ISLAMIC SCHOOL

Description
✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

3 weeks, 1 day ago

🎖  #የሚኒስትሩ_ጠባቂ_ጀብድ🎖
አሚር ሰይድ

ከወደ ፓኪስታን የአሜሪካ ድጋፍ የተቸራት የረሱልንﷺ
ስም የሚያንቋሽሽ የአሲያ ቤቢ ድምፅ ተሰማ። እንደ አውሮፓዉያን የዘመን ቀመር ኦክቶበር 2011 አሜሪካ ወዳጅ ብላ ያወደሰችው የፓኪስታን ሚኒስትር የሀገረ ፑንጃብ ገዥ ሰልማን ተይሲር የአላህን ነቢይ
ሙሀመድ ﷺ ለተሳደበችው ለአሲያ ቤቢ ከለላን ሰጠ። የመናገር መብቷ ሊነፈግ አይገባውም ሲል ተደመጠ። ረሱልን መስደብ ወንጀለኛ የሚያደርገው የሀገሪቱ ህግ መሻሻል አለበት ሲልም ተናገረ።

በዚህ ጊዜ የሚኒስትሩ ጠባቂ ይህን መሸከም ከበደው። መሳርያውን ጥይት አጉርሶ እየተንደረደረ ወደ ቢሮው አቀና። ከ20 በላይ ጥይት በሰውነቱ ላይ አርከፍክፎ ላይመለስ ወደ ቀብር ሸኘው፡፡
#ሙምታዝ_ቃዲሪ" ይሰኛል። በቁጥጥር ስር ውሎ የሞት ፍርድ ተወሰነበት። ከመሰቀያው ገመድ ላይ ተንጠልጥሎ ውሳኔው ተተገበረበት። ጀናዛው ለቤተሰቦቹ ሲሰጥ ታጥቦና ተከፍኖ ጀናዛ ተሰገደበት።

#ነፍሱን ለረሱል ﷺ ክብር ቤዛ ያደረገውን የዚህን ጀግና ጀናዛ ለመሸኘት የፓኪስታን ጦር አባላትን ጨምሮ ከ12 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተሰበሰበ።

#አላህ_ቀብሩን_ኑር_ማረፊያውን_ጀነተል_ፊርደውስ_ያድርግለት

#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

3 weeks, 5 days ago

💚
#ለሰረሱል_ክብር_ገድዬ_ለመሞት_ራሴን_አዘጋጀሁ

አሚር ሰይድ

አንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር 1910 በቤሩት ምድር በአንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ የሚርመሰመስ ሰው የአላህ መልእክተኛ ሙሀመድ ﷺድምፁን ከፍ አድርጎ ይሳደባል።

አንድ መንገደኛ ውስጡ በግኖና በንዴት ጦፎ ከኋላ ኋላው ይከተለዋል፡፡ ቢላዋ በሚሸጥበት ሱቅ በኩል ሲያልፍ አንዱን ቢለዋ መዞ በተሰዳቢው ጉሮሮ ላይ ሰካው። በኃይል ሰምጥጦ ደምስሩን በጥሶ ገደለው።
ገዳዩም እስር ቤት ገባ፡፡

ጉዳዩን ሲመረምር የነበረው የቤሩት ከፍተኛ ወንጀል ችሎት ከሁለት ዓመታት በኋላ ወንጀለኛው ለውሳኔ ይቀርብ ዘንድ አስጠራው። ተከሳሹ ችሎት ፊት ቆመ። አዳራሹ ከአፍ አስከ ገደፉ በሰው ተሞልቷል።

“ሰውየውን ለምን ገደልከው?" የዳኛው ጥያቄ ነበር

“የአላህን መልእክተኛ ﷺ ሲሳደብ በእጅጉ ተናደድኩ #ለረሱል_ክብር_ገድዬ_ለመሞት_ራሴን_አዘጋጀሁ ስለሳቸው ክብር ጉሮሮውን በጠስኩት" ሲል መሰሰ።

ዳኞቹ ከተወያዩ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተሳሰፋ

...."ሆን ብለህ የግድያ ወንጀል ፈፅመሀል ድርጊቱን የፈፀምከው ለረሱል ክብር መሆኑም ተጋግጧል፡፡ ፍርድ ቤቱ በነፃ ይለቀቅ ዘንድ ወስኗል መዝገቡ ተዘግቷል፡፡

ከውሳኔው በኋላ የታሰረበት ካቴና አንዲፈታለት ፖሊሱን አዘዘው ፡፡የመሀል ዳኛው ዩሱፍ አን-ነብሀኒ ከፍርድ ቤቱ የመቀመጫ ወንበር ወርዶ። ወደ ሰውዬው ቀረብ አለና “ልጄ ሆይ የምንወዳቸው ነቢን የተሳደበውን ሰው በየትኛው አጅህ ነው የገደልከው?" ሲል ጠየቀው

"በቀኝ አጄ" አለ

"አጅህን ዘርጋልኝ" እያለ በለቅሶ 😢 እጁን አቅፎ ይስመው ጀመር።

በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት አቀርቅረው ተላቀሱ። የቤሩት ፍትሕ ሚኒስትር የፍርድ ቤቶች ዋና ሀላፊ የገዳዩን አጅ የሳመውን ዳኛ ወደ መዲና ላኩት። የዘወትር ህልሙ ተፈፀመ።

" #ጌታዬ_ሆይ! የህይወቴን የመጨረሻ ቀናት ረሱል ባሉበት ከተማ ላይ አድርግልኝ ከሳቸው ጋርም አጎራብተኝ" በማለት ዱዓ ያደርግ ነበርና አላህ ዱዓውን ተቀበለው።

ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ

💞💞💚 ጠዋትም ማታም ሶሉ አላሀቢቡና ሰይዲና ሙሀመድ  ﷺ ﷺ

#ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

1 month ago

#ቀዕቃዕ_ኢብኑ_ዓምር
አሚር ሰይድ

ታላቁ የኢስላም የጦር መሪ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ የፋርስ ሙሽሪኮችን ለመዋጋት 10ሺህ ሙጃሂዶችን አዘጋጅቶ ወደ ጦር ሜዳ ዘመተ። የጦር ሜዳው ላይ የተሰለፉትን የፋርስ ወታደሮች ሲመለከት ከሙስሊሞች ሠራዊት በቁጥርና በትጥቅ የበለጡ እጅግ ግዙፍ ሆነው አገኛቸው። ሙጃሂዶቹን ማማከር የዘ።

“ወደ መዲና እንመሰስ? ወይንስ ሸሂድ እስከምንሆን ድረስ እንዋጋ?" በማለት ጠየቀ። ሁሉም በአንድ ድምፅ ተክቢራ አሰሙና አንዲህ በማለት መለሱ
.....“ከሀገራችን የወጣነው ሸሂድ ሆነን ለመሞትና በስሮቿ ጅረቶች በሚፈሱባት ጀነት ለመግባት አይደልን?!” አሉ።

ኻለድ የወታደሮቹ መልስ አስደሰተው። ግዙፉን የኪስራን ጦር ለመፋለም በቂ ሠራዊት አልነበረውምና ከመዲና ተጨማሪ ኃይል እንዲላክበት ለኸሊፋው አቡበከር ደብዳቤ ላከ።

የኻሊድ ሠራዊት ከሰፈረበት ርቀት የበረሀውን አሸዋ እያቆራረጠ የሚመጣን ፈረሰኛ ተመለከቱ። የሚያነሳው አቧራ የሚመጣውን ሰው በቅጡ እንዳያዩ ጋርዷቸዋል። የኸሊፋው አቡበከር አጋዥ ጦር እንደሆነ ግን ገምተዋል። በትኩረት ሲመለከቱት አጓድ ፊቱን የሸፈነ ፈረሰኛ ነበር። ለማረጋገጥ ወደ ኋላው ተመለከቱ። ምንም ነገር የለም። ኸሊፋው ምን ነክቷቸው ነው የኪስራን ግዙፍ ሠራዊት ለመግጠም አንድ ፈረሰኛ የሚልኩት! አንድ ሰው? አዎ! እስላም በብዛት አያምንም። ወደሠራዊቱ ተጠጋና ኸሊፋው አቡበከር የሰጠውን ደብዳቤ ይዞ ወደ ፊት አመራ። ፊቱን ገለጠና ስሙን አስተዋወቀ “እኔ አሚሩል ሙእሚኒን የላኩኝ ትጥቅና ሠራዊት ነኝ" አለ። አቡበክር የላኩለትን ደብዳቤ ለኻሊድ ሰጠ። ደብዳቤውን ማንበብ ጀመረ።

"የአላህ ባሪያ ከሆነው አቡበከር ለኻለድ የተላከ:-

ወንድሜ! የላኩልክ አንድ ሰው ብቻ እንዳይመስልህ የቃዕቃዕ ድምፅ ከአንድ ሺህ ፈረሰኞች ይበልጣል ቃዕቃዕ ያለበት ሠራዊት ፈፅሞ አይሸነፍም" ይላል። የኻሊድ ፊት በፈገግታ ደመቀ "የአላህ ሠራዊቶች ሆይ! ፋርሶችን ለመግጠም ተዘጋጁ! ተጨማሪ ኃይል ደርሶናል” አለ።

ጦርነቱ ተጀመረ። የጠላት ጦር መሪ ሁርሙዝ ወታደሮቹን አዘዘ “ከኻለድ ጋር ብቻ ለብቻ
በምንገጥምበት ሰዐት ከጀርባ መጥታችሁ ግደሉት" አለ።

የመሪዎቹ ግጥሚያ ተጀመረ። ኻለድ ሁርሙዝንን በመግጠም ተዘናግቶ ሳለ የጠላት ወታደሮች በጀርባው በኩል መጡ። ጀግናው ቃዕቃዕ እንደ አንበሳ የጦር ሜዳውን ተቀላቀለ። አንድ በአጓድ ሁሉንም አንገታቸውን በጠሰ። ጦርነቱንም ሙስሊሞች አሸነፉ።
    አቡበክር ሲዲቅ ይህን ሲሰሙ ለኻሊድ አንዲህ በማለት ደብዳቤ ላኩ “ቀዕቃዕ ያለበት ሠራዊት አንደማይሸነፍ አሁን ያወቅክ ይመስለኛ"

ያ የቀድሞው የድልና የክብር ታሪካችን የተገነባው አንደ ቃዕቃዕ አብኑ ዓምር ባሉ ጀግና ወጣቶች ነበር

ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

3 months, 2 weeks ago

እናንተ ሰዎች ሆይ! እርካታን ማግኘት ማለት ምንድን ነው? እርካታን ማግኘት ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ብቻ ነው ትላላችሁ? አይደለም! አይደለም! ሰዎች፡፡ እርካታን ማግኘት ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ልብ ለልብ መገናኘት፣ ሴትና ወንድ ባንድ በተቀደሰ የትዳር ትስስር ሥርዓት ውስጥ መተሳሰር ነው፡፡

✏️✏️ለሴቶችም እንደዚሁ የዚህ ዓለም ወንዶች ሊያረኳቸው ቢሰበሰቡም እርካታን አያገኙም፡፡ ግን ይሆን አልረካ ያለ ስሜት አንዲት የሐላል ሴት አንድ የሐላል ወንድ ያረኩታል፡፡

ሰዎች ሆይ፤ አንድ ሰው ገንዘቡ ሀብቱ እጁን ወደፈለገው ለመሰደድ ቢያስችለውም ጉልበቱ ይችል ይሆን? አካሉስ ስሜቱን መሸከም ይችል ይሆን? ቢችል እንኳ አንድ ቀን መሸነፉ! በበሽታ መጠቃቱ አይቀርም፡፡ ማድረግ እየፈለገ አይችልም፡፡ ዓይኑ እያየ እያማረው ያጣዋል፤ ያቅተዋል፡፡ እንደዚህ ከሆነ ታዲያ ለምን ከወንጀሉ አይታቀብም? አካሉንና ከብሩን ለምን አይጠብቅም? አካሉንና ከብሩን አጥቶ፣ነፍሱን በበሽታ አስጠቅቶ፣ያማረውን እርካታ ከማጣት በአዱኛ ከመሰቃየት በአኼራ ወደ ገሀነም ከመወርወር አሁን ቢቆጠብ አይሻለውም ትላላችሁ?

ወንድሞቼ ሆይ! ከአላህ (ሱ.ወ) አፈጣጠር ተአምራት ውስጥ አንዱ በቁንጅና የሚመሳሰሉ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን አለመፍጠሩ ነው፡፡ ሴቶች ሁሉ አይመሳሰሉም፡፡ ወንዶችም እንደዚሁ:: ከሁሉም ሴቶች ወንዶች የሚገኘው እርካታም አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ሕጋዊ ባለትዳሮች በተፈጥሯቸው የሰመረ ወሲባዊ ጥምረትን መፍጠር የተሻለ እርካታን ማግኘት ይችላሉ፡፡

#በቀጣይ_ክፍል ☞ዝሙት ስለሚያመጣዉ አደገኛ መዘዝ ይቀርባል

#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል...
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

3 months, 2 weeks ago

?#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ??

? #ምዕራፍ_ሰባት
አሚር ሰይድ

አቡ ሁረይራ ረዐ  እንዳስተላለፉት የአላህ  መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «በአደም ልጅ ላይ የዝሙት ድርሻ ተጽፎበታል። ይህን ድርሻውን  ያለ ጥርጥር ያገኛል። ሁለት ዓይኖች ዝሙታቸው ማየት ነው፡፡ሁለት ጆሮዎች ዝሙታቸው  መስማት ነው፡፡ የምላስ ዝሙት መናገር ነው፡፡ የእጅ ዝሙት መጨበጥ ነው። የእግር ዝሙት መራመድ ነው።ልቦና ያስባል፤ይመኛል። ብልት ደግሞ ይህን ምኞት እውነት ወይም ሐሰት ያደርጋል።» (ቡኻሪና ሙስሊም)

ዚና አይነቱ ብዙ ነዉ የአይን ዝሙት ብዙዎቻችን የተጠመድንበት ነዉ በየመንገዱ በየሰፈሩ ሴቱም ወንድም አፍጥ አግጥን ሆነን ኢማናቻን ከተንሸራተተ ዋል አደር ብሏል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በtiktok የምናየዉ ተቀራኒ አጂነብይ የአይን ዚና መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ዛሬ ሰፋ ያለ ፁሁፍ ያዘጋጀሁት የእጅ ዚናና የጆሮ ዚና ላይ ያተኮሩ ናቸዉ፡፡ወደ ፁሁፉ እናማራ

╔══════════════════════╗
?? #የእጅ_ዚና_ምንነትና_አደገኛነት ??
╚══════════════════════╝

? ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
  ከናንተ አንዳችሁ ከዚያ ያቺን ለርሱ የተከለከለችውን ሴት ከመንካት ይልቅ ጭንቅላቱ በብረት ወስፌ ቢሰፋ ይሻለዋል፡፡»ብለዉናል

ይህ እንግዲህ የእጅ ዚና ቅጣትን የሚመለከት ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ የባሱ ፀያፍና ሕገ-ወጥ ድርጊቶች:- ለምሳሌ መተቃቀፍ፣ መሳሳም፣ መተሻሸትና  ወሲብን መፈፀም ከዚህ የክፉ ቅጣቶችን እንደሚያስከትሉ ከዚሁ መገመት ይቻላል፡፡

⚡️⚡️ለምሳሌ ሕገወጥ መሳሳምን በተመለከተ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

«እርሱ ያ ያቺን ለርሱ ያልተፈቀደችውን ሴት በምኞት በጋለ የወሲብ ስሜት የተነሳ የሚነካት ሰው፣ በፍርዱ ቀን እጁ ከአንገቱ ጋር ታስሮ ይቀሰቀሳል፡፡ እርሱ ስሟት ከሆነ ከንፈሮቹ በእሳት ውስጥ ይቃጠላሉ፡፡ በመጨረሻም እርሱ ዝሙት ላይ ወድቆ ከሆነ ጭኖቹ እኔ ያልተፈቀደ ነገር ላይ ተኝቻለሁ ሲሉ በፍርዱ ቀን በርሱ ላይ ይመሰክራሉ፡፡ ከዚያ ከአላህ ቁጣ የተነሳ ወደርሱ ይመለከታል፡፡ በዚህን ጊዜ የሰውየው የፊቱ ሥጋ ተገሽልጦ ይወድቃል፡፡ እርሱም በትዕቢት እኔ ፈፅሞ ይህንን አልሠራሁም የሚል ከሆነ ከዚያም ምላሱ እኔ ያልተፈቀደን ንግግር ተናግሬያለሁ ሲል ይመሰክርበታል፡፡ እጆቹም እኔ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ነክቻለሁ ይላል፡፡ ዓይኖቹም እኔ ያልተፈቀደውን ነገር አይቻለሁ ትላለች፡፡ እግሮቹም እኔ የሄድኩት ወደተከለከሉ ነገሮች ነበር ይላሉ፡፡ በመጨረሻም ብልቱ እኔ በገቢር እዋልኩት ይላል፡፡ ጠባቂ መላእኮችን በተመለከተ አንዱ እኔ ሰምቻለሁ ሲል ሌላኛው ደግሞ እኔ ፅፌዋለሁ ይላሉ፡፡ በመጨረሻም አላህ እኔ ሁሉንም አውቃለሁ፣ ነገር ግን ለርሱ ደብቄለት ነው እንጂ ይላል፡፡

ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) ለመላኢኮቹ እርሱ ይቀጣ ዘንድ ወደ ጀሀነም????እሳት ውሰዱት፡፡ የኔ ቁጣ በነዚያ ከኔ ምንም ሐያእ በማያደርጉት ላይ በረታች ይላል፡፡ ይህም በአላህ (ሱ.ወ) በቁርአኑ  በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውሞ ይሠሩት በነበሩት እኩይ ነገር በሚመሰከሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አላቸው ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ (አን-ኑር 24:24), (ኢማም ዘሀቢ አል-ከባኢር ውስጥ እንደጠቀሱት)

??  በዑለሞች አተያይ የእጅ ዚና ሲባል የዘመኑ ቴከኖሎጂን በመጠቀም ባዳ ሴቶችና ወንዶች የሚፃፃፉትና የሚላላኩት የተለያዩ ሕገወጥ መልዕከቶችም በዚህ ውስጥ ይጠቃለላሉ፡፡
☞ስልክ ቁጥሮችን የሚከትቡና
☞ቴክስት ሜሴጆችን የሚፅፉ ጣቶችም ከእጅ ይቆጠራሉ፡፡
☞የሞባይል ሰክሪኖችን የሚነካኩና
☞በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ቻት ሴክስን፥ ፎን ሴከስንና የወሲብ ፊልምን ሳይቀር ጠቅ ጠቅ የሚያደርጉ ጣቶችም በዚሁ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ እውነታ ወደ ዓይን ዚና፣ ወደ ምላስ ዚና፤ . ጆሮ ዚናና ወደሌሎችም ሁሉ በየፊናቸው በሚኖራቸው ተሳትፎ ልክ ይለጠጣል፡፡

╔══════════════════════╗
?? #የጆሮ_ዚና_ምንነትና_አደገኛነት ??    
╚══════════════════════╝

የጆሮ ዚና ማለት ብዙ አይነት ነዉ ከነዛ ዉስጥ በጥቂቱ

☞ወሲባዊ ውይይቶችን ማዳመጥ፣
☞ወሲብ ቀስቃሽ ዘፈኖችን መስማት
☞በስልክና በሌሎችም የርቀት መገናኛ ዘዴዎች ስለወሲብ መስማትና ማዳመጥ፣
☞የወሲብ ፊልሞችን ከላሲካል ማጀቢያዎችን ማዳመጥ፣ ወዘተ ከጆሮ ዚና የሚቆጠሩ ናቸው::

ብዙውን ጊዜ ግን ከዚና ጋር የተያያዙ ድምፅ-ነክ ነገሮች ወደ ጆሮ የሚገቡት ዘፈንን በማዳመጥ በኩል ነው፡፡ እንደሚታወቀው ዘፈን ዛሬ ዛሬ የዚና ነዳጅ ሆኗል፡፡ እዎ ዘፈን ከዝሙት አበይት መዳረሻ መንገዶች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር ልብን ያሸፍታል፤ በአድማጩ ልብ ላይም ኒፋቅን ያሰርፅበታል፡፡ ይህም በግለሰቦች ኢማናዊ ኃይላቸው ላይ ከፍተኛ ድከመትንና መንኮታኮትን ያስከትላል፡፡

✏️✏️ ዘፈንን አስመልከተው ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) አል-ፈዋኢድ ውስጥ እንዲህ ብለዋል፦
የዘፈን ፍቅርና የቁርአን ፍቅር በአንድ ግለሰብ ልብ ውስጥ በጋራ አይመጡም! አንዱ ሌላውን የሚያስወጣው ቢሆን እንጂ፡፡”

✏️✏️ አንድ ሌላ ሰለፍ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡-

መሳም የወሲብ፤ ዘፈን የዝሙት፣ ማየት የፍቅር፣ በሽታ የሞት መነሻ እንደሆኑ ሁሉ ወንጀልም የከህደት መነሻ ነው፡፡,,ብለዋል

╔══════════════════════╗
?#ወንዶች_ሴትን_በሀራም_መቀያየር_ደስታ_የለዉም
╚══════════════════════╝

አንዳንድ ጋጠወጦች (ፋሲቆች) ሴት ሲያዩ በሙሉ ዓይናቸው አፍጠው ያያሉ፡፡ ልባቸውም ይከተላታል፡፡ ቁመናዋንና ፈታኝ ውብቷን በማሰላሰል ይባዝናሉ፡፡ ሊያግኟትም ይመኛሉ፡፡ ብሎም ያዱንያ ጣፋጭ ነገር፣ ደስታ ሁሉ በርሷ ውስጥ የተወሰነ ብቻ መሰሎ ይታያቸዋል፡፡ የዱንያ ሰቆቃና ስቃይ ደግሞ እርሷን በማጣት የሚመጣ ይመስላቸዋል፡፡በዱንያ ውስጥ የሚፈለገው ሁሉ በርሷ ውስጥ ያለ መስሎ ይታያቸዋል፡፡ ባስታወሳት ቁጥር ያብድላታል፡፡ ይህን ሁሉ አስቦ ያግኛት እንደሆነ ደስታው የግማሽ ደቂቃ ያህል ብቻ ሆና ትቀራለች፣ ትከስማለች፡፡ ሳይጠግባት ይሰለቻታል፡፡

በሐሳቡ ሲስላት የነበረው ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆንበታል፡፡ ከዚያም ስለሌላ ሴት ማሰብ ይጀምራል፡፡ የሚያስባትን ሊያገኝ ደግሞ እንደዚሁ ተስፋው ይከስማል፡፡ እንደገና ሌላ ይመኛል፡፡ ከዚህችኛዋ ያጣውን ደስታ ከሌላኛዋ የሚያገኝ መስሎ ይሰማውና እንደገና ሌላ ለማግኘት ማሰላሰል ይጀምራል፡፡ ይህችንም ሲያገኝ እንደዚሁ ተስፋው ይከስማል፡፡ እንዲህ እያለ ሊያገኘው የማይችለው ደስታን በመፈለግ እንደባዘነ አንዷን ካንዷ ሲያቀያይር አንድም ቀን የፈለገውን እርካታ ሳያገኝ፣ ሐሳቡ ሳይሞላለትና ሳይጠግብ ዕድሜው ያከትማል፡፡???

3 months, 2 weeks ago

የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡ እንደነርሱ እምነት ከሆነ እነዚህ መስፈርቶችም ኢኸቲላጥን በተገቢው ገደቦች ውስጥ የሚጠብቁ ናቸው::

ሆኖም ግን ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳል የምትሉት ኢኸቲላጥ  ዛሬ ዛሬ በየት/ቤቱ፣ በየኮሌጁ፣ በየዩኒቨርሲቲው፤ በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየገበያ ማዕከሉ፣ በየንግድ ታዎሩ፣ በየመጓጓዣው፣ በየአደባባዩ፣ በየማህበራዊና ሕዝባዊ ስብስቦቹ ላይ የምናየው ዓይነት ነውን? እሺ! እነዚህ ሁሉ የኢኸቲላጥ ዓይነቶች እናንተ ይፈቀዳሉ በምትሏቸው ገደቦች ውስጥ ናቸውን? ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳሉ የምትሏቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በገሀድ አሉን? ሲባሉ አጥጋቢ ምላሽ የላቸውም፡፡ በእውነቱ ዛሬ ዛሬ በየቦታው የምናያቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በወንዶችና ሴቶች መካከል ባለው ኢንተራከሽንና በምግባር ረገድ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሉም፡

ዛሬ ዛሬ ባሉ ኢኸቲላጦች ውስጥ የሴቶች መገላለጥ (ተበርሩጅ)፣ የሒጃብ መስፈርቶች ጥሰት፣ የሴቶች ልቅነትና በአጠቃላይም ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነበት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

እነሆ በኢኸቲላጥ ሳቢያም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፊትናዎችን እያየን ነው፡፡ በተቃራኒ ፆታዎች መካከል ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ሁሉ ምንጩና መፈልፈያው ኢኸቲላጥ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ኢኽቲላጥ ሲኖር በወንዶችና በሴቶች መካከል በቀላሉ የሚያስጠርጥሩ ግንኙነቶች ይፈጠራሉ፡፡ስለዚህ ዛሬ ዛሬ እየተከሰተ ያለው የኢኸቲላጥ ዓይነት ምንም ተቀባይነት የለውም፡፡

✏️✏️ ከሴቶች ልቅነት የተነሳ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉ ኢኽቲላጦችም ተውጠዋል፤ ከስመዋል ማለት ይቻላል፡፡ ወጣም ወረደም ሸሪዓው እንዲህ በታመቀበት አግባብ ውስጥ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉትን ኢኽቲላጦች እንኳን ማበረታታቱ አግባብነት የለውም፡፡

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለዝሙት ለም የሆነ የማብቀያ መሬትን በማዘጋጀት ይህንን ደዌ ለዚህ ደረጃ ያበቃው ትልቁ ነገር ኢኸቲላጥ (የፆታዎች ቅልቅል) ነው፡፡ዝሙትን መሥራት ውሀን የመጠጣት ያህል ቀላል ያደረገውና ከዚያም አልፎ ሰዎች በዝሙት እንዲፎካከሩ ያደረገው ይኸው ኢኽቲላጥ የተባለው ደዌ ነው፡፡

ዛሬ ዛሬ የዓለምን ማህበረሰብ ቀፍድዶ የያዘው የዝሙት ዛር በዋናነት የተፈለፈለው ከኢኸቲላጥ ነው፡፡እናም ከኢኸቲላጥ ጋር የተያያዘውን እውነታ መገንዘብና ማህበረሰቡን ከገባበት ሕመም መፈወስ እንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ ይታያል፡፡ እንደ ኢኸቲላጥ በዝምታ የዝሙትን መርዝ የረጨው ሌላ የመዳረሻ መንገድ የለምና፡፡ሌሎች የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡

ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ ያለማካበድ ከሌሎች ሀይማኖት በላይ ሙስሊሙ ላይ ይስተዋላል፡፡የኢኽቲላጥ መንገድ በኸይር ስራ ስም፡በሙስሊም የመድረክ ዝግጅቶች፡በሙነሺድ ተብየዎች በሚያዘጋጁት የነሺዳ ማስመረቂያ ሰም ኢህቲላጥ ተበራክቷል፡፡በፊት ታስታዉሱ ከሆነ የዛሬ 3አመት በፊት ሙነሺዶች መጣን መጣን ባሉ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ይዘዉ የመጡት ነገር ከባድ ነዉ ለወደፊት ከባድ መዘዝ ይዘዉ መጥተዋል እያልኩ ብቻየን ፁሁፍ ሳዘጋጅ በጣጣም ተቃዋሚ ይበዛ ነበር ትችቱ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ተዉኩኝ..ይሄዉ ዛሬ ነሺዳና ሙዚቃ መለየት እስከሚያቅተን በዜማ ሲጣሉ ሊደባደቡ ሲደርሱ
ነሺዳና ሙዚቃ ሲሰራረቁ እያየን ነዉ፡፡

የአሁን ሴት ሮል ሜድልሽ ማን ነዉ ብትባል አንዱን ሙነሺድ ነዉ? የምጠራዉ...ሚዲያ ላይ በፊት ብዙ ሴቶች በማስረጃ እንደነገሩኝ በጣጣም ብዙ የሙነሺዶች ገመና አቃለሁ የሚሰቀጥጡ ነገሮች በማስረጃ የማቀዉ አለ

አሁን ላይ የሚሻለዉ እነሱን አለመከታተል ነዉ ለምን የሚሰሩት ለአሏህ ብለዉ የአላህን ወዴታና የነብዩን ዉዴታ ለማግኘት ሳይሆን ታወቂ ለመሆን ለሴቱ የተሻለ ስራ እኔን ሴቱ እንዲወደኝ የትኛዉ ስራ ልስራ ስለሆነ እነሱን መከታተሉን ትቶ...አላህ ሆይ ቀጥተኛ መንገድ ምራቸዉ ወይ በዚሁ በዱንያ በሙነሺድ ስም የሚሰሩትን ግፍ ያሳየን ብሎ ዱአ ማድረጉ ይሻላል፡፡

«አደገኛው የኢስላም ጠላት አላዋቂ ሙስሊሞች ናቸው።በአላዋቂነታቸው ላይ ስሜታዊ ይሆኑና በድርጊታቸው የኢስላምን እውነተኛ ውበት ያጠለሻሉ።የሌላው ዓለም ሰዎች የነርሱን ድርጊት በመመልከት ኢስላም ያ እንደሆነ ያስባሉ። (ሽህ ኢሕመድ ዲዳት) የተናገሩት ንግግር የአሁን ዘመን ሙነሽዶችን ያካትታል??

? በተጨማሪ ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ በሙስሊሙ በዲን ስም ተጋኗል፡፡

? #ሙነሺዶች፡ሚንበር ቲቪ የተለያዩ ሙሀለጣ ባላቸዉ ፕሮግራሞች አኽቲላጥ አለ በዚህ ኢኽቲላጥ ወደ ዝሙት መስመር የሚገቡ አሉ

? #የሙስሊም_በጎ_አድራጎት_ማህበር እየተባሉ ሴትና ወንድ የሚደባለቁበት አለ፡፡አረጋዉያንን መንከባከብ..የተቸገሩ ለመርዳት ስበብ ለጀመአችን ማጠነከሪያ እየተባለ የሙስሊም ሴቶች ተበጃጅተዉ አንፀባራቂ ሎሚ ከለር ልብስ ለብሰዉ ከአጂ ነብይ ወንድ ለጀመአ ማጠናከሪያ በሚል ብር ማሰባሰብ..ለጀመአችን እየተባለ ሲዋክ መሸጥ...ቡና እያፈሉ በየመንገዱ መሸጥ...ጫማ የሚጠርጉ አለ...
የደካሞች ቤት ተብሎ የጀመአየ ልጅ አብረዉ ወንድ ጋር ሂደዉ ሴቶች ልብስ ሲያጥቡ ወንዱ ቤት ያስተካክላል..ሰዉ ያላስተዋለዉ ሙዱን የቀየረዉ የዝሙት መንገድ ነዉ☺️

#አሁንም እየሆነ ነዉ ለወደፊትም ታዩታላችሁ የዝሙት መንገድ ነዉ አሁንም አንዳንዶችም በድብቅ ገብተዉበታል::

የአላህን ዉዴታ አጅር ለማግኘትና ሴት ልጅ ቡና የምታፈላዉ ቤተሰቦቿን ለመሀደም እንጂ መንገድ ላይ ወንድ እንዲያት አይሆንም ነበር...ለጀመአየ ብላ ጫማ የምጠርገዉ የእናቷን የአባቷን ጫማ ረግጣ ወጥታ ነዉ...የአረጋዉያን ልብስ ልጠብ ብላ ስትወጣ የእናት የአባቷ ልብስ ግን ቆሾሾ ተቀምጧል...መቅደም ያለባቸዉ የአክስት የአጎቶቿ ልብስ የሚያጥብላቸዉ ተቸግረዋል ወይም ጎረቤቷ እማማ እንትና ልጅ የላቸዉ የሚንከባከብ የላቸዉ ልብሳቸዉን የሚያጥብላቸዉ የለ በርሀብ እየተሰቃዩ ይሆናል..ይህን ሁሉ አልፎ ሂዶ ጀመአየ አዘዘኝ አሚሬ አዘዘኝ ብሎ መንጦልጦል  ከምር አስመሳይነት ነዉ?፡፡በፊት ወንድ ሴትን ልጅ ለማዉራት ካፌ ወይ ወጣ ያለቦታ ነበር ዛሬ ግን  የጀመአ ፕሮግራም አለ በሚል ስም መገናኘት ሆነ አልሸሹም ዘወር አሉ ነገር ግን ኮዱን ቀየሩ? ነዉ የምንለዉ ወዳጄ..ቤተሰብ ሆይ ንቁ እባካችሁ‼️‼️

ግን ሴቶች ለብቻ ወንዶች ለብቻ የሆነ በጎ አድራጎት ወይ ጀመአዎች አሉ በተጨማሪ ትላልቅ ሰዎች ባለሀብቶች አሉ ለኸይር ስራ የተቋቋሙ እነዚህን ግን እንደማያካትት ልታቁልኝ ይገባል፡፡የእኔ ሀሳብ ኢኽቲላጥ ያለባቸዉ የወጣቶች ጀመአዎችን ነዉ

#በቀጣይ_ክፍል...የእጅ ዚና የጆሮ ዚና ላይ ያተኮረ ፁሁፍ ቢኢዝኒላህ ይዤ እቀርባለሁ

#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል....
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

3 months, 3 weeks ago

?እስጢፋኖስ አበራ ደግሞ እንደዚህ ብሏል «በአዲስ አበባ ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ መደበኛ ሴተኛ አዳሪዎች አሉ፡፡በየምሽቱ ደግሞ በከተማዋ ሰማይ ሥር ተጠልለው የወሲብ ንግድ የሚያካሄዱ ሴተኛ አዳሪዎች ብዛት 200 ሺህ ነው፡፡»ብሏል

?ረዳት ፕ/ር አደም ካሚል እንዲህ ብሏል
እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት በአዲስ አበባ ውስጥ 400ሺህ መደበኛ ሴተኛ አዳሪዎች አሉ፡፡ይኸው አኃዝ ደግሞ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችና በተለይ አሕጉራዊ ስብሰባዎች ሰሞን በእጥፍ በመጨመር 800 ሺህ ይደርሳል፡፡››ብሏል
ይህ ሁሉ ጥናት ከ2009 በፊት መሆኑ ይታወቅ፡፡

ሴት ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ቱሪስቶች በጣም በዝተዋል..ለእነዚህ ቱርስቶች የሚያገናኝ ደላላ በዛዉ ልክ በዩኒቨስቲ በመስሪያ ቤት በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወጥመድ ዘርግተዉ ድንግል የሆነችዉንም ያልሆነችዉንም በየምርጫዉ ያቀርባሉ፡፡

የዴይሊ ኔሽን ፀሐፊው አዲስ አበባን ከባንኮክ ጋር በማነፃፀር እንዲህ ይገልፃታል፡-

‹‹ብዙ የዓለም ሀገሮችን ጎብኝቻለሁ፡፡እንደ ታይላንዷ ባንኮክ የወሲብ ንግድ የሚካሄድባት ከተማ አላየሁም የሚለው አንድሪው በቀናት የአዲስ አበባ ቆይታው የተመለከተው የከተማዋ የምሸት ገፅታ እና የወሲብ ንግድ ባንኮክን እንዳስታወሰው እና ከባንኮክ ጋር  እንደተመሳሰለበት ይጠቁማል፡፡ ባንኮክ እና አዲስ አበባ በብዙ ነገሮች ይመሳሰላሉ፡፡ሁለቱም በወሲብ ያበዱ እና ወሲብ በስፋት የሚነገድባቸው ከተሞች ናቸዉ ሲልም ይገልፃቸዋል፡፡እንደ ባንኮክ ሁሉ በአዲስ አበባ ናይት ክለቦችም የጦፈ የወሲብ ንግድ ይካሄዳል፡፡ በጎበኘኋቸው ናይት ክለቦች ሁሉ ለሽያጭ የቀረቡ በርካታ ውብ ታዳጊ ሴቶችን ተመልከቻለሁ፡፡መኪና ውስጥ እና በየግድግዳው ሳይቀር ወሲብ የሚፈፅሙ ሰዎችን በተለይ ቦሌ አካባቢ ተመልከቻለሁ፡፡እንደ ባንኮክ ሁሉ በርካታ የወሲብ ቱሪስቶችን በአዲስ አበባ መመልከቴ ደግሞ በጣም አስገርሞኛል፡፡ባንኮክ የአውሮፓ የወሲብ ቱሪስቶች መዳረሻ እንደሆነችው ሁሉ አዲስ አበባም የብዙ የዓረብ የወሲብ ቱሪስቶች መናኸሪያ ወደ መሆን መቃረቧንም ተረድቻለሁ ይላል፡፡››

የውጭ ዜጎች ስለ አዲስ አበባ ከተናገሩት መካከል አንዱ እንዲህ ብሏል<<አዲስ አበባ ከሳምንት እስከ ሳምንት ጭፈራ የደራባት፣ሰርክ ጭሰት ያለባት፣ ናይት ክለቦቻ ሰርክ እንዳቃሰቱ የሚያነጉባትና ሰርክ በወሲብ ንግድ ያበደች የዓለማችን ልዩ ከተማ ናት። ከተማዋ ዕረፍት የሚባል ነገር የላትም፤ ጭፈራ፣ ዳንስና የወሲብ ንግድ የዘወትር ልማዶቿ ናቸውና፡፡»ብሏል

╔══════════════════════╗
?  #በአዲስ_አበባ_የድንግልና_ንግድ_መስፋፋት        
╚══════════════════════╝

ያደጉ አገራት በዕለታዊ ጋዜጦቻቸው ላይ ሴተኛ አዳሪን ሲያቀርቡ ..በኢንተርኔት ድንግልና ሲቸረችሩ አዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶቿን በሴተኛ አዳሪ ሞልታ ከማንም አላንስም እያለች ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ለድንግልና አፍቃሪዎች ለመገብየት የሚሠማሩ ደላሎች አሉ፡፡ ከትንሿ ሺህ ብር እስከ 20 ሺህ  ብር ድረስ እንደሚከፍሉ በመንገር አዳጊ እና ወጣት ሴቶቹን ለማማለል ይጥራሉ፡፡

ከኢትዮጵያዉን ድንግልና አሳሾች መሀከል እየጎሉ የመጡ ታዋቂ ባለሀብቶች፣የማስታወቂያ ባለሙያና ዳያስፖራዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡›

ነጮቹ ሴተኛ አዳሪ ከፈለጉ በቀላሉ የምሽት ከልብ ሄደው አንስተው መምጣት እንደሚችሉ ስለሚያውቁት ትኩረታቸው የቤት ልጅ ላይ ነው፡፡ ጥያቄያቸውን ከአጥጋቢው በላይ መመለስ ደግሞ ለወሲብ ደላሎች በጣም ቀላል ሥራ ነው፡፡

የላይኛዉ ምንጭ መፅሀፍ ስለዚህ ጉዳይ ይህንን መረጃ አጋርቷል

የእኛ አገር ሴቶች ብዬ ሁሉንም መጠቅለል ባልችልም የሚገጥሙኝ ሴቶች ሁኔታ ግን በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ፈረንጅ ይዘን ስንሄድ ዓይናቸው ይቀላውጣል፡፡ቆንጆ እና አማላይ የምትላት ሴት አጣብሰኝ እንጂ,ብላ ትጠይቅሀለች፡፡በፈጣጣ ሰላም ብለው ከየት ነህ? ብለው ነጩን የሚያዋሩት ብዙ ናቸው፡፡ በተለይ ወደ ቦሌ የውጭ አገር ዜጎችን ይዘዋቸው ከሄዱ እንግሊዘኛን እንደ ውሃ የጠጡ ወጣት እንስቶች ፈረንጆቹን ተቀላጥፈው ጋይዶቹን ከጨዋታ ውጭ ያደርጓቸዋል፡፡ለእኛ 10 ብር ለመስጠት የሚያምጡ ቱሪስቶች ለሴቶች ለጊዜያዊ ቆይታ እስከ 200 ዶላር ይሸኛቸዋል፤ ይላል የቱር ጋይዱ ጌታሁን፡፡ የፈረንጆ፥ ወሲባዊ ፍላጎት ጥግ ድንግል ሴት ድረስ የሚሄድ ሲሆን የእነ ጌታሁን እና ንጋቱ ዓይን ይፈጣል፡፡ደከመውም ቢሆን ግን ፍላጎታቸውን ይሞላሉ፡፡ ጥያቄው አሁን አሁን እየተበራከተ ስለመጣ ከተሳካላቸው እንግዶች ከማግኘታቸው በፊት ድንግል ሴቶችን አግባብተው ለመጠበቅ ይሞክራሉ፡፡ከተማዋ ላይ ያለው የድንግል ሴት እጥረት ግን ይፈትናቸዋል፡፡

╔══════════════════════╗
  #በአዲስ_አበባ_የግብረሰዶም_መስፋፋት    
╚══════════════════════╝

ግብረሰዶማዊነት (ወንድ ለወንድ እና ሴት ለሴት) በከተማዋ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡በምሽት መዝናኛ ቤቶች ውስጥ የሚከፈቱ ወሲብ ቀስቃሽ ሙዚቃዎች፣ጭፈራዎችና የራቁት ዳንስ  ለግብረሰዶማዊነት መስፋፋት በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡

ዊክሊክስ ድርጅት  ያጋለጠው ሀቅ ግብረሰዶማዊነት በአዲስ አበባ መስፋፋቱን አጋልጧል

“በሀገሪቱ ሕግ ግብረሰዶማዊነት በእስራት የሚያስቀጣ የወንጅል ተግባር ቢሆንም በተለይ ባለፉት አስር ዓመታት የግብረሰዶማዉያን ቁጥር በተለይ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡በግብረሰዶማዊ የወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ በርካታ ወጣት ወንድ እና ሴቶችን ጭምር በቀላሉ በከተማዋ ማግኘት ይቻላል፡፡ ግብረሰዶማዉያን በምስጢር የሚሰባሰቡባቸው ድብቅ የመዝናኛ እና የመገናኛ ቦታዎችም አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ስማቸው እንዲጠቀስ ከማይፈልጉና በማህበር ጭምር ከተደራጁ የከተማዋ ግብረሰዶማዉያን ያገኘሁት መረጃ እንደሚጠቁመው ሊደርስባቸው የሚችለውን ማህበራዊ መገለል፣ መድሎና ወገዛ በመፍራት እራሳቸውን የደበቁ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ወንድ እና ሴት ግብረሰዶማዉያን በአዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለው እውነትም ተመሳሳይ ነው፡፡በተለይ ዩኒቨርሲቲ በተስፋፋባቸው የሀገሪቱ ከተሞች መሰል ዝንባሌ ያላቸው ሰዎችን በብዛት ማግኘት ይቻላል፡፡(ጥናቱ ከ2009 በፊት የተጠና ነዉ አሁን 2016 እሰቡት)
እርግጥ ግብረሰዶም ከከተሞች አካባቢ ይልቅ በገጠር በጣም ይጠላል፡፡ ከአዋቂዎች ይልቅ ወጣቶች ግብረሰዶማዊነትን በተመለከተ አዎንታዊ አመለካከት አላቸው፡፡በዚህም የተነሳ ግብረሰዶማዊነት በወጣቶች መካከል በየጊዜው እየተስፋፋ ነው፡፡›>

?? #በቀጣይ_ክፍል ዝሙት እንዲስፋፋ በር የከፈተዉ የቤተሰብ እንዝላልነት እና የዝምድና ትስስር መላላት እንደሆነ እንዳስሳለን

#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ወንደኛ አዳሪ፣ወንድ ሸሌ፣ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት ኢላሂ ይወፍቀን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል...
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

3 months, 4 weeks ago

«መጥፎዎቹ ወንዶች ልጃገረዶችን ያበላሻሉ፡፡ ከዚያም ማግባትን ሲያስቡ ሷሊሕ  ሚስት ፍለጋ ይሄዳሉ፡፡ ግን የምታገኛት ሚስት ያንተው ዓይነት ሥነ-ምግባር ያላት ትሆናለች፡፡ አብዛኛው ወጣት ገርልፍሬንድ ብሎ የያዛትን ሕገወጥ የወሲብ አጋሩን በፍፁም አላገባትም ይላል፡፡ ታዲያ እኔ የምልህ ነገር ቢኖር የዝሙት ጓደኛህን ባታገባትም እንተ የምታግባት ሚስት የሌላ ሰው የዝሙት አጋር እንደነበረች ቅንጣት ታክል አትጠራጠር፡፡ ከፈለክ ይህንን የአላህ ተባረከ ወተዓላ ቃልን አንብብ፡- መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ (አን-ኑር 26)

╔══════════════════════╗
 #ሴቶች_በዝሙት_የሚያስተናግዱት_ጉዳት 
╚══════════════════════╝

በዚና ሳቢያ የሴቶች ወሲባዊ ህይወት ውጥንቅጡ ወጥቷል፡፡ትዳርና ቤተሰብን አጥተዋል፡፡ለሰቅጣጭ ወሲባዊ እብደቶች ተዳርገዋል፡፡ ከሰው ያልተፈጠሩ በሚመስል መልኩ የወሲብ መንገደኞች የጭካኔ አያያዝ አርፎባቸዋል፡፡ሴቶች የሕዝቡ መሠረት መሆናቸው ቀርቶ የሕዝብ ቢራቢሮ ሆነዋል፡፡እራሳቸውን ለማሻቀጥ እዚያም እዚህም ሲርመሰመሱ ይውላሉ፡፡
☞ ውርጃ እንደጉድ ይካሄድ።
☞የእንስቶች ማሕፀን እንደጉድ ይሳሳል፡፡
☞ የማሕፀን ግድግዳቸው ይደማል፡፡
☞ ሴትነታቸው ረክሶ የስሜት ማራገፊያ ዕቃ ተደርጎ ይታያሉ፡፡ ታዲያ የነዚህ ሁሉ ጉዳቶች ሰለባ የሆኑ ሴቶች ብዙኃኑ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የሙጥኝ ያሉ ናቸው፡፡

? ሴቶቹ በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው ወሲባዊ ጥቃቶችና በሚፈፀምባቸው ወሲባዊ እብደቶች የተነሳ እነሆ ዛሬ ዛሬ የወሲብ ሕይወታቸው ምስቅልቅሉ ወጥቶ በወንዱ ፍላጎት ውስጥ ታጥረው ይገኛሉ፡፡ ይህች ዓለም ከሴቶች ማግኘት የሚገባትን ፈርጀ ብዙ አስተዋፅኦ ተጨናግፎ፣ሴቶች የማህበረሰቡ የሕይወት አካል ሳይሆኑ ለወንዶች የስሜታቸው ማራገፊያ እንደሆኑ ተደርገው ታይተዋል፡፡

ዛሬ ዛሬ ሴቶች ስብዕናቸው ወርዶ፣ ገመናቸው ገሀድ ወጥቶ፣ ገላቸው በአሻንጉሊት ቅርፅ ሳይቀር ተሠርቶ፣ የሴትነት ወጋቸው ጠፍቶ፣ክብራቸው ተዋርዶ፣ዓለም በሴት ልጅ ላይ ፊቷን አዙራ የሚደርስባትን ችግር ብቻዋን ትጋፈጠዋለች፡፡የዓለማችን እኩያንና የኢስላም ጠላቶች ሴቶችን አራቁተው በገላቸው ይዝናናሉ፡፡ ሴት ልጅ የሕይወት አጋር መሆኗ ቀርቶ የወሲብ አጋር ብቻ ተደርጋ ትታያለች፡፡ይህም ችግር በዓለም ደረጃ ሥር የሰደደና የዝሙት መስፋፋትን በጉልህ የሚያሳይ ነው::

⚠️ከዚና ወንጀል ተውብትን ሳያደርጉ የሚሞቱ ግለሰቦች ቅጣት በመቃብራቸው ውስጥ ይጀምራል፡፡በረጅም ሐዲስ ውስጥ እንደተዘገበው አንድ ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ህልም ማየታቸውን ተናገሩ፡፡ከርሳቸውም ጋር ሁለት ሰዎች (ጂብሪልና ማሊክ በሰው ሱረት ሆነው) ነበሩ፡፡ሁለቱ ሰዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ኃጢአተኞች አንዴት በበርዘኸ(በሞትና በፍርዱ ዕለት መካከል ባለው ሕይወት ውስጥ) ሲቀጡ እንደነበረ ያሳዩዋቸው ጀመር፡፡ ይህንኑ ሲገልፁ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-

« በመሬት ውስጥ ያለ ጉድጓድ ዘንድ እስከምንደርስ ድረስም እንዲሁ እያሳየኝ ወደፊት መዛዛችንን ቀጠልንበት፡፡ የመጋገሪያ ጉድጓድ ይመስላል፡፡ ከላይ በኩል ጠባብና ከታች በኩል ደግሞ ሰፊ የሆነ ነው፡፡ ጉርምርምታና ድምፆችም ከርሱ ውስጥ ይወጡ ነበር፡፡ ወደ ውስጡ ተመለከትን፡፡እርቃነ ስጋቸውን የሆኑ ወንዶችና ሴቶችንም እየናቸው፡፡ከጉድጓዱ ስር ከታች በጣም የነደደ እሳት ነበር፡፡ እርሱ ድንገት በነደደ ቁጥርም ወንዶቹና ሴቶቹ ይጮኻሉ፡፡ወደላይም ከፍ ይላሉ፤ከሞላ ጎደል ከጉድጓዱ ውስጥ ለመውደቅ አስከሚቀርቡ ድረስ፡፡ እሳቱ እያነሰ በሄደ ቁጥርም ወደ ስሩ ይመለሳሉ፡፡እኔም እነዚህ እነማን ናቸው? ስል ጠየኳቸው፡፡እነርሱም,እነዚያን ራቁታቸውን በጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ወንዶችና ሴቶችን በተለመከተ፤ እነርሱ በዚና ላይ የወደቁ ወንዶችና ሴቶች ናቸው በማለት መለሱልኝ::(ሰሒህ ቡኻሪ)

╔════════════════════════╗
#ስሜትን_ለመቆጣጠር_የሚያስችሉ ጥበባዊ ምክሮች     
╚════════════════════════╝

ታላቁ ሊቅ ኢማሙ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ስሜትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ጥበባዊ ምክሮች አል-ፈዋኢድ ከተሰኘ መፅሀፋቸዉ የተወሰዱ ምክሮችን ያስተንትኗቸዉ

➊ የሰው ልጅ የመላዕክት አእምሮ የእንሰሳት ፍላጎትና የሰይጣን ትልም አለው፡፡ከነዚህም አንዳቸው ያይላል፡፡ አንተ ትልምህንና ፍላጎትህን ማሸነፍ ከቻልከ ከመላኢካ የበለጠ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ትሆናለህ፡፡ ትልምህና ፍላጎትህ ካሸነፉ ግን አንተ ከውሻ የበለጠ ዝቅ ያለ ደረጃ ላይ ትሆናለህ

➋ ነፍስያህን ተጠንቀቃት፤ምክንያቱም በርሷ ቢሆን እንጂ ምንም መጥፎ ዕድል አያገኝህምና፡፡ስለዚህ ከርሷ ጋር በጭራሽ አትታረቅ፡፡በአላህ እምላለሁ! ክብሯ የሚገኘው ለአላህ እጅ በመስጠቷ ነው፡፡ ልዕልናዋ የሚገኘው ከመተናነሷ ነው፡፡ሕዳሴዋ የሚገኘው ከስብራቷ ነው::ምቾቷ የሚገኘው ከፈተናዎቿ ነው፡፡ ደህንነቷ የሚገኘው ከአላህ ፍራቻዋ ነው፡፡እንዲሁም ደስታዋ የሚገኘው ከሐዘኗ ነው፡፡

➌ ለአላህ ጥራት ይገባው! ውጫዊ ገፅታዎቻችሁን በተቅዋ ልብሶች አስጊጦላችኋል፤ውስጣዊ ማንነቶቻችሁ ለከንቱ ስሜቶች እጅ በሰጠቡት ጊዜ፡፡ እናም ልብሶቻችሁ የትም ባወዱ ጊዜ፣የከንቱ ፍላጎቶቻችሁ ተፅዕኖ ብቅ ይላል፡፡ታማኝ ሙእሚኖች ግን ከዚያ ችላ ይላሉ፡፡ክፉ ሠሪዎች ግን ወደዚያ ያዘነብላሉ፡፡

➍ አንድ ሰው የእዝነት የለሽ ሚስት ባለቤት፣ምህረት የማያደርግ ልጅ አባት፣ የማይታመን ጎረቤት፣ ምንም ምክር የማይለግሰው ጓደኛ፣በተሳሳተ መንገድ የሚፋረደው የስራ አጋር፣ጠላትነቱ ፈፅሞ የማይቋረጥ ባላንጣ፣ ወደ ከፋት የተዘነበለች ነፍስያ፣ የተጋጌጠች ዓለም፣ ከንቱ ፍላጎቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስሜቶች፣ ከባድ ንዴት፣ የሰይጣን ሽንገላ እና የቁጥጥር ድከመት ባለቤት ሆኖ ሳለ እንዴት ነው ደህንነት ሊሰማው የሚችለው? በርግጥ አላህ እርሱን ከታደገውና ከመራው እነዚህ ሁሉ ችግሮች በቁጥጥሩ ሥር ይሆናሉ፡፡ ግን አላህ እርሱን ችላ ካለውና ከተወው፣ እርሱን ለራሱ ትቶት፣ እነዚህ ሁሉ ጭንቀቶች እርሱን ያጠፉታል፡፡

➎ ባሪያው ከፊት ለፊቱ የሚቆምለት ጌታ አለው፤ ብሎም የሚኖርበት ቤት አለው፡፡ ይህም በመሆኑ እርሱ ከአላህ ጋር ከመገናኘቱ በፊት የአላህን ውዴታ ማግኘት አለበት፤ ልክ ወደቤቱ ከመግባቱ በፊት የቤት ዕቃውን ማስገባት በዕቃ መሙላት እንዳለበት ሁሉ፡፡

➏ / መሬት ሰፊ ናት፡፡በርሷ ላይ የሚተከልባትን ማንኛውንም ነገርም ትቀበላለች፡፡አንተ የእምነትና የተቅዋ ዛፍን ከተከልክባት የአኼራን ጣፋጭነት ትሰጥሀለች፡፡ የድንቁርናና የስሜትን ዛፍ ከተከልከባት እርሷም መራራ ፍሬ ትሰጥሀለች፡፡

➐/ አላህ የመጪውን ዓለም ደስታዎች ቃል ገብቶላችኋል፡፡ስለዚህ ችኩል አትሁኑ፡፡እነርሱንም በዚህች ዱንያዊ ሕይወት ውስጥ አትፈልጉ፤ ልክ እናንተ ሰብሎችን ከመሰብሰቢያ ጊዜያቸው በፊት እንደማትቆርጧቸው ሁሉ፡፡ከቆያችሁ እነርሱ ለናንተ በላጭ ይሆናሉ፡፡ልክ እንደዚሁ የመጪው ዓለም ደስታዎች እጅጉን በላጮች ናቸው፡፡»

?በቀጣይ ክፍል ኢትዮጲያ እንዴት ዝሙት እንደተስፋፋ እና አዲስ አበባ ላይ ያሉ የተደበቁ የዝሙት እዉነታዎች ላይ እንዳስሳለን...

?#ምንጭ☞65%በዝሙት አንዘምን መፅሀፍ

#ምዕራፍ ➌ይቀጥላል.....

join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

4 months ago

?#የሙስሊሞችን_ሥጋ_የተመገበው_የእንግሊዙ_መሪ_ሪቻርድ

አውሮፓውያን "የአንበሳ ልብ" ሲሉ ያሞካሹታል። ታሪኩን በሚገባ ያወቁት ደግሞ “የአሳማ ልብ ባለቤት” ብለው ይጠሩታል። እርሱ አያቶቹ መስቀላዊያን በይተል መቅዲስን በተቆጣጠሩ ጊዜ ያደረሱትን በደል በአካ ከተማ የደገመው ሪቻርድ ነው። 
   ከግብፅ እስከ ዱባይ ከቦሊዩድ እስከ ፎረስት ጋምብ ጸሐፊዎች ገፃቸውን፣ ዳይሬክተሮች ስክሪብታቸውን ፕሮዲዩሰሮች ፊልሞቻቸውን በስሙ አስውበውበታል። በጀግንነት እያወደሱ ስብእናውን እያገነኑ አውስተውታል። ግና እርሱ ሙስሊሙን ጀግና ፈረሰኛ ኢሳ አል አዋምን ወደ ክርስቲያን ጦረኛ የቀየረ፣ የሙስሊሞችን ስጋ የበላ ሙስሊም ጠሉ ሪቸርድ ነው።
"ከቀናቶች በአንደኛው ቀን ምግብ ሰሪ አገልጋዩን ለምሳ ትኩስ የአሳማ ሥጋ እንዲያቀርብለት አዘዘ። ጣፋጭ አድርጎ እንዲሰራለትም ተናገረ። ምግብ ሰሪው አሳማ የት ሀገር እንደሚገኝ አያውቅም። ቢፈልግም ማግኘት አልቻለም። ከየት ያምጣ ግራ ገባው።  በምግብ ጠረጴዛው ላይ የአሳማ ስጋ ከሌለ መገደሉ አይቀሬ ነውና ተጨነቀ። አንድ መላ ዘየድ። ሁለት ሙስሊም እስረኞችን አረደና ስጋቸውን አብስሎ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ?። የምሳ ሰአት ደረሰ። ንጉስ ሪቻርድ ምግቡን መብላት ጀመረ። ተመግቦ እንዳበቃ በጥፍጥናው ተገረመ። የሰራለትን ሰው አመሰገነ ግና ስጋው የአሳማ አለመሆኑን ተገነዘበ። ምግብ ሰሪውን አስጠራና  "የአሳማውን ጭንቅላት አምጡ" ሲል አዘዘ።
   ምግብ ሰሪው ምን ያርግ? ምንስ ይበል?! ምላሱ ተኮላተፈ። በእጅጉ ተሸበረ። በፍርሃት ራደ። በድንጋጤ ተንቀጠቀጠ። በመጨረሻም እውነቱን ለማሳየት ወሰነ። የታረዱትን የሁለቱን ሙስሊም ምርኮኞች ጭንቅላት ወደ ሪቻርድ ማምጣት ነበረበትና ፊት ለፊቱ አቀረበ።
ሪቻርድ ቅንቅላቶቹን ሲመለከት በሳቅ እና በደስታ ቦረቀ። እንዲህም አለ:- "ስልሳ ሺህ ሙስሊም እስረኞች እስካሉን ድረስ የአሳማ ሥጋ ከእንግዲህ አንፈልግም እነሱን እያረዳችሁ አቅርቡልኝ ስጋቸው ጣፋጭና ጥዑም ነው" አለ።
ሰላሐዲን አልአዩቢ ሙስሊም ምርኮኞቹን እንዳይገድል ሠላሳ መልዕክተኞችን ላከ። ግና ሪቻርድ ሠላሳዎቹንም መልዕክተኞች ገድሎ ስጋቸው ተጠብሶና ተቀቅሎ እንዲመጣ በማድረግ ለጓደኞቹ የክብር መስተንግዶን አዘጋጀላቸው። ጭንቅላታቸው ተቀቅሎ እንደመረቅ ቀረበ።
በአካ ከተማ ሀያ ሺህ በሌላ ዘገባ ስልሳ ሺህ ሙስሊሞችን ጨፈጨፈ። ወንዶች ከከሴቶች ሳይለይ ህፃን ከአረጋውያን ሳይመርጥ አረደ። በርካቶችን ማርኮ አረደ። ብዙዎችን በቁማቸው ቀበረ"
   ይህ ነው የሙስሊሞችን ሥጋ ተመጋቢው ሪቻርድ።

ምንጭ-
                  البداية والنهاية
                  النوادر السلطانية والمحاسن اليوسفية
Mahi mahisho

ለሌሎች ያካፍሉ
join???
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago