Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

HOME || ቤት 🏚

Description
Feel at Home!

@yonis_home_bot
Advertising
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 2 days, 12 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 days, 20 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago

2 weeks, 1 day ago

እንዴት ናችሁ ቤተሰብ? በዓል እንዴት አለፈ?

ምን እንጨምር ወይ እንቀንስ? ምን ይስተካከል?

Let me know what you think via @yonis_home_bot

🖤

2 weeks, 1 day ago

መልካም በዓል!

በየዕለቱ የትንሳኤውን ምስጢር እና ኃይል ለመረዳት እንትጋ!

🖤

2 weeks, 5 days ago

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለመንግሥቱ ኃ/ማርያም እንዳሸበሸበው ምንም ብታጠፉ የሚያሸበሽብላችሁ ታማኝ ጓደኛ ይስጣችሁ!

መልካም ቀን!
በላባችሁ ለምታድሩ ደግሞ መልካም የላብ አደሮች ቀን!

😅

2 months, 3 weeks ago

Let's just hope we will meet again, my lovely people!

💛🌼

3 months ago

ዛሬ እሁድ ነው!

በጠዋት ተነሱ፣ ሙቅ ሻወር ውሰዱ፣ ቀለል ያለ ቁርስ ብሉ [Preferably ሽሮ ፍትፍት for your hangover 😅 ጁስ ጠጡ ስትባሉ አትሰሙ መቼስ]፣ በእጣን የታጀበ ቡና እየጠጣችሁ የዳዊት ቸርነትን "ጽዮን" ስሙ፣ ከዚያ ቤተክርስቲያን ሂዱ።

አንቂያችሁ ዮናታን ነኝ ከሐዋሳ ጊዜያዊ የስርጭት ጣቢያ። ደስ የሚል ቀን አሳልፉ!
💙

3 months ago

[ A Hymn About Hymn 🎶 ]

እሱ
ንጉሡ
ዝምታ ቢሆንም ፥ አንዳንዴ ምላሹ
ቅኔ ነው ጠረኑ ፥ ግጥም ነው ትንፋሹ
ሲሰባበር ልቤ ፥ ስከፋበት ልጁ
ዳስሶ ሚያፅናናበት ፥ ሙዚቃ ነው እጁ!

4 months, 2 weeks ago

ቅድም ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ ሎምባርዲያ ካፌ ያለበት ሕንፃ እየፈረሰ ነበር። ሲያፈርሱት ረዥም ደቂቃ ቆሜ አየሁ። ለምን እንደኾን እንጃ የምር አዘንኩ ፥ እምባ እምባ አለኝ። አንድ ሁለት ቀን እሷን እየጠበቅኹ ማኪያቶ የጠጣኹበት ቦታ ሲፈርስ እንዲህ ካዘንኩ ብዙ ትዝታ ያላቸው ሰዎች እንዴት ያዝኑ ይሆን ብዬ አሰብኩ። ግን ደግሞ እኔ ብቻ ልሆንም እችላለሁ ያዘንኩት because I'm a sensitive አስ ኒጋ - አላውቅም ብቻ። Maybe I'm just being a grumpy granny who hates change.

ቅድም በስንት ጊዜዬ ፒያሳ ሄጄ እንደገጠር ልጅ ተደነባበርኩ። ፒያሳ ተቀያይሯል። ታክሲ ተራውን ፍለጋ ከላይ ታች ስባዝን ነበር። It seems that half of the ፒያሳ I love is no more there. የምወዳቸው፣ የሚመስጡኝ እና በጥቂት ትውስታም ቢሆን ከአዕምሮዬና ከልቤ ጋር connected የሆኑ ቦታዎች አሁን በብዛት የሉም። ወደሌላ፣ ምናልባትም "ወደተሻለ" ቦታነት ተቀይረዋል።

እና ከ4 ኪሎ ሜክሲኮ ወክ እያደረግኩ ብዙ ለውጦችን notice አደረኩ። አምባሳደር እያየነው ከሞቀ መንደርነት ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል፣ ኪዳኔ በየነ ሕንፃ ግራጫ ቀለም እየተቀባ ነው፣ የሜክሲኮ ደብር የሆኑት መጻሕፍት መሸጫ ሱቆች ፈርሰዋል፣ ሌላም ብዙ ብዙ ...

ምናልባት ታሪክ ለእኔ ያለውን ያህል ሬለቫንስ ለሌላው የለውም ይሆናል። ወይም ጥሩ ነገር ይሆናል እያደረጉ ያሉት። ምናልባት nostalgia የምናስበውን ያህል ጥሩ ነገር አይደለም ይሆናል። አላውቅም! እዚህ ሀገር የሚሻለን ሳያስቡ እና ምንም ሳያውቁ መኖር ነው አባቴ ~

4 months, 3 weeks ago

የገጣሚው ኑዛዜ!

"ሃሳብ አልጎደለን ፥ እርዕስ አላጣን
ለሴት የምንገጥመው ፥ ኧረ ምን በወጣን?
ሐቀኛ ገጣሚ ፥ ግጥሞቹን ባይመርጥም
ስለሴት ብቻ ግን ፥ አይጻፍም ግጥም!"

ብዬ እየተቆጣኹ ፥ ስንቱን ሰው ሳሞኘው
ስለ`ሷ እየገጠምኩ ፥ እራሴን ላግኘው?

ቃል ሆኗት እንጎቻ ፥ ባትጎርሰው እንደእራት
ስንኝ ጥለት ሆኖ ፥ ምን ባያሳምራት
ሆኗት ድሪና አምባር ፥ ባይሸልም ባይኩላት
ኧረ እንኳን ጻፍኩላት ፥ እንኳን ገጠምኩላት!

ደስታ እንደመቸሯ ፥ እንደ ወርሃ ጥር
ነፍስ እንደማሞቋ ፥ በተጠጓት ቁጥር
እንደጠዋት ፀሐይ ፥ እንደመለስለሷ
እውን ይበዛል ወይ ፥ አንድ ግጥም ለ`ሷ?

ምን ዛሬ ብታገል ፥ ብዬ "ቃል አላጥፍም"
ቀለም ባያስደፋኝ ፥ የፍትወቱ ፍም
በቃሌ ፀንቼ ፥ ስለሴት ባልፅፍም
የ`ሷ ሴትነት ግን ፥ ከሕይወት አይገዝፍም?

ቢያስውባት አብልጦ ፥ ፈጣሪ እያዳላ
ምንም ቢሆን እንኳን ፥ ዳሌዋ ሞንዳላ
ዐይኗ የተኳለ ፥ ጎፈሬዋም ችምችም
ይኼን ግን አውቃለሁ ፥ ሴት ብቻ አይደለችም!

5 months ago
6 months, 1 week ago
በመላ ሸሽጌ ፥ በታይታ አዳፍኜ

በመላ ሸሽጌ ፥ በታይታ አዳፍኜ
ከሳቅ ቡቱቶ ሥር ፥ የያዝኳት ሸፍኜ
ገፄን የነቀሰች ፥ በእሳት ነበልባል
አለችኝ ጠባሳ ፥ ሕይወት የምትባል!

We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 2 days, 12 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 days, 20 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago