HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን ሕይወትና ምክሮች፡ለሕዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትንና ትምህርቶችን የሚሰራጭበት የቴሌ ግራም ቻናል ነው

Description
እግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ስለእኛ ጸልዩ ( ፩ ተሰሎ ፭÷ ፳፭ ) ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ትክክለኛ አድራሻዎቼ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
ቴሌግራም ? -https://t.me/hamernoah
My -email ☞[email protected]
መካነ ድር፡https:hamernoah.wordpress.comሁላችሁም ተሳታፊ ሁኑ
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 2 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

1 Monat, 3 Wochen her
" የተሰጣችሁን አደራ በትጋት በመወጣት ምእመናንንና …

https://hamernoah.wordpress.com/2024/12/07/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b0%e1%8c%a3%e1%89%bd%e1%88%81%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%8b%b0%e1%88%ab-%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8b%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%8b%88%e1%8c%a3%e1%89%b5-%e1%88%9d%e1%8a%a5/
" የተሰጣችሁን አደራ በትጋት በመወጣት ምእመናንንና እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ልትታደጉ ይገባል"ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

1 Monat, 3 Wochen her

ቅዱሳን ሐዋርያት በዲድስቅልያ በ ፳፯ አንቀጽ "#ሰማዕታት በእናንተ ዘንድ ይክበሩ፣አንድም ልታከብሯቸው ይገባል፣እናንተ የምእመናን ወገኖች ደክማችሁ ባገኛችሁት ገንዘብ እጃቸውን በሰንሰለት እግራቸውን በግር ብረት የታሠሩ ሰማዕታትን አገልግሏቸው "ብለዋል።( መንፈሳዊ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፳) በኒቅያ የተሰበሰቡ ሠለስቱ ምእት "የሰማዕታትን ዓፅም በቤተ ክርስቲያን በገዳም ያኑሩ፣ከመ ይኩኑ እመካነ ሥጋቲሆሙ ፈውስ ወበቊዔት ዐቢይ፣ ለድዉያን ወለሕሙማን ፣ሥጋቸው ከተቀበረበት መቃበር ለታመሙ ሰዎች ረብሕ ጥቅም ፣ድኅነት ለሚሹ ሰዎች ይገኝበት ዘንድ "ብለዋል።
መጽሐፈ ቅዳሴያችንም "ተዘከር እግዚኦ አበዊነ ወአኃዊነ ወአኃቲነ እለ ኖሙ ወአዕረፉ በርትዕት ሃይማኖት፣ በቀናች ሃይማኖት የሞቱትን ፣ያረፉትን አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ፣እኅቶቻችንም አስብ፣ በእንተ ቅዱሳን ሰማዕታት ናስተበቊዕ ከመ እግዚአብሔር የሀበነ ንፈጽም ኪያሃ ግዕዘ ፣እግዚአብሔር የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን "ይላል(#ሥርዓተ ቅዳሴ )
ቤተ ክርስቲያናችን ማዳከም ዓላማችንን ያሳካልና ብለው ያሰቡ ወገኖች ክርስቲያኖችን እንደ ሻማ አቅልጠዋቸዋል፣ እንደ ገል ቀጥቅጠዋቸዋል በቅድስት ቤተ ቤተ ክርስቲያን ከግራኝ አህመድ ዘመን ያልተናነሰ ጥፋት እየተፈጸመባት ትገኛለች ፣ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን በሰማዕትነት አከበረችበት እንጂ አልጠፋችበትም፣ መቃበሯንም አልቆፈረችበትም።
እነዚህ ሰማዕታት የእሳት መሰላል ሰርቶ ውኃ ሁኖ የሚወጡበት ፣የቢላዋ ርካብ አስቀምጦ ሞረድ ሁኖ የሚወርዱበት ሕይወት ነው።
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዐገሡ ሞተ መሪር በእንተ መንግሥተ ሰማያት ፣ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ። ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ። ስለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ ። (#ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ) በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር !
ተጨማሪ የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች
ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ ። መረጃውን መጠቀም ይቻላል፥ #ምንጭ ግን ይጥቀሱ
E-mail [email protected]
TikTok - https://www.tiktok.com/@temesgenzegeye175
telegeram https://t.me/+U-n_2um5SI7skWIk
Instagram temesgen.zegeye4
YouTube - www.youtube.com/@hamernoah208
Website -hamernoah.wordpress.com
Facebook https://www.facebook.com/temesgen.zegeye.7

1 Monat, 3 Wochen her

✍️ቅዱስ መርቆሬዎስ በሰማዕተነት ዐረፈ ✍️
༺ ༻
በዓላውያን ነገሥታት ፊት በመቆም ፈጣሪያችን አንክድም ለጣዓት አንሰግድም በማለት ለአምላካቸውን ያላቸውን ፍቅርና ታማኝነት ያረጋገጡ ቅዱሳን ሰማዕታት በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ክብር አላቸው፡፡ከእነዚህም ሰማዕታት መካካል አንዱ ቅዱስ #መርቆሬዎ ነው፡፡ ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡
አባቱ አሮስ አያቱ ደግሞ ሲድሮስ ይባሉ ነበር፡፡የትውልድ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ አያቱና አባቱ ተዳደሪያቸው አውሬ ማደን ነበር፡፡
አራዊትን አጥምደው ለነገሥታቱና ለሹማምንቱ ያቀርባሉ ለዚህም አገልግሎታቸው ዋጋቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ነበር አሮስና ሲድሮስ የተለመደውን ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ በአደጋ ጣዮች የተከበቡት ሲድሮስም ሞተ፡፡አሮን ግን ሕይወቱን ከሞት አፋፍ አመለጠች፡፡ በአስገራሚ ተኣምራት ከሞት ያመለጠው አሮን ከጥቂት ቀናት በኋላ በኤጲስ ቆጶስ እጅ ከባለቤቱና ከልጁ ጋር በአንድነት ተጠመቁ፡፡ የክርስትና ስማቸውም አሮስ (ኖኀ) ባለቤቱ (ታቦት) ልጁ ፒሉፓዴር (መርቆሬዎስ) ተባሉ፡፡
ፒሉፓዴር የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ታማኝ ሐቀኛ ማለት ነው፡፡ዳኪዎስ ቄሣር በሮም ነግሦ ሳለ ተቀዋሚ ክፍሎች ጦርነት አስነሱ ዳኪዎስንም ኖኀ ወደ ጦርነት እንደሄድ አዘዘው ኖኀም በዳኬዎስ ትእዛዝ ሰራዊቱን አስከትሎ ወደ ጦር ግንባር ሄደ በጦርነቱም ኖኀ ተማረከ፡፡ሰላዮችም ኖኀን ወደ ንጉሡ አቀረቡት ንጉሡም ኖኀን ለአራዊት እንዲሰጡት አዘዘ ኖኀም ወደ አምለኩ ጸለየ ለሁለተኛ ጊዜያት በሚያስገርም ተኣምራት ነፍሱን ካንዣበባት አደጋ ዳነች፡፡
ዳኬዎስ ቄሣር ግን የኖኀን መማረክ እንደሰማ የኖኀን ባለቤት ያገባት ዘንድ መልእክት ላከበት መልእክተኛውም ባለቤቷን መሞቱንና ዳኬዎስ ቄሣር እሷን ለማግባት ማሰቡን ገለጸላት፡፡
የኖኀ ባለቤትም ይህንን ስትሰማ አዘነች፡፡ከቄሣሩም ለማምለጥ ለመልእክተኛው ጥቂት ወርቅ እስጥሃለሁ ለነገር ግን ወደ ንጉሡ አታቅርብኝ በማለት ተማጸነችው የቄሣር መልእክትም እየመራት ከልጇ ጋር ወደ ሌላ ሀገር ተሰደደች፡፡የንጉሡ መልእክትም ለንጉሡ ኖኀ ባለቤት መጥፋቷን ገለጸለት ፡፡ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ኖኀ ወደ ሀገሩ በሰላም ተመለሰ፡፡ዳኪዎስም የኖኀን በሰላም መመለስ ሲሰማ ፈራ ፡፡ ምክንያቱም ባለቤቱን ለማግባት ማሰቡ በሰዎች ዘንድ ይታወቅ ስለነበር ነው፡፡
ቅዱስ መርቆሬዎስ የተወለደው ጣዓት ከሚያም አረማውያን ቤተሰቦች ፩፻፸፮ ዓ.ም ነው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎ ከአደገ በኋላ አምኖ ተጠመቀ ሲጠመቅም መርቆሬዎስ ተባለ፡ ፡ መርቆሬዎስ ማለት የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ (ገብረ ኢየሱስ) ማለት ነው፡፡ቅዱስ መርቆሬዎስ በቄሣርያ እሰር ቤት መከራውንና ስቃዩን እየተቀበለ በእስር ቤት ውስጥ የሚገኙትን እስረኞች ወንጌልን እያስተማረ ከአረማዊነት ወደ ክርስትና እምነት እየለወጠ ስለአስቸገራቸው ኀዳር ቀን ፳፭ ፫፻፲ ዓ.ም በሰይፍ ተከልሎ በሰማዕትነት ዐርፈ፡፡
#የቅዱስ መርቆሬዎስ መከራ ሲነሣ ይህንን ያህል የተሰቃየ ለምን ይሆን
1.#ስለ መንግሥተ #ሰማዕት “እንደ ዕብድ ሰው እላለሁ እኔ እበልጣለሁ በድካም አብዝቼ በመታሰር አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ አይሁድ አንድ ሲጎድል ዐርባ ግርፋት ዐምስት ጊዜ ገረፉኝ፤ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ መርከቤም ሦስት ጊዜ ተሰበረ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ ፤ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁበዴዎች ፍርሃት በወንዝ ፍርሃት በወንበዴዎች ፍርሃት በወገኔ በኩልፍርሃት በአሕዛብ በኩል ፍርሃት በከተማ ፍርሃት በምድረ በዳ ፍራት በባሕር ፍርሃት በውሸተኞች ወንድሞች ፍርሃት ነበረብኝ፤በድካም በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት በራብምና በጥም ብዙ ጊዘም በመጦም በብርድና በራቁትነት ነበረሁ፡የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው(፪ኛቆሮ. ፲፩፤፳፫-፳፰)
“ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል”(የሐዋ.፲፬፤፳፪)
2.#ሃይማኖትን ለመመስከር “ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ”ይላል(ማቴ ፲፤፴፪)
3.#አርአያ መሆን ፤ቅዱስ ኤፍሬም በሐሙስ ውዳሴ ማርያም ድርሰቱ “መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ወከዓው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዐገሡ ሞተ መሪር በእንተ መንግሥተ ሰማያት
4.እውነትን በሐሰት መለወጥ ስላልፈገ “የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል”(፪ኛ ቆር.፭፥፲፬)
የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት #በስማዳ ወረዳ #በፀዶዬ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በልዩ ሁኔታ ይከበራል ።
ሰማዕታት የሚባሉት እግዚአብሔርን ካዱ ለጣዖት ስገዱ ሲባሉ፤ እግዚአብሔርን አንክድም ለጣዖት አንሰግድም ብለው ጀርባቸውን ለጅራፍ፤ አንገታቸውን ለሰይፍ፤ ሰውነታታቸውን ለእሳት የሰጡ እግዚአብሔርን ላለመካድ ለአራዊት ተሰጥተው የተበሉ ናቸው እነዚህን ቅዱሳን ሰማዕታት የእግዚአብሔር ምስክሮች ብለን እንጠራቸዋለን።" ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው"(መዝ ፩፻፲፱፥፩፻፳፱)
"እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።" (ዕብ ፲፩፥፴፫-፴፰)
ከቅዱሳን ሰማዕታት ወገን የሆነ ከሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጠሎ የመጣ ታላቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው። ጸሎት ልመናው ለሁላችንም ይድረሰን...ሀገርን ሰለ ቅዱሳን የሚምር የሚታደግ አምላክ ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ብሎ ይጠብቅልን..."አብርሃምም ቀረበ አለም። በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን?፤ አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?፤ "#እግዚአብሔርም። በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ #ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ #እነርሱ #እምራለሁ አለ።"
ሰማዕትነት ማለት ስለ ቀናው ሃይማኖት መመስከር ስለ ክርስቶስ ፍጹም አምላክነት ራስን ለሞትና ለመከራ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው።ሰማዕትነት ለተሳለ ሰይፍ አንገትን ቀና አድርጎ በመስጠት ስለ ሃይማኖት በጅራፍ መገረፍ ወይም በገመድ መታሠርና በእሳት መቃጠል የሚወሰን አይደለም ።
የአክራሪዎችን ስድብ ፣የዓለማውያንንም ግልምጫን በትዕግሥት ማሳለፍ ከፍተኛ የመከራ መሥዋዕትነት ስለሆነ ሰማያዊውን ክብር የሚሰጥ ነው።የተጋድሎ መንገዱ ብዙ ነው። ለሰማዕታቱ መመሪያ የኾናቸው " ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ" የሚለው የጌታችን ቃል ነው(ማቴ10÷28)

1 Monat, 4 Wochen her
HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን …
1 Monat, 4 Wochen her
HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን …
1 Monat, 4 Wochen her

✍️ ሀገረ ስብከቱ አርቶዶክሳውያን ወጣቶች ላይ ችግር ፈች የሆኑ ሥልጠናዎችን በመሰጠት ላይ ነው፡፡✍️

እያንዳንዱ ዘመን የራሱ የሆነ የሃይማኖት ዐርበኛ አፍርቶ የሚያልፍ መሆኑን ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ የምንረዳው ነው፡፡ የየዘመኑም ተጋድሎ የተለያየ ነው፡፡ በዘመናችን ወጣቶችን ሰብሰቦ ነገረ ሃይማኖት ማስተማር ራሱ የዘመኑ ከባድ ተጋድሎ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን አለቀላተ ስትባል ተስፋዋ እየለመለመ ፣ጠፋች ስትባል ተራራ ላይ እንዳለች መብራት ለዓለም እየተገለጠች ፣ተጣለች ስትባል እየተነሣች እንደሆነ በጉራጌ ሀ/ስብከት በነበረን ታሪካዊ ሥልጠና ማየት ችያለሁ፡፡ በሃይማኖትና በምግባር የጸኑ ወጣቶችን እምድብር ከተማ መኖራቸውን በአንድም በሌላ መንገድ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ሁል ጊዜም ጊዜያዊ ችግሮችን በማስወገድ ላይ ብቻ መወሰን ዘላቂ ሥራ ለመሥራት አያመችም ። የጉራጌ ሀገረ ስብከት በዕቅድና በጥበብ መመራቱ ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ መናበብ እንዲቻል ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡
በቸሃ ወረዳ ቤተ ክሀነት አርአያነት ያለው ተግባር እንደ መጽሐፍ ይነበባል፡፡ በወጣቶቸ የምትገለገልና ወጣቶች ጽኑ ሃይማኖታዊ መሠረት የምታስዝ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ወቅታዊ ማዕበል ሁሉ ገፍቶ አይጥላትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልጆ?ቿን አቅፋና ሰብስባ እነርሱም ለእናት ቤተ ክርስቲያናቸው በመከራና በቸግር ጊዜ ደራሽ ይሆኑላታል፡፡
መሠረቷና ጉልላቷ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት “በጎቼን ጠብቅ ፡ጠቦቶቼን አሠማራ ፡ግልገሎቼን ጠብቅ”(ዮሐ.21፥25) በማለት አደራ የተሰጣት በመሆኑ ለበጎች፡ለጠቦቶችና ለግለገሎች የሚመጥን ነገር አዘጋጅታ መሠረተ እምነቷን፣ሥርዐትና ትውፊቷን ለሚቀጥለው ትውልድ እንደ ቸሃ ወረዳ ቤተ ክህነት እምደብር ከተማ ወጣቶች ቀጣይነት ባለው መነግድ መሥራት ከተቻለ ለሚቀጥለው ትውልድ ታሪክና ሃይማኖት ማሰረከብ እንችላላን፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ድርሳናት ተዘግቦ እንደምናገኘው በእግዚአብሔር ውስጥ ጉልሀ ድርሻ ወይም በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ሲፈጽሙ የነበሩ ወጣቶች ነበሩ፡፡
በዘመናችንም በጉራጌ ሀገረ ሰብከት በቸሃ ወረዳ ቤተ ክህነት እምድበር ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት ከተማ ያሉ ከ621 በላይ ወጣቶች የከተማው ከንቲባ ጨምሮ ” ኦርቶዶክሳዊ ወጣትና ቅድስት ቤተ ከርስቲያን “ በሚል ርእስ የተዘጋጀውን ሥልጠና በልዩ ትኩረት ሲከታታሉ ነበር፡፡
#ቤተ ክህነትና #ቤተ መንግሥት እንደ አንድ ልብ መካሪና እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ወጣቶችን ከክፉ ሥራና ከሱሰኝነት ወጥመድ ለማውጣት እያደረጉ ያሉት አንድነትና መናበብ ለሌሎችም አህጉረ ስብከት በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ብፁዕ አቡነ #መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራች እና የበላይ ኃላፊ፤የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢ በሥልጠናው ዕለት በመገኘት "#ሌሎች በሠሩት እየኖርን ነው እኛም በተሰጠን ዘመን ታሪካዊና ዘመን ተሻጋሪ ሥራ እንሥራ " በማለት ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ መክብብ ፲፪፥፩ የተናገረውን ኃይለ ቃል መነሻ በማድረግ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም “#ዣንጥላ መዘቅዘቅ ማቆም አለበት”ብለዋል፡ በተጨማሪም ብጹዕ ሊቀጳጳሱ ከተማዋ “እየተማሩ የሚያስተምሩ #ከንቲባና የወረዳ #አስተዳዳር አግኝታለች በዚህ እግዚአብሔር ሊመሰገን ይገባዋል ”ብለዋል፡፡የዚህን ዘመንን ትውልድ ለመታደግ ጊዜው የሚጠይቀውን ተግባር ዘመኑን እየዋጁ መፈጸም ይገባናል።፡
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወጣቶች ላይ በትኩረት በመሥራትዎ ስለነገዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚጨነቅ ትውልድ እያፈሩ ስለሆነ በእውነትም ደስ ሊለዎት ይገባል፡፡ቡራኬዎት ትድረሰኝ!፡፡ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ያለ ወጣቶች መመልከት እንደማይቻል ያሳዩበት አገላላጽ ወጣቶች በዐውደ ምሕረት እንዲቆዩ የሚያደርግ ተስፋ ሰጭም ነው፡፡
የኦርቶዶክሳውያን ሁለተኛው ዙር የሥልጠናው መርሐ ግብር ተሳታፊዎች ወ=352 እና ሴት =269 በአጠቃላይ ከ621 በላይ ኦርቶዶክሳውያን የተሳተፉበት የተረጋጋ ፣ ሥልጠና ነበር፡፡
ብጹዕነታቸው ይኽ ቀን ከሌሎቹ ቀናት ተለየ ቀን ነው። ምክንያቱም በዚህ መንገድ ወጣቶች ተሰብስበው ከመማር በላይ ምን የሚያስደስት ነገር የለም ”ብለዋል፡፡
በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ፣የወረዳ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች የተገኙበት በአርአያነት የሚጠቀስ ርቀው የነበሩትን ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር ያገናኘ ጉባኤ ነበር፡፡

መ/ር #ተመስገን ዘገዬ
ኅዳር ፳፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

ጉራጌ ሀ/ስብከት (#እምድብር ከተማ )

ተጨማሪ የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች
ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ ።መረጃውን መጠቀም ይቻላል፥ #ምንጭ ግን ይጥቀሱ
E-mail [email protected]
TikTok - https://www.tiktok.com/@temesgenzegeye175
telegeram https://t.me/+U-n_2um5SI7skWIk
Instagram temesgen.zegeye4
YouTube - www.youtube.com/@hamernoah208
Website -hamernoah.wordpress.com
Facebook https://www.facebook.com/temesgen.zegeye.7

2 Monate her
HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን …
2 Monate her
HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን …
2 Monate her
HamerNoah: መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ የአበው ቅዱሳን …
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 2 days ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago