Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 6 days, 8 hours ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 3 weeks ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 2 months ago
የዓለም ዜና
*የሕወሓት የረጅም ጊዜ ሊቀመንበርና አንጋፋ አባል አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት «የጥፋት ቡድን አመራሮች» ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ገለፀ። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መከላከያ ሚንስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበዉ አቶ ስብሐትን፣ ላለፉት 27 ዓመታት «የማተራመስ ስትራቴጂ የነደፈ፣ ያስተባበረ እና ያደራጀ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በሀገራችን ሠራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሠራዊቱን ያስጨፈጨፉ» ብሏቸዋል።የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ይኽንኑ ለኢዜአ መግለጣቸውም ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር ትናንት 4 የሕወሓት ባለስልጣናት መገደላቸዉንና ዘጠኝ መማረካቸዉን ዐስታዉቆ ነበር።
*የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የኮሮና ተሐዋሲ «ኅብረተሰቡ ውስጥ በከፍተኛ ኹኔታ» ሳይሰራጭ እንዳልቀረ ዐስታወቀ ሲል አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገበ። ዓለም አቀፍ ድርጅቱ በቦታው በተገኘ መረጃ የተጠናቀረ ባለው ሠነድ መሰረት በትግራይ ክልል ሐኪም ቤቶች መዘረፋቸው አንዳንዶቹም መጎዳታቸውን ጠቅሷል። በክልሉ ከሚገኙ 40 ሐኪም ቤቶች ከአምስቱ በስተቀር ሌሎቹ መመዝበራቸው እና ብዙዎቹም ሳይፈርሱ እንዳልቀረ በዘገባው ተገልጧል። የጤና አውታራት ከዋና ከተሞች ውጪ እንደማይሠሩም ተመድ አትቷል። በዋና ከተሞች ውስጥ ያሉትም ቢሆኑ አንዳንዶቹ እንቅስቃሴያቸው ውስን ነው፤ ሌሎቹ ደግሞ ምንም አቅርቦት እና የጤና ባለሞያዎች የላቸውም ብሏል ዓለም አቀፍ ድርጅቱ በዘገባው። በገጠራማ አካባቢዎች እንዲሁም እንደ መቀሌ፣ ሽራሮ እና ሽሬ ባሉ ከተሞች አቅራቢያ ውጊያ እንዳለ ይነገራል ሲል ተመድ መጥቀሱን የዜና ምንጩ ዘግቧል። አጠቃላይ የሰብአዊ ይዞታው «መጥፎ ነው» ሲልም አክሏል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በበኩሉ፦ 4 ከፍተኛ የሕወሓት አመራር መደምሰሳቸውን እና 9 ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በጠቀሰበት በትናንቱ ዘገባው ጁንታ ወንጀለኞች የሚላቸውን ቀሪ የሕወሓት አመራር «አድኖ ለመያዝ» ገባሁት ባለው ቃል መሰረት «ግዳጁን እየተወጣ» መኾኑን ዐስታውቋል።
*ከ3,500 በላይ ኢትዮጵያውን በመተማ በኩል ከሱዳን ወደ አገራቸው መግባታቸውን የመተማ ዮሐንስ አካባቢ የመንግስት ኃላፊዎችና ኢምግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐስታወቊ። ሱዳን ውስጥ በተለይም ገዳሪፍ አካባቢ በግብርና እና በቀን ሥራ ይተዳደሩ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን በኢትዮ ሱዳን ድንበር ላይ የተፈጠረው ውጥረት እንዲሁም ሱዳን ዉስጥ በተፈጠረዉ የኢኮኖሚ ቀወስ ምክንያት መመለሳቸዉ ተገልጧል። የመተማ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ስጦታው ጫኔ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገር እየገቡ መኾናቸውን ተናግረዋል። «በዚህ ሦስት ወር ውስጥ 3.600 [ገብተዋል።] አሁንም ግን የሚመጡ አሉ የሚል ሐሳብ ነው ያለኝ። እና ከኢትዮ ሱዳን [ግጭታ] ጋር ተያይዞ ያለው እንቅስቃሴ ይህን ይመስላል። በእግር ደግሞ በረሃ ላይ ሲሠሩ የነበሩ፣ እንደገና ደግሞ ቊጥራቸው የማይታወቅ እየገቡ ወደ እኛ ይመጣሉ።» ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የመተማ ቅርንጫፍ ኢሚግሬሽን ጽ/ቤት ባልደረባ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ከገዳሪፍና ከካርቱም አሁንም ወደ አገር እየገቡ መኮናቸውን ተናግረዋል። «ከገዳሪፍ እና ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ሴት 173፣ ወንድ 130 ናቸው። አሁንም እየመጡ ያሉ አሉ። ከካርቱም የመጡት 3,505 ናቸው። በተፈጠረው ችግር ምክንያት የመጡ ይገኙበታል፤ ሁለተኛ ደግሞ ያለው የሱዳን ገንዘብ ምንዛሪ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ እና በኑሮ ውድነት ወደ ሀገራቸው የገቡ ጭምር ናቸው። የእኛ ባለ ሐብቶች እየመጡ እየወሰዷቸው ነው።» በመንገድ እንግልት ዝርፊያና ሞት ያጋጠማቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉም አስተያየት ሰጪው አመልክተዋል። የባሕር ዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ወደ አገር ከገቡት መካከል አስተያየታቸውን ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም ወደ ቤተሰብ አሊያም ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ስለተሸኙ ማካተት እንዳልተቻለ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል። ከጥቅምት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ የሱዳን ኃይሎች በምዕራብ ጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች ያደረጉትን ትንኮሳ ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ሰፍኖ ቆይቷል።
*የዩናይትድ ስቴትሱ የአውሮፕላን አምራች ግዙፍ ኩባንያ ቦይንግ፣ በ737-ማክስ አውሮፕላኖቹ እንከን ለደረሰው አደጋ 2,5 ቢሊዮን ዶላር ካሣ ለመክፈል መስማማቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። እንዲያም ሆኖ ግን የማክስ አውሮፓላን አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ ይቅርታ እንደማይጠይቅ የሕግ ክፍሉ ዐሳውቋል። የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች እንደ ጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር በ2018 እና 2019 በአምስት ወራት ልዩነት ኢንዶኔዢያ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስክሰው ለ346 ሰዎች ሕይወት ኅልፈት መኾናቸው የሚታወስ ነው። ቦይንግ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነበረው 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ወቅት ሕይወታቸውን ባጡ ተሳፋሪዎች ቤተሰቦች 140 ግድም ክስ ይጠብቀዋል። ኩባንያው እስካሁን ድረስ ከኢንዶኔዢያው ላየን ኤር አውሮፕላን አደጋ ጋር በተያያዘ የየተከፈቱበትን አብዛኛውን ክሶች ከቤተሰቦች ጋር በመስማማት ማዘጋቱን የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ቦይንግ ኩባንያ የመደበዉ ካሳ ለአየር መንገዶችና በአደጋዉ ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች የሚከፈል መሆኑን የህግ ክፍሉ ዐሳውቋል። በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ የኩባንያው አውሮፕላኖች በዓለም ዙሪያ ከበረራ ከመታገዳቸውም ባሻገር ኩባንያውን ለ20 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደዳረገው ተዘግቧል።
*የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በዩናይትድ ስቴትስ ፓርላማ ሕንፃ (ካፒቶል)በፈጠሩት ነውጥ የተጎዳ አንድ ፖሊስ ዛሬ ሕይወቱ ማለፏ ተገለጠ። ፖሊሱ ጉዳት የደረሰበት ካፒቶል የተባለዉን ሕንፃ በመጠበቅ ላይ ሳለ ነበር። ፖሊሱ ረቡዕ እለት የትራምፕ ደጋፊ ነውጠኞች ባደረሱበት ጥቃት ተጎድቶ ሐኪም ቤት ውስጥ ሲረዳ ቆይቶ ነው ሕይወቱ እንዳለፈች የተነገረው። በእለቱ አንዲት ሴትም ከፖሊስ ተተኩሶባት ተገድላለች። በካፒቶሉ ኹከት እስካሁን የአምስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።
*ኢራን በፋርስ ባህረሠላጤ «ሥልታዊ» ያለችውን የጦር ሠፈር ዛሬ አስመረቀች። የኢራን አብዮታዊ ዘብ የምድር ውስጥ ሚሳይል ማከማቻ ጦር ሠፈሩን ዛሬ ማስመረቊን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። በጦር ሠፈሩ ምረቃ ላይ የተገኙት የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሆሳይን ሣላሚ ዛሬ የተመረቀው የጦር ሠፈር አብዮታዊ ዘቡ «ስልታዊ» ባለቸው ሚሳይሎች ከተደራጁት በርካታ ጦር ሠፈሮች አንዱ መኾኑን ጠቊመዋል።
«ዛሬ እዚህ የጦር ማደራጃ ውስጥ የምትመለከቱት የአብዮታዊ ዘቡ የባሕር ኃይል የሚሳይል ጦር ሠፈሮች ከያዟቸው በርካታ ተቋማት አንዱን ነው። ከጀርባችን የሚሳይሎቹን አምዶች እና ማስወንጨፊያ አካላቶቻቸውን መመልከት ትችላላችሁ።»
የኢራን መንፈሳዊ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ኻሜኒ፦ በጦር ሰፈሩ ምረቃ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር የሚሳይል መርሐ ግብሩ የተደራጀው ሀገሪቱን ከማናቸውም ጥቃቶች «ለመከላከል» ነው ማለታቸው ተዘግቧል።
@abyssinia2011
News bank
This channel aims to provide new news and other to Ethiopians and native Ethiopians in abroad. Welcome in open hands.
@abyssinia2011
https://telegram.me/newszena
Telegram
News bank
This channel aims to provide new news and other to Ethiopians and native Ethiopians in abroad. Welcome in open hands. @abyssinia2011
https://p.dw.com/p/3Nu5q?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
Deutsche Welle
በበረዶ ዘመን በባሌ ተራራ ሰዎች እንደኖሩ በጥናት ተረጋገጠ
የሰው ልጅ አመጣጥን የሚያጠኑ ኢትዮጵያውያንም ሆነ የውጭ ተመራማሪዎች ቅሪተ አካሎችን እስካሁን ሲያገኙ የቆዩት በሸለቆማ ቦታዎች ነበር። በኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ባለሙያዎች ትብብር በቅርቡ የተደረገ አንድ እና በዚህ ሳምንት ጥናት ግን የሰው ልጅ በበበረዶ ዘመን በተራራማ ቦታዎች ይኖር እንደነበር አረጋግጧል።
የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ላይ ቅሬታ አቀረበ!
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ #የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ላይ ቅሬታውን አቀረበ። የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል ካህሳይ ብሔራዊ ፈተናው በተሰጠበት ወቅት "በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የፈተና አሰጣጥ ሥነ-መግባር ጉድለት" ነበር ብለዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል ካህሳይ ለቢቢሲ ሲናገሩ "በክልላችን ፈተናው ሲካሄድ የፈተና አወሳሰድ ስነ-መግባርን ጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ስርዓቱን የጠበቀ አልነበረም" ብለዋል።
ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል ካህሳይ በወቅቱ ተስተውሏል ስላሉት የፈተና አሰጣጥ ስነ-ምግባር ጉድለት ለትምህርት ሚንስቴር አሳወቀው እንደነበረ ተናግረዋል።
"ከክልላችን እና ከሌሎች አከባቢዎች የተነሳው ቅሬታ ምላሽ ሳያገኝ ውጤቱ ይፋ ሆኖዋል። በዚህም ቅሬታ አለን።" ብለዋል። ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል "የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተና ውጤቱን አልቀበልም አለ" ተብሎ የተዘገበው ስህተት ነው ሲሉም አክለዋል።
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሄር በበኩላቸው በውጤቱ ላይ ለሚነሱ ቅሬታዎች በሙሉ አስፈላጊው ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ምላሽ ይሰጠዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አረያ ጨምረው እንደተናገሩት ከፈተና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የቀረበ ቅሬታ የለም ብለዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
@mosethiobitcoin
ከ200 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል!
በህንድ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ ከ2 መቶ በላይ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተሰደዋል፡፡ በአለፈው ዓመት በተመሳሳይ በደረሰ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ ከ450 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
Via #VOA
@mosethiobitcoin
#update የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ ጎንደር ዞን የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸውን አካባቢዎች እየጎበኙ ነው። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህና የውኃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ በስፍራው ተገኝተዋል።
ከፍተኛ ባለስላጣናቱ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች በጎርፍ የተጠቁ አካባቢዎች የደረሰውን ጉዳት ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው። የጎርፍ አደጋው ከርብ ግድብ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ የፌዴራል ውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቋል።
ምንጭ፡- አብመድ
@mosethiobitcoin
#update የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ ጎንደር ዞን የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸውን አካባቢዎች እየጎበኙ ነው። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህና የውኃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ በስፍራው ተገኝተዋል።
ከፍተኛ ባለስላጣናቱ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች በጎርፍ የተጠቁ አካባቢዎች የደረሰውን ጉዳት ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው። የጎርፍ አደጋው ከርብ ግድብ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ የፌዴራል ውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቋል።
ምንጭ፡- አብመድ
@mosethiobitcoin
ከደቦ ፍርድ ለጥቂት ያመለጠው የኤሌክትሪክ ሰራተኛ!
በደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በተሳሳተ መረጃ በመንጋ ውሳኔ ሊገደል የነበረው የመብራት ሃይል ሰራተኛ በፖሊስ ድጋፍ ህይወቱን ማትረፍ ተችሏል።
በዞኑ የጃማ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ተሾመ ለገሰ ለኢዜአ እንደገለፁት ትናንት ከሰዓት በኋላ አንድ የፌዴራል ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኛ ከዓለም ከተማ ወደ ቃስታ የተዘረጋውን መስመር በማስተካከል ስራ ላይ ተሰማርቶ ነበር።
ሰራተኛው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ ለመሰብሰብና የተበላሹ መስመሮቹን ለማስተካከል የተሰማራ ቢሆንም የህፃናት ኩላሊት ለመስረቅ የመጣ ነው የሚል የተሳሳተ መረጃ በመናፈሱ ምክንያት የአካባቢውን ህዝብ ለደቦ ውሳኔ እንዲነሳሳ አድርጎታል።
በወረዳው የ017 ቀበሌ ህዝብ ተሰባስቦ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የአካባቢው ፖሊስ በፍጥነት ደርሶ ህይወቱን እንዳተረፈው ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል ።
ሰራተኛው በህይወት ተርፎ በፖሊስ ከለላስር ከዋላ በኋላም በጉልበት ነጥቀው ለመግደል የሞከሩ አምስት ሰዎች በቁጥጥርስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ጥቂት ግለሰቦች በነዙት አሉባልታ ተነሳስቶ የሰው ህይወት ለመቅጠፍ መንቀሳቀስ ተገቢነት እንደሌለው የገለፁት ሃላፊው ሰራተኛው በማያውቀው ምክንያት ከመገደል የተረፈው ለጥቂት ነው ተብሏል። ህብረተሰቡ ለወደፊቱም ቢሆን በተሳሳተመረጃ ወደ ጥፋት በመግባት የህግ ጥሰት እንዳይፈጸም ዛሬ በደጎሎ ከተማ የምክክር መድረክ ተካሔዷል።
በመድረኩ ላይ ህብረተሰቡበተሳሳተመረጃ ተነሳስቶ ወደ ደቦፍርድ ከመግባት እንዲቆጠብ ትምህርት ተሰጥቷል። አጠራጣሪ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ለፀጥታ ሃይሎች መጠቆም እንጂ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ወንጀል መፈፀም ከተጠያቂነት እንደማያድን በአፅንኦት ተነግሯል።
@mosethiobitcoin
News bank
This channel aims to provide new news and other to Ethiopians and native Ethiopians in abroad. Welcome in open hands.
@abyssinia2011
https://telegram.me/newszena
Telegram
News bank
This channel aims to provide new news and other to Ethiopians and native Ethiopians in abroad. Welcome in open hands. @abyssinia2011
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚደገፉት የየመን ተገንጣዮች በዕለተ-ቅዳሜ ከተቆጣጠሯቸው የኤደን ቁልፍ ቦታዎች በማግሥቱ ለቀው መውጣት ጀምረዋል። የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት (southern transitional council) ተብሎ የሚጠራው ተገንጣይ ቡድን 70 ሰዎች ካለቁበት የአራት ቀናት ጦርነት በኋላ ነበር በኤደን የአብድረቦ መንሱር ሐዲ መንግሥት ይዞታዎችን በእጁ ያስገባው።
የደቡብ የመን ተገንጣዮችም ሆኑ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ የሚደረግለት የአብድረቦ መንሱር ሐዲ መንግሥት በጎርጎሮሳዊው 2015 ዓ.ም. የተጀመረው እና በሑቲዎች ላይ ያነጣጠረው ሳዑዲ መራሽ ግብረ-ኃይል ጦርነት አጋሮች ናቸው።
ኤደንን ከአብድረቦ መንሱር ሐዲ መንግሥት ለመንጠቅ የደቡብ የመን ተገንጣዮች ያደረጉት የአራት ቀናት ጦርነት በሳዑዲ መራሹ ግብረ-ኃይል መካከል መቃቃር መኖሩን ይፋ አድርጓል።
በደቡባዊ የመን 90,000 ገደማ አጋር ታጣቂዎች ከጎኗ ያሰለፈችው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በአካባቢው ከፍ ያለ ተደማጭነት እንዳላት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ይጠቁማል። ይሁንና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መቀመጫውን በሳዑዲ አረቢያ ካደረገው የአብድረቦ መንሱር ሐዲ መንግሥት ጋር ተቃቅራለች።
ከአራት አመታት በፊት የቀጠናውን አገራት አስተባብረው በሑቲዎች ላይ የዘመቱት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ሳዑዲ አረቢያ ማለቂያ ባጣው እና የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ባስከተለው የየመን ጦርነት እርስ በርስ የሚቃረን ፍላጎት እንዳላቸው እየታየ ነው።
ሳዑዲ አረቢያ ሰሜናዊ የመንን የሚቆጣጠሩት እና በተደጋጋሚ ድንበር ተሻጋሪ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅመዋል እያለች የምትከሳቸውን ሑቲዎች ዋንኛ የጸጥታ ሥጋት አድርጋ ትቆጥራቸዋለች።
ከየመን ወታደሮቿን ማስወጣት የጀመረችው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በአንፃሩ ማለቂያ ከሌለው ጦርነት ይልቅ የአፍሪካ እና የእስያ የንግድ መስመር አቅራቢያ በሚገኘው ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል የጸጥታ ሁኔታ ላይ አተኩራለች።
የደቡብ የመን ተገንጣዮች ኤደንን ከተቆጣጠሩ በኋላ ሳዑዲ አረቢያ ተኩስ እንዲያቆሙ እና ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ትዕዛዝ አስተላልፋ ነበር። የሳዑዲ መንግሥት የቴሌቭዥን ጣቢያ ትናንት እንደዘገበው ተገንጣዮቹ ከኤደን ለቀው መውጣት ጀምረዋል። ሳዑዲ መራሹ ግብረ-ኃይል በአብድረቦ መንሱር ሐዲ መንግሥት «ቀጥተኛ ሥጋት» ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሙን አስታውቋል። ድብደባው በማን ላይ ያነጣጠረ እንደነበረ የተባለ ነገር የለም። የየመን ባለሥልጣናት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚደገፉት ተገንጣዮች ከኤደን ጎዳናዎች ጥለው ቢወጡም የፕሬዝዳንቱን ቤተ-መንግሥት ጨምሮ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎችን አሁንም እንደተቆጣጠሩ እንደሆነ አስታውቋል።
የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት ቃል አቀባይ ኒዛር ሐይታም ሳዑዲ አረቢያ ላቀረበችው የተኩስ አቁም ጥሪ ተገንጣዮቹ እንደሚተባበሩ ትናንት ማማሻውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ቃል አቀባዩ የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት በኤደን ከተማ ከተቆጣጠራቸው ይዞታዎች ለቅቆ ስለመውጣቱ ግን ምንም ያሉት ነገር የለም። የደቡብ የመን የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አይዳሮስ አል-ዙባይዲ በበኩላቸው ከሳዑዲ መራሹ ግብረ-ኃይል ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። አል-ዙባይዲ በየመን ቴሌቭዥን ጣቢያ በተላለፈ እና በምክር ቤቱ ድረ-ገፅ ይፋ በተደረገ መግለጫቸው ኢራን በቀጠናው የምታደርገውን መስፋፋት ለመግታት በሳዑዲ አረቢያ መሪነት የተጀመረውን ዘመቻ በፅናት እንደሚቀጥሉ እና በሳዑዲ አረቢያ የቀረበውን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚያከብሩ ገልጸዋል።
ሳዑዲ አረቢያ ሁለቱን ተቀናቃኝ ኃይሎች ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደ ሪያድ መጥራቷን የሳዑዲ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የደቡብ የመን የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አይዳሮስ አል-ዙባይዲ ይኸንንው ስብሰባ እንደሚካፈሉ አረጋግጠዋል።
@mosethiopiabitcoin
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 6 days, 8 hours ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 3 weeks ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 2 months ago