HOME || ቤት 🏚

Description
Feel at Home!

@yonis_home_bot
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 2 months ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 1 week ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 4 months ago

3 months, 1 week ago

[? እንደ ስንብት ፥ As a Farewell ?]

"ሰማይን በስንዝር ልለካልሽ" ስላት
"ባሕሩን በገንቦ ልስፈርልሽ" ስላት
"ሺ ምንተሺ ኮከብ ላዝንብልሽ" ስላት
ውሸቴን መሰላት!

አታውቅም ይህቺ ሴት ፥ ደረጃና ልኳን
ለእሷ መዳፈሬን ፥ መለኮትን እንኳን!

አወይ የእኔ ብጤ ፥ ሞኝ አፍቃሪ መሆን
የወደደ ጉንዳን ፥ "ልጣል" ይላል ዝሆን!
ዝሆንን እንኳ አንዴ ፥ ይጥሉት ይሆናል
ተነስቶ ሲመጣ ፥ ግን እንዴት ይዳናል?

እኔና ወይኔ ላይ ፥ ስካር የለው ስልጣን
ስበላም በገደብ ፥ አያውቀኝም ቁንጣን
በልኬ እንዳልበላሁ ፥ በልኬ እንዳልጠጣሁ
መጥኖ ማፍቀሪያ ፥ ልብ ምነው አጣሁ?

ምድርን ተሸክሟል ፥ አትላስ ያ ገርጋራ
በዕውቀቱም° አዝሏል ፥ ምድርን ካትላስ ጋራ

ይኸው እኔም አለሁ...
ከሁለቱም በላይ ፥ ደክሜና ዝዬ
እሷን ከፍቅሯ ጋር ፥ ተሸክሜ አዝዬ!

የቆጠርኩት ሀሁ ፥ የገለጥኩት መጣፍ
የቤተስኪያን አፀድ ፥ የጸሎቴ ምንጣፍ
እሷ ፊት ሲቆሙ ፥ አይገዳደሯት
ጭራሽ አበረቷት ፥ ጭራሽ አደደሯት!

የመረሳት ልጅ ሆንኩ ፥ የመገፋት ወንድም
ምነው አይቆርጥ ልቤ ፥ እግሬ አይራመድም?
ጸሎቴ አይሰማም ፥ አይሰምርም ስለቴ?
ቆርጦ ጣለኝ መቁረጥ ፥ የት ሄደ ብስለቴ?
"ሙት" እንኳን ብትለኝ ፥ አላስብ ሁለቴ!
እሷን የጊዜ ገድ ፥ ሲያሳምር ሲኩላት
ስንቴ እየተነሳሁ ፥ ስንትዜ ሞትኩላት?

ያጣሁኝ ይመስል ፥ ሸክም ባይነት ባይነት
አሻፈረኝም ብዬ ፥ በእምቢ ባይነት
ጠርጣራ ልቤ ላይ ፥ እንዳልተሸከምኳት
ስዝል ራቀችኝ ፥ ሲደክመኝ ደከምኳት!

"እለቅ" ሲልኝ እንጂ
"ባክን" ሲለኝ እንጂ
የመከነ ፈንጂ
ሁን ሲለኝ ነው እንጂ
ልክ እንደ ልጥ ዘገር
እንደው ያለነገር
የነፍሴ ነበልባል ፥ አልተንቀለቀለም
አለቅኩ እንደ ላምባ ፥ ነጠፍኩ እንደ ቀለም!

ፍዝ ኩራዝ ተግ ይላል ፥ ላምባ ሲንቆረቆር
ስብራት ይገጥማል ፥ ይድናል ቆረቆር
በደል ይሠረያል ፥ ይካሳል በእጥፍ
ግን ምን ያድርጉታል ፥ ሰው ነፍሱ ሲነጥፍ?

ቢላ ቢዶለዱም ፥ መቁረጡንም ቢተው
ያስቀጠቅጡታል ፥ ለአንጥረኛ ሰጥተው
ሸማውን ላጣቢ
ገንዘብ ለቆጣቢ
ባደራ ይሰጣል
ያደፈ ይነጣል
ጎፈር ያድርጉታል ፥ ጨብራራን ከርክመው
ምን መላ አለው ለሰው ፥ ሰው መሆን ሲደክመው?

በእሷው ዝዬ ብታይ ፥ እሷው ሳቀችብኝ
እንደህል እንደ ውኃ ፥ ነፍሴ አለቀችብኝ!

የእሷ ገመምተኛ ፥ የማልቆርጥ ወላዋይ
በከንቱ ጩኸቴ ፥ እላለሁ እንጂ "ዋይ"
እሷ እንደኹ አይገርማት ፥ ሞቴንም ናቀችው
ቯለሰች °° በጣሬ ፥ ዕምባዬን ሳቀችው!

እንድድናት ታመምኩ
እንድትይዘኝ ዘመምኩ
በእሷው እንዳልመጣ ፥ ሕመም በሽታዬ
አንድ "ይማርህ" አጣች ፥ ለሺ እንጥሽታዬ?

ቧልቴ ወጋወጌ ፥ የአንደበቴ ፌዝ
እሷን ማሳቅ ከብዶት ፥ አጥሮት ለዛና ወዝ
እንዲያው ስድከመከም ፥ እንዲያው ስወዘወዝ

ይኸው አንድ ዘዴ ፥ ይኸው አንድ መላ
ቀልድ አደረኩላት ፥ ሕይወቴን በሞላ!

ይሄን ተመልክታ
ፈክታ ተንከትክታ
ስቃ ስታበቃ
ጥላኝ ሄደች በቃ?

ሁሌ እንድትስቀኝ ፥ ከፊቷ ባልርቅም
የተደገመ ቀልድ ፥ ለካ አያስቅም!
ሳቅ የተለበጠ ፥ ሺ ዕምባ ቀፍቅፌ
ብቻዬን ቀረኹኝ ፥ ቀልድ ሕይወት ታቅፌ!

ግን ይሁን!
መቀበል ነው እንጂ ፥ የሕይወት አሰስ
ዳኛውን ለራሱ ፥ ምን ይረባል መክሰስ?
ምን ያመጣል ልቤ ፥ ቢያዝን ቢበሳጭስ?
ወዳልፈለገው ነው ፥ ሰውና የእጣን ጭስ!

ባት[]ሚኝም ስሚኝ...
ባት[]ሚኝም ስሚኝ...

መልኩን አሳምሮ ፥ ቢኮፈስ ቢኮራ
ከ"እኝክ - እንትፍ" ዕጣ ፥ አያመልጥ ሸንኮራ
እኔም እንደዚያ ነኝ ፥ አገዳና ቅንጥሽ
ካፍሽ ብውል እንኳን ፥ ችዬ ማልዋጥሽ
መሆኔን አውቃለሁ ፥ ጣፋጭ ግን አላቂ
ስትጎርሺኝ አልቅሰሽ ፥ ስትተፊኝ ግን ሳቂ!

መተፋቱ ላይቀር ፥ መስቲካ ታኝኮ
ምንምሽ ነኝ እኔ ፥ ምንምሽ ነኝኮ!

፨ ፨ ፨

°° ቯለሰች - "ቯልስ ደነሰች" የሚለውን ቃል የሚተካ የቃላተ-ፈጠራ ሙከራ

3 months, 2 weeks ago

"እንገናኝ" ስትለኝ "እምቢየው - Insecure ነኝ" ስል ከርሜ ከስንት ልመና በኋላ እሺ ብያት ዴት ከወጣን በኋላ "አንድ የማወቀው የጣሊያን ቤት አለ። ሞሶሎኒያቸው በጣም አሪፍ ነው። ላፎንቴናቸውማ OMG you have no idea! እሱን መሞከር አለብሽ" ብያት ፈረንጅ የሚበዛበት ሬስቶራንት ከወሰድኳት በኋላ ለእኔ አፒታይዘር ቺክን ሳላድና ሚኒስሮ በስቴክ ከአሩስቶ ጋር፣ የሚጠጣ ነገር ደግሞ ሞሂቶ፤ ለእሷ half toasted corn with pumpkin soup (የበቆሎ ቂጣ በዱባ መረቅ)፤ ዲዘርት ደግሞ ለእኔ ቴራሚሶ ለእሷ ደግሞ ቴሊታቢስ አዘን ከበላን በኋላ ቢል 2.3 ሚሊየን ዶላር ሲመጣ ንፍጤን ልናፈጥ በሚል ሰበብ ሽንት ቤት ሄጄ mirror ሰልፊ ተነስቼ "Having a quality time with myself!" በሚል caption ፑስት!

#MenInWomenField
#ወንዶችበሴቶችዘርፍ

4 months ago

ማንን ነው የምታገለው? የፈጠረኝን? የፈጠርኩትን? ወይስ ራሴን? አላውቅም! ባውቅም የሚረባኝ አይመስለኝም። ለምን እታገላለሁ? ለማሸነፍ? የማሸነፍ ጥቅም ምንድነው? የአሸናፊነት ጉሮ ወሸባ?

አንዳንዴ - አንዳንዴ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜ - ታግለው ቢያሸንፉትም የኋሊት ተጉዘው የማያስመልሱት እልፍ ኪሳራ አለ። ትላንቴን በምን ዓይነት ገመድ የፊጥኝ አስሬ ብጎትተው ይመለሳል? ያስለቀሰኝን ታግዬ ብጥለው ፈስሶ ለባከነ እምባዬ መታሰቢያው ምንድነው? የፈሰሰን እምባ ምገው ወደ ከረጢቱ አይመልሱት ነገር! እንደ ጠመዥ ቆሎ ለተመነዠገ ባካና ወጣትነቴ፣ ለባከነ ልጅነቴ፣ በዋል ለፈሰሰ ጉብዝናዬ ስርየታቸው ምንድነው? ለማንስ "ያንት ያለህ" ይባላል?

ስለ ሕይወት እተክዛለሁ፤ ስለ እኔነቴ እቃትታለሁ። የሚጠቁምበት አጥቶ ተንከርፍፎ ለቀረው ለሌባ ጣቴ አዝንለታለሁ። የሚሰድበውን ላጣ የይሉኝታና የወግ ፋሻ ለሸበበው ለመሀል ጣቴ በኃዘን ከንፈሬን እመጥጣለሁ። ለቀለበት-አልቦው ቀለበት ጣቴ እብሰከሰካለሁ። ጥሏን ሳታውቅ እርቅ ለምትቃርም ትንሿ ጣቴስ?

"እየኖርኩት ያለሁት ኑሮ የማን ነው?" እላለሁ። ሕይወት ያሳረፈችብኝን ሰንበሮቼን እቆጥራለሁ፤ ብጉሮቼን እዳብሳለሁ። ጣቶቼን ባቀመቀመው ጢሜ መሀከል አርመሰምሳለሁ። "ማን ነኝ ግን?" ብዬ እጠይቃለሁ።

በጠራቢ እጅ እንደዋለ ሀውልት ነኝ ፥ መጠረቡ ባይከፋኝም ከሀውልቱ ድፍን ዓለት ላይ ተጠርበው ከሚጣሉት ረብ የለሽ ጠጠሮች መሀከል መሆኔ ብቻ ይከፋኛል - በስሱ ይከፋኛል - በስሱ ብቻ ሳይሆን በአያሌው ይከፋኛል።

የሕይወት ጉድፍ ከመሆን በላይ ምን ያማል? ገና ለጋ ሳለን ተላምጠን የተተፋን ቅንጥሾች እንሆን? ፍሬ ነን ወይስ ገለባ? እያንገዋለለ በዋለበት ሁሉ የሚጥለን ራስ ወዳድ ንፋስ ለገለባነታችን ምስክር አይሆንብንም?

ፀሐይ በጠለቀች ቁጥር ላባከንኩት ቀኔ የንስሓ እንባ በጉንጮቼ ላይ እዘራለሁ። ያለፈኝን የዳዊት ልጅ "እባክህ አትለፈኝ!" እለዋለሁ። ሟቹ እንደሆነ ረፍዶበታል - ለገዳዬ እማልዳለሁ።

አሁንም ለተላለፍኩት ልጅነቴ አርባ እሰግዳለሁ፤ የኋሊት እያማተርኩ እጅ እነሳዋለሁ። "አንተ ከልጆች መካከል የተባረክ ነህ!" እለዋለሁ። የምጠላው ወዳጄን - የምወደው ጠላቴን - ራሴን - "በመንግሥቴ በመጣሁ ጊዜ እንዳስብህ፤ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ!" እለዋለሁ።

4 months, 1 week ago

አይ የአዲስ አበባ ካፌዎች ?‍♂️

ገና ገብተህ አንድ ሁለት ሰዓት ከመቀመጥህ ያቁነጠንጣቸዋል። ጠረጴዛውን ዐስሬ ይወለውሉታል፣ ወንበሮቹን ያስተካክላሉ፣ ስኳር ዕቃውን ያነሳሉ፣ ያስቀምጣሉ። ደግሞ ሰው የሚበዛበት ካፌ ቢሆን እሺ። ባዶ ወንበር ታቅፈው እኮ ነው የሚውሉት።

የእኔዪቱማ በፋራ ሙድ እንዳልገባው ሰው ስገግምባት ደጋሚ መጥታ "ምን ልታዘዝ?" ውይ እናትዬ አሁን ቡና አጠጣሽኝ፣ ነገር አበላሽኝ እኮ!

ገና እስከ ማታ አንድ ሰዓት ነው የምቀመጠው። እስኪ አፍ አውጥተሽ "ውጣ!" ትዪኝ እንደሆነ እናያለን። ሲጀመር የመጣሁት እኮ የቀጠነ ቡና ለመጠጣት አይደለም የእኔ እናት! ተቀምጬ ሥራዬን ለመሥራት ነው።

?

4 months, 2 weeks ago

እኔ...
የውስጤን ችዬ ፥ የማላብራራ
አፈ-ላሁጫ ፥ ልበ-ጨብራራ
አምላክ ላይ እንኳን ፥ ጅንን ቀብራራ
ሟች የነበርኩኝ ፥ እግዜር ባይራራ!

እኔ...
ስንኩል መልከ-አምላክ ፥ መንፈሰ-ክልስ
ነፍሱ ሸካራ ፥ ምላሱ ልስልስ
ድቅል ተክል ነኝ ፥ ስንዴና እንክርዳድ
የተዘራ አብቃይ ፥ የሆዴ ሁዳድ!

እኔ...
ለሥጋ ታጋይ ፥ ለቅንጥብጣቢ
ገላው ቆሽሾ ፥ ስሙን አጣቢ
ሕይወት ትርዒት ፥ ኑሮም ድራማ
ሲገበርለት ፥ ጀማው ከራማ

የሙጥኝ ብዬ ፥ ያዳም ከል ቅርሴን
እንኳን ወዳጄን ፥ እንኳን ራሴን
አምላኬን እንኳን ፥ ምንኛ አለፋሁ
ስጠፋ አገኘኝ ፥ ሲያገኘኝ ጠፋሁ!

አትራራልኝም ፥ ዓለም አጅሪት
ክብ ሆኖብኛል ፥ ሕይወት አዙሪት
ኢያሪኮዬን ዛሬም ፥ ልዙረው
ትላንቴን አይደል ፥ ነገ ምኖረው?ባሮጌ አንቀልባ ፥ ነፍሴን አዝያት
ሾልካ ጭቃ ላይ ፥ ስትወድቅ እያት
ቀኔ ሲጓደል ፥ ሲርቀኝ ቆሌ
"ሆሳዕና" ነው ፥ ኦሜጋ ቃሌ
"አሁን አድን" ነው ፥ ፍጻሜ ቃሌ!አሁን አድነኝ...በጆችህ ልዋል ፥ ሁነኝ ጠራቢ
አንፀኝ ጌታ ፥ አድነኝ ረቢ
አድክመኝ ላለም ፥ ቆሜ ላለክልክ
አሳደህ ያዘኝ ፥ በሽሽቴ ልክ

አሁን አድነኝ...
ፈውሰኝ ረቢ ፥ እስቲ ላገግም
ዕምባዬን አብስ ፥ አላልቅስ ዳግም
መሮጥ ቢያቅተኝ ፥ በስሱ ላዝግም

አሁን አድነኝ...
ይደገፍ በጅህ ፥ መንገዳገዴ
ዋጀው ዕድሌን ፥ ይግደድህ ገዴ
በእቶን አባብለኝ ፥ አልሁን ለጋ
ሞት ደጃፍ አልሂድ ፥ ሕይወት ፍለጋ!
አሁን አድነኝ...ይፋፋም እንጂ ፥ ሕቅ እንቅ ትግል
ሥጋና ነፍሴን ፥ አላሸማግል
እንኳን ገላዬ ፥ ሃሳቤ አይዘሙት
ዓለም ትሙተኝ ፥ ለዓለም ልሙት!
አሁን አድነኝ...ክንፌን ስበረው ፥ ይብቃ መክነፌ
ሥጋ ይሸነፍ ፥ በመሸነፌዓለም ትርበድበድ ፥ በመርበድበዴ
እነሆኝ ፊትህ ፥ መንታ ወንበዴ
ነፍሴን በግራ ፥ ሥጋዬን በቀኝ
እመስቀልህ ጎን ፥ ባክህ ጠርንቀኝ!
ምኞት ሹክሹክታው ፥ ሲነዘንዘኝ
በፍቅርህ ገድለህ ፥ እስቲ ገንዘኝ!

አሁን አድነኝ...
ምኞት ሲንጣት ፥ ሲያርገፈግፋት
መልሳት ነፍሴን ፥ ልቤን ደግፋት
በብሉይ ፍቅር ፥ በአዲስ ኪዳን
ለመኖር ልሙት ፥ ለመሞት ልዳን!

5 months, 1 week ago

ያው ስልኬ እየለየላት ስለሆነ ሰሞኑን ቁጭ ብዬ ፋይሎቼን backup ሳደርግ ነበር። ልክ እንደዚህ ያሉ ለሦስት ዓመት የጻፍኳቸውን Nonsense የሆኑ ጽሑፎቸ፣ ብሶቶች፣ ያልተላኩ ቴክስቶች፣ የማያስቁ ቀልዶች እያየሁ ስፍታታ ነበር።

አንዳንዶቹ ያስቃሉ፣ አንዳንዶቹ አለማሳቃቸው ያስቃል፣ አንዳንዶቹ ያናድዳሉ፣ አንዳንድቹ ምንም ትርጉም የላቸውም፣ አንዳንዶቹ ለማን እንደሆኑ እንኳን የማላስታውሳቸው ቴክስቶች ናቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በጊዜው የነበርኩበትን ስሜት ያስታውሳሉ፣ አንዳንድቹ ስጽፋቸው የነበርኩበትን ቅጽበት ጥርት አድርገው ያሳታውሱኛል። ብቻ ደስ ይላል ሁሉንም አልፈው ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲያዩት። እና ዝም ብዬ ላካፍላችሁ ፈለግኩ። They will be deleted soon, I guess!

መልካም ምሽት!
?

5 months, 1 week ago
HOME || ቤት 🏚
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 2 months ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 1 week ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 4 months ago