Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Hakim

Description
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

1 month ago
አለማቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን

አለማቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን

ኦቲዝም በለጋ እድሜ ክልል የሚከሰት እክል ሲሆን፡ የማህበራዊ ግንኙነት ወይም መስተጋብር እዲሁም የተግባቦት ችግር ያመጣል፡፡

አንድ ነጥለን የምናወጣለት ምክንያት የለም ነገር ግን የተለያዩ መንስኤዎች ለኦቲዝም ሊያጋልጡ ይችላሉ፡ እነርሱም፡-

-ልጆች ያለ ጊዜ ከተወለዱ (7ወር እና ከዛ በፊት)
-ሲወለዱ ክብደታቸው አናሳ የሆኑ ልጆች
-በእርግዝና ጊዜ ኢንፌክሽን  እናት አጋጥሟት ከሆነ
-የዘረመል እክል/genetics/
-በርግዝና ጊዜ  የስኳር ህመም እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት
-በእድሜ ከገፉ በኋላ ልጅ መውለድ

ምን ምን ምልክቶችን ልናይ እንችላለን
-የእድገት ውስንነት ወይም መዘግየት
-የመጫወቻ እቃዎችን  በአንድ መስመር ብቻ ሁልጊዜ መደርደር
-በአከባቢያቸው ለሚፈጠሩ ክስተቶች የተዛባ ምላሽ መስጠት
-የማህበራዊ መስተጋብር ውስንነት
-የተደጋጋመ እና ለየት ያሉ ድርጊቶችን ማድረግ
-የንግግር ውስንነት

ህክምናው
✔️የባህርይ እንዲሁም
✔️የስነልቦና እና የመድሀኒት ህክምናን ያጠቃልላል።
✔️በጊዜ  ህክምናውን መጀመር ጥሩ ለውጥ እንዲመጣ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡
✔️ቤተሰብ፣ባለሞያ እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ሀላፊነት አለበት!

የእርሶን ጤና ለመጠበቅ እንተጋለን!
ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል

☎️ Make sure to call us on 0977717171/9171 to book an appointment.
📍 Address: Megenagna round about, Afarensis Bldg.

1 month ago
Hakim
1 month ago

የማህፀን መውጣት (Uterine prolapse)
በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

👉 ማህፀን በራሱ ቦታ ላይ እንዲቀመጥና ከቦታው ለቆ ወደታች እንዳይወርድ ወይም እንዳይወጣ የሚረዱ በዙሪያው ያሉ የተለያዩ ጅማቶች እና ጡንቻዎች ይገኛሉ።

👉 የማህፀን መውጣት አብዛኛውን ያገራችንን እናቶች በተለይም በገጠሩ ያሉ እና ብዙ ልጅ የወለዱ እናቶችን የሚያጠቃ የማህፀን ችግር ነው።

ለማህፀን መውጣት እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሱ ነጥቦች

💥በማህፀን አምጦ መውለድ
💥ረጅም ጊዜ ምጥ እያማጡ መቆየት
💥አንዲት ሴት እድሜዋ ጨምሮ የወር አበባ ማየት ስታቆም (ስታርጥ) ኤስትሮጅን (Estrogen) የተባለው ንጥረ ፈሳሽ በሰውነት ስለሚቀንስ ይህም በማህፀን አካባቢ ያሉ ጅማቶች እና ሽፋኖች እንዲሳሱ ስለሚያረግ ማህፀን በቀላሉ እንዲወጣ ሊያረግ ይችላል።

💥ለረጅም ጊዜ የቆየ ያልታከሙት ሳል ካለ
💥ለረጅም ጊዜ የቆየ ያልታከሙት የሆድ ድርቀት ካለ
💥ከፍተኛ የሆነ ውፍረት
💥ከባድ የሆኑ እቃዎችን ለብዙ ጊዜያት ማንሳት

💥የተለያዩ በቆዳችንና በመራቢያ አካሎች ሽፋን በጅማቶች እንዲሁም በተለያዩ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚገኝ Collagen የተባለ ንጥረ ነገር በተፈጥሮ ምክንያት በጣም ሲያንሱ ወይም ሲበዙ ይህ ችግር ሊከሰት ይችላል።

የችግሩ ምልክቶች

💥ከማህፀን ወደታች ገፍቶ የሚወጣ ነገር እንዳለ መሰማት እና በብልት በኩል ያበጠና የሚወጣ ነገር ማስተዋል

💥ከባድ ነገር ስናነሳ ወይም ስናስነጥስ፣ ስናስል ሽንት ማምለጥ ወይም ደግሞ ማህፀን በከባድ ሁኔታ ከወጣ ሽንት ለመሽናት እራሱ መቸገር

💥ሰገራን ሙሉ ለሙሉ ለማውጣት መቸገር፣ አንዳንዴ ደግሞ ሰገራ ማምለጥ

💥በሚወጣው የማህፀን ክፍል ወይንም ብልት ምክንያት የግብረስጋ ግንኙነት(sex) ለማድረግ መሸማቀቅ ወይም መደበር

💥የወጣው የማህፀንና ብልት ክፍል ውጭ ላይ ካለው ልብሳችን ጋር ሲነካካ የመቁሰል ወይንም የመድማት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።

👉 የማህፀን መውጣት ህክምና የሚያስፈልገው ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ሲያስከትል ብቻ ነው። አለበለዚያ ቀላል የሆነ የማህፀን ስፓርት ኬግል (Kegel Excercise) በማድረግ የወጣውን የማህፀን ክፍል እዛው ባለበት እንዲሆን እና ጨምሮ እንዳይወጣ ማድረግ ይቻላል።

👉 የማህፀን መውጣቱን ለህክምና እንዲረዳ በሚያመች መንገድ የማህፀን ሀኪምሽ በተለያየ ደረጃ የማህፀን መውጣቱን ሊከፋፍልና ህክምናውን ሊሰጥሽ ይችላል።

የማህፀን ስፓርት (Kegel Exercise) አሰራር

💥ስፓርቱ የሚሰራው በቀን ለ3 ጊዜ ሲሆን
💥ልክ ፈስ ወይም ሽንት ሊያመልጠን ስንል አፍነን እንደምንይዘው ለተወሰነ ሴኮንዶች በመያዝ ነው።
💥ይህም ለ 3 ሴኮንድ ያህል ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ሽንትና ፈስ ሊያመልጠን ስንል እንደምንይዘው አፍነን መቆየት ከንደገና ለ3 ሴኮንድ እረፍት መውሰድ ከንደገና መድገም ለ10 ጊዜ ያክል። ይህንን በቀን ለ3 ጊዜ ጠዋት፣ ምሳ አካባቢ እና ማታ ላይ ለ3 ወር ያክል መስራት ይኖርብናል።
💥ይህ ስፓርት በሁሉም ሴቶች ቢሰራ መልካም ሲሆን በተለይ የወለዱ ሴቶች ቢሰሩት ከወሊድ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የማህፀን መውጣት ይከላከልልናል።

👉 ሌላው ህክምና በማህፀን መግቢያ ጫፍ የሚቀመጥ በብልት በኩል የሚገባ ሰው ሰራሽ artificial የፕላስቲክ እቃ (pessary) ሲሆን ይህም ማህፀን ወደታች እንዳይወርድ ይከላከልልናል።

👉 የመጨረሻው የህክምና አይነት ደግሞ ኦፕሬሽን (operation) ሲሆን ይህም የተጓዳውን የማህፀን ረዳት ጅማቶች እና ግድግዳ ለይቶ ማጠንከር ሲሆን ህክምናው ወልደው ለጨረሱና ወልደው ላልጨረሱ ሊለያይ ይችላል።

👉ወልደው ለጨረሱ ሴቶች ማህፀኑ ብቻ ወቶ የተጎዳውን ቦታ በቀላሉ በማየት ማጠንከር ሲሆን ወይም ደግሞ ማህፀን እዛው እንዳለ የብልቱን ክፍል መድፈን ሊሆን ይችላል። ይህ ሁለተኛው እናቲቱ ምንም አይነት የወደፊት የግንኙነት ፍላጎት ከሌላት የሚሰራ ነው።

👉ወልደው ላልጨረሱ ሴቶች ደግሞ ማህፀን ሳይወጣ የማህፀን ወይንም የብልትን ጫፍ ከ ውስጠኛው የዳሌ ጅማቶች ጋር በማሰር ማህፀን እንዳይወጣ ሊደረግ ይችላል።

ዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት - 0911138054
Join the following telegram channel for more https://t.me/DrDawitMOBGYN

የሀኪም ቴሌግራም ገፅን ይጎብኙ: t.me/
@HakimEthio

3 months ago
Hakim
3 months ago

አመጋገብና ስሜቶቻችን

ምግብ በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ድርሻ የሚይዝ ነገር እንደመሆኑ መብላት/ መመገብ ከየዕለቱ ተግባራቶቻችን ውስጥ አንዱ እና ወሳኙ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ምግብ በስሜቶቻችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አለው፡፡በአመጋገብ፣ ስሜትና አዕምሮ ጤንነት መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነት አለ፡፡ የስሜትና የአዕምሮ መታወኮች የሰዎችን የተመጣጠነ አመጋገብ ምርጫ የሚያደናቅፉ ሲሆን በአንፃሩ ፍራፍሬዎችን፣ አትክልቶችን፣የቅባት እህሎችን እና ጤናማ የቅባት አይነቶችን የያዘ የተመጣጠነ የአመጋገብ ዘይቤ ልዩ ልዩ የስነ ልቦና መታወክ ምልክቶችን የማስታገስና የመቀነስ ውጤት እንዳለው
ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ በምግቦቻችን ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ንጥረ ነገሮች በአእምሮአዊ ንቃታችን እና ስሜታችን ላይ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል ስለዚህም አመጋገባችንን ማስተካከል ከአካላዊ ጤና በተጨማሪ የስነ ልቦና ጤናችንንም ለመጠበቅ ይረዳናል፡፡

ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የሜዲትራንያንን አመጋገብ (ማለትም አትክልትና ፍራፍሬዎችን፣ የቅባት እህሎች እና ጥራጥሬን አዘውትረው እና በከፍተኛ መጠን የሚመገቡ እንዲሁም ዶሮ፣ እንቁላል፣ የወተት ተዋፅዖንና ቀይ ስጋን ደግሞ አልፎ አልፎ) የሚመገቡ ሰዎች የድባቴ (የአዕምሮ ጭንቀት) ህመምን ከምዕራባውያን የአመጋገብ ዘይቤ (ማለትም ዝቅተኛ የአሰር መጠን፣ ከፍተኛ የሆነ ጤናማ ያልሆነ የቅባት መጠን፣ ስኳር እና ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ ማጣፈጫዎችን) ከሚከተሉት ሰዎች ባነሰ ሁኔታ ያሳያሉ፡፡

በሰውነታችን ውስጥ የነርቭ መልዕክትን በአንጎል እና በሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች መካከል የሚያስተላልፉት የመልዕክት አስተላላፊዎች በሰውነታችን ውስጥ የሚመረቱት በምንመገበው ምግብ ውስጥ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የደስታ ሆርሞን በመባል የሚታወቀው ሴሮቶኒን የሚሰራው በወተት፣ አጃ፣ ዶሮ፣ የቅባት እህሎችና የለውዝ ዝርያዎች ውስጥ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች ሲሆን ኤግዞርፊንስ የሚባሉት ደግሞ ከምግብ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ሲሆኑ በአንጎል መልዕክት ተቀባይ ክፍሎች ላይ የሚሰሩ እና ተፈጥሮአዊ ፀረ-ድባቴ (ፀረ-ጭንቀት) ናቸው፡፡

የጥሩ ስሜት ምግቦች፡

ቸኮሌት - ከተለያዩ መልዕክት አስተላላፊዎች ጋር በመገናኘት ስሜትን የማረጋጋት እና የምግብ ፍላጎትን የማስተካከል ተግባር አለው፡፡ ቸኮሌትን ሲመርጡ በተቻለ መጠን ንፁህ (ጥቁሩን) እና አነስተኛ የስኳር መጠን ያለውን መሆን ይኖርበታል፡፡

ወተት - በተፈጥሮ ውስጡ በሚገኙ ንጥረ ነገሮች ምክንያት የደም ግፊትን ዝቅ የማድረግ ውጤት እና ተፈጥሮዓዊ ፀረ-ድባቴ ባሕርይ ይታይበታል፡፡

ሙዝ - በውስጡ ባሉት ቫይታሚን ቢ6, ኤ እና ሲ፣ አሰር፣ ትራይቶፋን፣ ፖታሲየም፣ ፎስፈረስ እና አይረን ንጥረ ነገሮች አማካይነት ስሜትን የማነቃቃት ባሕርይ አለው፡፡

አረንጓዴ ሻይ - በውስጡ ውጥረትን/ ጭንቀትን የሚቀንስ ነጥረ ነገር አለው፡፡

ብሮኮሊ - በውስጡ ባለው ቫይታሚን ቢ6 አማካኝነት መጨናነቅን ይቀንሳል በተጨማሪም ያለው የፎሊከ አሲድ ንጥረ ነገር ድባቴን ለመዋጋት ያግዛል፡፡

ተልባ - ኦሜጋ 3 የተባለውን ለአዕምሮ እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ንጥረ ነገር ማምረቻ በውስጡ ይይዛል፡፡

ስሜቶችችን እና የስኳር አመጋገብ

የተጣሩ የኃይል ምንጭ ምግቦች (ለምሳሌ ስኳር እና የተፈተጉ እህሎች) ከመጠን ላለፈ ውፍረት እና ለስኳር ሕመም ከማጋለጣቸው በተጨማሪ በስነ አዕምሮ ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አላቸው፡፡ እነዚህን ምግቦች በከፍተኛ መጠን መመገብ በድባቴ እና ጭንቀት የመጠቃት ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፤ ይህም የደም ስኳር መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የመዋዠቅ ውጤት ነው፡፡

እንደ መደምደሚያ፡ በፍራፍሬ፣ አትክልት እንዲሁም ልዩ ልዩ እህሎችና ጥራጥሬዎች እንዲሁም በወተት፣ ዶሮ እንዲሁም ጤናማ የቅባት አማራጮች የተገነባ የተመጣጠነ የአመጋገብ ዘይቤን መከተል ለስነ ልቦና እና ስነ አዕምሮ ጤንነት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

ኢማን ዘኪ
የስነ ምግብ ህክምና ባለሙያ
በሚገባ እንዲያስቡ በሚገባ ይመገቡ!

የሀኪም የቴሌግራም ገጽ:- t.me/HakimEthio

3 months ago

የማንኮራፋት ችግር | Snoring disorder

የማንኮራፍት ችግር ማህበራዊ ጫና ከመፍጠሩ ባሻገር ጤና ላይ የሚያመጣዉ መዘዝ የጎላ ነው።

የማንኮራፋት ችግር የሚከሠተዉ አየር ከሳንባ ወይም ወደ ሳንባ በሚወጣበት እና በሚገባበት ጊዜ በሚያልፍባቸው የአየር ቱቦ በቂ የሆነ ክፍተት ካላገኘ ወይም የሚያልፍበትን የተመቻቸ መስመር የሚያስቀይር ችግር ካጋጠመው የሚፈጥረው የተዛባ ድምጽ (turbulent air flow) ነው።

ይህን የማንኮራፋት ችግር የሚያስከትሉ ምክነያቶች በህጻናት እና አዋቂዎች ላይ የተለያዩ ቢሆንም የሚከሠቱበትን ቦታ በ 4 ከፍሎ ማየት ይቻላል።

  1. ከአፍንጫ እስከ ላንቃ ያለው የአየር መተላለፊያ ሲሆን ህጻናት ላይ በአብዛኛው አዴኖይድ የምንለው የቶንሲል ክፍል መጠን መጨመርና በአፍንጫ የሚያልፈውን አየር ሲዘጋ የሚከሠት ነው። አዋቂወች ላይ ከዚህ ቦታ በሚነሳ ችግር ማንኮራፋት ከተከሠተ ካንሠርን ጨምሮ ሌሎች እብጠቶችን ማሠብ እና ምርመራ ማድረግ ግድ ይላል።

  2. ከምላስ የኋለኛው ክፍል እና በጎኑ ከሚገኙ ቶንሲሎች (posterior tounge and palataine tonsilar hypertrophy) ጋር ተያይዞ የሚከሠት ማንኮራፍት ነው። የዚህ ከምላስ ጎን የሚገኘው ቶንሲል የማንኮራፍት ችግር ከመፍጠሩ በላይ በ ተደጋጋሚ የቫይረስ እና የባክቴሪያ ኢንፌክሽን በመፍጠር ተጨማር የጤና እክል ያስከትላል።

  3. በአፍና መንገጭላ አካባቢ የሚከሠቱ የአፈጣጠር ችግሮች እንዲሁም ከነዚህ ቦታወች ተነስተው የኅለኛውን የአየር መተላላፊያ ሊዘጉ የሚችሉ እብጠቶች እንደ ምከንያት ይጠቀሳሉ።

  4. የኋለኛው የአየርና የምግብ የጋራ መተላለፊያ ግድግዳን የሚሠሩ ጡንቻወች መዛል ፣ በስብ መሞላት ፣ በእብጠት መጠቃት ወይም መግል መቋጠር ከተፈጠረ የሚከሠት ይሆናል።

ማንኮራፍት የሚከሠትባቸውን ምክነያቶች በወፍ ዘረር ካየን የዚህ ችግር መጠን ከሠው ሠው እንደተፈጠረው የአየር መተላለፊያ መስመር መጥበብ መጠን ይለያያል። ይሔም ከልማዳዊ ማንኮራፍት (habitual snorer) እስከ ሳንባ ከረጢቶች መጠን መቀነስ (pulmonary alveolar hypoplasia) ብሎም የሳንባ ደም ስሮች ግፊት እና የልብ ችግር ሊፈጥር ይችላል።

በተጨማሪም አካላዊና አእምሯዊ የእድገት ችግር ፣ የጸባይ ችግር (በተለይም ህጻናት ላይ) ፣ ቀን አብዝቶ የመተኛት ችግር ፣ በስራ የመዛልና ውጤታማ ያለመሆን እና የመሳሠሉ ተጽኖወችን ይፈጥራል።

በትዳር አጋር ላይ የሚፈጥረው ጫና እና ማህበራዊ ቀውሡም ሌላው ጉዳቱ ነው። ማንኮራፍት የፈጠረውን የጤና ችግር ደረጃ ለማወቅ አይነተኛ የሚባለው መሣሪያ (polysomnography ) ሲሆን በሀገራችን የለም ማለት ይቀላል። ነገር ግን ይሔንን ለመተካት የሚፈጠሩ ስሜቶችን እና ምልክቶችን በማየት እና የልብ ፣ የአተነፋፈስ ምርመራወችን በማድረግ ደረጃውን ማወቅ ይቻላል። የዚህን ጀረጃ ማወቁ ጥቅሙ ለእያንዳንዱ ደረጃ የሚሠጠው ህክምና የተለያየ መሆኑ ነዉ።

ወደ መፍትሔው ስንመጣ ፤ መፍትሔው የሚወሠነው ማንኮራፍቱን በፈጠረው ችግር እና የችግሩ መጠን ሲሆን

  1. በአብዛኞች ህጻናት ላይ ከአፍንጫ ጀርባ እና ከምላስ ጎን ያለውን ቶንሲል በሠርጀሪ በማስወገድ የሚስተካከል ይሆናል።

  2. በአዋቂወች ደግሞ እባጮች (እጢወች) እንደሌሉ ከተረጋገጠ በኋላ ክብደት መቀነስ ፣ የኦክስጅን ህክምና (CPAP) ብሎም የአየር መተላለፊያን ቱቦ ለማሥፍት የ ሚደረጉ ሠርጀሪወች (uvuloplalatopharyngoplasty
    ,uppp እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ሠርጀሪወች) የህክምና አማራጮች ናቸው።

ስለዚህ፦ ማንኮራፋትን እንደ ቀላል ችግር በማየት አንዘናጋ፤ቢያንስ ያለንበት የማንኮራፍት ጀረጃ በምን መሥተካከል እንደሚችል ሀኪሞችን እናማክር።

ዶ/ር አለማየሁ እሸት (ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት ፣ መምህር እና ረዳት ኘሮፌሰር )
አቢሲኒያ ሆስፒታል ደሴ

ለጥያቄ እና ቀጠሮ ለማስያዝ: 0908880810
alemayehueshet19@gmail.com

የሀኪም ቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ: t.me/HakimEthio

5 months ago

ጥቂት የሰር ዊሊያም ኦስለር ጥቅሶች

•ጎበዝ ሀኪም ህመምን ያክማል፡፡ የበለጠ ጎበዝ ሀኪም ግን በህመም የተያዘውን ግለሰብ ያክማል፡፡

•የሀኪሞች ቁልፍ ተግባር ሰዎች መድሀኒት የማይወስዱበትን መንገድ ማስተማር ነው፡፡

•ግለሰቡ ምን አይነት ህመም አለው ብለህ ሳይሆን ህመሙ ምን አይነት ግለሰብ አለው ብለህ ጠይቅ፡፡

•ከበሽታው ጥቃቅንና ረቂቅ መገለጫዎች ይልቅ ግለሰቡ ላይ ትኩረት አድርግ፡፡ ራስህን በሱ ጫማ አድርግ.....ፈገግተኛ አቀባበል፣ መልካም ንግግር፣ ችግሩን ማዳመጥ፡፡ እነዚህ ነገሮች ታካሚዎች በደንብ ይገቡዋቸዋል፡፡

•ያለ መፅሀፍት የሚያክም ሀኪም ያለ ኮምፓስ እንደሚቀዝፍ መርከበኛ ነው፡፡ ታካሚዎችን ሳያይ መፅሀፍ ብቻ የሚያነብ ሀኪም ጭራሽ ወደ ባህርም አልሄደም፡፡

•በሰዎች መካከል ልዩነት ባይኖር ህክምና ጥበብ የሌለበት ደረቅ ሳይንስ ይሆን ነበር፡፡

•ልዩነት የህይወት ህግ ነው፡፡ ሁለት አንድ አይነት ፊቶች የሉም፡፡ ሁለት አንድ አይነት አካል ያላቸው ሰዎች የሉም፡፡ ህመም ሲያጋጥማቸው አንድ አይነት ምላሽና አንድ አይነት ፀባይ የሚያሳዩ ሁለት ሰዎች የሉም፡፡

•አንዳንድ ሰዎች ምክር የሚጠይቁት ቀድመው የያዙትን አቋም ሰዎች እንዲያረጋግጡላቸው ነው፡፡

ሰር ዊሊያም ኦስለር ከህክምና ሳይንስ እኩል ከታካሚ ጋር ሰለሚኖር ሰብአዊ ግንኙነት የሚያሳስበው ታላቅ ሀኪም ነው፡፡ የህክምና ትምህርት ከክፍል ውስጥ ትምህርት በይበልጥ ታካሚን ወደ ማየት እንዲያዘነብል ባደረገው አስተዋፅኦ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በአለማችን ትልቅ የሚባለው የጆንስ ሆፕኪንስ ሆስፒታልን ከመሰረቱት ጥቂት ሰዎች አንዱ ነው፡፡

በዩቲዩብ ተቀላቀሉን https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

5 months ago

To post your papers on the channel, use this link t.me/HakimAds to send your PDF

@HakimEthio

5 months ago

Association between the stage of labor during cesarean delivery with adverse maternal and neonatal outcomes among referred mothers to tertiary centers in resource-limited settings

Dereje Zewdu, Temesgen Tantu, Fikretsion Degemu, Mukerem Abdlwehab

http://dx.doi.org/10.1136/bmjopen-2023-077265

@HakimEthio

5 months, 1 week ago

የስነ ልቦና የንግግር ህክምና አላማ

ጋሊሊዮ ጋሊሊይ ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት ምድር ጠፍጣፋ ሳትሆን እንደእንቁላል አይነት እንደሆነች ንግግር እያደረገ ነው፡፡ ከኃላ የተቀመጡ አንዲት ሴት ድንገት ሳቁ፡፡ ጋሊሊዮ ለምን እንደሳቁ ሲጠይቃቸው፡፡ "ስትሳሳት ገርሞኝ ነው፡፡ ምድር የኔ ልጅ እንደምጣድ ጠፍጣፋ ስትሆን የምትቀመጠውም የአንድ ኤሊ ጀርባ ላይ እንደሆነ አያቴ ነግራኛለች፡፡" አሉት፡፡ ጋሊሊዮ በተራው ሳቅ አለና "ኤሊዋስ ምን ላይ ነው የምትቀመጠው?" አላቸው፡፡ እሳቸውም ትንሽ ተናደው "ሌላ ኤሊ ላይ!" ብለው መለሱ፡፡ "ሌላዋስ ኤሊ?" ጠየቃቸው፡፡ አሁን በጣም ተናደዱ " ሌላ ኤሊ ላይ ነው፤ አስከታች ድረስ ኤሊ ላይ ነው!!፡፡"

አብዛኛው ስነልቦናችን የተቀረፀው በቤተሰቦቻችን በተለይ በወላጆቻችን ነው፡፡ ሰዎችንና አካባቢያችንን ማመን አለማመን፣ ጭንቀት ወይም ግድየለሽነት፣ ለስኬት መጣጣር፣ ደስተኝነት...ወዘተ፡፡ ጥሩ የሆኑትም ጥሩ ያልሆኑትም ማንነቶቻችን በብዛት ከወላጆቻችን የወረስናቸው ናቸው፡፡ ጥሩ ላልሆኑት ወላጆችን ከመውቀስ በፊት እነሱም እንዴት እንደዛ እንደሆኑ ማሰቡ ጥሩ ነው፡፡ እነሱም ወላጆቻቸው፤ ወላጆቻቸውም ወላጆቻቸው.... እያለ ይቀጥላል፡፡

ያለፉ ነገሮችን መለወጥ አንችልም፡፡ ወደፊታችንን ግን መለወጥ እንችላለን፡፡ የስነ ልቦና የንግግር ህከምና አላማ እንደ ሬኖልድ ኔህቦር ፀሎት ነው፡፡ ፀሎቱ እንደሚከተለው ነው፡፡ " አምላኬ መለወጥ የማልችለውን የምቀበልበት ፀጋ ስጠኝ፤ መለወጥ የምችለውን እንድለውጥ ብርታት ስጠኝ፤ ሁለቱን እንድለይ ደግሞ ጥበብ ስጠኝ፡፡" በቤተሰቦቻችን ያገኘናቸውን ስነ ልቦና የተወሰነውን መቀበል የተወሰነውን መለወጥ ይኖርብናል፡፡ የልጆቻችን ስነ ልቦና ላይ የምናሳርፈውን ተፅእኖም ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡

በዩቲዩብ ተቀላቀሉን https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako