዋጋ ውጭና ከንግድ ባንኮች ውጭ የሚፈጸመው የውጭ ምንዛሬ ግብይት #ወንጀል ነው።
በቀጣይ ግን የምንዛሬ ዋጋ በገበያ እንዲተመን ፣ #በጥቁር_ገበያ የሚደረገው ግብይት ይፋዊ ሆኖ #ፍቃድ አውጥተው ግብር በሚከፍሉ የምንዛሬ አገልግሎትን ብቻ ለመስጠት በሚከፈቱ ተቋማት ለመተካት ታስቧል ማለት ነው።
በአጭሩ በ3 አመታት ውስጥ #BLACK_MARKET ህጋዊ ይሆናል ነው ቁምነገሩ።
በዚህም አለ በዛ ግን የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ሀይሎች እጁ እየተጠመዘዘ መሆኑ ማሳያ ይመስለኛል!
ዋልታ ቲቪ የዶ/ር ደ/ ፅዮን የውሸት ሞት ዜና ከየትኛው ኮምፒውተር እንደተፃፈ ኢንሳን ምርመራ አድርግልኝ ብሎ ጠይቋል።
ዋልታ ኢንፎርሜሽን የትግራይ ብሄራዊ ክልል መንግስት ም/ርእሰ መሰተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ሂወታቸው አልፏል በሚል waltainfo.com ገፁ ላይ ዛሬ ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም የለቀቀወን ሰው ለማወቅና ለፍርድ ለማቅረብ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) በኮምፒወተሮቹ ላይ ምርመራ እንዲያርግ ጥያቄ አቅርቧል ሲሉ የውስጥ ምንጮቼ ነግረውኛል።
Via tesfaye getnet
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከልን እንደሚከስ አስታውቋል!
ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር የትግራይ ብሄራዊ ክልል መንግስት ም/ርእሰ መሰተዳደር ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ሂወታቸው አልፈዋል ብሎ በዛሬው እለት ያሰራቸው ነጭ የፈጠራ ወሬ ፈፅሞ ሀሰት መሆኑን ለመላው ህዝባችን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ዋልታ ኢንፎረሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር waltainfo.com በሚል ፌስቡክ ገፁ ላይ ዛሬ ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም ከሰአት በኅላ ያሰራጨው ሀሰተኛ የአሉባልታ ወሬ፣ ይህ የመገናኛ አውታር ባለፉት አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ የብሄር ተኮር ጥቃት እንዲደርስ ስያካሂደው የነበረ ዘመቻ ኣካል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል፡፡
በመጨረሻም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር በህግ የሚጠቅይ መሆኑን ይገልፃል፡፡
የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ
ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc