#UPSC , #SSC #BPSC #STATE #PET #Banking, #Railway, #RRB, #IBPS, #SBI, #Defence, #Police, #RBI etc.
??This Channel Has Been Established With The Aim Of Providing Proper Guidance To Youths Preparing For All Govt. Exam.
✆ Contact.? @abhi67899
Last updated 2 months, 2 weeks ago
Ставим всех на место одной фразой?
По всем вопросам: @Makhmudjanov
(За скидкой ко мне! Оплаты через меня!)
Менеджеры: @sharp_rek
Last updated 2 years, 7 months ago
Last updated 2 years, 10 months ago
የወገኖቻችን ሥነ አፈታት ከየት ወደየት👀
እስቲ ተመልከቷት💀 ኦርቶዶክሳውያን በልምምዶቻቸው የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ይመስላሉ? በዛውም እንደተለመደው እንጠራራ 😁
ትላንት ማታ እና ዛሬ የኦርቶዶክስ አቃብያን በአሉባልታ ሲከሱን ነበር አሉ☹️ ለማንኛውም እዚህ ላላችሁትም ይኸው✌️
በሥላሴ እሳቤ ውስጥ Immanent/Ontological Trinity/ ውስጣዊ ግብር የምንለው በአካላቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ሲሆን፤ Economic Trinity/ውጫዊ ግብር የምንለው ደግሞ ሥሉሱ አምላክ ከፍጥረት ጋር ያለውን ግንኙነት ነው።
ታዲያ በዚያ ውስጥ ኢየሱስን አባት የማንልበት Strict sense እና አባት የምንልበት መንገድ አለ። ቪድዮውን ተመልከቱት።
መልስ ቢጤ ተወርውሮልናል? እስቲ እንያት
? በቅድሚያ ግን ውይይታችንን ከምን አደረስካት የውሃ ሽታ ሆነህ ቀረህብኝ በሉልኝ? ሲቀጥል እስቲ ጋቪንን በእርሱና በሌሎች ወገኖች Suggestion መሠረት ቁጭ ብዬ 4ቱን ቪድዮዎች ፈልጌ አያለሁ?። ለማንኛውም፦
? የቀኖና ልዩነት Tolerable ከሆነ ፕሮቴስታንቶችን መርጠህ 66ቱን ብቻ ስለተቀበሉ ስለምን ትወቅሳቸዋለህ lol? በዛ ላይ "infallible ቀኖና አለን መች አልን?" ነው ያለው? እና ታዲያ ቀኖናችሁ ፋሊብል ከሆነ እስካሁን ለምን አደከምከን lol? Your whole theory falls over there እኮ? ጉዳዩ ቤተክርስቲያን የዮሐንስን ወንጌል መስጠቷ ሳይሆን ያቺው Infallible ያልካት ቤተክርስቲያን በጉባኤም ይሁን በሌላ መንገድ የማይሳሳት ቀኖና ስላልሰጠችህና "የምትሳሳተውን" ሎካል ቤተክርስቲያንም በዚሁ ምክንያት ልታርማት ስለማትችል Infallible church claim ሃሳባዊ እንጂ አካላዊ አለመሆኑ ነው።
? ቤተክርስቲያን infallible ናት መጽሐፍ ቅዱስንም infallibly ሰጥታናለች ብሎ ከጨረሰ በኋላ "አይ infallible ያልናት በሃይማኖት በአለማቀፍ ደረጃ ነው"? what a hypnosis! በአለም አቀፍ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስን አልሰጠችህም ማለት ነው? ይህ እኮ መጽሐፍ ቅዱስን Fallible ነው ከማለትና ቤተክርስቲያንም በሆነ አቅጣጫ (ቢያንስ በመጻህፍት አሰጣጥ ረገድ) Fallible ናት ማለትም ነው? ኧረ ከድጡ ወደማጡ ሆነብን?
? የኢትዮጵያው መጽሐፍ ቅዱስ ያው ከአለም አቀፋዊቷ የተገኘ ስላልሆነ ለጊዜው Fallible መጽሐፍ ቅዱስ ይዛችሁ መቀጠላችሁ ነው እንግዲህ።
?ታዲያ ከማትሳሳተው ዘንድ የማይሳሳተውን መጽሐፍ ቅዱስ መች እንጠብቅ lol?
በሉ ማታ እንገናኝ?
በአንድ ውይይታችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ የማይሳሳት እንደሆነ ለማወቅ የማትሳሳት ቤተክርስቲያን ታስፈልጋለች ያለኝ የኦርቶዶክስ አቃቤ ትላንት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳቸው ስህተት እንዳለበትና ሊታረም እንደሚገባው ነግሮናል?? እስቲ ለማንኛውም በቪድዮ እስከምመጣበት የእርሱን ሃተታ ተከትለን ለኦርቶዶክስ ወገኖቻችን ተከታዩን ጥያቄ እንጠይቅ፦
1) ከማትሳሳተው ቤተክርስቲያን የተቀበላችሁት የማይሳሳት መጽሐፍ ቅዱስ እጃችሁ ላይ አለ? ካለ አሳዩን
2) እጃችሁ ላይ ያለው 81 መጽሃፍ ቅዱስ ህትመት እንጂ ቀኖና አይደለም ተብላችኋል። ቤተክርስቲያናችሁ በይፋ ይህንን ብላለች ወይስ በግምት ነው?
3) እንበልና 81 መጽሐፍ ቅዱሳችሁ ቀኖና ካልሆነ የትኛውን መጽሐፍ ቅዱስ ነው ትክክለኛ ብላ የሰጠቻችሁ? ቀኖናዊ መጻህፍቱስ የት አሉ?
4) እጃችሁ ላይ የማይሳሳት ተብሎ የተሰጣችሁ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌለና እናንተ ደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ አይሳሳትም፤ ከማትሳሳት ቤተክርስቲያን ልንቀበለውም ይገባል ብላችሁ ካመናቸሁ ያቺው የማትሳሳተው ቤተክርስቲያን ሃሳባዊና በምድር የሌለች መሆኗ አይደለምን?
ውድ ኦርቶዶክሳውያን እስቲ በቅደም ተከተል መልሱልን?
በዚህ ርእስ ወንድማችን ጆን የሰራውን Review እዚህ ተመልከቱ
ወንጌላዊ ተግባር
ትራፊክ ፖሊሱ መኪና በሚያስተናብርበት ቦታ ላይ የዳንስ ትርኢት ያሳያል፣ ስራውን እየሰራ ይደንሳል፣ የሚያገለግላቸው ሰዎችም ያጅቡታል። ይህንን ማስታወቂያ ያላየው ያለ አይመስለኝም። የማስታወቂያው አላማ ዘና በሚያደርግ ተንቀሳቃሽ ምስል የተጠቃሚን ትኩረት መሳብ በመሆኑ መልካም የሆነ የንግድ ሃሳብ ነው። በትክክለኛው አለም ይህንን ስራ የሚሰራ የትራፊክ ፖሊስ ግን ከሙያው ስነምግባር ውጪ በመውጣቱ ምክኒያት ከሳቅ ይልቅ የስነ ምግባር እርምት ያስፈልገው ይሆናል። በዘመናት መሃል ክርስትናን በዚህ መንገድ ለመኖር የሚፈልጉ፤ ህይወታቸውን ከተሰራበት አላማ ውጪ እንዲሁም ሰዎችን ለማማለል ብቻ የሚጠቀሙበት ሰዎች ኖረዋል፣ ይኖራሉም (እንደ ጠንቋዩ ስምኦን አይነቱ)። መፅሃፍ ቅዱስ ግን ለእንደነዚህ አይነት ሰዎች ፍቱን የሆነ ምክር ይመክራል፤ ራሥህን ካድ በማለት።
ወንጌል ያለ አማኙ የተግባር አስተዋፅኦ የሚያድን መልካም ዜና እንደሆነ ሁሉ የአዳኛችንን ማንነት በተግባር የምንገልፅበትና የምናሳይበት የህይወት ምልልስም ነው። አማኝ በአኗኗር ዘይቤው ወንጌልን ለማሳየትና ለመኖር የተጠራ ሰው እንደመሆኑ የሚከተሉትን ሁለት የህይወት ስልቶች ያለማወላወል እየተገበረ ለመሆኑ ሁልጊዜ እርግጠኛ መሆን ይኖርበታል፦
ሀ) ብርሃንነቱን፦ ጌታ ኢየሱስ ብርሃን ለመሆን የሰጠው ትርጉም <እግዚአብሄርን የሚያስከብር መልካም ስራ> የሚል ነው (ማቴ5:16)። እስቲ በየእለት ኑሮአችን የምንተገብራቸውን ተግባራት ቆም ብለን እናስታውስ፣ እግዚአብሄር በሰጠን ሰአታት እርሱን የሰማይ አባታችንን ለማክበር አስበን የምንሰራው ምን ያህሉን ነው? እነሆ ትልቅ የነፍስ ጥያቄ?
ለ) ተሸካሚነቱን፦ ክርስቲያን ምን ይሸከም፧ የኢየሱስ መልስ <መስቀሉን> የሚል ሆኖ ይገኛል። ኢየሱስ ሊከተሉት የሚፈልጉ ሁሉ ራሳቸውን ይክዱ ዘንድ ይወዳል። መስቀላቸውን ይሸከሙ ዘንድም ይጠይቃል። ራሱን የካደ ክርስቲያን ከራሱ ጥቅም ይልቅ የእግዚአብሄርን መንግስት፣ ከራሱ ደስታ ይልቅ የወንድሞቹን ሃሴት፣ ከራሱ መወደስም ይልቅ የጌታው ፅድቅ ያስደስተዋል፣ያረካውማል፣ ስለዚህም ዝቅ ብሎ መስቀሉን ይሸከማል፣ ማለትም ስለዳነበት የመስቀሉ እውነት መሰዋት ያለበትን ሁሉ ይሰዋል፣ መተው ያለበትንም ሁሉ ህይወቱን ጨምሮ ያለስስት ይተዋል እንጂ ክርስትናውን ለጊዜያዊ ጥቅም አይሰዋውም።
? እኔስ ማን ነኝ?
?ክርስትናዬስ በምን ይገለጣል?
?ብርሃኔስ ምን ያህል ያበራል?
ለ?ንግድ የማውለው ብርሃን፣ ተመልካቾቼን የማማልልበት የትርኢት መስቀልስ ይኖረኝ ይሆን?
?ማስተዋልን የሚፈልግ ህይወት ይህ ነው
#UPSC , #SSC #BPSC #STATE #PET #Banking, #Railway, #RRB, #IBPS, #SBI, #Defence, #Police, #RBI etc.
??This Channel Has Been Established With The Aim Of Providing Proper Guidance To Youths Preparing For All Govt. Exam.
✆ Contact.? @abhi67899
Last updated 2 months, 2 weeks ago
Ставим всех на место одной фразой?
По всем вопросам: @Makhmudjanov
(За скидкой ко мне! Оплаты через меня!)
Менеджеры: @sharp_rek
Last updated 2 years, 7 months ago
Last updated 2 years, 10 months ago