Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 6 days, 8 hours ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 3 weeks ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 2 months ago
አሸዋና አለት
(እስክንድር ከበደ)
….ይህ ታሪክ ስለ ሁለት በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነው፡፡ጓደኛሞቹ ከልጅነት ጀምሮ አብረው ያደጉ ናቸው:: ጓደኛሞች ሀገራቸውን ጥለው ወደ እሩቅ ሀገር እየተሰደዱ ነበር :: በተለያዩ መጓጓዣዎች ጫካና ተራራውን አንተ ትብስ አንተ ትብስ ብለው ድንበር አቋርጠው ብዙ ተጓዙ ::
ሁለቱ ጓደኛሞች በበረሃ ይጓዙ ነበር፡፡ ከተወሰነ ጉዞ በኃላ በሆነ ባልሆነው ይከራከሩና ይጨቃጨቁ ጀመር፡፡አንደኛው ሌላውን ጓደኛውን በጥፊ መታው፡፡በጥፊ የተመታው በጣም ደነገጠ :: ጓደኛው ቢጎዳውም ምንም ሳይናገር አሸዋ ላይ እንዲህ የሚል ጻፈ
"ዛሬ የልብ ጓደኛዬ በጥፊ መታኝ…"
በጥፊ የተማታው ጓደኛ በድርጊቱ ቢጸጸትም ፤ የጎዳውን ጓደኛውን ይቅርታ አልጠየቀም ነበር :: ሁለቱም በዛ ተኮራረፉ ::
ሁለቱ ጓደኛሞች መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ብዙ ከተጓዙ በኃላ ለምለም እና ውሃ ያለበት ረግረግማ አካባቢ ደረሱ፡፡ ገላቸውን በመታጠብ እና ለጥቂት ጊዜ ዛፍ ጥላ ስር አርፈው ለመሄድ ወሰኑ፡፡
በጥፊ የተመታው ጓደኛ በድንገት በረግረጉ መሬት ሊሰምጥ ሆነ ፡፡ በጭቃው ተውጦ ሰምጦ እንዳይገባ ይፍጨረጨር ጀመር :: ይሄኔ ጓደኛው በጥፊ የመታው ደንግጦ ጓደኛውን ለማዳን ብዙ ጥረት አደረገ ::
ያ- ጓደኛውን በጥፊ የመታው ጓደኛ ህይወቱን አዳጋ ላይ ጥሎ በመጨረሻ ጓደኛውን ከሞት አተረፈው ፡፡
ቀደም ሲል ጓደኛው በጥፊ ሲመታው በአሸዋው ላይ ""ዛሬ የልብ ጓደኛዬ በጥፊ መታኝ…" ብሎ ጽፎ ነበር:: የጎዳው ጓደኛው መልሶ ከሞት ሲያድነው በአለት ወይም በድንጋይ ላይ የተሰማውን ስሜት ጻፈ ::
"ዛሬ የልብ ጓደኛዬ ህይወቴን አዳነ" ብሎ ዲንጋይ ላይ ጻፈ
ጓደኛውን በጥፊ የመታው በጣም ተገረመ፡፡
"….በጎዳሁ ወቅት ድርጊቴን በአሸዋ ላይ ጻፍከው ፤አሁን ደግሞ ከሞት ሳድንህ ድርጊቱን በድንጋይ (አለት) ላይ ጻፍክ ፡፡ለምን እንዲህ አደረክ?" ብሎ ተገርሞ ጠየቀው፡፡
"አንድ ሰው ቢጎዳን ድርጊቱን አሸዋ ላይ ብንጽፈው የይቅርታ ንፋስ በቀላሉ ሊያጠፋው ይችላል፡፡ነገር ግን አንድ ሰው መልካም ነገር ሲያደርግልን የትኛውም ንፋስ ጠርጎ እንዳይወስደው በድንጋይ ላይ መጻፍን መልመድ አለብን… ጉዳትህ በአሸዋ ላይ ያገኘከውን ….መልካም ነገሮች ደግሞ አለት ላይ መጻፍ ተማር " በማለት ጓደኛው መለሰ፡፡"መጥፎ ድርጊት በልባችን አጠንክረን እንዳንይዘው ፤መልካም ያደረገልንን ግን በማይጠፋ ማህደር መመዝገቡ እጅግ ይጠቅማል አለው::
https://t.me/ethioyibe
Telegram
ልዩ ልዩ ሀገረኛ እይታዎች😂😳🤔😒😏🤷♂😡😋
አዳድስ ስነልቦናዊ ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እይታዎች፣ሀሳቦች እንድሁም እውነታዊ ፍልስፍናዎችን እንጋራለን እናጋራለን። ሰላም ለሀገራችን Join and share @ethioyibe
መዋቲነት- ሃይዲገር
በምድር ላይ ዘላለም እንዲኖር የተፈረደበት አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህን ፍርጃ ሲሰማ ሳቀ... ዘላለም መኖርስ እንዴት ቅጣት ይሆናል? አራት መቶ አመታት አለፉ ... አንድ ማለዳ ላይ ከአልጋው ሳይወርድ ማስብ ጀመረ... ዘመናትን በምድር ላይ ያሳለፈ... የአለማችን ምርጥ ሰዓሊ፣ ምርጥ ሙዚቀኛ ሆኗል፡፡ ብዙ ጀግኖች በጦር ሜዳ ገድሏል... የሚወዳቸው የቅርብ ወዳጆቹም እድሜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል። ሁሉንም ምግብ ቀምሷል፤ ያልረገጠው የምድር ክፍል የለም። አሁን ላይ ግን ለምን ከአልጋው መውረድ እንዳለበት ግልጽ አልሆነለትም። ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። ለእርሱ ምድር እስር ቤቱ ሆናለች፡፡ ቀናቶቹ በሙሉ ትርጉም አልባ ናቸው፡፡
ጀርመናዊው የሃያኛው ክፍለ ዘመን ፈላስፋ ማርቲን ሃይድገር ይህ ሰው “ሰውነትን” አጥቷል ይልናል። በቀን ውሎህ ውስጥ የምትፈጽመው ነገር አለና ጠዋት ላይ ከአልጋህ በጥድፊያ ተወርዳለህ፤ በጥድፊያ ውስጥ ሆነህ ሁሉ ነገርህን ትከውናለህ። ከእያንዳንዱ ድርጊቶችህ ጀርባ ጊዜ ባላንጣህ ነው።
በተቻለህ አቅምም ጊዜን ለመቅደም ትሮጣለህ፡፡ ሆኖም ጊዜ 'ማያሳስብህ ቢሆን በሕይወትህ ላይ ምን ይፈጠራል? ዘላለም ኗሪ ብትሆን እና ከጊዜ ጋር መሽቀዳደምህን ብታቆምስ?
ሰዎች በዘመናችንን በሙሉ ሙዋቲነታችንን አውቀን እንዳላወቀ ሆነናል። በእርግጠኝነት መጨረሻህ ሞት እንደሆነ ታውቃለህ ፤ ሆኖም ከሟችነት ራስህን ታርቃለህ። ከሞት መሸሺያ መንገዶችንም ትጠቀማለህ። ሲያምህ ሆስፒታል ትሄዳለህ... ከሞት በኋላ ዘላለማዊ ሕይወትን እንደምትኖር ታምናለህ...
ሞትን እንሸሸዋለን፣ እንደበቀዋለንም አንድ ሰው ስለ ሞት ካነሳም “አቦ አታሟርት!” እንለዋለን።
ዘመናችንን ሙሉ ከሞት ለማምለጥ ብንመኝም ሃይድገር ሞት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው ይለናል፡፡ ያለ ሞት “መኖር” ትርጉም ያጣል፡፡ አብዛኛው የሕይወት ክፍልህን ብዙ ጉዳዮችን ለመጨረስ ስትራራጥ ታሳልፋለህ ፤ ሆኖም ኢ-መዋቲ ከሆንክ ማርጀትም ሆነሞትና የማያስጨንቅህ ከሆነ ስለምን ከአልጋህ ላይ ትወርዳለህ? ጉዳይህን ጨረስከው ወይም በጅምር ተወከው ምን ለውጥ ያመጣል?
ዘላለም የሚኖረው ሰው እያንዳንዱ ቅፅበቶቹ ጣዕም አልባ ይሆናሉ። አይንህን ጨፍንና ዘላለም ኗሪ እንደሆንክ አስብ... ይህ የሰውነት ዓለም አይደለም... በዘላለማዊነት ውስጥ የሰውነት ባህሪ ይታጣል። ሰው ይሮጣል፣ ይደክማል፣ ያሸንፋል፣ ይሸነፋል... ሩጫ እና ድካም በሌለበት ዓለም ላይ “ሰውነት” ይታጣል፡፡
ሞት እና ጊዜ የተባሉ መልህቆች በሕይወታችን ውስጥ ያስፈልጉናል። ለማያልቅ ምግብ የሚስገበገብ ሰው አይኖርም... በወንዝ ውስጥ ያለ አሳም ውሃ ብርቁ አይደለም... ጊዜያችንም ዋጋ ካጣ ለመኖር ያለን ፍላጎት ይረግባል። የሚያኖረን ፍርሃታችን ነው ! የጸሐይ ግብአት ውበት ያለው ከመጥለቋ ላይ ነው፤ የፍቅር ግለቱ ያለው ከማለቁ ላይ ነው ... የእያንዳንዱ ደቂቃ ማለፍ የተሻለ ነገን እንድናልም ምክንያት ይሆነናል፡፡
ምንጭ:-ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ
https://t.me/ethioyibe
Telegram
ልዩ ልዩ ሀገረኛ እይታዎች😂😳🤔😒😏🤷♂😡😋
አዳድስ ስነልቦናዊ ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እይታዎች፣ሀሳቦች እንድሁም እውነታዊ ፍልስፍናዎችን እንጋራለን እናጋራለን። ሰላም ለሀገራችን Join and share @ethioyibe
ይገርማል ሁሌም ድክም ብሎኝ ስቀር ምርኩዝ ይልክልኛል፤ አንቺም የበቃልዬ ምርቃት ይድረስሽ ሲል ምርኩዝ አርጎ አመጣሽ። በቃልዬ አብነትን የመረቃትን ሰምተሻል? "እውቀት እንደ ምንጭ ይፍለቅብሽ፣ እንደጅረት ወርዶ ለዓለም ሁሉ ይድረስ ብሎ ነው የመረቃት" ። ለአንቺም ከምርቃቱ ይድረስሽ። አሜን፤ ጎሽ ልጄ አዎ፤
እማማ እንመለስ? ደከመዎት?
አየ ልጄ መመለስማ የለም፤ ወደኋላ ዞሬ መመልከቴ ከመነሻየ ምን ያህል ርቀት ተጉዤ እንደመጣሁ ለማወቅ፣ ወደፊት ለመጓዝ ተስፋ እንዲሆነኝ ነው፤ መመለስማ የለም።
ብዙ መከራ አይቻለሁ፣ ብዙ መከራና ስቃይ ፈትኖኛል ልጄ፤ ያኔ ከአበባየ መርገፍ በኋላ ጉልበት ተስኖኝ እቤት ቀርቼ ነበር።
ሰው የጭረት ጠባሳውን እየገለጠ፣ የሌላውን ቁስል እየወጋ፣ በቂም መከፋፈሉን አይታ፣ መቁሰሌ ሌላውን ሰው ወደ ሞት የሚወስድ አይሁን፣ ለእርቅና ለይቅርታ ይሁን ብላ የመንደሩን ሰው በአደራ መራችው። ወደኋላ መመለስ የለም ብላ ሁሉን በአንድነት አስተሳስራ የኔ ልጅ ወደፊት መራችው። ለወደደችው፣ ላመነችበት ዋጋ ከፈለች፤ ዋጋ ከፈለች እኔ ግን እሷ የከፈለችውን ዋጋ ከንቱ ለማስቀረት እቤቴ ቁጭ አልኩ፣ እቤት ቀረሁ፤ ግን ትውልድ አይጥፋ፣ ተስፋ አይጥፋ ይሄው አንቺ መጣሽልኝ እና ምርኩዝ ሆነሽ ይዘሽኝ ወጣሽ።
ዛሬ እግሬ እንዲቀጥልና እንድበረታ ያጸናኝ ተስፋ ነው።
የኔ ልጅ በዚህ እድሜሽ የደረሰብሽን እናትሽን ማጣትሽን ሰምቻለሁ ልጄ ግን ወደኋላ መመልከቱ ምን ያህል ትተሽው እንደመጣሽ ለማወቅ እንጂ ወደኋላ ለመመለስ አይሁን፤ አይሁን ልጄ።
ከመጣንበት ይልቅ ገና የምንሄድበት ብዙ ነው።
አሁን ምንድን ነው የሚመረቀው?
ዛሬ ሸክላ በመስራት ነው የሚያስመርቁት ብለዋል።
ጎሽ ጥሩ አድርገዋል የሰው ልጅስ ከመነሻው እንዲሁ አይደል እንደሸክላ ከአፈር፤ ሁሉም የሰው ልጅ እኮ ከአፈር ተነስቶ ወደ አፈር ነው።
ከአፈር እስከ አፈር!!!
https://t.me/ethioyibe
Telegram
ልዩ ልዩ ሀገረኛ እይታዎች😂😳🤔😒😏🤷♂😡😋
አዳድስ ስነልቦናዊ ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እይታዎች፣ሀሳቦች እንድሁም እውነታዊ ፍልስፍናዎችን እንጋራለን እናጋራለን። ሰላም ለሀገራችን Join and share @ethioyibe
የመዝጊያ መልዕክት ከእረኛየ!!!
ጋዜጠኛው አርባ ዓመት በትዳር የቆዩትን ወ/ሮ እያናገረ ነው
"ከባለቤትዎት ጋር አርባ ዓመት በትዳር ያለ ጸብ የቆዩበትን ምስጢር እስኪ ይንገሩን"
"ምን መሰለህ የኔ ልጅ የሰርጉ ቀን መጀመርያ ከቤተሰቦቼ ቤት ይዘውኝ የወጡ ግዜ በሽልም ፈረስ ላይ አድርገው ነበረ አብረን ሆነን እሳቸው ልጓሙን ይዘው እየጋለቡ እኔ ከኋላቸው ሆኜ ትንሽ እንደሄድን ፈረሱ ለገመ ይሄኔ እሳቸው
"አንተ ፈረስ ተው ብየሃለሁ አንድ" አሉ
ፈረሱ መሄድ ቀጠለና ትንሽ ቆይቶ አሁንም ለገመ ይሄኔ እሳቸው
"አንተ ፈረስ ተው ብየሃለሁ ሁለት" አሉ
ፈረሱ የግዱን ሄደ ሄደና ሲደክመው እንደገና ቆመ ያኔ እሳቸው በንዴት ከፈረሱ ላይ ዘለው ወርደው እኔንም አውርደው ሽጉጣቸውን መዘዙና
"አንተ ፈረስ ተው ብየሃለሁ ተው ሶስት" ብለው በግንባሩ ለቀቁበት ፈረሱ ክልትው አለ እኔም ደንግጬ
"ምን ሆነው ነው አንቱዬ?" ስላቸው ወደኔ ዘወር አሉና
"አንቺ ሴቲዮ ዝም በይ ብየሻለሁ ዝም በይ አንድ" አሉኝ
በቃ ይሄ ነው አርባ ዓመት በትዳር ያቆየን ምስጢር
????
https://t.me/ethioyibe
Telegram
ልዩ ልዩ ሀገረኛ እይታዎች😂😳🤔😒😏🤷♂😡😋
አዳድስ ስነልቦናዊ ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እይታዎች፣ሀሳቦች እንድሁም እውነታዊ ፍልስፍናዎችን እንጋራለን እናጋራለን። ሰላም ለሀገራችን Join and share @ethioyibe
Please don't spend the rest of your days punishing yourself just because someone who couldn't see your value made you doubt your worth .
Morning ✨
https://t.me/ethioyibe
Telegram
ልዩ ልዩ ሀገረኛ እይታዎች😂😳🤔😒😏🤷♂😡😋
አዳድስ ስነልቦናዊ ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እይታዎች፣ሀሳቦች እንድሁም እውነታዊ ፍልስፍናዎችን እንጋራለን እናጋራለን። ሰላም ለሀገራችን Join and share @ethioyibe
???ፊታውራሪ ዳምጠው???????
ፊታውራሪ ዳምጠው በምኒልክ ቤተመንግሥት ውስጥ የተከበሩ መኮንንና ዲፕሎማት ነበሩ። በዲፕሎማትነታቸው ከአድዋ ዘመቻ በፊት በጦርነቱ ላይ ለሚጎዱ ኢትዮጵያውያን ህክምና ማግኘት ይቻል ዘንድ ቀኝ አዝማች ገነሜን እና መምህር ገብረ እግዚአብሔርን አስከትለው ሩሲያ ድረስ በመሄድ ከሩሲያው ንጉሥ ኒኮላ ጋር መክረው ለአድዋ ጦርነት የቀይ መስቀል የህክምና ድጋፍ እንዲገኝ አድርገዋል።
ከሩሲያ ሲመለሱ አፄ ምኒልክ የጦርነቱን ጉዞ ጀምረው ነበር። ይህንን የሰሙት ፊታውራሪ ገስግሰው አባ ዳኘው ላይ ቢደርሱባቸው አባ ዳኘው መንገድ ያደከማቸው መሆኑን ተረድተው ሀገር ይጠብቁ ነግረው ቢያሰናብቷቸም ፊታውራሪ ግን በውሳኔያቸው ፀንተው አብረው ተጓዙ። ይህንን የሰማ የወሎ ህዝብም
እሪ በሉ ግሼ ስማ ተሁለደሬ
ሰፈር ጠብቅ አሉት የጦሩን ገበሬ! ብሎ ገጠመ።
በጦርነቱ ዕለት በሰማዕታ ጉብታ በኩል ባለው የጦር ግንባር የጠላትን ጦር ገጥመው፤ ክፉኛ አርበድብደው በማባረር ላይ እንዳሉ ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ወደቁ። በኚህ ጀግና ሞት መላው ሠራዊቱ ከልብ አዘነ። እንዲህም ብሎ ገጠመላቸው።
https://t.me/ethioyibe
ለሃሳብ አስተያየት
https://t.me/yibiopia
"የሴት ስራ በመስራቴ የተቀየረው መሀይምነቴ እንጅ ወንድነቴ አልተቀየረም"??????
ከህፃንነቱ ጀምሮ በሚጠይቃቸው እና በሚያነሳቸው ከተለመደው ማህበረሰብ ለየት ያሉ ጥያቄዎና ሃሳቦች በአካባቢው ሰዎች እና በወላጆቹ እንደህመምተኛ ተቆጥሯል።የመተሳሰብ እና የእኩልነት ተምሳሌት የሆነውን የአውራንባ ማህበረሰብ መስራች እና ሊቀመንበር ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዶክተር ዙምራ ኑሩ።የተወለደው በፅማዳ ወረዳ ያደገው ደግሞ በእሴቴ ወረዳ በጎንደር ከተማ ነው።ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በሚያነሳቸው ለየት ያሉ ሃሳቦች ተቀባይነትን ለማግኘትና ሃሳቡን የሚያካፍላቸው እንዲሁም የሱን ሀሳብ የሚጋሩ ሰዎችን ለማግኘትን ለበርካታ አመታት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እና እልህ አስጨራሽ ጉዞ ማድረግ ነበረበት።
በመጨረሻም ፎግራ ወረዳ ላይ ሀሳቡን የሚጋሩት ሰዎች ያገኛል።ከዚያም የአውራንባን ማህበረሰብ ከ 19(፲፱) ሰዎች ጋር በመሆን እና አራት መርሆች ያቀፈ ህግ በማውጣት መሰረቱ።
እነዚህ መርሆች
1ኛ) የፆታ መተሳሰብና እኩልነትን ማስፈን
2ኛ) የህፃናት መብትን ማክበር
3ኛ) ችግረኞችን፣ ህሙማንንና አረጋውያንን መርዳት እና
4ኛ) ማታለል፣ መዋሸት፣ ነፍስ-ማጥፋት እና ሥርቆት የሌለበት ማህበረሰብን መፍጠር ናቸው፡፡
ይህንንም ሀሳብ ሚድያ ላይ ለማውጣት እና ለህዝቡ ለማሳወቅ ከ1964-1993 ዓ.ም እልህ አስጨራሽ ትግል ይህንን ማህበረሰብ ለማቋቋም ዶክተር ዙምራን ካነሳሳው ነገሮች መካከልም በእናቱና በአባቱ እንዲሁም በአካባቢው የነበረው የስራ ክፍፍልና በተለምዶ የነበረው አስተሳሰብ መሆኑ ይነገራል።
በመጨረሻም ዶክተር ዙምራ ላበረከቱት ስራቸውም በ2002 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቱ የክብር ዶክትሬት ተሰቶታል።
https://t.me/ethioyibe
????ሶስቱ ስጦታዎች????
አንድ ወቅት በቢችሪ ከተማ ውስጥ የሚኖር በሁሉም ህዝቦቹ የሚወደድ እና የሚከበር አንድ ደግ ልዑል ነበር።
ነገር ግን አንድ እጅግ ድሃ የሆነ ሰው ልዑሉን አምርሮ ይጠላውና እሾህ ምላሱንም ያለማቋረጥ ይዘረጋበት ነበር፡፡
ልዑሉ ይህን ቢያውቅም ነገሩን በትዕግስት መያዝ መርጧል፡፡ አንድ የክረምት ምሽት ላይ ሊያስተምረው ወስኖ አንድ አገልጋዩን ጠርቶ አንድ ጆንያ ዱቄት፣ አንድ ከረጢት ሳሙናና አንድ ቁና ስኳር አሸክሞ ወደ ሰውየው ቤት ላከው፡፡
«ልዑሉ በማስታወሻነት ይህን ስጦታ ልኮልሃል» አለው አገልጋዩ፡፡
ሰውየው፤ ልዑሉ ስጦታውን የላከለት አክብሮት እንደሆነ በማሰብ ተደሰተ፡፡ ይህን ኩራቱን ይዞ ወደ ጳጳሱ በመሄድ ልዑሉ ያደረገለትን ነገር ነገራቸው፡፡ «ልዑሉ የእኔን መልካም ፈቃደኝነት መፈለጉ አይታይዎትም?» አላቸው፡፡
«እንዴት ብልህ ልዑል ነው!» አሉ ጳጳሱ። «አንተ ደግሞ ምኑም አልገባህም፡፡ በምልክት እየነገረህ ነውኮ፡፡ ዱቄቱ ለባዶው ሆድህ ነው፣ ሳሙናው ለአደፈው ቆዳህ፣ ስኳሩ ደግሞ መራር ምላስህን እንድታጣፍጥበት ነው።»
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰውየው በራሱ ማፈር ጀመረ፡፡ ለልዑሉ የነበረው ጥላቻ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠነከረ፡፡ የልዑሉን ሃሳብ የገለጡለትን ጳጳስ ሳይቀር ጠላቸው:: ይሁን እንጂ ከዚያች ዕለት በኋላ እንዲት ቃል ተንፍሶ አያውቅም፡፡
https://t.me/ethioyibe
Telegram
ልዩ ልዩ ሀገረኛ እይታዎች😂😳🤔😒😏🤷♂😡😋
አዳድስ ስነልቦናዊ ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እይታዎች፣ሀሳቦች እንድሁም እውነታዊ ፍልስፍናዎችን እንጋራለን እናጋራለን። ሰላም ለሀገራችን Join and share @ethioyibe
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 6 days, 8 hours ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 3 weeks ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 2 months ago