ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ]

Description
በሰለፊይ ኡስታዞች በሀገራችኝ በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ መስጂዶች፣መርከዞች የሚሰጡ ደርሶች፣ኮርሶች፣ሙሓዳራዎች፣ እና የቁርዓን ተፍሲሮች እና ሙስሊሞችን የሚመለከት ልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ።
{ وَقُل رَّبِّ زِدْنِى عِلْمًا } سورة طه : ١١٤
[ " ጌታዬ ሆይ! እውቀትንም ጨምርልኝ" በል። ] ሱረቱ-ጧሃ: 114
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

3 months ago

?ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራም በጦራ ከተማ በትልቁ አቡበክር መስጂድ!!!!!!

? አስ ሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ  ወበረካቱህ፣

?የፊታችን ቅዳሜና ዕሁድ በጦራ ከታማ በትልቁ አቡበክር መስጂድ ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ ሁላችሁም ተጋብዛችሃል! !!!!!!!

? ተጋባዥ እንግዶች
???ከ አ አበባ???
??ሸይኽ አህመድ ሸይኽ ኣደም

??ኡስታዝ አብዱረህማን ዒልማ

??ኡስታዝ ሀሰን፡አብዱልሀሚድ

??ከወራቤ??
??ኡስታዝ ኻሊድ ሙሀመድና ሌሎችም

❤️?? ከጦራ❤️??
??ኡስታዛችን ኡስታዝ መሀባ ሳይዲ

??ኡስታዝ ሱልጣን ወርቂቾ

??እናም ሌሎችም የጦራ መሻኢኾች ይኖራሉ

?ይህንን የደዕዋ መድረክ ሊዩ ከምያደርጉት

?1 ሁለት ቀን የምቆይ ነው።ቅዳሜ ይጀመራል ዕሁድም ቀጥሎ ይውላል!!!

?2 ተላላቅና ውድ ዱዓቶቻችን በአንድ መድረክ የምናገኝበት ትልቅ መድረክ ነው!!!!

3 ኡመቱን ስያባሉ ፣ስያጣሉ፣ ስያራሪቁ፣የነበሩ ጉዳዮች በስፋት እንደሚዳሰሱ የምጠበቅበት!!!!

4 የተለያዩ ጥያቄዎች መልስ የምያገኙበት!!!!!!

5 ከተማችን ጦራ በአሏህ ቃል ናበመልዓክተኛ ሰ ዐ ወ ሀዲስ ደምቃ የምትውልበት ነው!!!

ስለዚህ ሁላችንም በጉግት የምንጠብቀው ልዩ መድረክ ነው!!!!!!

?መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይታሰብ ነው!!!! ከወዲሁ ፕሮግራሞቻችሁን አስተካክሉ ። ተዘጋጁ። የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ አይሰረም።ነቃ እንበል!!!!!

?ሌላው ለደዕዋ እንደ ድሮ  እሩቅ ቦታ በእግራችንም ሆነ በትራንስፖርት ተሳፍረን መሄድ እንለማመድ።እሩቅ ነው ፣ስራ አለብኝ አንበል?☹️

???አዋጅ         አዋጅ        አዋጅ  የሰማ ላልሰማ ያሰማ????

?ሼር በማድረግ መልዕክቱ ለብዙ ሰው እንዲደርስ የበኩልችሁን ተወጡ!!!

??ማሳሰቢያ ምንም አይነት ጥያቄ ያላችሁ ወንድሞች በአካል በመቅረብ መጠየቅ ትችላላችሁ ። በርቀት የምወረው ተራ ወሬ ሳይሸነግላችሁ ነፍሲያችሁን ረግጣችሁ ያለውን
እውነታ እንድታውቁ ለማለት ነው ።ሹክረን!!!!!

??ለይሰ አል ኸበሩ ከልሙዓየነህ!!!

??ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ??

https://t.me/selfochsilteworabee22

3 months ago

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
በመቀጠል የወራቤ ሙስሊም ሴቶች ጀምዓ ለተከታታይ ሁለት ቀን ለሙስሊም ሴት ወጣቶች ያዘጋጀዉ የምክርና የኮርስ ፖሮግራም በጣም ደስ በሚል መልኩ ለወደፊት ህልምን አሰንቆን ከትዉልዱ መስተካከል ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን ተስፍ ተስፋ ሰጥቶልን ፤ለትዉልዱ መስተካከል ቀጣይነት ያለዉን መፍትሄን ከታዳሚያን ተወያይተን አቅጣጫ ይዘን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለትዉልዱ መስተካከል የበኩሉን እንዲሰራ ሀላፍነትን ተቀባብለን ዛሬ ኡሁድ ቀን 17/2/2017 ፖሮግራሙን ለማጠናቀቅ በቅተናል!!!ይህ ህልማችን ሁሉ ወደ መሬት እንዲወርድ ለወፈቀንና ላሳካልን ጌታችን አሏህ ወደር የሌለዉ ምስጋና ይድረሰዉ!!!!الحمد لله!!! በመቀጠልም በሰዉ ደረጃ ለዚህ ፖሮግራም መሳካት እገዛ ያደረጉልንን እህት ወንድሞች جزاكم الله خير الجزاء ማለትን እንወዳለን!!በዚች በትንሿ አቅማችን በትንሿ እዉቀታችን በምናደርጋት የደዕዋ እንቅስቃሴያችን ከጎናችን ለምትቆሙ ለምታበረታቱን ሁሉ እጅግ ኣርገን እያመሰገን አሁንም በድጋሚ የወደፊቱ ትዉልድ  ሀላፊነት የጋራችን ስለሆነ እገዛቹና ትብብራቹ አይለይን የሚለዉ አማናችን ግን እንደቀጠለ ነዉ!!!!!  ላልተሳተፋት ወደፊትም ይደገማል አብሽሩ ብለን እያፅናናን  ለተሳተፋት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ በፖሮግራሙ ከተዳሰሱ ርእሶች ፦ 1ኛ/ ስለ ሀያእ በስሩም ስለአሏህ ሀያእ ማድረግ፣ ስለመላኢኮች ሀያእ ማድረግ፣ ስለሰዉም ሀያእ  ማድረግ እና ስለ ነፍስም ሀያእ ማድረግ በሰፊዉ ተዳስሷል 2ኛ/ስለ አማና በስሩም ተማሪ ሲማር ወደፊት ትልቅ አማናን ልሸከም እንደሆነ አስቦ መማር እንዳለበትና አማናን ተሸክመዉ ያሉ እህቶች አማናቸዉን/ሀላፊነታቸዉን በአግባቡ መወጣት የሙስሊም ማንነት እንደሆነ ተዳስሰዋል 3ኛ/መልካም ትዳርን ለማግኘት ቀድሞዉኑ ሚን መሆን ይጠበቅብናል የሚልም ርእስ ተዳስሷል ፤ በስሩም ትዳር ርዝቅ ስለመሆኑና ርዝቅ የሚፈለገዉ ከአሏህና አሏህን በመፍራት እንደሆ፣በወጣቱ ትዳር ዉስጥ ከመሰተር እንቅፋት ከሚሆኑበት ነገራቶች ዉስጥ ለምሳሌ የትዳርን ለዛ ከትዳር ዉጪ ማጣጣም፤  ከሚዲያዎች አጉል ቆዪታን እያደረጉ ግዜያቸዉን ያለ ፖሮግራም መግደል፤ ለምሳሌ  በቲክቶክ ወዘተ   ሌሎችም ተዳስሰዋል
4ኛ/ ዘረኝነት የጃሂሊያ ተግባር ስለመሆኑና የዘረኝነት አደጋዎች ተዳስሰዋል! እነዚ ለምሳሌ ያሂል የተዘረዘሩ ሲሆን ቡዙ አስተማሪና መሳጭ ትምህርቶች ተስተላልፈዋል አሏህ አድማጩንም ተናጋሪዉንም ይጥቀምበት እያልን
والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته

?جعلنا الله كالغيث اين ما وقعنا نفعنا!!?

የወራቤ ሙስሊም ሴቶች ጀምዓ

3 months ago
በስልጤ ዞን በዳሎቻ ከተማ ብረሃን(النور الإسلامية) …

በስልጤ ዞን በዳሎቻ ከተማ ብረሃን(النور الإسلامية) መርከዝ በአሁኑ ሰአት ሁፋዞችን እያስመረቀ ይገኛል

3 months ago
ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ]
3 months ago

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

ኢስላማዊ ዕውቀትን መፈለግ ግድ ነው፣ሆኖም ማንነታቸውንና ምን እንደሚያስተምሩ በሚገባ አጣርታችሁ ሳታውቁ በየ ማሕበራዊ ሚዲያው በሚለቀቁ የዋትሳፕ፣የቴሌግራም...ወዘተ ግሩፖች እየሮጣችሁ ጆይን አታድርጉ።

ኦንላይን ተራ ዕቃ ለመግዛት እንኳን ምን ያህል ነው የምትጠራጠሩትና የምትጠነቀቁት?፣ታድያ ለዲናችሁ የምታደርጉትን ጥንቃቄ ከዕቃ ጥንቃቄ አሳንሳችሁት ኢስላምን እንዳትቀሙት ስጉ።

ከአክፍሮት ሐይላት እስከ ባጢል አንጃዎች በአብረቅራቂ ስሞች በየ ሚዲያው ብቅ ብቅ እያሉ ሰው እያጠመዱ ነው የሚውሉት፣ለዝህ ተጨባጭ ማስረጃ ስለማውቅ ነው።በአሁን ጊዜ ከጴንጤና ጠማማው ሺዓ እስከ ቁርዓኒይ ነን የሚሉ መሐይሞች ብሎም ኸዋሪጆች...ወዘተ ያሉ አጥማሚ አንጃዎች እስከ ቤታችን ወይም መስጂድ ድረስ ሳይመጡ፣ማን እንዳስቀራውና ዬት እንዳለ እንኳን በማይታወቅ የፊትና ኡስታዝ የሚልን ተቀፅላ በያዘ አጥማሚ ግለ-ሰብ አማካኝነት በተለይም እዝህ መንደር ተጥዳችሁ የምትውሉት እየታደናችሁ ነው።

ዲንህን ጊዜ ሰጥተህ ለመማር ባትችል፣በኦንላይን እንኳን ዬት መማር እንዳለብህ የምትጠይቀው አንድ የተሻለ ግንዛቤ ያለው ወንድም በዙሪያህ አይጠፋም መቼም።ይሄንን ስፅፍ ያየኋቸውንና ገብቼ ውይይት ያደረግኩባቸውን ቦታዎችን ብጠቅስ፣የሆነ ሰው «እስቲ እኔም ነገሩ ምን እንደሆነ ደርሼ ላጣራ» ብሎ ሄዶ እንዳይሰምጥ በመስጋት እንጂ አታች አደርግላችሁ ነበር።

ዞሮ ዞሮ ዲንህ ለአንተ ከነፍስህ በላይ ነው።ነፍስህ የተፈጠረችውም ለዲንህ፣የምትድነውም በዲንህ ነው።ለዝህ አላማ የተሰጠህ ጊዜና እድል አንድ ብቻ ሲሆን፦ እሱም አሁን እየኖርከው ያለው የዱንያ ሕይወትህ ብቻና ብቻ ነው።ኣኺራ ደርሰህ አንዴ ከወደቅክ ላሻሽል የማይባልበት የአንድ ጊዜ እድል።

እስቲ ሀቅ እናውራና፦ አላህ ሀላፊነቱን ስለወሰደልን ኑሮና ሪዝቅ የምንጨነቀውን አንድ በመቶውን እንኳን ስለ ዲናችን፣ኻቲማችን እንጨነቃለንን? ከኛ መካከል አላህ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር።

በዝህስ ሁኔታችን ለመሞት እንወዳለንን? ሀቂቃ ብዙዎቻችን ዲናችንን በሚዲያ ከሚናፈሰውና ከሚነዛው ፖለቲካ ሁሉ ቀላቅለን ነው የምንረዳውም የምንኖረውም።እንደውም በርካቶቻችን ስለ ዲን ምንም የማናውቅ፣ስለ ፖለቲካም ሆነ፣ስፖርት...ወዘተ ብዙ የምንፈተፍት ነን። ወላሁልሙስተዓን! አላህ ይዘንልን ብቻ።

✍️ ሙከሚል ከማል አብደሏህ

3 months, 1 week ago

الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات!
عمل يثلج الصدر ويبث الفرح في قلب كل محب للدين وظهوره.
سائلين الله لكل من ساهم في تحقيق هذا الانجاز خير الحزاء وأوفره.

3 months, 1 week ago

የቴሌ እና ሌሎች አክሲዮኖችን ስለመግዛት

«የቴሌን ሼር መግዛት ኢስላማዊ ብይኑ (ሑክሙ) ምንድን ነው?»

በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

3 months, 1 week ago

የቁርኣን ጀባት፦
በጩሚ ኡስታዝ ሙከሚል ከማል ወራቤ

3 months, 2 weeks ago

? አስደሳች ዜና | بشرى سارة ?

? ልዩ የምርቃት እና የ2017 የበጋ ቂርዓት መክፈቻ ፕሮግራም ?

➢ በወራቤ ከተማ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ

እንደሚታወቀው የአቡበክር አስ-ሲዲቅ መድረሳ በስሩ ከ 500 በላይ ተማሪዎችን አቅፎ የዲን ት/ት ሲያስተምር የቆየ መድረሳ ነው።

መድረሳው እነሆ በዘንድሮው አመት ከምንግዜውም በበለጠ የትምህርት አሰጣጡን ለማሻሻል ደፋ ቀና እያለ ሰነባብቷል።

ከነዚህም መካከል ላለፉት 2-3 አመታት ሲያስተምርባቸው የነበሩ የቆርቆሮ ክፍሎችን በማፍረስ፤  ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ መማሪያ ክፍሎችን እና ደረጃውን የጠበቀ መፀዳጃ ቤት በመገንባት  መድረሳውን ከምንግዜውም በላይ ለቂርዓት ምቹ አድርጎ እየጠበቀ ይገኛል።

ይህን በማስመልከት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 2 /2017 ዓ.ል በአይነቱ ልዩ የሆነ የምርቃት እና የበጋ ቂርዓት መክፈቻ ፕሮግራም መሰናዳቱን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው።

ፕሮግራሙ በመድረሳው ተማሪዎች በሚቀርቡ ልዩ ልዩ መሰናዶዎች ይደምቃል።
እርሶም በዚህ ልዩ እና አጓጊ ፕሮግራም እንዲሳተፉ   በአክብሮት ተጋብዘዋል።

? ማሳሰቢያ:

➢ ወላጆች የተማሪዎች ክፍል ድልደላ እንዲሁም በቂርዓት ዙሪያ ልዩ የውይይት መድረክ ስለሚኖር በአካል ልጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትገኙ ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን ።

?  ወራቤ ከተማ አቡበክር መስጂድ         
?  ቅዳሜ ጥቅምት 02/2017 ዓ.ል
  ከከጠዋቱ3:00 ሰዓት ጀምሮ

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago