የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ

Description
💥ይህ ቻናል የወልቂጤ ዩነቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ ዋናው ቻናል ነው ።
ስለጀማዓው ያሉ መረጃዎች፣ አስተማሪ እና መሳጭ እስላማዊ ትምህርቶች በዚሁ ቻናል ይለቀቃሉ ።
ይከታተሉን ፣ለሌሎችም ይጋብዙት
አላህ የሱን ፊት ፈልገንበት የምንሰራ እና ሙስሊሙን ኡማ የምንጠቅምበት ያድርግልን!

📩ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላቹ በ @wkumuslimsbot መላክ ትችላላችሁ
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

1 month, 2 weeks ago
1 month, 2 weeks ago

ገቢ ስታደርጉ
በ 0917601725/0928690312
መልዕክት በመላክ ይህን ያህል ልኬያለሁ በሉኝ ከሌሎች ሂሳቦች እንዳያወዘጋግበኝ። በተቻለ ፍጥነት እርስበርስ መረጃ ተለዋወጡና በዚህ ረመዳን ይጠናቀቅ።
ባረከላሁፊኩም።

1 month, 2 weeks ago
3 months, 2 weeks ago

አላሁ አክበርርርርር!!!!
አላሁ አክበርርርርር!!!
አላሁ አክበርርርርር!!!!

ዛሬ ጁመአ አንድ ወንድማችን ወደ ተፈጠረበት ሀይማኖት(እስልምናን )ተቀብሏል:: አላህ ፅናቱን ይስጥህ ሀቢቢ :: ቤተሰቦችህንም የምትወደውን ሲራጦል ሙስተቂም ይወፍቃቸው :: ዱንያህን ያሳምር :: ቀብርህን ያስፋ :: አኼራህን ይሙላ:: ሁሌም ከጎንህ ነን እስልምናን ስታዉቀው ይበልጥ ትወደዋለህ ሀያትህ ያምራል አላህ ኢማንና እውቀት ይወፍቅህ።

3 months, 2 weeks ago

አራት ትልልቅ  ጥቅሞቺ በጁምአ

➊ ለጁመአ  ሰላት መዘጋጀትና  መማለድ ያለው  ጥቅም 

ረሱል (ﷺ) እንዲህ  አሉ፡-

ለጁምአ ሶላት ያስታጠበና  የታጠበ ከዚያም የማለደና በመጓጓዣ ሳይሆን በእግሩ የሄደ ፡ ከኢማሙ  ቀርቦ ሳያለግጥ ያዳመጠ ሰው፡

በየ እርምጃው  ሌሊቱን  ቁሞ  ቀኑን  ፁሞ እንዳሳለፈው  አንድ አመት  ኢባዳ  ያገኛል ፡፡

የጁምዐ  እለት  ታጥቦና በሚቺለው ፀድቶ ቅባቱን  ተቀብቶ ወይም  ከቤተሰቡ  ሽቶ  እንኳን ቢሆን ተቀብቶ ወደ መስጅድ የሄደ፡ በሁለት ሰዎቺ መካከል ሳይለያይ አላህ ያለለትን ሰግዶና ኢማሙ ሲናገር ፀጥ ብሎ አዳምጦ የተመለሰ ሰው እስከሚቀጥለው ጁምአ ድረስ ያለው ወንጀል ይማርለታል ፡፡

➋  ረሱል (ﷺ) ሰላዋት ማውረድ ጥቅም

ነብዩ  ﷺ እንዲህ አሉ ፡-

አንድ  ግዜ  በእኔ  ላይ ሶለዋት  ያወረደ ሰው በእርሱ  ላይ  አላህ  አስር ጊዜ ሶለዋት  ያወርድበታል ፡ አስር  መንጀልም  ይሰረዝለታል፡ አስር ደረጃ ይጨመርለታል ፡፡

➌  የሱረቱ  ከህፍ (ከዋሻ ምዕራፍ ) መቅራት ጥቅም

ነብዩ ﷺ እንዲህ  አሉ ፡-

ከሱረቱ ከህፍ አስር  አንቀፅ የሐፈዘ  ሰው  ከደጃል  ተንኮል  ይጠበቃል፡  ደጃልን  ያገኝ  ሰው  በሱ  ላይ ሱረቱል ከህፍ  መግቢያ ያንብበት ብለዋል ፡፡

የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል ፡፡

➍   በጁምዐ  ቀን  ዱአ  ማረግ ጥቅም

አላህ  በጁመአ  ቀን የዱአ አድራጊን  ዱአ የማይመልስበት (ዱአውን የሚቀበልበት )  አንድ ሰአት አለቺ  ብለዋል ፡፡

ዑለሞቺ በተለይም  የቀኑ መጨረሻ ሰአት  ላይ  እንደሆነ  ተናግረዋል ፡፡

አላህ  የምንጠቀምበት  ያድርገን !!!

3 months, 2 weeks ago

...ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም ...
ርእስ- ለዐለና ነተፈከር...
ታች ክፍል እንደነበርኩ ፊዚክስ ስንማር optics ላይ behaviour of magnetic wave አካባቢ 7 ከለሮችን ለመሸምደድ VIBGYOR የሚል ኮድ ተጠቅሜ ነበር ...
ስንተነትነውም ፦
1. V - violet 2. I - indigo
3. B - brown 4. G - green
5. Y - yellow 6. O - orange
7. R - red
ነዉ ።
ለማንኛውም ብዙ ጊዜ ቁርዐን ውስጥ ቁጥራዊ ተዐምር አለ ሲባል እንድናስተነትን ነውና ዛሬም እንድናስተነትን ይረዳን ዘንድ አንድ ቁጥራዊ ተዐምር ይዤ መጥቻለሁ ተከተሉኝ
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ዋና ዋና ከለሮች የሚባሉት 7 ቱ የቀስተደመና ከለሮች ቀይ,ደማቅ ሰማያዊ,ቡናማ,አረንጓዴ ,ቢጫ , ብርቱካናማ እና ሀምራዊ ናቸዉ ። በሚገርም ሁኔታ በተመሳሳይ ቁርዐን ውስጥ አልዋን (ቀለም) የሚለው ቃል 7 ጊዜ ተጠቅሷል። የተጠቀሰበት ቦታም እንደሚከተለው ነዉ
1.ሱረቱ ነሕል አያት ቁጥር 13.
2.ሱረቱ ነሕል አያት ቁጥር 69.
3.ሱረቱ ሩም አያት ቁጥር 22.
4.ሱረቱ ፋጢር አያት ቁጥር 27.
5.ሱረቱ ፋጢር አያት ቁጥር 27.
6.ሱረቱ ፋጢር አያት ቁጥር 28.
7.ሱረቱ ዙመር አያት ቁጥር 21.
->7 ቀለማት 7 አልዋን (ቀለም) ከሚል የቁርአን ቃል ጋር ...
ይህ የአላህን ተዐምር በግልፅ የሚያሳይ ነዉ ።
👉በተጨማሪም ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) በሀዲሳቸው ጀሀነም መጀመሪያ ቀይ ከዛ ነጭ ከዛ ጥቁር እንደሆነ እና አሁን ጥቁር እንደሆነ አስገንዝበዋል ። ጀነትን ደግሞ ከአረንጓዴ ጋር ማያያዝ እንችላለን የቁርአን አያም ስላለ, እንዲሁም የጀሀነም በር ብዛት 7 ሲሆን የጀነት ደግሞ 8 ነው።
በቁርዐን ውስጥ አረንጓዴ የሚለው ቃል 8 ጊዜ እንዲሁም ጥቁር የሚለው ቃል 7 ጊዜ ተጠቅሰዋል ።
ይህም ሌላው የቁርዐንን ድንቅ ተዐምር የሚያሳይ ነዉ ።
~ሱብሐነ መን ዐዘ ፈርተፈዕ~
አላሁመ ጅዐልና ሚነል ሙፍሀሚን
ምንጭ : Dr. Abduldaim kaheel
ጸሀፊ : reyu habib

3 months, 3 weeks ago

😘 #እናት! 😘

✔️በኡመር ረ.ዐ ዘመን ነው አንድ ሠውዬ እናቱን ሀጅ ሊያስደርጋት ከየመን መካ ድረስ ተሸክሟት ይመጣል ።
አስቡት መኪና በሌለበት አውሮፕላን ባልታሰበበት ዘመን እናቱን በጀርባው ተሸክሞ ከ2.000ኪሎ ሜትር በላይ ዳገቱን ቁልቁለቱን ተራራውን አቋርጦ መካ ድረስ መምጣት? በዛ ላይ ሰውየው ምን እንዳለ ታውቃላችሁ?

… "በአላህ ይሁንብኝ ግመሎች ሁሉ መንገዱን ቢፈሩት እኔ ግን አልፈራሁትም "… ይል ነበር ።
ጉዞውን ጨርሶ መካ ሲገባ የአማኞች መሪ (ኡመር ኢብኑልህጣብን )ረ.ዐ ያገኛቸዋል።

⭐️ከጀርባው እናቱን እንደተሸከመ ሳያወርዳት ውስጡ ያለውን ጥያቄ ጠየቃቸው
…" አንቱ የአማኞች መሪ ሆይ አሁን የእናቴን ሀቅ አልተወጣሁምን ? "…ማለት ይጠይቃቸዋል ።
ኡመር ኢብኑል ህጣብ የሰውየውን ድካም ቢረዱም የሠጡት መልሥ ግን አስገራሚ ነበር ።

🍃" በአላህ ይሁንብኝ አንተን ለመውለድ ስታምጥ አንድ ጊዜ የተጨነቀችውን አይሆንም ወይም አንድጊዜ እንቅፋት ሲመታህ የተጨነቀችውን አይታካም " በማለት ነበር የመለሡለት ።

‼️ሱብሀን አላህ !!!
አስተውል ጀነት ያለው በእናት እግር ሥር ነው

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

3 months, 3 weeks ago

በዝምታ ወደ ክፍሉ እንድራመድ አዘዘኝ። ወደ መቅደሱ ወሰደኝ። ምንጣፍ፣ መደርደሪያ ላይ የተቀመጡ መጽሐፍትና ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለን ሠይፍ ክፍሉ ውስጥ አየሁ፡፡
በእርጋታና እጄን ይዞ ዝቅ ባለ ድምፅ እንዲህ አለኝ:- “ልጄ! አሁን ትልቅ ሰው ሆነሀል፡፡
ለረዥም ጊዜ ከአንተ የደበቅነውን ምስጢር ልነግርህ እፈልጋለሁ። ከሁሉም ሰው ደብቀህ ልታቆየው ትችላለህን? ይህ ምስጢር ከተሰማ የአባትህ ሰውነት በዲዋን አት-ተፍቲሽ ወታደሮች ለሥቃይ ያጋልጣል” አለኝ። የዲዋን ተፍቲሽን ሥም ስሰማ ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጣቶቼ ነዘረኝ፡፡ እርግጥ ነው ገና ልጅ ነበርኩ። ነገር ግን የዲዋን ምርመራ ምን እንደሆነ ጠንቅቄ አውቃለሁ። በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ የተገደሉ ሰዎችን አስክሬን በመንገዴ ላይ አሸታለሁ። አንዳንዶች እንጨት ላይ ተንጠልጥለው አያለሁ። አንዳንዶችም በቁማቸው ተቃጥለው ከስለውና ጠቁረው እመለከታለሁ። ከሴቶችም ሆዳቸው ተተልትሎ አጥንታቸው ተሰብሮ በፀጉራቸው የተንጠለጠሉ አስክሬኖችን በአይኔ ገርምሜ አልፋለሁ። አዎ ይህ ሁሉ ሙስሊሞች ላይ የሚከወን ነው። ዝም አልኩ ምንም መልስ
አልሰጠሁም፡፡ “የምነግርህን በድብቅና በምስጢር መያዝ ትችላለህን?” ሲል ዳግም ጠየቀኝ። “አዎ” አልኩት፡፡ “ድምፄን ከፍ ማድረግ ስለማልችል በደንብ አድምጠኝ። ግድግዳዎቹ ንግግሬን የሚሰሙበት
ጆሮዎች ኖሯቸው ወደ ዲዋን ቢሮ ይመሩኝና በሕይወት ያቃጥሉኛል ብዬ ስለምሰጋ በሚገባ ስማኝ” አለ፡፡ ጭንቅላቴን በመነቅነቅ እሺታዬን ገለፅኩለት፡፡ መደርደሪያው ላይ ወዳለው መጽሐፍ እየጠቆመ “ልጄ! ይህን መጽሐፍ ታውቀዋለህን?” ሲል ጠየቀኝ። እንደማላውቀው ነገርኩት፡፡ “ይህ የአላህ መጽሐፍ ነው” ዓይኖቹን አይኔ ላይ ተከለ። “እየሱስ የተላከበት መጽሐፍ ቅዱስ ማለትህ ነው?” ብዬ ጠየቅኩት። “አይደለም ይህ ቁርኣን ነው የብቸኛው ጌታ የአላህ ቃል! ከፍጡራኖች ሁሉ ምርጥ በሆኑት ነብይ ሙሐመድ ላይ የወረደ” ዓይኖቼ ፍጥጥ አሉ ግራ ገብቶኝ ንግግሩን ቀጠለ “ይህ የእኛ የሙስሊሞች መጽሐፍ ነው። ሰዎችን ወደትክክለኛው እምነት እንዲጣሩ በረሱል ላይ የወረደ፡፡ ከባህር ማዶ ከምድረ በዳው ከሞቃታማው በረሃ በመካ ምድር ሙሽሪኮችን ወደተውሂድ ተጣሩ። አላህም በሳቸው አማካኝበት ህዝቦችን ወደ ቅናቻው መንገድ መራ። ህብረት እና አንድነት፣
እውቀት እና ሥልጣኔን ቸራቸው። ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድል አድርገው በማሸነፍ ከኢስላማዊ ግዛት ጠቀለሏቸው። እዚህም ስፔን ደረሱ። ንጉሱ ጨካኝ ስርአቱም ኢ-ፍትሃዊ ነበር። ኢስላም ሳይደርሳት በፊት እጅግ ኋላቀር የነበሩ ህዝቦች ይኖሩባት ነበር። አምባገነናዊ አስተዳደር የሰፈነበት፣ ድንቁርና ያየለበት፣ ንፅህና የማይታወቅበት፣ ገላቸውን በዓመት አንዴ ወይም ሁለቴ ብቻ በሚታጠቡ
ህዝቦች የተሞላች ፍፁም ድቅድቅ ጨለማ የነገሰባት ሀገር። አንዳንድ ጎሳዎቿ እንኳንስ መፃፍና ማንበብ ይቅርና ቋንቋ ያልነበራቸው በምልክት ብቻ የሚግባቡ ነበሩ። ከኢስላማዊው ድል በፊት የመሀይምነት ጥግ ላይ የደረሰች አህጉር ነበረች። የኢስላም ጀግኖች ጨቋኙን ንጉሥ አሸንፎ ኢ-ፍትሃዊውን መንግሥት አስወገዱ። ስፔንንም ተቆጣጠሩ። ፍትሕን አሰፈኑ። ነዋሪዎቿን መልካም አያያዝን ያዟቸው። ለሕይወታቸውና ለገንዘባቸው ደህንነት ሰጡ። ለስምንት መቶ ዓመታት እኩልነትን ሰፈነ። በሥልጣኔ የመጠቀች እጅግ ውብ ከተማ አደረጓት አዎ! ልጄ እኛ ሙስሊሞች ነን ...” በድንጋጤ፣ በመደነቅና በፍርሃት አንደበቴ ተሳሰረ። “እኛ? ... ሙስሊሞች!” አዎ እኛ ሙስሊሞች በእያንዳንዱ የአንደሉስ ቦታ ዱካችን አለ። በእያንዳንዱ ስንዝር መሬት የአያት ቅድመ አያቶቻችን አፅም ተቀብሯል። እነርሱ ሸሂዶቻችን ናቸው። ይህንን ከተማየሠራነው እኛ ነን። እነዚያን ድልድዮች የገነባነው መንገዶችን ያነጠፍነው እኛ ሙስሊሞች ነን። ጉርጓዶችን ቆፍረን ዛፎች
ተክለናል፡፡ ከአርባ ዓመት በፊት ግን... ድምፁ ተቋረጠ። ዓይኖቹ ዕንባን ማርገፍ ጀመሩ።
ንግግሩን ቀጠለ “ከዛሬ አርባ ዓመታት በፊት የዚህ ምድር የመጨረሻው ሙስሊም ንጉሥ በቃል ኪዳናቸው ተታሎ የገርናጣን ቁልፎች አስረከበ። ከተማዋ የሙስሊሞች መቃብር ሥፍራ ሆነች፡፡ ቁልፉን ሲረከቡት ነፃነት፣ ፍትሕ እና ለሕይወታችን የዋስትና ቃል ኪዳን ገብተውልን ነበር። የሥልጣኑ ወንበር ላይ ሲቀመጡ ግን ቃል ኪዳናቸውን አፈረሱ። የምርመራ ዲዋን አቋቋሙ። ሁላችንንም በግድ
ክርስትናን አጠመቁን። ቋንቋችንን አስተውን። ልጆቻችንን ነጠቁን። ክርስትናን አልቀበልም ያለን ሁሉ በመርፌያማ ብረት ውስጥ እያስገቡ፣ አናቱን ዘቅዝቀው ከወገቡ እየቀጩ ሰውነቱን በጋለ እሳት እያቃጠሉ ያሰቃዩና ይገሉታል። በድብቅ ቤታችን ውስጥ ሰላታችንን እየሰገድን ጌታችን አላህ እንዲምረን
መለመኑን ተያያዝነው። የልጆቻችን በአላህ መካድ የሀዘናችን ምስጢር ሆነ። አርባ ዓመታት የድንጋይ አለቶች ሊሸከሙት በማይችሉት ስቃይ ውስጥ ሆነን ታገስን። ልጄ! ይህ ነው ምስጢሩ ደብቀህ ያዘው። የአባትህ ሕይወት በከንፈሮችህ ላይ እንደተንጠለጠለ እወቅ፡፡ በአላህ እምላለሁ ሞትን ፈርቼ
አላውቅም። ከአላህ ጋር መገናኘትንም አልጠላም። ከክርስትና ወደ ኢስላም ብርሃን እስክታደግህ ድረስ ግን በሕይወት መቆየትን ፈለኩ። አሁን በአላህ ፈቃድ አድገሀል” አለኝ።
ቀናት አለፉ። አባቴ ያስተዋወቀኝ አንድ ሰው ነበር። አንድ ነገር ቢከሰት እርሱ ዘንድ እንድሄድ
ነግሮኛል፡፡ ወደ ሞሮኮ ለመሄድ እንድዘጋጅ ነገረኝ፡፡ “አባቴ እና እናቴስ?” አልኩት እጄን እየጎተተ “አባትህ እኔን እንድትሰማኝ አላዘዘህምን?” አለኝ። ከከተማዋ ርቀን ፀሓይ ለማታዋ ፈረቃ ተራዋን ስታስረክብ “ልጄ! ወላጆችህ ሸሂድነትን ተጎናፅፈዋል።
በደይዋኖች ተይዘው ተገድለዋል” አለኝ፡፡
ይህ የታሪካችን ተራኪ በሕይወት የተረፈው ልጅ ታላቁ ምሑርና የኢስላም ሊቅ ዓሊምና ጸሐፊ
ሙሐመድ ኢብን ዐብዱራፊዕ አል-አንደሉሲ ነው።
<<ታሪኩን የማያውቅ ትውልድ ታሪክ አይሰራም! >>
ሙሐመድ ሰዒድ(ማሒ)
https://t.me/wkumuslims
https://t.me/wkumuslims

3 months, 3 weeks ago

ታላቁ ቀን ጁምዓ!

ረሱል ‏(ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦

﴿خَيْرُ يَومٍ طَلَعَتْ عليه الشَّمْسُ يَوْمُ الجُمُعَةِ، فيه خُلِقَ آدَمُ، وفيهِ أُدْخِلَ الجَنَّةَ، وفيهِ أُخْرِجَ مِنْها، ولا تَقُومُ السّاعَةُ إلّا في يَومِ الجُمُعَةِ﴾

“ፀሀይ ከወጣችባቸው ጥሩ ‘የጁምዓ ቀን’ ነው።
➜ አደም የተፈጠረበት ነው።
➜ ወደ ጀነት የገባበት ነው።
➜ ከሷም ከጀነት የወጣበት ነው።
የትንሳዔ ቀንም በጁምዓ ቀን ቢሆን እንጂ አትቆምም።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል:  ‍854

5 months, 3 weeks ago

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

በ2015 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ል ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2014 ዓ.ል የመጀመርያ ሴሚስተር በውጤት እና በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድሮዋል (Withdrawal) በመሙላት ላቋረጣችሁ የዳግም ቅበላ (Readmission) ተማሪዎች

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹ አዲስ ገቢ ለሆናቹህ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን
በመጀመሪያ ምስጋና ሁሉን ቻይ ለሆነው ለሀያሉ ጌታ አላህ የተገባ ይሁን ::

በመቀጠልም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ሙስሊም ወንድም እህቶቹን መምጣት በናፍቆት እየጠበቀ  እናንተን በኢስላማዊ እሴት አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን አስናድቶዋል ::  ስለሆነም ከአሁን ሰዓት ጀምራችሁ ስለ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማወቅ የምትፈልጉትን ማንኛውንም መረጃ እንዲሁም ወደ ጊቢያችን ስትመጡ የሚቀበሏቹን ወንድሞች እና እህቶች ስልክ ከዚህ በታች በተቀመጡት ቁጥሮች በመደወል ማወቅ እና የሚያስፍልጋቹን ትብብሮች በመደወል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን

📞ማንኛውንም ጥያቄ አስተያየት እገዛ እና ትብብር የምትፈልጉ ወንድም እህቶቻችን በነዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ

📞+251963244320   ሰሚር አብዱሰመድ
©
📞+251935510034   ፈላሁዲን ናሲያ
©
📞++251916774673 አሊ ተካልኝ
©
📞 +251976810523 ሙሀመድ ፈቱዲን
©

የእህቶች አሚራ ስልክ ለማግኘት📞+251935510034 ከላይ ባሉት ስልክ ደውላችሁ መቀበል ትችላላችሁ

©ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

https://t.me/wkumuslims
https://t.me/wkumuslims

Telegram

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ

***💥***ይህ ቻናል የወልቂጤ ዩነቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ ዋናው ቻናል ነው ። ስለጀማዓው ያሉ መረጃዎች፣ አስተማሪ እና መሳጭ እስላማዊ ትምህርቶች በዚሁ ቻናል ይለቀቃሉ ። ይከታተሉን ፣ለሌሎችም ይጋብዙት አላህ የሱን ፊት ፈልገንበት የምንሰራ እና ሙስሊሙን ኡማ የምንጠቅምበት ያድርግልን! ***📩***ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላቹ በ @wkumuslimsbot መላክ ትችላላችሁ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago