ሳሙኤል አለሙ-Samuel alemu

Description
ሌላ መገኛዬ...
facebook.com/samialemu
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

4 weeks ago
የማይጨንቀው ሲጨንቅ...

የማይጨንቀው ሲጨንቅ...
(በሳሙኤል አለሙ
.
በኩለ ቀንን አይባል
በኩለ ሌሊቱ አይባል
ሀብታም የውስኪ ፅዋውን ሲያጋጭ
ድሃ የቋጠረውን ዕንባውን ሲራጭ
"ተፈፀመ" ተብሎ ታይቶ ለሚጠፋው
ያፈጣል ከኩርሲው
ያፈጣል ከሶፋው
.
አንተስ ላይባሉት...
በኖረበት ሲያዝን
በኖረበት ሲደሰት መልሶ መላልሶ
ድራማው ህይወቱን አይቶ ጨርሶ
በድራማው ዓይኑ ቀልቶ ዓይኑን ያሻል
ይቀጥላልን ሲጠባበቅ ውሎ ያመሻል
።።።።።

@Samuelalemuu

1 month ago

ያንድ ምሽት ሀሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)

ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤

ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ ዘበት፤

የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሀውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሳይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥

የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-እንባየን ልሼ
ደረቴን ሰብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥እረፍት ሸመትሁኝ
ቁርጤን አወቅሁኝ ፤

ለካ ሰው ቢማር፥
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከእድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የእውቀት ፍጻሜ;:

@Samuelalemuu

1 month, 1 week ago

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።
ዒድ ሙባረክ !

@Samuelalemuu

3 months ago

ከሞተች ቆይቷል
[ ገብረክርስቶስ ደስታ ]

ከሞተች ቀይቷል
ብዙ ዘመን ሆኗል
ብዙ ነበር ጊዜው
ግን ፎቶግራፏ አለ
ደብዳቤዋም አለ
በጠጉሯ ጉንጉን የጠቀለለችው
ምን ቀን ቀጠሮ ነው
ቀን የቀን ጎደሎ
የቀን ጥቁር መጥፎ
አበባ ሄድኩ ይዤ
እዛ አበባ አልጠፋም
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው
ነፍሴን ነቀነቃት ገላዬን በተነው፡፡
ነፍሴን ነቀነቃት
እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው
ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው!
ለተረሳ ነገር
ምን ጊዜው ቢረዝም
የዚህ ዓለም ጣጣ እያንከራተተኝ
የዚህ ዓለም ስቃይ እየቦረቦረኝ
ሲጨንቀኝ ሰውነት
ፍቅሬ ይሁን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት
ህይወት ነዶ ጠፍቶ
ሞት ፍሙን ሲያዳፍን
ያን ጨለማ ጓዳ ሄጄ ልተኛበት።

ይመስላል ዘላለም
ሰው ሰውን ሲወዱት
አይኑን አይኑን ሲያዩት
ይመስላል ዘላለም
አድማስ አልፎ አድማስ
ምጥቀት አልፎ ምጥቀት
ጠፈር አልፎ ጠፈር
ይመስላል ዘላለም
ሰው ባካል የሚኖር
ድሮ አውቀዋለው
ተረድቼዋለው
ፀሀይ ጥቁር ስትሆን
ቀን ቀንን ሲያጠላው
ሌት ሌትን ሲሸፍን
እረስቸው እንደሁ፡፡
እንዴት አንቺን ልርሳ
ነፍሴ አብሯት የሚኖር
የፍቅርሽ ጠባሳ፡፡
˝ፍቅርሽና ፍቅሬ የተወሳሰበው
አልበጠስ አለኝ ብስበው ባስበው˝
ማን ነበር ማ ነበር
ማ ነበር እንደዚህ ብሎ የገጠመው?

ይመስላል ዘላለም
አንቺ የኔ እመቤት ብያት የነበረ
አንተ የኔ ጌታ
አንተ የኔ ጌታ ብላኝ የነበረ
አንቺ የኔ እመቤት

ይመስላል ዘላለም፡፡
እንባዬ ወረደ ልቤን አቃጠለው
ልቤ ተነደለ
የሰቀቀን እሳት አካሌን ሲያነደው
ደሜ ገነፈለ
የደም ጥቁር እንባ
ቆዳ የሚያሳስር መንፈስ የሚያባባ
አለቀሰቅሳትም
ቡዳ እሷን አይበላም
ቢስ አሷን አያይም
አልቀሰቅሳትም በነብሴ ተጉዤ እጠይቃታለው
አውቃለው አውቃለው
በመቃብሯ ውስጥ
ጢስ እንጨት ይጨሳል
ከርቤ ብርጉድ እጣን
መቃብሯ ሽቱ
ጣፋጭ መኣዛ አለው አጥንቷ ታቦቱ
መቅደስ ቤተልሄም ቅኔ ማህሌቷ
እጣኑ ይጨሳል ይታጠናል ቤቷ
ፍቅሬ ሙሽራዬ
እመቤቴ ፍቅሬ ያለም አለኝታዬ
አቴቴዋ ይታጠናል
ልዩ መዓዛ አላት
በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ፤
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ፤
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ
ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ፤
ፍቅሬ አለኝታዬፍቅሬ አለኝታዬ
እንባዬ ወረደ…………………..
እንግዲህ ይበቃል ይቅር ይቅር ይብቃ
በድካም መድከም ባሳብ ሀሳብ አለ
ባዘን………….. ሃዘን……….ሃዘን

@Samuelalemuu

3 months, 3 weeks ago
4 months ago
የወረት ዕንባ

የወረት ዕንባ
(ሳሙኤል አለሙ)
°
°
ጭለማው እንደ ነበረ
ጥልቁም እንደ ነበረ
እንደነበረ ሳይነጣጠል
አይንህ ካይኔ
አይርቁም ያን ያህል
°
ይሁን አለ ሆነ።
መለየት ኳተነ።
°
ከወንዙ እንደ--- ራቀ
ካይንህ እንደ --- ራቀ
እንደ ራቀ ዕንባየ ሲያውቀው
ሳላይህ ሳታየኝ
ብፁዓን ሆኖ ማልቀስ ናፈቀው
°
ይሁን ብሎ አረፈ።
ዕንባየም ነጠፈ።

@Samuelalemuu

4 months, 3 weeks ago

ስት---ሄጂ ንገሪኝ...!
°
°
ኩኩሉ...
ሻርቡን ተከናንበሽ
ኩኩሉ...
ቢጃማውን ለብሰሽ
ኩኩሉ...
ዘንቢሉን ሸከፍሽው
ነግቷልን ስጠብቅ
ጠረንሽን ገበያ ወሰድሽው።
°
°
የማይሸመተው ፥ ከመደብ የሌለው
የኔ'ኳ የምለው ፥ አንዷን ያቺን ጠረን
ከስንቅ ሳላኖረው ፥ ከጦሙ አዋለኝ
ስምሽ ብቻ ቀረኝ።
ፎቶሽ ብቻ ቀረኝ።
°
°
ጓሮ አይል
ጓዳ አይል
ይጠይቃል ባሌለሽበት
ይጣራል እስካለሽበት
"እ" ---ና---ቴ!
"እ" ---ና---ቴ!
"እ" ----ሩቅ ሆንሽ ለቤቴ
°
°
ኩኩሉ...
መንገዱ--- እንደ ልጅነቴ መስሎኝ
ኩኩሉ...
መሄዱ---እንደ ልጅነቴ መስሎኝ
ኩኩሉ...
መምጣቱ ---እንደ ልጅነቴ መስሎኝ
ካሁን አሁን ስጠብቅሽ
አሁን ካሁን ጋራ ተደባለቀብኝ
እንዴት ልለየው ነው...
መምጣት ከመቅረት ጋ ፤ ሲመሳሰለብኝ
°
°
ካሁን አሁን ፤ እያሉ የሚሸነግሉትን
ድንገት እየሄዱ ፤ ወጥተው የሚቀሩትን
ለምዶብኛል'ና ፤ እጠብቃለው ያደኩበትን።

ሳሙኤል አለሙ

@Samuelalemuu

5 months, 3 weeks ago

ጥለሽኝ ልውደቅ
ከክብሬ ልልቀቅ
ደብዛዬ ይጥፋ
ደግሜ አልጽደቅ።
ጀግና ይበሉሽ
ይበሉኝ ሰነፍ
ከድል እኩል ነው ባንቺ መሸነፍ ።

@Samuelalemuu

By Hab Hd

6 months, 1 week ago

አለሁ እንደ ሾላው
(በእውቀቱ ስዩም)

በገዛ ጆሮና ፥ በገዛ አይኖችሽ ላይ
ሙሉ ስልጣን ያለሽ
ከቶ እንደምን አለሽ?

አለሁ እንደ ሾላው
እንደ ወፍ መነሻው
እንደ ወፍ መሸሻው
ጸሐይ እየሞቀ ከመተንፈስ በቀር፤ ሌላ እንደማይሻው፤

መኖር ብቻ ሲሆን ፥ የሰው ልጅ እቅዱ
በሲኦልም ቢኖርም፥ አይቀርም መልመዱ
እኔም ከመበላት፥ መብላት ይሻል ብየ’
‘ፍሪደም ‘ ቢርቀኝ፥ ፍሪዳየን ጥየ
ነጻነት ቢርበኝ፥ እየበላሁ እህል
አለሁ ይህን ያህል ፡ ፡

( ከ"የማለዳ ድባብ " የተወሰደ)

@Samuelalemuu 

6 months, 1 week ago

ሚበርዳቸው ይመስለኛል
ወንዙ ሀይቁ
ውቅያኖሱ
አራዊቱ ለምለም ዛፉ
በኔ በኩል በእቅፍሽ ካልታቀፉ።

ሚበርዳቸው ይመስለኛል
ታሪክና ትንቢታችን
አሁንና ትላንታችን
ጊዜ ስፍራ
ግራቀኙ ደስታው
ዋየይታው
መኖር መሞት ማግኘት ማጣት
ሚበርዳቸው ይመስለኛል
ካልነካሁሽ ካልነካሽኝ በፍቅር ጣት
ለምን?
በደምሽ ውስጥ
በደሜ ውስጥ ሁሉም ነገር አለው ቅንጣት።

ቅዝቃዜሽ፣ የኔ መብረድ
ሲተላለፍ ሲቆላለፍ
ከሚመጣው ከሚሄደው
ከሚወጣው ከሚወርደው
ነይ እቀፊኝ
ነይ ልቀፍሽ
ብሎ ብሎ እግዜራችን እንዳይበርደው።

ትንሽ መሻት
ጥቂት ናፍቆት አንጠልጥለው
ነፍስ አጠገብ ካልተገኙ
ቆፈን አለ እሳት አቅፈው እየተኙ።

[ ያዴል ትዕዛዙ ]

@Samuelalemuu

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago