Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ISLAMIC SCHOOL

Description
✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago

2 months ago

የረመዳን ተአምራት እና ዮሺኖሪ

በ አውሮፓያኑ አቆጣጣር 2016 የ አለማችንን ትልቁን ሽልማት Nobel Prize in Physiology or Medicine ሽልማት ያሸነፈው ፊዚዮሎጂስት Yoshinori Ohsumi ነው። ያሸነፈውም የ ሰውነትን controlled autophagy “የጽዳት ዘመቻ” ሳይንስ በድንቅ ምርምር ከደረሰበት በኋላ ነው። ታድያ ይህ ድንቅ ሰው የሰራው ስራ ስለ ረመዳን ጾም የተለየ ግንዛቤን የፈጠረ ነበር። እናብራራው...

የሰው ልጅ ለ 12 ሰአትና ከዚያም በላይ ብቻ ከጾመ "ኦቶፋጂ" (autophagy) በመባል የሚታወቀውን የሴል ሂደት ለመጀመር ያስችለዋል። ይህን ሂደት "የ ሰውነት የጽዳት ዘመቻ" በማለት ልንጠራው እንችላለን። እናም በዚህ የ "ኦቶፋጂ ጽዳት ዘመቻ በ ሰውነት በየቦታው የወዳደቀ ፕሮቲን (Damaged protein) የተበላሹ ሴሎችን ሳይቀር በሙሉ ጠራርጎ በማቃጠል ያስወግዳል።

በተፈጥሮ ያረጁ ሴሎች በ ህይወት እያሉ በምትካቸው ወጣት ሴል አይመረትም። ለምሳሌ ይህንን ሁኔታ በ መከላከያ ሴሎች (Immune system) አንጻር ብናይ የሰውነት ባረጁ ሴሎች መሞላት ተጸኖው ቀላል አይደለም። ሽማግሌ ፖሊስ ከሌባ እንደማያስጥለው ሁሉ ሽማግሌ የ መከላከያ ሴልም ከ በሽታ አያድንም። አንድ ሰው 12 ሰአት ጾም ሲጾም ሰውነት የ ምግብ ጉድለቱን ለመሙላት ሲል ሽማግሌ ሴሎችን ገድሎ ለምግብነት ይጠቀማቸዋል (ይበላቸዋል) (ሰው በተፈጥሮ የሚከሳው የራሱን አካል በልቶ ነው)። ሆኖም ስናፈጥር (ስንበላ) አዲስ ንቃት ያለው ወጣት ሴል እንዲፈጠር እድል ይሰጣል (immune cell recycling) ። በዚህም ሂደት ሁሉም ሴል ሲታደስ በዛውም የመከላከያ ሚኒስተር ታደሰ ማለት ነው። ያማለት የበሽታ መከላከል አቅም በ ጾም ምክኒያት ተሻሻለ ማለት ነው።

ይህ ሂደት ሴሎች የራሳቸውን ክፍሎች የሚያድሱበትና እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያደርግም የተፈጥሮ አሠራር ነው።ይህ ሂደት በተለይ ኒውሮዲጀነሬቲቭ ሁኔታዎችን ካንሰርን ጨምሮ ገዳይ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ስለሚችል ለሰው ልጅ እጅጉን አስፈላጊ ነው ።ይህም ሴሎችን ለመጠገንና ለማጽዳት የሚረዳ ከመሆኑም በላይ ለረጅም ዕድሜና እርጅናንም ለመከላከል ተጽእኖ አለው።
እጅግ የሚገርመው ሰውነት autophagyን ለመጀመር በትንሹ ለ12 ሰዓት እና በላይ ያህል ይፈልጋል። ከሃይማኖት ጾም አንጻር ስናየው ከእስልምና ጾም ጋር ብቻ ትይዩ ነው (ፊጥራ)።

ዛሬ ላይ ፈረንጆች እንደ ጤናማ ባህል promote እያደረጉት ነው።ዩሽነሪ በሽልማቱ ለጋዜጠኞች ስለ autophagy ሲያብራራ ጾሙ ለ4 ሳምንት ሲተገበር እጅግ የተዋጣለት ይሆናል።
እናም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በጤና እንድንከርም በ ፊጥራ ይህንንም ሲስተም በዓመት አንድ ጊዜ ሰውነት ላይ ለአንድ ወር እንዲካሄድ የወሰነለት ሀቅ ይሆን እያልን ተገረምነ 😍😍😍 “ተባረከላሁ አህሰኑል ካሊቂን” አልን።

ፎቶው የ ፕሮፌሰር Yoshinori Ohsumi ነው።

2 months, 1 week ago

ምናልባት Telegram ላይ እና Facebook ላይ ከሚሊየን በላይ ተከታይና ጓደኛ ሊኖሩህ ይችላል። አላህን የማያስታውሱህ ከሆነ ምንም አይጠቅሙህም።

2 months, 1 week ago
4 months ago
ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ …

ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ቴፕላይን ካምፓኒ ሃላፊን አስጠራ
"አንዲት የነዳጅ ጠብታ ወደ እስራኤል እንዳይላክ" ሲልም አዘዘ።

አሜሪካ ትዕዛዙን ጥሳ ለእስራኤል እርዳታ እንደላከች ሲሰማ ከአሜሪካ ጋር የነበረውን የነዳጅ ሽያጭ ውሉን አቋረጠ።
በሀገረ አሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ ነገሰ
ሰዎች በነዳጅ ማደያዎች ፊት ተሰልፈው
ነዳጅ እንጂ እስራኤልን አንፈልግም የሚለውን መፈክር አስተጋቡ።
በዚህ ጊዜ ንጉስ ፋይሰል ታዋቂ ንግግሩን አደረገ
"ነዳጅ ከቁድስ ክብር አይበልጥብንም። አያቶቻችን በተምርና በወተት ኖረዋል እኛም ወደዛው ህይወት እንመለሳለን"
አላህ ይዘንልህ

ዛሬስ አረቦች
ዛሬስ የአለም ሙስለሞች??
በቀን ይሄን ያህል ንፁሀን ሞቱ ቆጣሪ ሁነናል

4 months ago
9 months, 2 weeks ago

......, #ፍቅር ...,
አሚር ሰይድ

🔰አንዲት እህቴ ፍቅር ይዞኛል ግን ፍቅር ምንድን ነዉ ብላ ጠይቃኝ የዛሬ 2አመት በፊት የመለስኩላት ነዉ እናንተ ስለፍቅር ምን ትላላችሁ⁉️
☞ፍቅር ህልም ነዉ ስትነሺ የማታገኚዉ
☞ፍቅር ንፋስ ነዉ ከየት በኩል እንደመጣ የማታየዉ
☞ፍቅር ዉሀ ነዉ ጨብጠሽ ይዘሽ የማታስቀምጪዉ
☞ፍቅር የእሳት እረመጥ ነዉ አንዴ የእሳት ረመጥ በእግርሽ ከረገጥሽዉ እግርሽ እንደመግል ሁኖ ያመረቅዛል በዛ እግርሽ መሬት መንካት አትችይም ሳታነክሽ ብዙ ወር ትቆያለሽ ከዛ በስንት ድካም ይሻልሻል
☞ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ በዉንም በህልምም አብሮ እሱ ጋር እየኖሩ አብረዉ ልጅ ሲወልዱ ተከባብረዉ ሲኖሩ የሚያሳይ የህይወት ስዕል ነዉ ...ስዕል ደግሞ እዉነት አይደለም ያዉ ስዕል ነዉ...,ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ ልብሽ ላይ ስለሽ ያንን ስዕል እንዳይጠፋብኝ እያሉ የመጨነቅ የመጠበብ ኑሮ ነዉ..ስዕሉ እንዳይጠፋ የመታገል ህይወት ነዉ
☞ፍቅር ተራራ ነዉ ይላሉ ግን ፍቅር ተራራ አይደለም ሜዳ ነዉ ..ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...ተራራ ስትወጪ ይደክምሻል ግን በግድም ቢሆን ወጥተሽ ትጨርሻለሽ ከተራራዉ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ በስንት ድካም ብለሽ  ራስሽን ታደንቂያለሽ ደክመሽም ቢሆንከተራራዉ ጫፍ በመድረስሽ
...ፍቅር ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ሂደሽ ሂደሽ አጨርሽዉም ጫፉ ላይ የማይደረስ ነዉ...ለምን ብትይ ተራራ ወጥተሽ ከጫፍ ትሆኛለሽ...የወጣሽዉን ተራራ ደግሞ መዉረድ አያቅትም ተራራ የሚከብደዉ መዉጣቱ ነዉና
ሜዳ ግን ብትሄጅ ብትሄጅ ብትሄጅ አያልቅም....ለምሳሌ ከደሴ አዲስ አበባ 401 km ነዉ ያንን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሽዋለሽ?በጭራሽ አጨርሺዉም ግን ጠንካራ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ አያቶቻችን መኪና በሌለበት ዘመን ሂደዋል እኔም በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ከተሳካልሽ ☺️ አአ  ከሄድሽ😉 ከአአ አሶሳ ሱዳን ድንበር 660 km አለ እሱን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሺዋለሽ?በጭራሽ አሞክሪዉም ...አይታወቅም የሰዉ አቅሙ☺️ ጠንካራ ከሆንሽ ሄድሽ እንበል አሶሳ ደረሽ ምድር ታበቃለች?ምድር ተሂዶ አያልቅም ከሱዳን ጀምሮ ስንት ሀገር አለ...በእግርሽ በመኪና በአየር ሂደሽ የማጨርሺዉ....በእግርሽ ሱዳንን አልፈሽ ብትሄጅ ስትሄጅ ስትሄጅ ዉቅያኖስ ወይ ባህር ታገኛለሽ በእግርሽ ከሞከርሽ ሰምጠሽ ትቀሪያለሽ ...ወደ ጀመርሽበት አትመለሽ ሩቅ ነዉ ባለሽበት ቀባሪ ሳትገኝ ትሞቻለሽ ማለት ነዉ☺️ ፍቅርም ሂደዉ ሂደዉ የማይመለሱበት የቁም ሞት መሞቿ ህይወት ነዉ
ፍቅር ተራራ ሳይሆን ሂደሽ ሂደሽ የማጨርሺዉ የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...
እናም ይሄን ረጅም መንገድ ሂደሽ የማጨርሽዉ አለም ...በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ማሳመን ነዉ ፍቅርም እወጠዋለሁ ብለሽ ሂደሽ የማጨርሽዉን ጉዞ መጀመር ነዉ...ከጀመርሽም ይሄን የማይጨረስ አለም አንድ እርምጃ ሳትረመጅ ሀሳብሽ ተበታትኖ እግርሽ ተሳስሮ ሳትሄጅ ትመለሻለሽ ..,ፍቅር አሰቡበት ሳይደርሱ ወደ ፊት የሆዱ መስሎ በማያቁት መንገድ ወደ ሆላ መመለስ ነዉ.. ግን ወደ ሆላ መመለስሽ የሚገባሽ ቡሀላ ሳትሄጅ ከተመለሽ ቡሀላ ነዉ
☞ፍቅር ካልተሳካ ከህይወት ተስፋ መቁረጥ ነዉ ...ደግሞም ሴት ነሽ ይከብዳል ወንዱ ሌላ ሊኖረዉ ይችላልና ....እሱ ካልተረዳሽ ስቃይ ነዉ
☞ፍቅር ያለዉ አማረኛ ፊልም እና ዘፈን ላይ ነዉ...አማረኛ ፊልም ስናይ ዘፈን ስናዳምጥ ያንን ያየነዉ ያዳመጥነዉ ሙዚቃ ወደ ዉስጣችን ገብቶ ያንን ለማዋሀድ እኔስ የለኝም ወይ? ብለን በአየነዉ ፊልም ሙዚቃ ፍቅርን እየሳልን የምንረበሽበት የሙዚቃዉ የፊልሙ አይነት አፍቃሪ ሳናገኝበት የምንኖርበት የፊልምና የሙዚቃ ኑሮ ነዉ

☞ፍቅር ጥልቀት ያለዉ ክብ ዲንጋይ  ነዉ...ያንን ዲንጋይ ለማዉጣት ብቻሽን ብትቆፍሪም ሰዉ ቢረባረብ የማይወጣ ነዉ...ፍቅርም ጥልቀት ያለዉ ከልብ የማይወጣ ክብ ዲንጋይ ነዉ

☞እኔ የምልሽ ፍቅር ከሚይዝሽ ኮረንቲ ያዝ አርጎ ቢለቅሽ ይሻላል...ለምን ኮረንቲ አስደንግጦ ይተዉሻል ፍቅር ግን ያፈቀርሺዉ የኔ ይሆን በሚል እልክ ....እራስሽን በራስሽ አሳምነሽ የምትኖሪበት ህይወት ነዉ፡፡

☞ፍቅር ያፈቀሩትን ሰዉ የማያገኙበት ህይወት ነዉ...ትዋጀሻለሽ ግን አብሮ ለመሆን የምትሰቃይበት ኑሮ ነዉ.
  የማይረዳሽ ለትዳር የማይሆን ከሆነ የወደድሽዉ አደራ አደራ ፍቅርሽን አፍነሽ አላህ እንዲያነሳልሽ ዱአ አርጊ ካልሆነ እሱ በፍቅር ልብሽ ላይ ይጫወትብሻል ሀራም ያሰራሻል...የሴት ልጅ ፍቅር ከባድ ነዉ ፡እኔ ይሻላል የምለዉ ወንድ ቢያፈቅር ነዉ ወንድ ከወደደ ይታገሳል ተስፋ ቆርጦም ይነሳል...ሴትግን ብታፈቅር ትጎዳለች በተለይ
የማይረዳ ለትዳር የማይሆንሽ ከሆነ

ደግሞ ማወቅ ያለብሽ በፍቅር መለየት አለ ምክንያቱን ሳታቂ የኔ ነዉ ያልሽዉ ሊከዳሽ ይችላል.....ወይም በቤተሰብ ወይ በእትህት ወንድም ወይ በተሳሳተ መረጃ ልብ ላይ ያርፍና የሆነ ጊዜ ይቆረፍዳል የዛን ጊዜ ከወዳጅ ከምወጂዉ ትለያለሽ የዛን ጊዜ ማፍቀርሽን ትጠያለሽ ፍቅር ልብሽ ላይ ተቀምጦ ትሰቃያለሽ ከሰዉ በታች ልትሆኝ ትችያለሽ....ከሚወዱት መለየት ከባድ ነዉ እምባስ ይወጣል የልብ እምባ ግን እዛዉ አልቅሶ ይቀራል😔...የማይወጣ ነገር የቀረ ደግሞ ለዉስጥ በሽታ ነዉ መቼም ጤነኛ አትሆኝም....
አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንኳን ከወዳጅ መለያየት
ሀዘኑ በጣም ጥልቅ እንደሆነ ይናገራል
የአይን ብርሃን እስከማጣት

( وتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ ٱلْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌۭ )
" ከእነሱም ዘወር አለና ኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው ፡፡"
_....የየሱፍ አባት ወደዉ አልቅሰዉ አይናቸዉን ያጡት ነብይን ነዉ..እኛ ግን አላህ ለፈጠረዉ ተራ ሰዉ አልቅሰን አይናችንን ታመን ልባችንን ማድማት የለብንም
ሆነም ቀረ...የሰዉ ልጅ ለራሱ ሳያቅ የራሴ ህይወት ሳይገባኝ  በሰዉ እፈርዳለሁ ...
በጥላቻ ድልድይ መረማመድ ቁልቁለት ነው።
ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነው።
ስለ በደል ማውራት ተራ ነው።
የተበዳይን እንባ ማበስ ከባድ ነዉ😔
መፍረድ ቀላል ነው።
ፍትሀዊ መሆን ምጥ ነው።
መለያየት ቀላል ነው። አንድ መሆን ፈተና ነው።
ትልልቅ ነገሮችን ማሰብ ቀላል ነው። ትንንሽ ነገሮችን ማድረግ ከባድ ነዉ።
በምኞት መኖር ቀላል ነው። እውነትን መቀበል መራር ነው።
ተስፋ ማድረግ ቀላል ነው። አማኝ መሆን ፅናት ነው።
ብቻ አሏህ ከሁላችንም ጋር ይሁን ከፍቅር የዉሸት ኑሮ ይሰዉረን

እናም እኔ የምለዉ ልብን አትዉደድ አይባልም ግን መጀመሪያ ለይል ተነስተሽ አልቅሰሽ ዱአ አርጊበት

ይቅርታ ግን እኔ ለፍቅር ጥሩ አመለካከት የለኝም😊 እኔ ለአንቺ የምረዳሽ ቢኖር ከፍቅር ተስፋ ማስቆሮጥ....የምወጂዉን እንደማታገቢ ተስፋ ማስቆረጥ ...ፍቅር በሌለበት አለም አፍቃሪ እንዳትሆኝ አእምሮሽን እንድትጠርጥሪ ማድረግ...የፍቅር ህይወትሽ እንዲጨልም ማረግ ብቻ ነዉ😂
ለፍቅር ጥሩ አመለካከት ያላቸዉ በፍቅር ያተረፉ ካሉ እነሱን ብትጠይቂ ጥሩ ነዉ ባይ ነኝ☺️
⚠️ Warning
ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነዉ
መለያየየት ቀላል ነዉ አንድ መሆን ግን ፈተና ነዉ
ጨርሻለሁ ከአጠፋሁ አዉፍ በይ 😊
እርስዎ ስለፍቅር ምን ይላሉ
#ለአስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

9 months, 3 weeks ago

እያለቀስክም ቢሆን የበሩ መከፈት ቢዘገይ እንኳን አትዘን፡፡ ዋናው ሳትሰለች በሩ ላይ ቆመህ መገኘትህ ነው፡፡ በሀይልና በተደጋጋሚ የተንኳኳ በር መከፈቱ ግድ ነው፡፡ እስልምናህን የምትወድ ከሆነ አላህ ይከፍትልሀልና ተስፋ አትቁረጥ፡፡ አላህ ይሰጥሀል፡፡ ውስጥህ ያለውንም ተስፋ ያድሳል፡፡ አል-ፈታሕ ብለህ በስሙ ጥራው፡፡ በርግጠኝነት ይከፍትልሀል፡፡

🟡 ነብዩ ሰዐወ በለሊት ተነስቶ ሚስቱንም ቀስቅሶ ሁለት ረከአ ለሰገዱት አላህ ይዘንላቸዉ ብለዋል፡፡
እናም ተኝቶ ድምፃችን ይሰማ እያሉ ከማንኮራፋት ተነስቶ ሚስትህ ጋር መስገድ አብራችሁ ዱአ ማድረግ ለዚህ ቅጥ ላጣ ዘመን መፍትሄ ነዉ፡፡

ዱንያ የደስታ ምንጭ አይደለችም ይሄን ማወቅ አለብን አላህ የትንኝ ክንፍ ለኔ ቦታ የላትም ብሎ እኛ ደስተኛ እንሆናለን ብለን ራሳችንን አናሳምን

አል ኢማም አር ራዚ ቆንጆ ልብስ መልበስ ይወዱ ነበር፡፡ አንድ ቀን ከመስጅድ ወጭ እያሉ አንድ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ጋር ተገናኙ፡፡ ሰውዬው የተበጣጠሰ ልብስ ነበር የለበሰው፡፡ ለኢማም አርራዚ እንዲህ አላቸው የናንተ ነብይ ይህች ዓለም ለአማኞች እስር ቤት ለከሐዲዎች ጀነት ናት፡፡› ይላል፡፡ ይህን የመሰለ ፀጋ ውስጥ እያለህ ከየትኛው እስር ቤት ውስጥ ነህ? እኔስ በየትኛው ጀነት ውስጥ ነኝ? አላቸው፡፡ ኢማም እርራዚም እኔ አሁን ያለሁበት ሁኔታ በጀነት ውስጥ ካለው ድሎትና ፀጋ አንፃር እስር ቤት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በጀሃነም ውስጥ ለከሐዲያን ካዘጋጀው ቅጣት ደግሞ አንተ አሁን ያለህበት የችግር ኑሮ ጀነት ነው፡፡ አለው፡፡ ሰውዬውም ጥቂት ካስተነተነ በኋላ በርግጥም የናንተ መልእከተኛ የተናገረው እውነት ነው፡፡› አለና ሰለመ፡፡

ይህች ዓለም እስር ቤት መሆኗ፣ አላህ (ሱወ) ጀነትን ለኛ ማዘጋጀቱ፣ አኺራ በላጭና ዘላለማዊ መሆኗ ... ይህ ሁሉ አላህ (ሱ.ወ) እኛን ሊያስደስተን የፈለገ መሆኑ ያመላክተናል፡፡ _ ስለሆነም ጀነት ሊያስገባን ብሎ ይከታተለናል፣ ይጠብቀናል፣ በችግሮችም ይፈትነናል፡፡

🟡 በተጨማሪም ሲህርም ባይሆን ማንኛዉም ህመም ሲያጋጥመን ሀኪም ቤት ልሂድ ከማለት መጀመሪያ አላህ እንዲያሽረን እንማፀን

ዑሥማን ኢብን ጦለሐ የሚባል ሰሐባ ነብዩ (ሰዐወ) ዘንድ መጣና የአላህ መልእተኛ ሆይ!!! ሰውነቴ ውስጥ ህመም ይሰማኛል፡፡ አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰዐወ)  በአላህ (ሱ.ወ) መካከል ያለው ግንኙነት የጠበቀ እንዲሆን ፈለጉ፡፡ እናም በሚያምህ ቦታ ላይ እጅህን አኑርና ሶስት ጊዜ ቢስሚላህ በል፡፡ ከዚያም ሰባት
ጊዜ አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚን ሸር ማ አጂዱ ወኡሓዚሩ፡፡" በል አሉት፡፡ ሰሐባውም እሳቸው እንዳሉኝ አደረኩኝ፡፡ ህመሙም ለቀቀኝ፡፡ በአላህ እምላለሁ ከዚያ ቀን ጀምሮ ለቤተሰቤና ለማውቀው ሰው ሁሉ ከማስተማር ወደኋላ አላልኩም፡፡› ብሏል፡፡

ታማሚም አስታማሚም አላህ ፅናቱን ጥንካሬዉን ይስጠን...እኛም ለዲናችን ጠቃሚ ለሰዉ የምንተርፍ ያድርገን
ለሰዉ ክፋት መጥፎ የምናስብ ሰዎች እባካችሁ ቶብቱ በሰዉ ደስታ ለምን እንደኛ ይቸገር እንላለን??
ክፉዉን ማዳመጥ ማየት የክፋት መጀመሪያ ነዉ
ክፋት በሰዉ ባህሪ ዉስጥ አብሮ የተፈጠረ ሳይሆን ክፋትን ማስወገድ ባለመቻሉና ዉጫዊ ተፅእኖዉን መቋቋም ስላቃተዉ የመጣበት ነገር ነዉ፡፡
ህይወት ወጪዉን የማትሸፍን ንግድ ነችና በእሷ ስኬትን በሀራም በጠንቋይ በሳሂር እገዛ እጨብጣለሁ ብለህ አትሰብ እናም በሰዉ ስቃይ ሀዘን ለቅሶ መደሰት ምን የሚሉት ህሊና ነዉ ?? አላሁ የስቱርና አላህ ከመጥፎ ባህሪ አመል ይጠብቀን

🔰 አላህ ሆይ ከደጋሚዎች ከሳሂሮች ተንኮል ጠብቀን...ምቀኛን ቀናተኛን ከጎናችን አርቅልን..ስቀዉ ከሚጎዱ የቅርብ ሰዎች ጠብቀን ያረብ...
🔰 ሲህር የተየደረገብን የታመምን ወይ ሲህር ተደርጎብን ሳናቅ ብዙ አመታት ፈጅቶ ከረፈደ ያወቅን አልሀምዱሊላህ ከረፈደም ማወቃቸዉን ...እንደ አጋጣሚ ያለወቅን ካለ አላህ አሳዉቀን ያረብ
🔰 ጠንቋይ ቤት ለሚሄዱትም ሂድያ ስጣቸዉ...

🔰 ኢላሂ  ለዲነል ኢስላም  የምንጠቅም ባንጠቅም እንኳኝ በኛ እንዳይሰደብ የምንሆን ጀሊሉ ያድረገን
አንዳንዴ በማህበራዊ ሚዲያ ሙስሊሞች አለቅጥ ወንጀል ፈሳድ ላይ ተጥለቅልቀዉ የሌላ ሀይማኖት ወይም አንዳንድ ኢስላም ሲደፈር የሚቆጫቸዉ እህት ወንድሞች ሙስሊም አይደለሽ እንዴ ብለዉ ሰመከሩ
የማምለጫ ዘዴ አለች...እኔ ሙስሊም ነኝ ችግር ካለብኝ እኔን እንጂ እስልምናየን አትናገሩ ብለዉ ኮስተር ሲሉ ይታያሉ ይገርመኛል እነሱ ኢስላምን እያሰደቡ እስላምን አትሳደቡ እያሉ ቀጭን ኢስላምን አትንኩብኝ እያሉ የዉሸት ተስፋ ይዘራሉ...ተስፋ ጥሩ ቁርስ ቢሆንም መጥፎ እራት መሆኑን አንዘንጋ 
እናም በሚዲያ ላይ ሙስሊም ሁነን ጅልባብም ጀለብያም ለበስንም አለበስንም በኛ ኢስላም ሊሰደብ ሊመዘን አይገባም እኛ በኢስላም ሀይማኖት ማዕቀፍ ዉስጥ ነን አማኝ ነን ካልን ሙስሊም ተብለናል ...አማኝ ሙስሊም ባንሆን እንኳ ህሊናችን የሚሰራ ሰዉ እንሁን... አረ ሰዉ ሰዉ እንሁን እባካችሁ...ኢስላም በኔም በአንተም በእኛም በእናንተም እየተሰደበ እየተዋረደ ነዉ...አላህ ዲነል ኢስላምን እኔ ነኝ የምጠብቀዉ ስላለ ነዉ እንጂ በእኛ ስራ ቢሆን አፍርሰን ትቢያ አመድ አርገነዉ ነበር
🔰 ኢንሻ አላህ እያሉ ከመሾለክ ዝም ብሎ በምሉላስ አሏሁ አክበር እያሉ ሙስሊምን ከመጉዳት ያለችንን ትንሽየ ኢማን አላህ ያድስልን፡፡አላህ ጠንካራ የማይበገር ኢማን ይስጠን

📚📚📚 #ዉድ የተከበራችሁ  አንባባዎች በ➊➎ part ስለሲህር ድግምት አይነጥላ ..ስለትዳር ስለስንፈተ ወሲብ በሁሉም ባሉት ቸግሮች ትኩረት አድርጌ አቅሪቢያሁ
የሰዉ ልጅ ነኝ እሳሳታለሁ ከኔ በላይ እዉቀት ያላችሁ እዚህ ቦታ ተሳስተሀል በሉኝ  edit ማድረግ እችላለሁ edit አሁኑ ላድርግ ከወር ቡሀላ edit ማድረግ ስለማይቻል ...ብዙ ሰዉ እያነበበዉ ሼር እያደረገዉ ስለሆነ ...ግን የተዘጋጀዉ ከመፅሀፍ እና ከሀዲስ ከሚያቁ ጠይቄ ስለሆነ እስከ አሁን በአስተያየት መስጫ አስተካክል የተባልኩት የለኝም፡፡ በአስተያየት ስሰጡ ሳነባቸዉ  በሲህር ተለክፈዉ የነበሩ እና በይፋ  ያደረገባቸዉ ሰዉ እየነገረን ነዉ ያሉኝ አሉ  ፡፡
ወደ 5 የሚሆኑ አስተያየቶች እኔን ካላገባሽ መቼም አታገቢ ብለዉ ከወንድየዉ ተነግሯቸዉ  እንዳላገቡ በተጨማሪ  አንዷ አግብታ ኒካሁ ታስሮ ሳይቆዩ እንደተፋታች የነገረችኝ አለች ...ሌሎቹ ይሄን ፁሁፍ ሲያነቡ ራሳቸዉን ፈትሸዉ ሩቃ ሊጀምሩ እንደሆነ አሳዉቀዉኛል...እናም በተለይ በትዳር ላይ የተተበተበ ጉድ ከባድ ነዉ ራሳችንን ማኔጅ ብናደርግ ጥሩ ነዉ

ለ15 ቀን በ15 ክፍል የቀረበዉን ፁሁፍ ሀምሌ 1 ጀምረን ሀምሌ 15 2015 ጨርሰናል ፡፡ባለመሰልቸት ባለመታከት አንብባችሁ ስለጨረሳችሁ ጀዛችሁን አላህ ይክፈላችሁ ለምን እኔም እናንተ ባነበባችሁበት ራሳችሁን በፈተሻችሁበት አጅር ስለማገኝ እናንተም ባነበበባችሁት እኔም ባዘጋጀሁት ተጠቃሚ ያድርገን፡፡

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሁ ወበረካትሁ
#ተ.......... #ፈ.......... #ፀ........... #መ

⚡️⚡️⚡️አንብባችሁ ምን ተረዳችሁ?
ምን አስተያየት አላችሁ?
👇👇👇እዚህ ላይ ይፃፉ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ከፁሀፉ ያልገባችሁ ያልተዋጠላችሁ ካለ👇👇

9 months, 3 weeks ago

💛 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች።
❤️በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር ይቅር ባይነት የዘወትር ስንቁ ነበር። ስቃይ በተሸከመው አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ለሊቱን በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል ሰዎችን ይቅር ይሉ ነበር ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ 
እናም ፈተና  መብዛት ችግር መደራረብ ባይኖር ዱንያ የደስታ ሀገር ብትሆን ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ባልተፈተኑ ነበር እናም አንተም አንቺም እሱም እሷም እናንተም ፈተና ላይ ናቸሁ ፈተና ጨርሳችሁ ትንሽ ከተደሰታችሁ ቡሀላ ሌላ የከበደ ፈተና እንደሚጠብቀን እርግጠኛ ሁን የዛን ጊዜ ነዉ ኢማንህ የሚለካዉ፡፡
ኢማናችን መለካት እንጂ መነካት የለብንም ወገን

📌 እጅግ አምልኮ በማብዛት የሚታወቀው ታላቁ ታቢዒይ አልፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ ፈገግታ አያበዙም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግን ልጅ ሲሞትባቸው ፈገግ አሉ፡፡ ለምን ፈገግ እንዳሉ በተጠየቁ ጊዜ “አላህ የወደደው ነገር ነውና እኔም ወድጄ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የወደደውን እንድትወድ ነፍሴ ፈገግ እንድትል አስገደድኳት” አሉ፡፡

ዑለማዎች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለቀሱበትንና አልፉደይል ግን ፈገግ ያሉበትን ሁኔታ በማንሳት ለመተንተን ሞክረዋል፡፡ በመታገስ ደረጃ አፉደይል ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይበልጣሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ትርጉሙም፡- ሞት በሚመጣበት ቅፅበት ቀልብን በሁለት ሰሜት ውስጥ ይከታል፡፡ እዝነትና ውዴታ፡፡ ማንም ሰው ሁለቱን ስሜቶች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ አይችልም፡፡ አልፉደይል ሁለቱን ማሳካት አልቻሉምና በውዴታ ስሜት አንድም ፈገግ ማለት አለባቸው አሊያም አብዝተው ማልቀስ ነበረባቸው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ሁለቱን ማሳካት ችለዋል፡፡ አላህ የወደደውን ወደዋል በሌላ በኩል ደግሞ አልቅሰው እዝነት ስሜት አሳይተዋል

📌 የነቢያችን አክስት የሆነችው : እመት ሶፊያ በኡሑድ ጦርነት ወቅት ቁስለኞችን ውሃ ታጠጣ ነበር፡፡ ታላቁ ጀግና ሐምዛ (ረ.ዐ) ተገደሉና አካላቸውም እንዲቆራረጥ ሆዳቸው እንዲቀደድ ተደረገ፡፡ ሒንድ በበቀል ስሜት ጉበታቸውን እስከማኘክ ደረሰች። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለልጇ ዙበይር ኢብኑ አልዐዋም ዝበይር ሆይ! ሶፊያን ወደ መዲና ይዘሀት ሂድ ሐምዛን ማየት የለባትም፡፡” አሉት። ልጇም ሄደና “እናቴ ሆይ! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ተመለሽ ብለውሻል፡፡” አላት፡፡

ልጄ ሆይ! ይህን የምታደርጉት ሐምዛን እንዳላይ ብላችሁ ነው አይደል? አለችው፡፡
....“አዎን” አላት፡፡
....እሷም “ልጄ ሆይ! አላህ ከዋለልን ፀጋ አንፃር በሐምዛ ላይ የደረሰው በጣም ቀላል ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደድ አለመውደዳችንን ለማየት ነው፡፡ ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሂድና የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አላህ በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደዳችንን ለመፈተን ነው ብላለች ሶፊያ በላቸው ፡፡ ልጁም ወደ ነብዩ (ሲዐወ) በመመለስ ነገራቸው፡፡
... ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) “እንግዲያውስ ማየት ትችላለች፡፡” አሉ፡፡ ሄደችና አይታው አለቀሰች፡፡ ኢንና ሊላህ ወኢንና ኢለይሂ ራጂኡን የኛዑን እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን፡ በማለትም ዱዓእ አደረገችለት፡፡
እናም አላህ በሚያመጣብን ፈተና የዱንያም ሆነ የጂን የሲህርም አላህ ወዶን እየፈተነን እንደሆነ አንዘንጋ

ጅን ሲህር ሳሂር ደጋሚ ጠንቋይ ደብተራ እንደማይጎዳ አሏህ ብቻ ጎጂ እንደሆነ ማወቅን ከኢማኖች ውስጥ ጠንካራ ኢማን ሁኖ እናገኘዋለን!! በአሏህ ላይ የቂን እጅግ የምንፈልገው መሳርያ ነው!! ሌቦች ቤትን ሊዘርፉ ሲመጡ አለሁ ብሎ ድምፅን ማሰማት ሲቀጥልም የመሳርያን ድምፅ ማሰማት እነርሱን እንደሚያስበረግጋቸው ሁሉ የቂን ልክ እንደዛው ጅኖችን ያስፈራቸዋል እንዳይቀርቡን!! ይሁንና ያለ እውቀት ያለ መጠበቅያ የቁርአን አያዎች እና ዚክሮቸች ማለት ያለ መሳርያ መሳርያ ታጥቀው የመጡ ሌቦችን ማስፈራራት ብቻ ነው፡፡ ለኛ መሳርያችን ለጅኖች ሊያውም ከባለጌዎች ለመጠበቅ የምንታጠቀው መሳርያ ዚክርና ቁርአን እንዲሁም ዱአእ ነው፡፡ ሌላውን አይነት የመሀይማን መሳርያ የሆነውን ጥንቆላ መተት ፀበል እና አንጃ ግራንጃዎች ልክ ሌቦችን እንደመማፀን እንደመደራደር ነው የምንቆጥረው፡፡ ከሌባ ጋር ድርድር የለም ባንተ ንብረት ላይ መጥቷልና ፡፡ ከጅን ጋርም እያጠቃህ መደራደር የለም በቁርአን በዚክር ልኩን አሳይተሀው  መከባበር እንጂ፡፡

🖍🖍 እናም ፈጣሪ ይሁን ብሎ ተፅፎብን ከሆነ ትዕግስት ጥንካሬ ፅናት ያስፈልጋል፡፡ በሲህር በጂን የሚፈተን ሰዉ በዛዉም የፀና የጠነከረ አላህ ወዶን ይሆናል ዱአ ላይ መበርታት ግዴታ ነዉ...ከዱአ በጭራሽ ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም
{ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِی عَنِّی فَإِنِّی قَرِیبٌۖ أُجِیبُ دَعۡوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِۖ فَلۡیَسۡتَجِیبُوا۟ لِی وَلۡیُؤۡمِنُوا۟ بِی لَعَلَّهُمۡ یَرۡشُدُونَ }
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡[አል በቀራህ: 186]

🟢  አንድ ድንቅ የሆነ ሐዲስ አልቁድስይ ላካፍላችሁ፡፡ ነቢዩ ባስተላለፉት ሐዲስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- “የአደም ልጅ ሆይ! እኔም እፈልጋለሁ አንተም ትፈልጋለህ፡፡ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የሰጠህ እንደሆነ የምትፈልገውን አመጣልሃለሁ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የማትሰጥ ከሆነ በምትፈልገው ነገር ላይ  እንድትደከም አደርግሃለሁ፡፡ በመጨረሻ እኔ የምፈልገው ነገር ብቻ እንጂ የሚሆን የለም፡፡” ይለናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ ቃሉ “አላህ ካሻ በስተቀር አናንተ አትሹም (አል-ኢንሳን ፡3) ብሏል፡፡

🟢 ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ዱዓዬ መቼ ተቀባይነት እንደሚያገኝ አውቃለሁ፡፡ አሉ፡፡ “እንዴት ልታውቅ ትችላለህ? ተባሉ፡፡፡ “ቀልቤ በጥልቀት የአላህ ፍራቻ ካደረበት፣ መላ አካላቴ ከተንቀጠቀጠ፣ ዐይኔ ካነባች፣ ይህች ሰዓት ዱዓዬ ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በማለት በዱዓዬ እጠናከራለሁ፡፡ ብለዋል፡፡

ለዱአ መቸኮል አያስፈልግም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “እስካልቸኮላችሁ ድረስ ምላሽ ይሰጣችኋል፡፡” አሉ፡፡ መቸኮል ሲባል እንዴት ነው? ሲሏቸው አንዳችሁ “ዱዓእ አደረግኩ፤ ዱዓእ አደረግኩ ምላሽ አላገኘሁም፡፡ ይላል፡፡ (ተስፋ መቁረጥ) ዱዓእ ይተውን ይተዉና በዚያው ምላሽ ያጣል፡፡” ብለዋል፡፡
ሲህር ከተደረገብን ወደ አላህ የማይቋረጥ ቀጣይ የሆነ ዱአ ያስፈልጋል፡፡

🟢 ኢብኑ አልቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ ብትባረርም እንኳን ከአላህ በር ላይ ከመቆም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ቢመልስህም እንኳን ምክንያት ከማቅረብ አትውረድ፡፡ በሩ ተቀባይነትን ላገኙት የተከፈተ እንደሆነ ቀስ ብለህ በስርአቱ ግባ፡፡ ድሀ ነኝ ምፅዋት እፈልጋለሁ፡፡ በለው፡፡ ምፅዋት የሚሰጠው ለድሆችና ለችግረኞች ነው፡፡ እኔም ምስኪን ደሃ ነኝ፡፡ በለው፡፡👇👇👇

9 months, 3 weeks ago

⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም*⚡️
አሚር ሰይድ*

#የመጨረሻዉ_ክፍል

🔰 #ራስን_በራስ_ማከም_ከዛም_ለሌላ_መትረፍ

🌙🌙
ከpart ➊➍ ቀጥታ የቀጠለ.....
  ከዛር ዉጭ ያለን ሩቃን ለማድረግ ባንፈራ ጥሩ ነዉ ብቻ መጀመሪያ አላህን ይዘን ነይተን ሀስበነሏህ ብለህ መጀመር  ነዉ ፡፡

📚📚 ከተሞክሮ እስኪ ጀባ ልበላችሁ ወላሂ ይሄን የምነግራችሁ ጀሊሉ ያቅብኛል ለጉራ አይደለም ባልፅፈዉ ደስ ይለኛል ግን እንድትደፍሩ እንዳትፈሩ ለመጠቆም ነዉ፡፡ እኔ የዲን እዉቀት የለኝም በማንበብ እና የሰሙትን በመተግበር ላይ አተከለራለሁ ...እና ማንኛዉም ነገር አንድ እርምጃ ያስፈልገዋል የብዙ ሰዉ ችግር ሶስት አራት እርምጃ ይራመዳል ሳያጣራ ከዛ ግብ ሳይመታ ይመለሳል ...እኔ የማምነዉ አንድ እርምጃ ካልሆነ ወደፊት ሳይሄዱ መለስ እርምጃዉ የተሳካ ከሆነ ቀኝን እግርህን ካስቀደሙ ግራህን አስተከትለህ ሁለት እርምጃ ላይ ትቆማለህ ከዛ ነገሮችን እያገናዘቡ መሄድ ነዉ...
#ከተሞክሮ

✍🏼 አንዲት ክርስቲያን ጎረቤታችን  የ7 አመት ልጇ አላት ለሊት አይተኛ ቀን ታዝሎ ይዉላል ስራዉ ማልቀስ ምግብ የሚበላዉ ትንሽ ለዛዉም ያስመልሰዋል እንደ እድሜ እኩየቹ አይጫወትም ብቸኛ ነዉ ... ይሄ ህመም የጀመረዉ ገና በ4 አመቱ ነዉ 3 አመት ያህል ተሰቃይቷል  ያልሄደችበት ፀበል የለም ሌላም ሀገር ሂዳለች ፡፡በፀበል መፍትሄ ሲያጡ ሌላ ሀገር ጠንቋይ ቤት ሄዱ አረንጓዴ እስስት አምጡ ብሏቸዉ አረንጓዴ እስስት ለማግኘት አራት ወር ፈጀ በግድ ተገኘ ጠንቋዩ በአረንጓዴ እስስት ሌላም  ጨምሮ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ሰጠው ምንም ለዉጥ የለም...ከ3አመት ስቃይ ቡሀላ ሲጨንቃት ቁርአን ቅሩልኝ አለች...

#አላህ_ሆይ እንዳታስፍረኝ የቁርአንን ሀይልን ለነዚህ ክርስቲያኖች አሳያቸዉ ብየ ዱአ አደረኩ ...ከዛማ በስፒከር ሩቃ ከፈትኩ ሁለት ሁነን በቻልነዉ ቀራን ወላሂ 45 ደቂቃ ባልሞላ እንቅልፍ ወስዶት ላብ በላብ ሆነ ቁርአኑን ስንጨርስ ጩኾ ተነሳ በዛዉ ለቀቀዉ ከዛ ቀን ቡሀላ ታሞ አያቅም ይሄዉ እንቅልፍም ይወስደዋል እናቱም አታዝለዉ ምግብም መመገብ ጀመረ የሚያስመልሰዉ ቀረለት  ትምህርትም ተመዘገበ አልሀምዱሊላህ....እናት አባቱ አጥባቂ ክርስቲያን ነበሩ አሁን ግን ከምነግራችሁ በላይ ለሙስሊም ያለቸዉ አመለካከት ደስ የሚል ነዉ አላህ ሂድያ ይስጣቸዉ የቁርአንን ሀይል ቤተሰብ ዘመድ ልጁን ተሽሎ ሲያዩት ይገርማቸዉ ይደንቃቸዉ ይዟል፡፡

✍🏼 አክስቴ ክርስቲያን ነች ታማ ፀበል ብትመላለስ ምን ብትል ያልተሻላትን በ30 ደቂቃ ሩቃ በመቅራት በአላህ ፍቃድ እንዲሻላት አድርጊያለሁ

✍🏼 ከነዚህ ዉጭ  3 ሰዎች ጎረቤት ምናምን ሲታመሙ በአላህ እገዛ ተሳክቶሎኛል እናም እንደዚህ ልላችሁ ያሰብኩት ሩቃ ማድረግ ከባድ አይደለም መጀመሪያ ጀሊሉን አላህየን ከያዙ ምንም የሚያስቸግር የለም እናም እህት ወንድምህን እናት አባትህን ...እናት አባትሽን እህት ወንድምሽን ለሌላ ባዳ አሳልፋችሁ አትስጡ

----- ጂን ሲናገር  ሊዋሽም ላይዋሽም ስለሚቾል አንዳንዴ ሲናገር እዉነት ነዉ ብለን ከተናገረዉ ሰዉ ጋር ሂደን መጣላት አያስፈልግም፡፡

🌟 ከዚህ ርዕሱ ጋር ባይሄድም በፊት ክፍል ላይ ዘንግቼ ሳላስገባ የቀሁት ጉዳይ አሁን ያለቦታዉም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ ትንሽ ልበል...
በቅርብ አመታት በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ ወንድና ሴት ዚና ሲሰሩ ወይ በባል ወይ በሚስቱ ላይ ሲማግጥ  ተጣብቀዉ እያየን ነዉ፡፡ ይሄ ባልየዉ ሚስቱን ካላመናት ወይም ሚስት ባሏን ካላመነችዉ ጠንቋዮች ጋር ሂደዉ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ወይም ሌላ ሴት ጋር ከተኛ እዛዉ እንዲጣበቅ ሰዉ እንዲያዋርደዉ ይሁን ብለዉ አስደግመዉ ሊሆን እንደሚችል አንዘንጋ...ካልሆነም ደግሞ ፈጣሪ እኛን ለማስተማር እነሱን ምሳሌም እያረገ ሊሆን ይችላል፡፡እናም ለትዳራቸዉ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች መጀመሪያ  ባለመተማመን ይጋባሉ ከዛ ይሄ ይፈጠራል፡፡
እናም ወይ የአላህ ቁጣ ነዉ ካልሆነ ድግምት ነዉ ...
ግን በተለይ በትዳር ላይ የሚሰሩ ሲህሮች በአሁን ዘመን ላይ በሰፊዉ ተንሰራፍቷል፡፡

⚡️⚡️⚡️ #በጂን_የተያዘ_ወይም_ሲህር_ወይ#በአይነጥላ_የተያዘ_ሰዉ_ወይም_አስታማሚዉ#ምን_ማድረግ_አለበት*⁉️*⁉️**
      ኩን ፈየኩን ...አላህ ኩን ብሎት አላህ ሱወ በሲህር በጂን በአይነጥላ ሊፈትነን ይችላል ፡፡  ዱንያ የፈተና አለም ነች ለአላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ላለን ዱንያ ደስታን እናጣጥማለን ማለት አይደለም፡፡  ዱንያ በሀዘን ማቅ የተተበተበች ደስታ እንደመብረቅ ብልጭ ብሎ የሚጠፋበት የኑሮ መድረክ የፈተና መሸጋገሪያ ድልድይ ነች የጀነት መግቢያ የኸይር መሸመቻ የፈተና ማለፊያና መዉደቂያ የቁጥጥር ጣቢያ ነች፡፡  

በርዚቃችን ትዳር እንዳናገባ ነገሮች እንዳይሳኩ ወዘተ ሲህር ድግምት  ከተደረገብን የአላህ ዉሳኔ ነዉ ፅናት ብርታት ጥንካሬ ያስፈልጋል ፡፡

♻️♻️ አላህ (ሱ.ወ) የወሰነውን ነገር መደው የተቀበሉ  ነብዩ ሰዐወ ናቸዉ በሲህር ተሰቃይተዋል.....በተጨማሪ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኢብራሂም የሚባል ልጅ በተወለደላቸው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ተሸክመውት ወደተለያዩ ሰሐቦች ቤት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ ለሰዎችም ልጇን ኢብራሂምን ተመልከቱት፡፡› ይሉ ነበር፡፡ ትንሹ ኢብራሂም አባት ለልጅ በእጅጉ በሚጓጓበት የህፃንነት ዕድሜ ጡት መጣያው አካባቢ ሞተ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አለቀሱ😢፡፡ እንባ የልብ እዝነት ውጤት ነውና የአላህን ውሳኔ ካለመውደድ አይቆጠርም፡፡ እርሳቸውም ዐይን ያለቅሳል፣ ቀልብ ያዝናል፣ ጌታችን የሚወደውን ነገር እንጂ አንልም፡፡

#ኢብራሂም_ሆይ!!!! ከኛ በመለየትህ አዝነናል፡፡” አሉ፡፡ ከዚያም ወደቤታችው በመግባት ለአላህ (ሱወ) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ጥሪህ ሰምተን በደስታ ወዳንተ መጣን፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ መጥፎ ካንተ አይደለም፡፡” ብለዉ የጌታቸዉን ዉሳኔ ተቀበሉ...

መቼም የሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ታሪክ ታቃላችሁ
💚በእናታቸዉ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቁ
💛ዕድሜያቸዉ ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናታቸዉን ቀበሩ።
❤️ በስምንት ዓመታቸዉ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጓቸዉ አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው።

💚 እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት።
💛  ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።
❤️ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

💚 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው።👇👇👇

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago