የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

Description
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago

5 days, 3 hours ago
5 days, 4 hours ago
[**#የኢትዮዽያ**](?q=%23%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8B%BD%E1%8B%AB) **ቲር ፈንድ ቢሮ ቤተክርስቲያን እና …

#የኢትዮዽያ ቲር ፈንድ ቢሮ ቤተክርስቲያን እና የማህበረሰብ ለዉጥ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ቦርድ አቋቋመ። በኢትዮዽያ የቦርዱ ሰብሳቢ የካዉንስሉ ተወካይ የሆኑት ፓስተር አሸብር ከተማ ሆነዉ ተመርጠዋል።

ከህዳር 3 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017ዓ/ም በኬኒያ በተካሄደዉ ስብሰባ የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ ጨምሮ አራት ተወካዮች በስብሰባዉ ተካፍለዋል።

በስብሰባዉ ከሯንዳ፣ቡርንዲ፣ከዲሞክራቲክ ሪፐፕሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ከደቡብ ሱዳን እና ኢትዮዽያን ጨምሮ ከስድስት ሀገራት የተወጣጡ ወደ 30 የሚሆኑ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ስብሰባዉ የትኩረት አቅጣጫዉን ያደረገዉ ቤተክርስቲያን ማህበረሰቡን መለወጥ እንደምትችል እና በሰላም፣ተስፋ በማደስ እነዚህን እና በመሳሰሉ ጉዳዮች የለዉጥ ሐዋሪያ ሆና ማገልገል እንደምትችል በዋነኝነት ተወያይተዋል። ከዉይይቱ ባሻገር የስልጠና ጊዜ እና በሌሎች ሀገራት የተሰሩ ስራዎች የግምገማ ጊዜ ተከናዉኗል።

በመጨረሻም በኢስት አፍሪካና በሴንትራል አፍሪካ ሪጅን ምርጫ ተካሂዶ የካዉንስሉ አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓስተር አሸብር ከተማ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዉ ተመርጠዉ ስብሰባዉ ተጠናቋል።

#ለበለጠ_መረጃ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/ ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732 ቴሌግራም፦ https://t.me/EGBCC tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

1 week, 1 day ago
3 months, 1 week ago

#የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤተክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ_ለጎፋ_ዞን_ማህበረሰብ_ከ15_ሚሊየን_ብር_በላይ_የሚተገበር_ፕሮጀክት_አዘጋጀች

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ወረዳ በኬንቶ ሻቻ ጎዚዴ ቀበሌ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች መልሶ ለማቋቋም የአስራ አምስት ሚሊዮኝ ብር ፕሮጀክት በመንደፍ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ደ/ር ዮናስ ይገዙ የተመራው የቤተክርስቲያኒቱ እና የደቡብ ምዕራብ ሲኖዶስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በስፍራው በመገኘት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተሰማቸው ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ አካባቢውን እና ህብረተሰቡን በቋሚነት መልሶ ለማቋቋም በሚሰራው ስራ ቤተክርስቲያኒቱ ከጎናቸው እንደምትቆምም አስታውቀዋል፡፡

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት በደረሰ አደጋ ሕይወታቸውን ካጡ ሰዎች ውጪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ሴቶች እና ሕጻናትን መልሶ ለማቋቋም ቤተክርስቲያኒቱ የአስራ አምስት ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት በመንደፍ በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደምትገባም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ደ/ር ዮናስ ይገዙ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን የፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ አብያ በበኩላቸው በደረሰው አደጋ የሚፈጠረውን ማህበራዊ ቀውስ ለመቀነስና ተጎጂዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም ቤተክርስቲያንቱ ፕሮጀክት ቀርፃ እንደሚትሰራም ገልጸዋል።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪይ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው አደጋው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እያደረገች ያለውን ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም ቤተክርስቲያኒቱ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች መልሶ ለማቋቋም በምትሰራው ፕሮጀክት ላይ ዞኑ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡
በደቡብ ክልል በጎፋ ዞን ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት ከ300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን በርካቶችም ጉዳት ደርሶባቸው በጤና ተቋም እስከአሁን እንደሚገኙም ይታወቃል።
መረጃዉን ከቤተክርስቲያኒቱ ፅ/ቤት አገኘነዉ።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://t.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago