Solcu Gazete Telegram kanalı.
Reklam ve iletişim için: @iletisimads
Last updated 2 weeks ago
🔥Canlı ve Maç Öncesi Tahminler 🔥
⚽️ FUTBOL 🏀 BASKETBOL 🏀 NBA
🎮 FİFA-ESPORTS 📉 Excel tahminleri
Last updated 18 hours ago
ግዴታው: ሀብታም መሆን ወይስ ራስን መቻል?😉
ለትብብራችሁ እናመሰግናለን፣ ተገኝቷል!
ሸማቾች/ገዢዎች/ ብር ሳይዙና ለመግዛት ሳይወስኑ ገበያ ወጥተው ጠይቀው በምን ሊያስቀይሱ(ሊፈረግጡ) ይችላሉ?
(ነጋዴዎች ስለከፋቸው ለማቻቻል የተዘጋጀ😁
👟 ገበያ አሁን ነው የወጣሁት፣ ጠይቄ ልምጣ፣ ዞር ዞር ብዬ ልይ
(ይሄኔ እግራቸው እስኪቀጥን ዞረዋል😉
🧣ልክክ ብሎላቸው ይዞኛል
(ኧረ ሌላ የላችሁም🙄
🧦 በገመቱት ዋጋ ሲሰጣቸው
(ባንክ ሄጄ ብር ይዤ ልምጣ😂፣ ከዛ ብስ
💼 ደንበኛዬ ጋር ልግዛ ብዬ ነው እንጂ የተሻለ አግኝቻለሁ
(አንዴም ገዝተው አያውቁም እኮ😋
🧵ተደራድረው ጨርሰው ሌላ ሰው ጠርተው በቃ ይቅር
(ሲፈረግጡ
🧶 የሚፈልጉት ከለር ሲሰጣቸው እንዲህ አይነት የለህም
(ፋብሪካ የማያውቀው ከለር ምርጫ😁
.
.
.
መነሻ ሀሳብ ከኮሜንት የተወሰደ
እስቲ እናንተም ጨምሩበት?
በጊዜ መሸሽ ማሸነፍ ነው!
የገረመኝን ትዝብት ላጋራችሁ
(በረከት በላይነህ ስለ ወላይታ ህዝብ ከሰጠው ምስክርነት ጋር የሚጣጣም)
በጠዋቱ በቅርቡ በግፍ የተገደለ አንድ ወንድማችን ችሎት ለመካፈል ተደራቢ ሆኜ ሄጄ ነበር። ለምስክር ከቀረቡ ሁለት የፖሊስ አባላት የሰማሁት ምስክርነት ስለገረመኝ ላጋራችሁ አመጣሁት።
ክስተቱ ከተከሰተ 6 ወር ሆነው። ገዳዮቹ ሟችን ከአዲስአበባ ሀዋሳ ኮንትራት ያዙ። አላማቸው ዝርፍያ ስለነበር አዳማ ፈጣን መንገድ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው፣ ሬሳውን በዘግናኝ ሁኔታ ጥለው መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ።
የዛሬ ፖሊሶች ከወላይታ ሶድ ድረስ ለመመስከር የመጡት ከዚህ ቡኋላ የተከሰተውን ክስተት ነው(ሀሳቡ ሲጨመቅ)
ገዳይ መኪናውን ከወሰደ ቡኋላ አባቱ ዘንድ ወላይታ ሶዶ ወስዶ ያስቀምጣል። መኪናው የተቀመጠባቸው አባት ለልጃቸው ሶስት ቀን በተደጋጋሚ ቢደውሉ ስልክ አላነሳም። ይሄኔ ወደ ፖሊስ ዘንድ ሄዱ . . .
"እኔ ልጄን አላሳደኩትም። ከኔ ጋር አላደገም። አሁን ያለበትን ተጨባጭ ባህሪ አላውቅም። አንድ መኪና ባለሙያ ይዤ እመጣለሁ ብሎ አስቀምጦ ሄዷል። ስደውልለት አያነሳም። መኪናው የራሱ ከሆነ አመሳክራችሁ ትሰጡታላችሁ። መኪናው ለጊዜው ፖሊስ ጣቢያ ይቀመጥ" ለፖሊስ አመለከቱ
ገዳይ የመኪናውን ቁልፍ የቤቱ መግቢያ ላይ አንጠልጥሎ ነበር። ፖሊስም ጉዳዩ እስኪጣራ መኪናውን ተረክቦ ጣቢያ ወስዶ አስቀመጠ።
አባት ማለት እኚህ ናቸው። ለእውነት የቆሙ።
(ለመኪና ስርቆት የሰዎችን ህይወት ለሚቀጥፉ ጥሩ መቀጣጫ የሆነ ቅጣት ያገኛቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ❤
ካወጉኝ እንኩ?
አንድ ሰውዬ ነበር፣ መስጠት አይወድም። መቀበል እንጂ መስጠት ይጠየፋል። የንፉግነት ጥግ ነበር።
በአንድ አጋጣሚ ወደ ጉድጓድ(ቱቦ) ውስጥ ይወድቃል። አላህ የሰው እጅ ላይ ጣለው። ሰዎች ሲመለከቱ ጉድጓድ ውስጥ ወድቋል።
ለምን አናወጣውም ብለው በሰብአዊነት ተረባረቡ (እንደ ንፉግነቱ አይገባውም ነበር?)።
"እጅህን አምጣ" አሉት፣ መስጠት የሚጠየፈው ግለሰብ "አምጣ" ጎላችበትና ፣ ዝም አለ?።
ባህሪውን የሚያውቅ ውስጠ አዋቂ ፦ "ኧረ ይሄን ሰውዬ እጅህን አምጣ አትበሉት፣ ይልቅ እንካ በሉት" አላቸው
ሰዎቹም እንደተባሉ "እንካ" አሉት?። ከአንድ አንድ እጁን ዘረጋና ከጉድጓድ አወጡት? ይባላል።
አንዳዶቻችን "አምጡ፣ አምጣ፣ አምጪ" ስንባል ደማችን ቅዝቅዝ ይላል። በተቃራኒው "እንካ፣ እንኩ፣ እንኪ" ስንባል ሁለመናችን ይነቃነቃል።
አንድ የማውቀው ግለሰብ ሰው ሲጠራ "እንካ" ብሎ ነበር። ማንም ችላ ብሎት የሚያውቅ አይመስለኝም?
ስናያይዘው፦ ወንድማችን Mohammedawel Hagos በጦርነቱ ሳቢያ ብዙ መገፋት እንደደረሰበት እዚሁ አውግቶናል። ተምሯል፣ አስተምሯል። አሁን Phd እየሰራ ነው። በአንትሮፖሎጂ ምሁር ነው።
እንደ እውነቱ ከሆነ ሀሳቡን ለማሳካት 100ሺ ብር ፈንድ ፍለጋ Bejai Nerash Naiker ላይ መወዳደሩ ቆራጥነቱን ያሳያል። ሀሳቡ ግን በቀላሉ የሚሰራ አይመስልም። ሁላችንም ብንረባረብ ቢያንስ መስመር እናሲዘዋለን በአላህ ፈቃድ።
የመረጠው ዘርፍ ከትምህርት ዝግጅቱ ጋር ተስማሚ ስለሆነ ምርምሩንም እንዲገፋበት ምክንያት ይሆነዋል።
ከኡማለዎች ጋር ቅርብ መመካከር እያደረገ ከሰራው ዘርፉ ያልተነካ እምቅ ዘርፍ ነው። ብዙ መራመድ ይችላል ብዬ አስባለሁ። ስጡኝ አላለም፣ ወዳጆቹ ናቸው እንስጥህ ብለው ዘመቻ የከፈተቱት።
እስቲ ዛሬን ጁሙዓ ለሙሀመድ እንካ እንበለው❤
MOHAMMEDAWEL HAGOS
CBE 1000235604365
Mobile +251912995755
100 ወዳጆች 1000 ብር እንካ የሚሉት ቢገኙ። በቀላሉ 100 ሺ ሰጠን ማለት ነው።
እኔ ጀምሬዋለሁ፣ ተከተሉኝ!
Solcu Gazete Telegram kanalı.
Reklam ve iletişim için: @iletisimads
Last updated 2 weeks ago
🔥Canlı ve Maç Öncesi Tahminler 🔥
⚽️ FUTBOL 🏀 BASKETBOL 🏀 NBA
🎮 FİFA-ESPORTS 📉 Excel tahminleri
Last updated 18 hours ago