የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 1 month, 3 weeks ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 7 months, 4 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 9 months, 4 weeks ago
[....ሞት እና ልጅነት°°°°]
°
እሷ....
በመራቅ....
በመተው.....
(በመሄድ )
አመነች፣
ሰጋር በቅሎ ጫነች፡፡
(ዳግም ላላገኛት....)
ወደ ማትመጣበት....
ወደ ማትዞርበት....
ወደ መራቅ ገዳም ....
ወደ መሸሽ ደብር.....
ወደ ሩቅ በረሀ....
ወደዚያ መ ነ ነ ች፣
ልጅነቴን ሆነች፡፡
°
(ደግሞ በዚህ በኩል...)
ጭራሽ ባልቀርባቸው....
ከሩቅ ብፈራቸው....
ባላናግራቸው....
ሰርክ ብሸሻቸው.....
(በዚያም አለ በዚህ ....)
ብሮጥ ብንደረደር --የማላመልጣቸው....፣
ከ`ሷ ውጭ ሴቶች----
ልክ እንደ ሞት ናቸው፡፡
°
አይገርምም ??
ልቤም ይሄን አውቆ....
ከመኖር ምስጢር ጋር ስለተናበበ፣
ወደ ሞቱ ይራመዳል---ልጅነቱን እያሰበ፡፡
[ በቃሉ ሹምዬ ]
ይድረሰ:- ለኩርፊያ
(ሳሙኤል አለሙ)
°
°
የሻማው ብርሃን ደብዝዞ
የንፋስ ሽውታ ጠረገው፤
አፋችኑ ቃላት አርግዞ
አምጦ መውለድ አቃተው፤
ዝም...ዝም...ዝም
ጭልም-ልም-ልም
ገዘፈ ድቅድቁ ጨለማው፤
ቃላችንን ሾተላይ ቀማው።
°
°
እንደ'ኔና እንደ እሷ
ጀምበሩ ሳይነጋ
መሰሎቻችን ጋ
አፋቸውን ሊያዘጋ
ጥድፍ-ድፍ-ድፍ...ሲል
ርብት-ብት-ብት...ሲል
ደርሶ አፋችንን ቆልፎበት።
ደጃፉ ላይ ፥ ስደርስበት።
°
°
ቀኝህን ለሚመታ
ግራውን ስጡት እንዳለው ጌታ
ሳትነፍገው የእግዜሩን ሰላምታ
እንደ ዲዳ ዝም ካለህ
ላፍታም... ላፍታም.... ሳታመንታ
ኩርፊያን <እንኳን ደስ አለህ!>
በልልኝ!
°
°
ይኸው እኔና እሷ
ሰርክ ኩርፍ ኩ-ርፍ-ርፍ
ሰርክ እቅፍ እ-ቅፍ-ቅፍ
ይኸው እኔና እሷ
እንደ ቄጤማው ፥ እንደ አውዳመቱ፤
ድንገት ካየኸው ፥ የኩርፊያን ፊቱ፤
ትላንቱ ለምልሞ ፥ ዛሬ ክስመቱ።
°
°
እንደ ጳጉሜ ሶስት ዕለቱ
ዕንባውን አዘነብነው።
የሩፋኤል ፀበል አይደል
ክፋቱን አያድነው።
ከጫጫታው አልፈን
ነጎድጓዱን አክለነው።
ጭቅጭቁን አድ'ምጦ
በዜማ አቀነቀነው።
°
°
ተወው በክረምቱ ፥ ይርገጥ ዳንኪራ
ተወው በዕንባችን ፥ ይስከር ያሽካካ
በፀደዩ ብርሃን ፥ እንደምንፈካ
ዘንግቶታናልና!
°
°
የዛሬዋን ዕድል
ከቆጠረው ከድል
ትርኢት ያዘጋጅ
እንግዳም ይጥራ ፥ ድግሱንም ይደግሰው
እንደ ንጉስ አይዙር ፥ ግማሽ ቀኑን የሚነግሰው
ተወው!
_ ከሚላ ከሚላ_
''ከሚላ ከሚላ
ከሚላ ከሚላ'' ሙዚቃ ነው ብዬሽ ወይን ነው ብለሽኝ
ቀኑ ጨለም ሲል አንዴ ቺርስ ብለሽ አንገቴን ስመሽኝ
አንገቴን አንገቴን
አንገቴን አንገቴን
በግራዬ በኩል ቀጭን የደሜን ስር
ከፍ እንዳለ ቀረ ልቤም እንደ_ንስር
ካልጠፋ ሰውነት
ስለምን ፈልጎ አንገት ይስማል ሰው
ደም አይደለም እንዴ የሚመላለሰው ?
ደም አይደለም እንዴ ከልብ የሚደርሰው ?
''ከሚላ ከሚላ
ከሚላ ከሚላ''
ዘፈን እኮ ነበር
ሙዚቃ እኮ ነበር ስንቱን ያበጠ ልብ ምርኮ ያደረገው
የናፋቂን አንጀት እየጨመቀቀ ማን ወይን አደረገው ?
እግዚኦ ጭካኔ
አቤት የሰው በደል መገን የሰው ቅጣት
ከባሩድ ያንሳል ወይ
ወይን እና ሙዚቃን አንድ ላይ መጠጣት ?
ከዚያ ቀን በኋላ
ከንፈር ቀማሽ ደሜ
ግራ ገብቶት ቢቆይ
ከሚላ ከሚላ
ወይን እና ሙዚቃን እያቀነቀነ
እንኳን የደሜ ስር ድምፄ መነመነ
ይመንምን ይመንምን
ይመንምን እንደ_ሰው ይሳሳ እንደ_ገላ
ምን ልናገርበት
ምን ቃል አልኝ እና ከዛ ቀን በኋላ
ምን ቃል አለኝ እና
ምን ወግ አለኝ እና የሚለኝ ቅር ቅር
ድፍረቴ ነው እንጅ
ይህ ግጥም ራሱ ተጀምሮ ይቅር።
[ አማረ ዘውዱ ]
ከሩቅ ያሳውዳል
ስሟ የመቅደስ ዕጣን
ተብረከረከላት
የኔው ድኩም ሰይጣን
ተንዘፈዘፈላት
እሷ የቄስ ጥምጥም
መፃበሏ እንጂ
መፋቀሯ አይገጥም
ምን ይሉት ታምር ነው
ከሰይጣን መቆንጀት
ስምሽን ለሚጠሩ
ኡኡታን ማበጀት
ምን ይሉት ገቢር ነው
በምን አጠመቅሽኝ
አብም ወልድም ሳሉ
ባንቺ ስም ወለድሽኝ
ከየት አመጣሽው
እንደ ሄሮድስ መክፋት
በነካሽኝ ቁጥር
የጣትሽ አሻራ ስጋዬን ሲልፋት
በተጠራሽ ቁጥር
ተቃጠልኩ እያልኩኝ
ሁሌ ስብከነከን
ከየት ነው የተማርሽው
እንደ አይሁድ መጨከን
አበድሪኝ ስምሽን
"ወየሁ" ልበልበት
አንድም እንደ አቤት
አንድም እንደ ጩኸት
[ ቶማስ ትግስቱ ]
"ወርዉሬ መታሁት ጥላሽን በእምቧይ፣
ደሞ ባንች በኔ ከልካይ አለን ወይ።
ወደ አንች ስመጣ ተመለስ የሚለኝ፣
ማን ይሆን ወገኛዉ የሚከለክለኝ።
ወንዞ አይፈሬዉ ቀሚስ የተሸነሸነዉ፣
ትፍትፉ መቀነት ወገቧን የዞረዉ፣
ልቤን በጉንፏ አዉሎ አሳደረዉ።
እንኳን ዛጎል ማርዳዉ አምባሩም መስቀሉ፣
ሽርብት አደሬ ማተብሽ ድንግሉ፣
አንችን ለማሳመር መች አነሰ ባሉ።"
የዘገሊላ : Yehunie Belay
ግጥም: አቤል መልካሙ
ዜማ: አስቻለው አየለ
ሙዚቃ ቅንብር: ዳዊት ጥላሁን
[ ድረስ ጋሹ ]
ሞት ሆይ ገደምዳሜ ፥
ተሸነፍክ በዕድሜ ?
ሞት ሆይ ቀበጥባጣው ፥
መርዝህን ምን ጠጣው?
ሞት ሆይ ጥልመያኮስ ፥
ማን ጣለህ ከፈረስ?
ሞት ሆይ ጽልማሞቱ፥
ምን ጣለብህ ብርቱ?
እመጣለሁ ብለህ ...
እኔን ለሀሳብ ጥለህ...
ጭልጥ አልክ በዚያው ፥
ሰከን አለ ጥርጊያው ፥
ዛሬም ልለምንህ...
ተጫነኝ ዓለሙ ፥ አለበሰኝ ደኮ ፣
ብቅ በል እባክህ፥
ራሴን ከገደልኩ ፥ ሰነበትኩኝ'ኮ።
አንተ እንባዬ ምረጥ
ልግለጥህ?
ልዋጥህ?
ላፍንህ?
ልልቀቅህ?
ላፍስስህ
ላምቅህ?
ምን ላርግህ? ምከረኝ
ምንድነህ? ንገረኝ
እህል ትሆን ጠፊ?
ወይስ ሽል ነህ ገፊ?
በጊዜ ልወቅህ...
ላቅርብ ወይ ላርቅህ...
አጫጅ ነህ አራሚ?
ተጓዥ ነህ ከራሚ?
አላፊ ነህ ቋሚ?
ምንድነህ?
ምን ላርግህ?
ላግድህ?
ላውርድህ?
ጋርጄ ልካድምህ?
አውርጄ ልካድህ?
ቢያፍኑህ ቀሪ ነህ?
ቢለቁህ ኗሪ ነህ?
እንባዬ ምን ላድርግህ?
ላስርግህ?
ልጥረግህ?
እንዳ'ይን እንዳ'ፍንጫ
ቋሚ መገለጫ
መታወቂያ መልኬ ፡ ሆነህ ትኖራለህ?
ወይስ ላ'ንዴ ወርደህ፡ በዚያው ትቀራለህ?
አንተ እንባዬ ምረጥ
ላብስህ?
ላልብስህ?
ወይስ እንዳላየ፡
ከኔ የወጣ ሁሉ፡
የኔ አይደለም ብዬ
ልተውህ እንባዬ?
ወይስ ልገላገል?
እውነቱን ልናገር?
እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ
እያልኩኝ ከማበል
አላውቅህም ልበል?
By #red_8
የሆነ ብርሃን
ደጇ ላይ መራን
ቤቷ ከተምን
እኛም እንደሷ
ፈገግታ አተምን
ጅስሟን ዘለቅነው
ነብሷ ታየችን
ሰው ሆና መታ
ሰው አረገችን
ተስገበገብን
ተስለመለምን
ብራ ነው ፊቷ
አይመሽ አይዳምን
ዛቅን ወሰድን
ጠግበን ተራብን
እፍፍፍፍ ትበላ
ነብስ ትዝራብን
በቤት በደጇ
ታእምር ሞልቷል
ዘርሰብ ጠርቶ
ቀን ይገዝታል
የነብስ ፍታት
የልብ ግዝት
ሽንጧን ወድራ
አይዋት ስትዝት
አስደነገጠች
አስፈራራችን
ለማንደርስባት
አንጠራራችን
"አጃኢብ አቦ !!
ይውረገረጋል ገላ ተስቦ "
ተውቦ መላኣክ ለዝቦ ሰይጣን
አደነጋግሮ አቅል አሳጣን
ቅድሚያ ካፎቱ ጎራዴ ስለን
የለሊት ቅዠት የቀን አራራ
ጠልፎ ሳይጥለን
ትፍቀድ ትራራ
[ አዲብ መሃመድ ]
መጭውን ጠበቅሁት
(በእውቀቱ ስዩም)
'ከማዶ እሚመጣው፥ ዘመድ ነው እንግዳ
ከላይ የተለጋው፥ ኳስ ነው ወይስ ናዳ?'
ብየ መች ጠየቅሁኝ፤?
መጭውን ጠበቅሁት...
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብየ፤ ጸሀይ እየሞቅሁኝ፥
መከራም አላጣም፥ ተድላም አልጎደለኝ
ደንታ ነው የሌለኝ።
ባካል በስሜትም፥ ታሞ ላገገመ
ወድቆ ለተነሳ ፥ እየደጋገመ፤
ከገዛ ጉድጓዱ ፥አጽሙን ለሚለቅም
ሞትም ብርቅ አይደለም፥ ትንሳኤም አይደንቅም ::
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 1 month, 3 weeks ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 7 months, 4 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 9 months, 4 weeks ago