Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Yene Maleda psychological service and Training Center

Description
Advertising
We recommend to visit

[ 📍Premium Content Channel 🎯]
Join ✅ Now This backup channel 👇
@verified_channels

Last updated 4 месяца, 2 недели назад

Malu Trevejo 🍓🍒18+ 💦

Last updated 3 недели, 2 дня назад

@schr0dinger - admin

Last updated 2 месяца, 2 недели назад

2 months, 1 week ago

መልካም የሴቶች ቀን

👉ከዚህ በፊት በዚህ ቀን መልካም ምኞቴን የመግለፅ    ልምድ አልነበረኝም ነበር።አሁን ግን ለማለት እገደዳለሁ ምክንያቱም እናተ ጀግና እናቶች ልዩ ፍላጎት(special need) ለሚፈልጉ ሰዐታቹን እና እድሜያቸውን ሰታቹ በማሳደግ ለምትገኙ ዉድ ሴቶች ይህ ከፈጣሪ ዘንድ  የተሰጠ እርግማን አይደለም ይልቁኑ ልዩ ስጦታ አድርጎ የሰጣቹን ልጅ በፍቅር እንድታሳድጉት ጭምሪ ነዉ። በመጠኑ በዚህ ስራ ውስጥ ባየውት ከባድ ሃላፊነት እና ጭንቀት ምን ያህል መስዋዕትነት እንዳለበት በጥቂቱ አይቻለሁ ፣ብቻ እናተ ጀግና ሴቶች በብርቱ ማንነታቹ አለም ጭምር ያስመሰግናቸዋል።
👉ይህም ብቻ አይደለም በዚህ ሙያ እያገለገላቹ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ እንዲሁም እንዚህን ልጆች ለገንዘባቹ ምንጭ ሳተደርጉ ለምሰሩ ባለሙያዎች አሁንም እንኳን አደረሰን።
እግዚአብሔር የምትፈራ ሴት ሁሌም ትመሰገናለች።

ለተጨማሪ ፦
➪ የስነልቦና  ባለሙያ ለማግኘት
ይደውሉ 👇👇
☎️ +251905141127
የቴሌግራም ገፅ 👇👇
https://t.me/yelwxal
YENE MALEDA BEHAVIORAL THERAPY CENTER

3 months, 2 weeks ago

🔶Parent-Child Interaction Therapy for Aggressive Behaviors

የልጅዎን የባህሪ ችግር የወላጅ እና የልጅ መስተጋብር ቴራፒ (PCIT)
🔶በጥሩ ሁኔታ የተመራመረ እና በጣም Pውጤታማ የሆነ የባህሪ ህክምና ነው ለትንንሽ ልጆች (ከ2-8 አመት) ያሉ የባህሪ ችግሮች ለምሳሌ ያለመታዘዝ፣ ተቃውሞ፣ እምቢተኝነት እና ጥቃት።
🔶PCIT ልጁን እንዲሁም በሕክምና ላይ ያሉትን ወላጆች/አሳዳጊዎች ያጠቃልላል። ሕክምናው በሁለት ደረጃዎች ይካሄዳል. 1:)የመጀመሪያው ምዕራፍ በተለያዩ አወንታዊ የማጠናከሪያ ቴክኒኮች የወላጅ እና ልጅ ግንኙነትን ማሻሻል ላይ ያተኩራል።
2:)ሁለተኛው የሕክምና ደረጃ ወላጆች/አሳዳጊዎች የልጃቸውን ታዛዥነት ለማሻሻል እና የባህሪ ችግሮችን በብቃት እና በተከታታይ ለመቆጣጠር ልዩ ችሎታዎችን ያስተምራቸዋል። የተወሰኑ ቴክኒኮችን በመማር, ተንከባካቢዎች ከልጃቸው ጋር የተሻለ ግንኙነት መገንባት ይችላሉ, እና ህጻኑ የተሻሻለ ባህሪን ማሳየት ሊጀምር ይችላል. ባጠቃላይ፣ (PCIT) በቤተሰብ ውስጥ አሉታዊ ባህሪያትን እና ግንኙነቶችን ለመቀነስ በመስራት የቤተሰብን ተለዋዋጭነት ለማሻሻል ይረዳል። የ PCIT ክህሎቶች ተንከባካቢዎችን ወይንም ሞግዚቶችን የሚያበረታቱ እና የሚያረጋግጡ አዳዲስ የመገናኛ መንገዶችን ያስታጥቃቸዋል. በተከታታይ ሲለማመዱ፣ እነዚህ አዳዲስ ክህሎቶች እና ቴክኒኮች በልጁ ላይ የበለጠ በራስ መተማመን እንዲፈጥሩ፣ ንዴትን እና ሃይለኝነትን ይቀንሳሉ።
እንዲሁም በልጁ እና በተንከባካቢው ወይንም በሞግዚት መካከል የተሻሉ ግንኙነቶችን ያዳብራሉ።

🔆 ስለዚህ የትኛውም ወላጅ ለልጁ በቤት ውስጥ መስራት ያለበትን ስልጠናዎችን በመውሰድ ልጆቻችንን እንርዳችሁ!

🌟ይህንን ስልጠና መውሰድ የሚፈልግ
በዚህ ስልክ ይደውሉልን👇👇
☎️ +251905141127
የስነልቦና ባለሙያ
ሜሮን ካሳ

🔆 የትኛዉም ልጅ የፈጣሪ ስጦታ ነዉ!👏👏

3 months, 3 weeks ago

ቸል ማለት /Neglect/

እነዚህ ሕፃናት የወላጅ ቁጥጥር ያልተደረገላቸው
እና በዓለም ላይ ያለውን የሕይወት ውጣውረድ በሙሉ በብቸኝነት እንዲጋፈጡት የተፈረደባቸው ናቸው።
ችላ የተባሉ (የተተዉ) ሕፃናተም እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ; -
ዓለምን የመፍራት /Fear of the world/
ጠንካራ የሆነ ሌሎችን ያለማመን ስሜት/Strong sense of mistrust of others/
ጥብቅ የሆነ ወዳጅነትን ለመመሥረት መቸገር/Difficulty to form intimate relationship/ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ሊጋፈጡ ይችላሉ።

እስኪ ወደ ልጅነታችሁ መለስ ብላችሁ የራሳችሁን አስተዳደግ አስታውሱት : የዛሬ ማንነታችሁ ላይ ምን ያህል ተፅዕኖ እንዳለው አስቡት።

ከአስተዳደጎት  ተከትሎ ለመጣ ማንኛውም የአዕምሮ ችግር እና ስለልጆች አስተዳደግ መወያየት ከፈለጋችሁ በእዚህ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ ፦
➪ የስነልቦና  ባለሙያ ለማግኘት
ይደውሉ 👇👇
☎️ +251905141127
https://t.me/yenemaleda

4 months, 1 week ago
Yene Maleda psychological service and Training …
4 months, 1 week ago
" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም …

" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
(የሉቃስ ወንጌል 2:11)
መልካም በዓል

4 months, 2 weeks ago

Hello families
Peace for all of you

የዛሬ ምርጫችን  ወደ ዕጣችን ያደርሰናል ፣ምርጫችን  ህልማችን  ከሆነ በእጃችን ላይ ትጋት ከያዝን የተጓዝንበት መንገድ ቢያደክምም ዎጋ ወደ ሰጠነው የህይወት ጎዳና ያደርሰናል "Every wait has a worth"
   ስለዚህ ትጋትህን አጥብቀህ ያዛት ምክንያቱም      
   የተጋህለት ህይወት የነገን ዕጣህን ያሳምርልሃል

Will back to this☝️next time😊

Stay connected

@Yenemaleda psychological service

With @Meron kassa

Psychologist &Behavioral therapist

6 months ago

ሰላም ጤና ይስጥልን !!!

ለወላጆች ብቁ የሆኑ የሰለጠኑ በሳይኮሎጂ የተመረቁ ልምድ ያላቸውን  ባለሙያዎችን እያቀረብን ስለሆነ በአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆኑ ዘንድ በአክብሮት እንገልፃለን።

እንግዲህ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የወላጅ ስጋት የሆነው ጥሩ ስነምግባር የሌለው ባለሙያ መቅጠር ነበር፣የእኛ ማዕከል ይህንን ተረድቶ በጥሩ ስነምግባር የታነፁ ፣ጥሩ ልብ ያላቸውን በእዉቀት የተመሠረተ ስልጠና ስሰጥ ቆይቷል ስለዚህም ይህንን በመረዳት ለእናንተ ወላጆች ማቅረባችንን በደስታ እንገልፃለን።

ልጆች የፈጣሪ ስጦታዎች ናቸው።
ሀላፊነታችን በፍቅር እንወጣ!!!!

ለተጨማሪ ፦
➪ የስነልቦና  ባለሙያ ለማግኘት
ይደውሉ 👇👇
☎️ +251905141127
የቴሌግራም ገፅ 👇👇
https://t.me/yelwxal

6 months, 2 weeks ago

አጀስትመንት ዲሶርደር | Adjustment Disorder

🔹ህይወት በውጣ ውረድ የተሞላች ናት:: ኢኮኖሚያችን ተናግቶ ኪሳችን ባዶ ሁኖብን፤ አልያም ከህግ አንጻር ትክክል ያልሆነን ነገር ፈጽመን ፍርድ ቤት የማያስቆም ነገር ገጥሞን፤ የፍቅርና ትዳር ህይወታችን እክል ገጥሞት፤ የትምህርት ውጤታችን አሽቆልቁሎብን ተጨንቀንና ተጠብበን ይሆናል::

🔹ብዙዎቻችን እኒህን ጊዜያት እንደአመጣጣቸው አለሳልሰን አሳልፈናቸው ይሆናል:: ለእንዳንዶች ደሞ እነዚህ የህይወት ሁነቶች ለከባድ የስሜት እና ስነልቡና ቀውስ መንስኤ ሲሆኗቸው ይስተዋላል::

🔸አጀስትመንት ዲሶርደር: በተፈጠሩብን አስደሳችም ሆኑ አስከፊ የጭንቅ ሁነቶች ምክንያት የሚመጣ የአእምሮ ህመም ነው::

🔸እንደ DSM 5 ገለጻ ከሆነ: አንድ ሰው አጀስትመንት ዲሶርደር አለበት ለማለት: ምልክቶቹ ሁነቱ በተከሰተ በ 3 ወራት መከሰት ይኖርባቸዋል: ሁነቱ በተፈታበት 6 ወራት ውስጥ ደሞ ምልክቶቹ መሻር አለባቸው ይላል::

🟣የህመሙ ዋና ዋና ምልክቶች:

ድባቴ ፣የብቸኝነትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት፣ ራስን ዝቅ የማድረግ እና ወቀሳ፣ራስን የመነጠል፣ የመቅበጥበጥ፣
ድንጉጥ የመሆን፣
ግልፍተኝነትን
ከልክ ያለፈ ጭንቀት
አካላዊ ምልክቶች (የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ እንቅልፍ የማጣት ህመሞች እና የመሳሰሉ)
ራስን የማጥፋት ሃሳብ
- ለአደንዛዥ እጽ መጠቀም መጀመር (ምናልባትም ነገሮችን ለመቋቋም ሲባል የሚጀመር)...
የባህርይ ለውጥ

አንዳንዶቹ ለህመሙ ተጋላጭነታቸው ለምን ይጨምራል

አንድ ሰው አስጨናቂ ሁነት ሲገጥመው ነገሮቹን ለማሰናሰል የተለያዩ ሂደቶችን ያልፋል::

1️⃣- ሁነቱ የተመለከቱ መረጃዎች ለአእምሯችን ስለሚደርሱ: የሁነቱን መከሰት እናገናዝባለን:
2️⃣- ሁነቱ ለመርሳት በመሞከር እና በትውስታ መሃል ሄድ መጣ እያለ ይቆያል:: ከዚህ ጋርም ተያይዞ ስለ አስተሳሰባችን፣ ስነባህርይ፣ ስነማህበራዊ ነገሮችን በተመለከተ አእምሯችን መረጃዎችን ያጠናቅራል::

3️⃣- ሁነቱን በተመለከተ የተጠናከሩ መረጃዎችን አእምሯችን በ አስተሳሰብ ማዕቀፋችን በማካተት፣ ለመላመድ መሞከር እና ትርጉም ለመስጠት ይሞክራል::

ይህ ስራ በተገቢው አኳኋን ካልተካሄደ: ለስሜት መቃወስ ምልክቶች መጋለጥ ይከተላል::

🔹 ሰዎች ስለ አስጨናቂ ሁነቶች ጋር ተያያዥ ስሜቶች ልምዱ ከሌላቸው፤ ለሚያጋጥማቸው ክስተት በቀላሉ ከመላመድና ወደቀደመ ህይወታቸው ቶሎ ከመመለስ ይልቅ: ስለሁነቱ ራስን መውቀስ ይቀናቸዋል፣ ለሌሎች አዋይቶ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ብቻ ለመጋፈጥ ይጥራሉ፡፡ ይህም ለድብርት አልያም ጭንቀት እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል::

🔹ከልክ በላይ በድሎት የኖሩ እና ሁሉንም ነገር በሰዎች እርዳታ ማለፍ የለመዱ ሰዎች: ክስተቶችን በራሳቸው ለመጋፈጥ ዝግጁነት ስለሚጎላቸው፣ በሚያጋጥማቸው ውጣ ውረድ ስሜታቸው ሲጎዳ እና ለስነ ልቡና ቀውስ ሊጋለጡ ይችላሉ::

🔹 አንዳንዶቹ ደሞ ፈተና ያጠነክራቸዋል፡፡ Resilience ያዳብራሉ:፡

🔵ህክምናው:-

የህክምናው አበይት አላማዎች:

ምልክቶችን እና ተጓዳኝ ህመሞችን (እንደ እጽ ተጠቃሚነት ያሉ) ማከም
የተፈጠረው አስጨናቂ ሁነትን መፍታት
ወደ ቀደመ አቋማቸው መመለስ

🔷ስነ ልቡናዊ ህክምና:

- Supportive psychotherapy (ታካሚዎች ስሜታቸውን እንዲገልፁ ማድረግ፡ መመካከር፡ የመፍትሄ ሃሳቦችን መዘየድ..)

- Cognitive behavioral therapy (አረዳዳችንን እና የባህርይ ማፈንገጦችን ማቃናት)

- Interpersonal therapy- የተፈጠሩ ክስተቶችን(ሃዘን/grief፡ የሚና ለውጦች/role transition፡ ብቸኝነት/interpersonal deficit፤ መቃቃር/dispute) ለይቶ መፍትሄ ማበጀት

- Meditation training (ጽሞናን እና አርምሞን መሰረት ያደረገ) እና የመሳሰሉ…

🔷የመድሃኒት ህክምና

- እንደ ህመሙ ምልክቶች ደረጃ: መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ::
- እንቅልፍ ማጣትን፣ የጭንቀትና የድባቴ ምልክቶችን ለማከም መድሃኒት ሊሰጥ ይችላል::

🟢ማጠቃለያ-

በፈተና ውስጥ እያለፋ ላሉ ሰዎች ከንፈር ከመምጠጥ የዘለለ እዝነት ማሳየት: አለንላችሁ በማለት ከጎናቸው መቆም እና ያጋጠማቸውን ችግር በተመለከተ በጋራ መፍትሄ ማፈላለጉ እድግ ወሳኝ ሚና አለው::

ቸር ይግጠመን!

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው: የአዕምሮ ህክምና ሬዚደንት

6 months, 2 weeks ago

ስንላመድ

ከዚህ በፊት በህይወቴ ጠዋት እንደመነሳት የሚያስጨንቀኝ ነገር አልነበረም፡፡ ማታ ወደ መኝታዬ ስሄድ በጣም በርዶኝ ነው ወይም ድቅቅ ብሎ የደከመ አካሌን ለማሳረፍ ይሆናል፡፡ ልክ አልጋዬ ላይ ስወድቅ አካሌ ውስጥ የሚያልፈው እረፍት እጅግ ይናፍቀኛል፡፡ ስተኛ ድካሜ አልፎ ነገ በጊዜ እንደምነሳ አስባለሁ፡፡ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ተነስቼ የአካል እንቅስቃሴ እሰራለሁ፡፡ ቁርስ አበስላለሁ፡፡ ከዚያን በኃላ ንቁ ሆኜ …... እያልኩ አስባለሁ፡፡ ሲነጋ ግን ነገሩ ሁሉ እንዳሰብኩት ሆኖ አይገኝም፡፡ እረፍት አግኝቼ በጥሩ ሁኔታ ለመንቃት ብዬ የጀመርኩት እንቅልፍ ዱካክ ይሆንብኛል፡፡ እንኳን ከብርድ ልብስ መውጣት ይቅርና ባለሁበት አይኔን መግለጥ እንደ ሰማይ ይርቅብኛል፡፡ የተኛሁበት አልጋ እንደ እናት ማህጸን ይሞቀኛል፡፡ ብውልበት የሚከፋኝ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ገላዬ ሙቀቱን በሚገባ ተለማምዶታል፡፡
እንደ እናት ማህጸን ስል’ኮ የምሬን ነው፡፡ ህጻን ሲወለድ አንድ ያስተዋልኩት ነገር አለ፡፡ ልክ ከእናቱ ማህጸን ወጥቶ ይህችን ዓለም ሲቀላቀል ለቅሶ ነው የሚያሰማው፡፡ ለእርሱ ዓለም ማለት የእናቱ ማህጸን ነው፡፡ የእሱ ገላ የለመደውን ሙቀት ከእናቱ ማህጸን ትቶት ወጥቷል፡፡ ለ9 ወራት ከሚያውቀው ኑሮው ድንገት ተፈነገለ፡፡ እናም ህይወትን በእንባ ይጀምራታል፡፡ ነገር ግን ቀስ እያለ ከዚህኛው ዓለም ጋር መላመድ ይጀምራል፡፡ ህይወት የምታስጠላ ሆና ታይቶት እንኳን ከመሞት መኖርን አጥብቆ ይሻታል፡፡ ምክንያቱም ያኔ የፈራትን ህይወት ተላምዷታልና፡፡
ህይወትን ሳስተውላት በአብዛኛው የዚህ ህግ እስረኛ ነች፡፡ አንድን ነገር በመፈለግ የሆነ ነገር ውስጥ እንገባለን፡፡ ከገባን በኋላ ግን ከገባንበት ነገር መውጣት ስለሚያስቸግረን የነገሩ ባርያ ወይም ሱሰኛ ሆነን እንገኛለን፡፡ ብዙ ልምዶቻችን ወደ ሱስ ይቀየሩብናል፡፡ ማንበብ ሊያስጠላን፤ ፊልም ካላየን የሚደብረን፤ ሙዚቃ ካልሰማን የሚከፋን፤ ቡና ካልጠጣን እንቅልፍ የሚሸነፍ የማይመስለን፤ ሲጋራ ካላጨስን፣ ጫት ካልቃምን፣ መጠጥ ካልጠጣን ኑሮን ወደ መቃብር የምንልካት የሚመስለን ብዙዎች ነን፡፡ ሱስ እንደ ብዛቱ እና እንደ ዓይነቱ ይቀመጣልና፡፡
ማንኛውም ሱስ ህይወታችን ላይ አደጋዎችን የመፍጠር አቅም አላቸው፡፡  ቢሆንም አደጋዎቹን ፊት ለፊታችን በገሀድ  እየታዩን በሱስ የታሰሩ ሰዎችን በብዛት እንመለከታለን፡፡ ሁላችንንም የሚያስማማን ነገር ግን፤ ማንኛውም የሱስ እስረኛ ከመሆኑ በፊት ሱስ ውስጥ ሲገባ ጉዳቱ ታይቶት አይደለም፡፡ ይልቅስ ከሱስ የሚገኝ ደስታን እና ጥቅምን በማሰብ እንጂ፡፡ ሲጋራ አጫሹ ሲጋራውን ሲጀምር የሚያጨሰው ንቅት፤ ድምቅ ብሎ ስራውን ለመስራት ነው፡፡ ውሎ እያደረ ቀኖቹን ሊያሳምር ሲጋራውን ይቀጥላል፡፡ ከርሞ ከራርሞ ግን እጁ የሚቅበጠበጠው፣ አፉ የሚያዛጋው ከሲጋራ ደስታን ስለሚያገኝ ሳይሆን ካላጨሰ ድብርት ስለሚይዘው፤ ገላው ከለመደበት ስርዓት መውጣት በረሃ ላይ ለብቻ እንደመገኘት ስለሚሰማው ነው፡፡ ልክ ገላውን እንደ ሚታጠብ ህጻን ይሆናል፡፡ ገላውን መታጠብ ሲጀምር ጥቂት ውሃ ቀስ በቀስ እየተደረገለትም ይፈራል፡፡ ቆይቶ ግን ውሃውን ሲላመደው የሚፈራው ከውሀው መውጣትን ይሆናል፡፡ ሲገባ የፈራውን ህይወት ለመውጣት ያስፈረዋል፡፡ ምክንያቱም ገላው ከለመደው ስርዓት ውጪ ሲሆን እንግዳ ነገር ስለሚያስፈራው ነው፡፡ አእምሮአቸን ከሚገጥመን አዲስ ነገር ጋር አካላችንን እንድናስማማ ይረዳናል፡፡
ሜሮን ካሳ
ይቀጥላል ......

8 months ago
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
🌼🌼🌼ልዩ መርሐግብር🌼🌼🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ከ ሜሮን ካሳ ጋር

ዛሬ ከምሽቱ  3:00 ላይ በቀጥታ ስርጭት  በሴጅ ኢትዮጵያ ቴሌግራም ቻናል ላይ እንገናኝ ።

ርዕስ 👉  አሳታፊ

ቀን 👉 ዛሬ  መስከረም  05/2016 ዓ.ም

ሰዓት 👉 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3:00 ላይ

የምትሳተፉባቸው እድሎች ተመቻችተዋል
ሊንኩን ሼር በማድረግ ይቀላቀሉን

#ሴጅ ኢትዮጵያ
#የእናቶች ወግ በልጆች አስተዳደግና አመጋገብ
#እፍታ ኢንተርቴመንት
# እናት ለእናት

ይህንን መርሃግብር በሴጅ ኢትዮጵያ ቴሌግራም  ገፅ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል ።

👉Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100089830925445...
👉Instagram https://www.instagram.com/sageethiopia/
👉 Telegram https://t.me/sage_ethiopia
👉YouTube https://youtu.be/MKOQGiURYnU
#ከዚያስ #sage_ethiopia

We recommend to visit

[ 📍Premium Content Channel 🎯]
Join ✅ Now This backup channel 👇
@verified_channels

Last updated 4 месяца, 2 недели назад

Malu Trevejo 🍓🍒18+ 💦

Last updated 3 недели, 2 дня назад

@schr0dinger - admin

Last updated 2 месяца, 2 недели назад