قناة احمد علي على تيليجرام ( شروحات تقنية ، تطبيقات ، أفلام ومسلسلات ، خلفيات ، و المزيد )
Last updated 1 year, 3 months ago
يرمز تيليجرام إلى الحريّة والخصوصيّة ويحوي العديد من المزايا سهلة الاستخدام.
Last updated 1 year, 4 months ago
- بوت الإعلانات: ? @FEFBOT -
- هناك طرق يجب ان تسلكها بمفردك لا اصدقاء، لا عائلة، ولا حتى شريك، فقط انت.
My Tragedy Lies With Those Things That Happen in One Second And Remain
- @NNEEN // ?: للأعلانات المدفوعة -
Last updated 1 year, 5 months ago
«የተክፊር አመለካከት የተነሳው በ1950ዎቹ መጨረሻና በ60ዎቹ መጀመሪያ ቀናጢር እስር ቤት ታስረው የነበሩ ከፊል የኢኽዋን ወጣቶች መካከከል መሆኑን እንዲሁም በሰማእቱ ሰይድ ቁጥብ አመለካከትና መጣጥፎች ወጣቶቹ ተጽእኖ እንዳደረባቸውና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ጃሂሊያ ውስጥ ነው የሚልን ነገር ከመጣጥፎቹ መቅሰማቸውን ቀደም ሲል ጥቆማ አድርጌያለሁ... የዚህ አመለካከት ባለቤቶች ጀማዓዎቻቸው በአይነት ቢበዙም እንኳ በአሁኑ ሰኣት ያሉትን ኢስላማዊ ማህበረሰቦች ካፊር (ከኢስላም የወጡ) አድርገው ነው የሚያምኑት፤ ጃሂሊያነታቸውም በረሱል ዘመን የነበሩት ኩፋሮች ሳይሰልሙ በፊት እንደነበሩበት የጃሂሊያ አይነት ነው ብለው ያምናሉ...»
https://t.me/abuabdillahseid
?الإِخْوانُ المُفْسِدُون يُكفِّرُونَ الأُمَّةَ بِالجُمْلة?
ኢኽዋኖች የእነሱን ፈለግ የማይከተለውን ሙስሊሙን ማህበረሰብ በጅምላ ሲያከፍሩ ተመልከቱ‼
???
قال حسن البنا مؤسس جماعة الإخوان المسلمين:
«إننا نُعلِنُ في وُضوحٍ وصَراحةٍ أنَّ كُلَّ مسلمٍ لا يُؤمن بهذا المِنهاج ولا يعمل لتحقيقه لا حظَّ له في الإسلام!»
?(الرســائــل، صـ : ٨٦)
? የኢኽዋነል አንጃ መስራችና ቀዳማዊው መሪ ሐሰኑል በንና ለወጣቶች ያዘጋጀው "አር ረሳኢል" በመባል የሚታወቀው ኪታቡ (ገፅ: 86) ላይ እንዲህ ይላል፦
«በዚህ መንገድ የማያምንና ምድር ላይ እንዲገኝ ወይም እውን እንዲሆን ጥረት የማያደርግ እያንዳንዱ ሙስሊም፦ እስልምና ውስጥ ምንም አይነት ዕጣ ፈንታ የሌለው መሆኑን (አቋማችንን) በገሃድ እንገልፃለን‼»
ويقول علي العشماوي وهو آخِر قادة التنظيم الخاص للإخوان المسلمين:
«فمن أراد أن يَلْحَقَ بِنا فَهُوَ مسلمٌ، ومَن وقفَ ضِدَّنا فقد حكم على نفسه بِالكُفر!!»
? (التاريخ السري للإخوان المسلمين)
ص: ١٨٦) طبعة مركز ابن خلدون.
? "አትታሪይኹስ_ሲርሪይ ሊልኢኽዋኒልሙስሊሚን" የተባለው ኪታብ (ገፅ: 186) ላይም የኢኽዋን ልዩ ድርጅት የመጨረሻ መሪ የነበረው ዐሊይ አል ዐሽማዊ እንዲህ ይላል፦
«እኛን መከተል የፈለገ ሰው፦ ሙስሊም ነው፤ ከእኛ ተቃራኒ የሆነ አቋም የያዘ ሰው ግን ራሱ በራሱ ላይ ካፊርነቱን ፈርዷል»
وأما تكفير سيِّد قطب للمجتمعات الإسلامية فقد فاقتْ نظريات وجرأة رفاقه؛ فكثير من كُتُب سيد قطب ـ أمثال: "ظلال القرآن"، و"معالم في الطريق"، وغيرهما ـ مشحونةٌ بتكفير المسلمين.
? ሰይ፞ድ ቁጥብ የተባለው አንጋፋው የኢኽዋን ግለሰብ ድፍረትና በጊዜው ለነበረው ሙስሊም ማህበረሰብ የነበረው እይታ ደግሞ ከአቻዎቹ የተለየና እጅግ የገዘፈ ነበር። "ዚላሉል ቁርኣን" ፣ "መዓሊም ፊጠ፞ሪይቅ" እና መሰል መፅሃፎቹ ሙስሊሞችን በጅምላ ያከፈ፞ረባ፞ቸው በሆኑ ፅሁፎች የታጨቁ ናቸው!
فهذا الدكتور يوسف القرضاوي يقول في برنامج "فقه الحياة":
«الكتاب يَنْضَحُ بِفِكرةِ تكفير المجتمع، وأنا آسفٌ أن أقول هذا لولا أن الأمانة اقتضتني أنْ أقوله».
وعندما تعقبه المذيع بقوله: "أليس كل التفاسير لها وعليها؟"
أجاب القرضاوي: «نعم هناك أخطاء جزئية لكل مفسر، ولكن الخطأ في الظلال هو في الاتجاه حيث إنه محمَّل بفكرة كلية حول المسلمين الحاليين وأنهم كفار لا مسلمين».
? አንድ ወቅት ዩሱፍ አልቀረዿዊ "ፊቅሁል ሐያት" የተባለ ፕሮግራሙ ላይ:
«የሰይ፞ድ ቁጥብ ኪታብ ሙስሊሙን ማህበረሰብ አክፋሪ የሆነ አመለካከትን ያዘንባል፤ (የእውቀት) አማና (እውነታውን) እንድናገረው አስገድዶኝ (እንጂ ልናገረው የማልፈልገውን) ይህን ንግግር በመናገሬ አዝናለሁ» በሚል ተናገረ፤
? የፕሮግራሙ አዘጋጅም ቀርዿዊን እንዲህ ሲል ለማረም ሞከረ፦
«(ለምን "ዚላል" ብቻ) ሁሉም የተፍሲር ኪታቦችስ የሚመሰገኑበትና የሚወቀሱበት ነጥብ አላቸው አይደልን!?»
? በዚህ ጊዜ ዩሱፍ አልቀርዿዊ የሰይድ ቁጥብ ተክፊር ከዚህ የተለየ መሆኑን እንዲህ ሲል ገለፀለት፡
«አዎ ሙፈሲሮች ከፊል ስህተቶች ይኖርባቸል፤ (የሰይድ ቁጥብ) "ዚላል" ውስጥ ያለው ስህተት ግን አቅጣጫው ላይ ነው፤ ምክንያቱም ኪታቡ ዛሬ ጊዜ በሚገኙ ሙስሊሞች ዙሪያ በሰይ፞ድ ጠቅላይ አመለካከት የታጨቀና እነዚህ ሙስሊሞች፦ ኩፋሮች እንጂ (ትክክለኛ) ሙስሊሞች አለመሆናቸውን የገለፀበት መፅሀፍ ስለሆነ ነው።»
وقال القرضاوي أيضا:
«في هذه المرحلة ظهرت كتب الشهيد سيد قطب التي تمثل المرحلة الأخيرة من تفكيره، والتي تنضح بتكفير المجتمع، وتأجيل الدعوة إلى النظام الإسلامي، والسخرية بفكرة تجديد الفقه وتطويره وإحياء الاجتهاد، وتدعو إلى العزلة الشعورية عن المجتمع وقطع العلاقة مع الآخرين، وإعلان الجهاد الهجومي على الناس كافة، والاستخفاف بدعاة التسامح والمرونة ورميهم بالسذاجة والهزيمة النفسية أمام الحضارة الغربية، ويتجلى ذلك أوضح ما يكون في تفسير (في ظلال القرآن) في طبعته الثانية، وفي (معالم في الطريق) ومعظمه مقتبس من (الظلال)، وفي (الإسلام ومشكلات الحضارة) وغيرها»
? "أولويات الحركة الإسلامية"
? "አውለዊያቱል ሐረከቲል ኢስላሚያ" የተባለ መፅሀፉ ላይም ቀርዿዊ በድጋሚ እንዲህ ብሏል፦
«በዚህ ጊዜ የመጨረሻ የአስተሳሰብ እርከኑን የሚያንፀባርቁ፣ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚያስከፍሩ፣ ኢስላማዊ ስርዓት እስኪመጣ ድረስ ዳዕዋ ይዘግይ የሚሉ፣ ፊቅህን ማደ፞ስና ማዘመን በሚለው አመለካከት ተሳላቂ የሆኑ አመለካከቶችን የሚያዘንቡ…የሸሂዱ ሰይ፞ድ ቁጥብ መፅሀፎች ብቅ ብለዋል … ይህ አቋሙ "ዚላሉል ቁርኣን" በተሰኘው የተፍሲር ኪታቡ ሁለተኛው ዕትም ላይ፣ "መዓሊም ፊጦሪይቅ" በተባለውና በመሳሰሉት መፅሀፎቹ ውስጥ በጣም የጎላ ሆኖ ይታያል»
وقد قال فريد عبد الخالق عضو الهيئة التأسيسية لجماعة الإخوان المسلمين:
«ألمعنا فيما سبق إلى أن نشأة فكر التكفير بدأت بين شباب بعض الإخوان في سجن القناطر في أواخر الخمسينات وأوائل الستينات، وأنهم تأثروا بفكر الشهيد سيد قطب وكتاباته، وأخذوا منها أن المجتمع في جاهلية، وأنه قد كفر حكامه الذين تنكروا لحاكمية الله بعدم الحكم بما أنزل الله، ومحكوميه إذا رضوا بذلك».
إلى أن قال: «إن أصحاب هذا الفكر وإن تعددت جماعاتهم يعتقدون بكفر المجتمعات الإسلامية القائمة وجاهليتها جاهلية الكفار قبل أن يدخلوا في الإسلام في عهد الرسول صلى الله عليه وسلم، ورتبوا الأحكام الشرعية بالنسبة لهم على هذا الأساس» إلخ.
? "الإخوان المسلمون في ميزان الحق"
?የኢኽዋን ማህበር መስራች አካላት አባል የነበረው ፈሪድ ዐብዱልኻሊቅ የተባለው ግለሰብም "አልኢኽዋኑል ሙስሊሙን ፊ ሚዛኒል ሐቅ" የተሰኘው መፅሀፉ ላይ እንዲህ ይላል፦
???
قال بعضهم:
«طلبتُ الرَّاحةَ لِنفسي فَلَمْ أجِدْ لها أرْوَحَ مِن تَرْكِ ما لا يَعنيها، وتوحَّشتُ في البَرِيَّة فلم أَرَ وحشةً أكبرَ مِن قَرين السُّوء، وغالَبْتُ الأقرانَ فَلَمْ أَر قرينًا أغلبَ للرَّجل من المرأةِ السُّوء، ونظرتُ إلى كُلِّ ما يُذِلُّ القَوِيَّ ويَكْسِرُهُ فلم أرَ شيئًا أَذَلَّ لهُ ولا أكسَرَ مِن الفاقة»
? (التذكرة الحمدونية) لابن حمدون المتوفى سنة ٥٦٢هـ
https://t.me/abuabdillahseid
ሙግት የሚወድ ጭቅጭቅ
ስም መለጣጠፍ መለቅለቅ
ጠምዘዝ ጠምዘዝ ባይ ገልባጣ
ፋሽን ያረገ ዝርጠጣ
አንቀህ ስትይዘው ሽምጠጣ
ብስለት አትለው ሞኝነት
ደግሞ ደጋግሞ መወስለት
ላየው ይገርማል የእውነት
ህፍረት አያውቅም ለውሸት
✍ أبو نعمة الله سعيد شيخ حسن رحمه الله
ሙስጠፋ ጋራ አይቀብሩህ
ስትሞት ብቻህን ገቢ ነህ
ጠምዘዝ አትበል አብረከው
ፋፍቶ በውሸት አትርዳው
አስተውል ወንድም ልብ በል
ብልህነት ነው ተው ብሰል
ደግመህ ከሱ ጋር አትበድል
ላይኛው አምላክ ያይሃል
ህያው ነው እሱ ይይዛል
✍ أبو نعمة الله سعيد شيخ حسن رحمه الله
ሙርጂእ ሲል ዋሽቶ ተቀበልክ
ስማኝ ስላለህ ተረከብክ
ጠላት ነው ሲልህ ነቢልን
ፋጅር አድርገህ ስትመዝን
አቤት አቻቻል በደልን
ብዙ ተመኘህ መጣልን
ደሞም ድብድብ አስበህ
ላፍታ ያን ፍቅር እረስተህ
ህብረታችንን ሰባብረህ
ተረት ለጨቅሎች ስታጎርስ
ክፋት ላይጠቅም ትርምስ
ፊክራን አደረክ የለት ጉርስ
ርስትህ ሆነ ማስለቀስ
ይብላኝ ላልገባው የምባ ሱስ
✍ أبو نعمة الله سعيد شيخ حسن رحمه الله
☝️☝️☝️
الحمد لله الذي حقَّق أُمنِيتَنا التي كنَّا قد تمنَّيناها قبل أشهر.
? ዓፊያ መጠይቅን አብዙ‼
كَانَ عَبْدُ الْأَعْلَى التَّيْمِيُّ يَقُولُ:
? *«أَكْثِرُوا سُؤَالَ الْعَافِيَةِ، فَإِنَّ الْمُبْتَلَى وَإِنِ اشْتَدَّ بَلَاؤُهُ لَيْسَ بِأَحَقَّ بِالدُّعَاءِ مِنَ الْمُعَافَى الَّذِي لَا يَأْمَنُ الْبَلَاءَ،
? وَمَا الْمُبْتَلَوْنَ الْيَوْمَ إِلَّا مِنْ أَهْلِ الْعَافِيَةِ بِالْأَمْسِ، وَمَا الْمُبْتَلَوْنَ بَعْدَ الْيَوْمِ إِلَّا مِنْ أَهْلِ الْعَافِيَةِ الْيَوْمَ، وَلَوْ كَانَ بَلَاءٌ يَجُرُّهُ إِلَى خَيْرٍ مَا كُنَّا مِنْ رِجَالِ الْبَلَاءِ،
? إِنَّهُ رُبَّ بَلَاءٍ فِي الدُّنْيَا قَدْ أَجْهَدَ فِي الدُّنْيَا، وَأَجْزَى فِي الْآخِرَةِ، فَمَا يَأْمَنُ مَنْ أَطَالَ الْمُقَامَ عَلَى مَعْصِيَةِ اللهِ أَنْ يَكُونَ قَدْ بَقِيَ لَهُ فِي بَقِيَّةِ عُمْرِهِ مِنَ الْبَلَاءِ مَا يَحْذَرُهُ فِي الدُّنْيَا، وَيَفْضَحُهُ فِي الْآخِرَةِ،
ثُمَّ يَقُولُ عِنْدَ ذَلِكَ:
? الْحَمْدُ لِله الَّذِي إِنْ نَعُدَّ نِعَمَهُ لَا نُحْصِيهَا، وَإِنْ نَدْأَبْ لَهُ عَمَلًا لَا نُجْرِيهَا، وَإِنْ نُعَمَّرْ فِيهَا لَا نَبْلَى»*
?• رواهُ ابنُ أبي الدُّنيا في "كتاب الشكر" بسنده إلى عَبْدِ الْأَعْلَى التَّيْمِيِّ.
?• وذكره ـ أيضًا ـ ابنُ قيِّمِ الجوزية في كتابه "عُدَّة الصابِرين وذَخيرة الشاكرين"
https://t.me/abuabdillahseid
?لِمَاذَا اخْتَرْتُ الْمَنْهَجَ السَّلَفِيّ?
የሰለፊያ መንሀጅን የመረጥኩበት ምክንያት፦
● ተውሒይድንና ትክክለኛ ዐቂይዳን (እምነትን) ልዩ በሆነ ትኩረት ተምረውና ተላብሰው ለሌሎችም የሚያስተምሩት እነሱ ብቻ በመሆናቸው ነው።
● ከሺርክ እምነት፣ ከመቃብር አምልኮ፣ ከደጋሚዎች፣ ከጠንቋዮችና አጭበርባሪዎች በቁርኣንና በሐዲስ መረጃ በማስጠንቀቅ፤ እነዚህን እኩይ ተግባራት የሚፋለሙ ብቸኛ ጀግኖችም እነሱ ስለሆኑ።
● የነቢዩ ﷺ ሐዲሦችንና ከሰለፎች የተወሰዱ ፋናዎችን፤ ሰሒይሑን ከደዒይፉ ለማወቅና ለመለየት ልዩ ትኩረትና ጥናት የሚያደርጉት እነሱ ብቻ በመሆናቸው ነው።
● እነሱም ብቻ ናቸው፤ ዲይነል ኢስላም ላይ የተጨመሩ አዳዲስ ፈጠራዎችንና ቢድዓዎችን በሙሉ የሚያስጠነቅቁትና የሚፋለሙት።
● ከረሱል መዝሀብ ውጪ የሚደረግን የመዝሀብ ተዐስሱብንና ተሐዝዙብን (ቡድንተኝነትን) የሚኮንኑና የሚያስጠነቅቁም እነሱ ብቻ ናቸው።
● ትልልቅ ዑለማኦቻቸውን፣ መሻዪኾቻቸውንና፣ አኢማዎቻቸውን እንኳ በተቅሊይድ (ጭፍን ተከታይነት) መከተልን ርቀው፤ በደሊል የሚጓዙና ደሊል የሚገዛቸው (የሚሾፍራቸው) ሙተጀሪዶችም እነሱ ብቻ በመሆናቸው ነው።
● ህብረተሰቡ በተለይም ዲይነል ኢስላምንና ሀገር ተረካቢ የሆነው ወጣቱ ክፍል በተለያዩ አጉል ሱሶች ተጠምዶ የሸይጧን ምርኮኛ እንዳይሆንና ወደ ቅኑ ጎዳና ተመልሶ ለዓለማዊውም ሆነ ለዘላለማዊ ህይወቱ የሚበጀውን ስንቅ እንዲስሰነቅ፤ የተለያዩ መስዋእቶችን እየከፈሉ የሚገስፁ፣ ሴቶችም እርቃናቸውን እንዳይወጡ የሚመክሩና ሸሪይዓው ከሚከለክላቸው ከተለያዩ እኩይ ስነ ምግባሮችም እንዲርቁ፣ እንዲሁም በኢስላማዊ ስነ ምግባር እንደታነፁትና እንደተላበሱት መልካም ቀደምት ሰለፊይያት እንዲሆኑ የተቻላቸውን ጥረት የሚያደርጉ ናቸው።
● ሰለፊዮች ሽብርን፣ አመፅን፣ የፍንዳታ ተግባርንና መፈንቅለ መንግስትን፣ እንዲሁም ቤቶችንና ንብረቶችን አውዳሚ፣ ደም አፍሳሽና ህይወት ቀጣፊ የሆኑ አብዮቶችን ወደ መተውና መራቅ የሚሰብኩ ናቸው።
● የማንንም ስልጣን የማይሻሙ፤ ለመንግስታቶችም የማያስመስሉ (የማያታልሉ) ፤ ባለስልጣናት ደጃፍ ሄደው የማይዋደቁ፤ አድሎ ቢፈፀምባቸውና በደል ቢደርስባቸውም የሀገር መሪዎቻቸውን በመልካም የሚታዘዙና የሚሰሙ ናቸው።
● ሰለፊዮች፦ የትክክለኛ ፊቅህ ባለቤቶችና ሙሐድዲሦች ናቸው፤ ሙጅተሂዶችና መልካም መካሪዎችም ናቸው።
● የእኩይ ባህሪ ባለቤት የሆነን ሰው እኩይ ተግባሩን በመረጃ ከገለፁ፤ ሰዎች ዘንድ ምን ያህል ክብር ቢኖረውም፤ ክብረ ቢስ አድርገው ይጥሉታል።
ለዚህም ነው ኢማም ሙቅቢል ቢን ሃዲ አልዋዲዒይ: «አህሉሱንናዎች (በመረጃ) ያጥጣፍፉት ሰው ከወደቀበት መነሳት አይችልም» ይል የነበረው!!
● ብልሹ ተግባርን ከተመለከቱ የተከፋ ቢክከፋ የድርጊቱን ከንቱነት ይገልፃሉ።
● መሪያቸው ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ናቸው።
● መንገዳቸውም መልእክተኛው ሙሐመድ ﷺ እና ሶሓቦች ረዲየሏሁ ዐንሁም የነበሩበት ጎዳና ነው።
● ደዕዋቸው ድብቅ ነገር የላትም፤ ይልቁንም ውስጧ እንደውጯ ነው።
● ደዕዋቸው ውስጥ በሰው ህይወት መነገድ የለም።
● በደዕዋ ስራቸው ከሰዎች ምንዳንም ሆነ ምስጋናን አይፈልጉም።
● ከአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ፅናትን መጠየቅም የሁልጊዜ ዱዓቸው ነው።
● ቀዳሚ ደዕዋቸው ተውሒይድ ነው።
● ፈለጋቸው የነቢዩ ሱንናዎች ናቸው።
● መለያ ባህሪያቸውም የነቢዩን ፋና እግር በግር መከተል ነው።
● የሰዎች ውዳሴ አያታላቸውም፤ ወቀሳቸውም አያስጨንቃቸውም።
● በሐቅ ጎዳና ላይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የተቃረናቸው ጠላትም ሆነ፤ እርዳታውን የነፈጋቸው ወዳጅ አይጎዳቸውም። ይልቁንም ቅሮት የሌለው ሞት እስኪመጣቸው ድረስ በአቋማቸው ላይ ፅኑ ሆነው ይጓዛሉ።
─••──═••???•••═──••─
ያ አላህ! ምን ያህል ውብና የላቀ ደዕዋ ነው!!
─••──═••???•••═──••─
جعلنا الله من الذين يتبعون الكتاب والسنة بفهم سلف هذه الأمة : عقيدة وعملا ومعاملة ...، ونسأله سبحانه أن يثبتنا على الملة البيضاء التي ترك النبيُّ ﷺ أصحابه الأبرار عليها، ملةٌ ليلُها كنهارها لا يزيغ عنها إلا هالك .
{رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْوَهَّابُ}
?ከዐረብኛ የተወሰደ።
✍3/12/1441
https://t.me/abuabdillahseid
اللهم لك الحمد
قناة احمد علي على تيليجرام ( شروحات تقنية ، تطبيقات ، أفلام ومسلسلات ، خلفيات ، و المزيد )
Last updated 1 year, 3 months ago
يرمز تيليجرام إلى الحريّة والخصوصيّة ويحوي العديد من المزايا سهلة الاستخدام.
Last updated 1 year, 4 months ago
- بوت الإعلانات: ? @FEFBOT -
- هناك طرق يجب ان تسلكها بمفردك لا اصدقاء، لا عائلة، ولا حتى شريك، فقط انت.
My Tragedy Lies With Those Things That Happen in One Second And Remain
- @NNEEN // ?: للأعلانات المدفوعة -
Last updated 1 year, 5 months ago