? Big Offer ? Buy Gagan Sir Books : https://linktr.ee/gaganpratapbook ✅
Maths By Gagan Pratap is a channel which helps you to prepare for all gov. exams.
Gagan Pratap Sir is providing high quality education on Careerwill App for various competitive exams
200 Crore Cash Prize Winner : Fantasy Cricket Expert : Cricket Trader : 32 Wheels : YouTuber / Content Creator : On a Mission
Instagram Channel: https://ig.me/j/AbbbdNImVuSuiesY/
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Sports Analyst | Entrepreneur
Verified Facebook
https://www.facebook.com/ranbirranjanroy
Verified Twitter
https://twitter.com/vsgranbir?t=p1zOMDHi7Ceu0lFPheP9jg&s=09
Verified Instagram
https://instagram.com/vsgranbir
https://linktr.ee/vsgranbir7
Last updated 2 months, 2 weeks ago
[…ማኀበራዊ ዝሙት አዳሪነት…]
—መግቢያ—
የአንዳችን ትራጀዲ ለአንዳችን ኮሜዲ ነው። አንተ ትስቅ ዘንድ እኔ ማልቀስ አለብኝ። የዘለለት ስቃይኽና መከራኽ ለአንዳንዶች ስሙ «ፖለቲካ» ነው —ይዝናኑበታል፣ ይተነትኑታል፣ ይነግዱታል፣ ይበሉበታል። መጣላትም ለትርፍ ነው፣ መታረቅም ለትርፍ ነው። እንባም ጥበብ ነው፣ ኀዘንም ሒሳብ ነው።
መንገዱ ይለያይ ይኾናል እንጂ ማኀበራዊ ዝሙት አዳሪነት ውስጥ ነን። አንዳንዱ ገላውን ይሸጣል፣ አንዳንዱ ዕውቀቱን ይሸጣል፣ አንዳንዱ ክፋቱን ይሸጣል። አንዳንዱ በክርስቶስ ስም ይነግዳል፣ አንዳንዱ በሰይጣን ስም ያተርፋል። አንዳንዱ መናፍቃን እያለ ይበለጽጋል፣ አንዳንዱ አሕዛብ እያለ ይከበራል። እምነትና ተስፋ በገበያው ዋጋ ይመነዘራሉ … ፍቅር ግን አልፎበታልና ወደዚያ ይጣላል።
— አንድ ታሪክ እዚኽጋ…—
እናት ልጇ የት ይግባ የት ሳይታወቅ ድንገት በወጣበት ጠፍቶ ይቀራል። ወሬ ስታፈላልግ መንግሥት አሥሮታል ትባላለች። የቀበሌው ሊቀመንበር ጋር አቤት ትላለች። ቀበቶውን እያላላ «ያው መቼም አሠራሩን ታውቂዋለሽ» አላት። ደነገጠች። «መፍትሔው የወረዳው ሊቀመንበር ጋ ነው፣ እርሱ ጋር መቅረብ ከፈለግሽ ለአልጋ ተስማሚኝ» አላት —አማራጭ አልነበራትም። ከነድንጋጤዋ ተስማማች።
የወረዳው ሊቀመንበር ጋ ቀረበች። እርሱም እንደ በፊቱ «የአውራጃው ገዢ ጋ እንዳደርስሽ አብረን እንተኛ» አላት። ድንጋጤዋ አኹንም አለ። ቢኾንም ጥቂት ለምዳዋለች።
የአውራጃው ገዢ ጋ ቀረበች። ተኛችው። እርሱ ወደ ሀገረ-ገዢው ላካት —እዚያም ተኛች። ልጇን ፍለጋ በየቦታው መውደቅን ሥራ አለችው —በቃ ለመደችው። ተዋረዱን እያለች እያለች ንጉሡ ጋር ደረሰች። ንጉሡ ፊት ቀርባ እጅ እንደነሣች ምንም ሳይላት ልብሷን ማውለቅ ጀመረች —እንደቀደሙት መስሏት ። በሀገሩ እንዲህ ያለ ግፍ እንዳለ ያልጠረጠረው ደግ ንጉሥ ተደናግጦ
«ምን ኾነሻል? ልብስሽን ለምን ታወልቂያለሽ?» ሲላት እዚያው ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች።
«ምነው?»
«ንጉሥ ሆይ ምነው አልወደዱኝም? ልጄን አስፈታ ዘንድ ምኔን ልስጥዎት? እባክዎት»
— መውጪያ —
አስገድዶ መድፈር ግዴታ እጅ መያዝ፣ አንገት ማነቅ፣ በኃይል ጭን መክፈት ብቻ አይደለም። እንዲኽ በአቅም ማጣት የተስማማናቸው፣ ሳንወድ በግድ «እሺ» ብለን ከአልጋ የወደቅንላቸው፣ ከአልጋ የጣልንባቸው፣ የቅድስና ስም የሰጠናቸው ኃጢአቶች አሉን። መቃወም፣ ማፍረስ ፣ demythologize ማድረግ ያለብን እርም አለ —ማኀበራዊ ዝሙት አዳሪነት
“ማንም ስለ እናንተ ግድ የለውም” | ጥቂት የግል ምልከታ
.
ሼክስፒር «ዓለም የቴአትር መድረክ ናት፣ ተዋናዮቹም እኛው ነን» ያለው “እኛን” ሳያይ መኾኑ ይገርማል። በስመአብ —አደገኛ ቴአትረኞች ነን። የተካንን አስመሳዮች፣ “ቪሊያን” ካራክተሮች ነን። በተለይ እንደ ልብ መተጣጠፍ፣ መለጠጥ፣ መለወጥ፣ መቀየጥ የሚቻልበት የማኀበራዊ ሚዲያ ሜዳ ይኽን አመሳሶነታችንን ጎልቶ ያወጣዋል። ማናችንም ከዚህ ፍርድ አንተርፍም።
ትንሽ ጨከን ብለን መነጋገር ካለብን በተለይ ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ ወይም በሌላ ምክንያት ሲሞቱ የምናሳየው ባሕርይ በአጥንታችን ውስጥ ያለውን ዘግናኝነት ያጋልጣል። ያመመን እናስመስላለን እንጂ ያን ያሕልም አያመንም። ሰውን በአፍጢሙ ለመድፋት በምላሱና በግብሩ የተሰለፈ ኹሉ ልክ «እገሌ ሞተ …» ሲባል የተጠና ሙሾ አውራጅ ኾኖ ብቅ ይላል። ትንሽ ወቀሳ ካደረግኹት ይቅርታ!
የኾነ ሰው ሲሞት እየጠበቁ “ጓደኛዬ አልደረስኩልኽም/ሽም …” የሚሉ፣ የተላላኩትን መልዕክት የሚለጥፉ፣ በድንገተኛ ኀዘን የደቀቁ የሚመስሉ ትዕንግርቶች እዚኽም እዚያም ብቅ ብቅ ይላሉ። ይኽ የሚያሳየው ቀሽም ጓደኛ መኾናቸውን መኾኑ ግን አይገለጥላቸውም። “እናውራ…”፣ “በሕይወት እያለን እንዋደድ …”፣ “ሲከፋችኹ አለኹላችኹ አውሩኝ… ” ምናምን ምናምን የሚል የተሰላ ሽሙጥ መሳይ እዝነታቸውን ለአደባባይ ያበቃሉ።
እነዚኽ ሰዎች ኀዘናቸው ለይምሰል መኾኑን ለማወቅ ጎበዝ ታዛቢ መኾን አያስፈልግም። ድርጊታቸውን ብቻ ማየት በቂ ነው። እነዚኹ ሰዎች በነጋታው ኹሉን ነገር ረስተው በሁካታና ቱማታ፣ በሳቅና ቀልድ፣ በብሽሽቅና በስድድብ ውስጥ ተጠምደው ይታያሉ። ከመቼው ከእንባ ወደ ፌዝ እንደተከረበቱ እንጃ!
የግል ሐሳቤ ትርጉም ካለው ይኽንን እላለኹ!
ለሰው አደገኛ ተስፋ አትስጡ! ላትኖሩ “አለኹልኽ” አትበሉ። ላታዳምጡ “ንገረኝ” አትበሉ! መሸከም የማትችሉትን “እንሸከማለን” አትበሉ! የማንንም ሕመም የማስታመም ግዴታም የለባችኹም። ከማስመሰል “ጆሮ ዳባ” ማለት ሰውን ያተርፋል።
ለሰው “ያልፋል!” ብቻ ሳይኾን “ላያልፍ ይችላል፣ ባያልፍም ግን መኖር ትችላለኽ” በሉ። ለደከማቸው እውነቱን ንገሯቸው! አንዳንዴ የሠሚም ጆሮ ይዝላል … አንዳንዴ ማንም ላይሰማኽ ይችላል። በጣም የቅርብ ጓደኛኽ ቀርቶ እናትህ እንኳ ስላንተ ግድ ላይሰጣት ይችላል። ሕይወት ይኽንንም ችሎ መኖር ነው። በቃ እንዲኽም ከባድ ነው።
ኹሉም ነገር በንግግር አይፈታም። አንዳንዱ ችግር አንተ ጋር ብቻ የሚቀር ነው። እናትኽ፣ አባትኽ፣ ወንድምኽ፣ ጓደኛኽ፣ ፍቅረኛኽ የማይራመዱልህ መንገድ ሊኖር ይችላል። ኹሉም በራሱ ዓለም ውስጥ የተጠመደ ነው። ለራሳችኹ ራሳችኹ ብቻ አዳኝ ኾናችኹ የምትቀሩበት ጊዜ አለ። ለብዙዎች ስታትስቲክስና የከርሞ ዜና ብቻ ናችኹ።
የአንድ ሰው ራስ ማጥፋት “የአንድ ሰው ጉዳይ” ሳይሆን ከሥር ያለውን መዋቅራዊ ችግር የሚያሳይ ትንሽዬ ምልክት (tip of the iceberg) ነው። የሰዎች ራስ ማጥፋት ጥላ (shadow) ነው። ጥላውን የጣለው ቅርጽ (shape) ላይ አተኩሩ። ሴተኛ አዳሪነት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ተስፋ ማጣት ኹሉ ጥላ ናቸው …ወደ አንድ ትልቅ ምስል ይጠቁማሉ። ኹሌ ነገሩን ዜናና ሰሞነኛ ወሬ ማድረግ ምንም አይፈይድም። በዚህ መንገድ ሊሞቱ ያሉ ተሰልፈዋል። ገና ለብዙዎች ተመሳሳይ እንባ ልናለቅስ ጊዜ እየጠበቅን ነው። ምክንያቱም ብዙ ፈሪዎች ለመሞት የመጨሻዋን ድፍረት በጽዋቸው ውስጥ እያጠራቀሙ ነው።
Dostoevsky በ “The Karamazov Brothers.” መጽሐፉ ላይ አንዲት መሥመር አለች…
“Adelaida Ivanovna muisov's action was similarly no Doubt, an echo of other people's Ideas”
ለቀደመው አረፈድን ካላችኹ ለሚቀጥሉት ድረሱላቸው። ከንግግር በላይ ግን ተግባሩ ላይ አተኩሩ። ሰው በስውር የነገራችኹን በሰው ፊት አትግለጡ። የመጣው ማዕበል ከ“ቴራፒ” ወይም ንግግር ይበልጣል። ብቻውን መኾንን ያልተማረ፣ ለብቻው ዋጥ አድርጎ መቻልን ያልሠለጠነ ሰው እንደ ምዕራባውያን በትንሽ ዱላ የሚሰበር፣ በትንሽ ወሬ የሚፈራርስ ሴንሰቲቭ ልፍስፍስ …ትውልድ ይፈጥራል። ይኽን መዋቅራዊ ችግር እስካልፈታን “አውሩኝ…” እያሉ የሰውን ሕመም ጥም ማርኪያ ማድረግ በቦሃ ላይ ቆረቆር ዓይነት ነገር ነው።
P.s:- ሳቃችሁን ከሰው ጋር አድርጉ ለቅሷችሁ ግን ከጸሎት ቦታችሁ አይለፍ!
———-
Sorry for the incoherence — T.P
. * . • . . : . • . * . . * . . • . . * . . • . . •. • . * . . • . . •. • . . * . . • . . • . • . . * . . • . • . . * አየሻቸው ክዋክብትን. . • ? . .
. • * . ለአንቺ ብለው የበሩትን • . . * . • . * . . •. . • * . . . • . • . . * . . • . . * • . • . • . . * . . • . . * • . • . • . . * . . • . . * • . • *. •
« …ፍቀድልኝ ላልቅስ…»
የተወለድኹ ቀን እናቴ
ጡቷን ሳታጠባ
ግቷን ሳታባባ
ሳታቅፈኝ አንድ አዳር
ጣለችኝ መንገድ ዳር
የተወለድኹ ቀን
ክዋክብት አልበሩ
መላ’ክት አልዘመሩ
ልሙጡን ሰማይ
አዝኜ እያየኹኝ
ደስታ ቃል ብቻ አንደኹ
አወቅኹኝ … ጨከንኹኝ
ወርሐ ጥቢ
ወርሐ መስከረም
ልጆች አበባ ሲኾኑ
እኔ ስኾን አረም
አወይ መረገም!
ልጆች ሥጦታ ናቸው
የጸሎት የስለት መልስ
የሆድ ፍሬ በ’ርግጥም
ግን ደግሞ ሥጦታ
በግድ አይሰጥም
ልጅን ለሰቀቀን
ልጅን ለመከራ
ባትፈጥርስ ጌታ ?
ኀዘን ሲኾን ለልጅ
የወላጆች ደስታ
ብቻ
ከዓመቱ አንድ ቀን
እቀድዳለኹ ልብሴን
በትናለኹ ትቢያ
የልደቴ ቀን ነው
የዚኽ መታሰቢያ
እናም አኹን ብቻ
ይኽቺን ቀን ብቻ
ላያሳድጉ ስለወለዱኝ
‘ባማራጭ እጦት ስለወደዱኝ
ዓመት ሙሉ ልቻል
ሳልነግር ልሸከም
እሺ በልና ግን
ዛሬን ብቻ ልድከም
እንደቻልኩት ልቻል
ወንድ ነኽ እንዳሉኝ
ወንድ ልኹን ከርሞ
መሳቅ ነው ወንድነት
ኀዘን ተሸክሞ
የልደቴ ቀን ነው…
ዛሬን ግን እንቢ አትበል
“እሺ” በል ይልቅስ
ትንሽ እንባ ላፍስስ
ትንሽ ብቻ ላልቅስ
ከበደ ሚካኤል ሥልጣኔን የተመለከቱ ዐራት መጻሕፍት አሏቸው። አንደኛው «ጃፓን እንዴት ሠለጠነች?» የሚል ነው። ለአንድ ትንሽ ልጅ ይሄን መጽሐፍ ሰጥቼው ሲመልስልኝ
«ወደድከው?» አልኹት።
«አዎ…»
«እስቲ ያነበብከውን አጠር አድርገኽ ንገረኝ?»
«ያው በአጭሩ ምቀኛ አትኹኑ ነው የሚለው»
..
የሚገባውን ካልሠራንበት አዲሱም ዓመት 365 ቀናት የቀሩት አሮጌ ዓመት ነው። በርቱ። አይዟችኹ።
.
እና ያው በአጭሩ «እንኳን አደረሣችኹ፣ መልካም ዐዲስ ዓመት» ለማለት ነው።
??
? Big Offer ? Buy Gagan Sir Books : https://linktr.ee/gaganpratapbook ✅
Maths By Gagan Pratap is a channel which helps you to prepare for all gov. exams.
Gagan Pratap Sir is providing high quality education on Careerwill App for various competitive exams
200 Crore Cash Prize Winner : Fantasy Cricket Expert : Cricket Trader : 32 Wheels : YouTuber / Content Creator : On a Mission
Instagram Channel: https://ig.me/j/AbbbdNImVuSuiesY/
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Sports Analyst | Entrepreneur
Verified Facebook
https://www.facebook.com/ranbirranjanroy
Verified Twitter
https://twitter.com/vsgranbir?t=p1zOMDHi7Ceu0lFPheP9jg&s=09
Verified Instagram
https://instagram.com/vsgranbir
https://linktr.ee/vsgranbir7
Last updated 2 months, 2 weeks ago