♥️❤️ ፍቅር እና ጨዋታ??

Description
Tags
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion ? @Share_Home

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 6 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 8 months, 3 weeks ago

6 months, 2 weeks ago

በጥፋቱ የሚኮራ ሰው በበዛ ቁጥር እንደማህበረሰብ ለሃዘን መቀመጥ አለብን!

ብቻ በማያኮራው የሚኮሩ፥ በነውር ማጌጥ ቁም ነገር የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።

? ? ? ? ? ? ?

ለመቀላቀል? @yekeberedaha

ለአስተያየት ? @mood_zeki

6 months, 2 weeks ago

በጥፋቱ የሚኮራ ሰው በበዛ ቁጥር እንደማህበረሰብ ለሃዘን መቀመጥ አለብን!

ብቻ በማያኮራው የሚኮሩ፥ በነውር ማጌጥ ቁም ነገር የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።

ለመቀላቀል? @yekeberedaha

ለአስተያየት? @mood_zeki

3 years, 3 months ago

​​​​♦️ምኞት♦️

♠️ክፍል 14

.
.
.
ምክንያት የማያልቅበት ብሩኬ እቃዉን እንዲያቀብላት ሊነግረው
ጓደኛው ጋር ሲደውል እናቱ ሞተው ሀዘን ላይ እንደሆነ ሰምቶ
ድንገት እንደመጣ ነገራት ባይዋጥላትም ለማንኛውም ምናልባት
ዋስ ካስፈለገ ብላ ሚኪ ጋር እንደደወለች ስትነግረው ፊቱ
ተቀያየረ "ምን ሆንክ?"አለችው••
እኔ ከቆይታ ቡሀላ እወጣለሁ ዋስ አያስፈልገኝም እሱ ጋር
መደወል አያስፈልግሽም ነበር " አላት ቀጠል አርጎም ሚኪ ከእሷ
እና ከሱ የደበቀውን ሚስጥር
እንደደረሰበትና በሚኪ በጣም እንዳዘነ ለሷም ከስር ቤት
እንደወጣ እንደሚነግራትና ሚኪ ምን ያህል ጨካኝ መሆኑን ስትረዳ
በእርግጠኝነት ለሡ ያላት አመለካከት እንደሚቀየር እያጋነነ አወራላት።
ስለሚኪ ጭካኔ ካንተ አፍ መስማቴን ማመን አልችልም እኔኮ
ጭንቅላቱን የተመታው ወንድሜ ብቻ ነበር የመሰለኝ ለማንኛውም
ስትወጣ ደውልልኝ " ብላው ካጠገቡ ሄደች ።
ማታ እራሷን እንዳመማትና ሁሉንም ነገር ስገናኙ እንደሚያወሩ
ብሩኬም ስለተፈታ መምጣት እንደሌለበት ለሚኪ ደውላ
ስትነግረው እባክሽ የጓደኛዬን ድምፅ አሰሚኝና ልረጋጋ ሲላት እኔ
ከወንድሜ ጋር ነው ያለሁት እሱ አጠገቤ የለም ብላ ስልኩን
ዘጋችና"አይ ሚኪዬ ጓደኛ አግኝተህ ሞተሀል አንተ ድምፁን ልስማው ትላለህ እሱ ድምፅህን ለማጥፋት ይሯሯጣል ።
አለች ለራሷ።
ፅናት ከንቅልፋ እንደነቃች ሞባይሏን አንስታ ሰአት ተመለከተች
ከጥዋቱ 2:30።
ዛሬ ጥዋት ወደ አዲስ አበባ ለመብረር ትኬት ቆርጠው ነው
ያደሩት ። ወንድሟ ወደ ተኛበት ክፍል በመሄድ ቀሰቀሰችው "
ተነስ ተዘገጃጅ 3:30 ላይ እኮነው በረራው ተነስ " ብላ
ቀሰቀሠችውና ወደክፍላ ተመለሰች።
ሚኪ ከተፈታ ቡሀላ ሊያገኛት ፈልጎ ቢደውልም ሁኔታው
ስላልጣማትና ስለሚኪ መጥፎ ነገር መስማት ስላልፈለገች
ስልኩን አላነሳችለትም።
ከወንድሟ ጋር ከሆቴሉ ሲወጡ የብሩክን መኪና ራቅ ብላ
ቆማለች።
ሰውየሽ በጥዋት መጥቶ ተገትሮልሻል ።
አላት ወንድሟ። ጥሎቦት ብሩኬን አይወደውም።
እንዴ እንደውም እስከ አየር ማረፊያው እሱ ይሸኘናል" መኪና
ይዘን እንምጣ ስልሽ ይቅር ያልሽው እሱ እንዲሸኘን ነው እንዴ "
እኔ በዚህ ሰውዬ መኪና መሄድ አልፈልግም" አላት ወንድሟ
ጥሎበት ብሩክን አይወደውም " እሺ በቃ ቻው ብየው ልምጣ"
በማለት ብሩክ ጋር ሄዳ በመኪናው መስኮት ተሰናብታው ልትሄድ
ስትል "ነይ ግቢ እንጂ ስለ ሚኪ እነግርሻለሁ ያልኩሽን ልንገርሽ
አላት ስለ ሚኪ እነግርሻለሁ ያልከኝ ምን ነበር ብላ ስላልጠየቀችው ተናዶ " አዲስ አበባ አይደርስም? አስቸኳይ
ነው?" ስትለው ይበልጥ "አዋ መኪና ውስጥ ግቢ ብዙም አትቆይም"አለ መስማት ባለመፈለጓ ይበልጥ ውስጡ እየተቃጠለ።
ወንድሟን ዘወር ብላ አየችውና መኪና ውስጥ ገባች ወድያው
ምኞት ለሚኪ የፃፈችለትን ደብዳቤ አወጣና ሰጣት ትንሽ
እንዳነበበች እምባዋ ደብዳቤው ላይ መንጠባጠብ ጀመረ።
ብሩክ ግራ ተጋባ "እቺ ልጅ ልጅቷ በመጎዷቷ ነው ወይስ ሚኪ
ሌላ ፍቅረኛ እንደነበረው ማወቋ ነው ለማንኛቸው ነው እምታነባው? አለ በውስጡ። ፅናትን በስስትና በትኩረት
እየተመለከታት የለቅሶዋ ምክንያት ግን አንደኛው ብሩኬ እንዳሰበው አዝናላት
ቢሆንም ሁለተኛው ግን ብሩኬ በህይወት እያለ መስማት የማይፈልገውና የሦስቱን ግኑኝነት ዳግም ላይመለስ ሊያፈራርሰው
የሚችል ነገር መሆኑን አልጠረጠረም እንደጨረሰች " አንተ ግን
እንዴት ሳያነበው እዚህ ይዘህ ትመጣለህ" አለችና ከነ እምባዋ
አፈጠጠችበት.....
ብሩኬ ያልጠበቀው ጥያቄ ስለነበር ተደናገጠ " እሱ ምን ለውጥ
አለው ልጅቷ እኮ ወደ መጣችበት ሄዳለች ደሞ ስደውልለት
አያነሳም ከዛ ያው ታውቂያለሽ እኔም አጋጣሚ ነው እዚህ የመጣሁት " አለ " ለውጥማ ሊኖረው ይችል ነበር ሚኪ በዚህ ሳምንት ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ትናንት ስላንተ ልነግረው
ስደውል ነው የተረዳሁት እሄ ደብዳቤ ቶሎ ቢደርሠው እራሱን በፀፀት ከሚጎዳ ወይ ሀሳቡን ሊቀይር ይችል ነበርኮ " አለች በተቆራረጠ ድምፅ።
ብሩክ ሁኔታዋን ለመረዳት ተቸገረ " ቆይ ፅኑ እስቲ ተረጋጊና ንገሪኝ የልጅቷ ነው ወይስ የሚኪ መጎዳት ነው ያሳዘነሽ እሄ እኮ እኛ ሳናውቅ ብቻውን የፈፀመው ነገር ነው " አላት።
" እኔ .......እኔ...........እኔ" አለችና በመኪናው መስታወት ወደ
ወደ ውጪ አይናን ወርውራው ተተክላ ቀረች።
" አንቺ.....አንቺ ምን...." እላት ብሩኬ ልትናገር ያሰበችውን
ለማስማት ከመቸኮሉ የተነሳ ቃሏን በግድ ፈልቅቆ ያስወራት
ይመስል አገጯን ቀና እያረጋት "የልጅቷንም ህይወት እንዲበላሽ
በፍፁም አልፈልግም ግን ስለ ሚኪ ደግሞ ከዚህ ሁሉ ግዜ ቡሀላ
የመጨረሻውን እውነቱ የማውቅበት ግዜ ሥለሆነ...." ብላ ዝም
አለች።
የምን እውነት ነው እምትይው እውነቱ እጅሽ ላይ ያለው ደብዳቤ
አይደል እንዴ እሡ በደፈናው አንድ ቀን ንግሥቴን ልእልቴን
ሣታሥቡት ነው እዚህ ቤት ይዣት የምመጣው ከማለት ውጪ
ምን ነግሮን ያውቃል አሁን ደሞ እሄው እውነቱን አወቅነው !"
ሲላት
" የእውነቱ መጨረሻ ግን እሄ አይደለም ገና አለየለትም" አለችው
ጮክ ብላ
" ታዲያ ከዚህ ውጪ ምን እውነት አለ ያችን ሚስኪን አምጥቶ
ሜዳ ላይ ጣላት እሷም የስንብት ደብዳቤ ፅፋ ወደ መጣችበት
ሄዳለች "
ፅናት " ግን ሚኪ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም እያልኩህ እኮ ነው
ብ..ሩ..ኬ ያለውን ስሜት ዛሬ እንደገባን እሄንን ደብዳቤ
ሰጥተነው ካነበበ ቡሀላ ብቻ ነው ልናውቅ የምንችለው ያኔ እኔም
ቁርጤን አውቄ ውሳኔውን በማክበር ከጎኑ እሆናለሁ" ስትለው
ብሩክ ከመደንገጡ የተነሳ ጉሮሮውን እሚያረጥብበት ምራቅ
አጠረው "ምን....ምን..አልሽ ፅናት ስለምን ቁርጥ ማወቅ ነው
እምታወሪው አንችን ደግሞ ከዚህ ጋር ምን አገናኘሽ!" አላትና በጭንቀት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ መልስን ይጠባበቅ ጀመር
እምባ ባቀረሩ አይኖቿ ዝም ብላ አይን አይኑን እያየች ዝም አለች
በሁለት እጁ ግራና ቀኝ ትከሻዋን ይዞ " ንገሪኝ ፅኑ ምንድን ነው"
እያለ አወዛወዛት
" ብሩኬ እኔ.......ኮ.....ሚኪን አፈቅረዋለሁ!!!
" ብሩኬ እኔ.......ኮ.....ሚኪን አፈቅረዋለሁ!!! ሥትለው ብሩክ
የራሱን ጆሮ ተጠራጠረው
"ም......ምን አልሽ ፅናት ምን...ድን ነው የሰማሁት" እየቀለድሽ
ነው ?" አላት እጅግ በሚያሳዝን

?ክፍል 15 ♥️ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like? ማድረግ አይርሱ።

3 years, 3 months ago

​​​​♦️ምኞት♦️

♠️ክፍል 13

.
.
.
ሮጣ እታች እንደደረሰች እሷ ካለችበት ቀጥሎ ባለው
ኮንደሚንየም ጨለማ ውስጥ ግድግዳ ተደግፋ በመቆም ትንፋሽ
ወስዳ ከተረጋጋች ቡሀላ ወደላይ ቀና ብላ አየች መብራቱ
እንደጠፋ ነው ።
" ማን ይሆን ውስጥ ያለው የውጪ እገር ዜጋም ይመጣል እንዴ
ወይ ፈጣሪ ! " አለች በሩን ልትከፍት በምትሞክርበት ወቅት
"ማነው? ካለ ቡሀላ ያወራው ምን እንደሆነ በደንብ ባይሰማትም
ከአነጋገሩ ግን ኢትዬጲያዊ እንዳልሆነ ገምታ።
"አሁን የት ላድር ነው " አለችና ሸርተት በማለት እግሮቿ ላይ
ተቀመጣ ማሰብ ጀመረች።
በቅርብ ወዳለ ቤተ እምነት ለመሄድ አስበች። ግራ መጋባትና
ፍርሀት ውስጥ እንደተዋጠች እዛው ጭለማ ውስጥ ተቀምጣ
አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ ደሞ ወደ ላይ በየተራ
እየተመለከተች ቆየች።
በመሀል ካቀረቀረችበት ቀና ስትል እሷ ተደብቃ ከምትኖርበት ቤት
መብራት ሲበራ ተመለከተች ወድያው በሩ ተከፍቶ አንድ ወጣት
ሴት ወጣች ብዙም ሳይቆይ አንድ ወንድ ተከትሏት ወጣና
ተመልሶ በመግባት መብራቱን አጥፍቶ ብዙ ሞባይል ብርሀን በሩን
ቆለፈ "እየወጡ በሆነ አምላኬ" አለች ወደላይ እንዳንጋጠጠች ...
ጨለማው ውስጥ እንዳደፈጠች እታች እስኪደርሱ መጠባበቅ
ጀመረች ከተወሰኑ ሠከንዶች ቡሀላ አንድ አጭር ወፍራም
ቻይናዊና አንዲት ኢትዬጲያዊት ወጣት በአጠገቧ እያወሩ አለፉ ...
ልጅቷ ውብ ነገር ነች ቻይናዊው እየተኮላተፈም ቢሆን አማርኛ
ያወራል ልጅቷ ዛሬ ባትችልም በሚቀጥለው ተዘጋጅታበት
በመምጣት እንደምታድር ለቻይናዊው ቃል ስትገባለት ሰማች ።
እንደሄድ " ወይ ጉድ እስቲ ባልጠፋ ቦታ ሴቶቹን እየጎተቱ እዚህ
ማንም እማይደርስላቸው ቦታ እሚያመጧቸው የሆነ ተንኮል
ቢያስቡ ነው እንጂ እሄ የተሻለ ቦታ ሆኖ አይደለም መቼስ" አለች
ምኞት ልጅቷ ሳምንት መጥቼ አድራለሁ ስትል በመስማቷ ከወዲሁ
ስጋት ገብቷት...
" እይ ሚኪ" አለች ቤቱን እምንጠቀምበት እኔና ሁለት ጓደኛቼ ነን
ብሏት እንደነበር እስታውሳ ወድያው ሚሞሪውን የሰረቀችው
ሰውዬ ቁልፍ ከአንዱ ወደ ሌላው እየተቀባበለ እዚህ ቤት
የሚመጣው የሰው ብዛት እንደማይታወቅ ለቀጭኗ ልጅ ሲነግራት የሰማችውን ትዝ አላትና እውነቱን ያወራው እሱ
እንደሆነ እያሠበች እሁንም ውስጥ የቀረ ሌላ ሰው እንዳይኖር በሚል ውስጧ ፈራ ተባ እያለ ደረጃውን ወጥታ ጨረሰች ።
በሩ ጋር እንደደረሠች ትንሽ ቆማ ካዳመጠች ቡሀላ አመሠግናለሁ
ያገሬ ልጅ ለማደር ብትስማሚ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር እያለች
ከፍታ በመግባት ክፍሎቹን አየት አየት አድርጋ ወደ እቃ ቤቷ
በመግባት ተጠቅልላ ተኛች ።
ፅናት ከወንድሟ ጎን እስከ እሁድ ሆስፒታል ቆየች እሁድ
ከጥዋቱ 3:00 ላይ ከእንደወጡ ወንድማን አልጋ ወደ ያዙበት
ሆቴል አድርሳ ብሩክ ወደ ታሠረበት ፖሊስ ጣብያ እየሄደች
ምናልባት ለመለቀቅ ዋስ ከተጠየቀ ብላ በማሰብ ወደ መኪ
ደወለች....
ሥልኩን በማንሳት " "ሄሎ ፅናቴ እንዴት ነሽ " አለ ሚኪ "ወይኔ
ጉዴ አሞሀል እንዴ ሚኪዬ " አለች ድምፁ እንደሰማች "
አላመመኝም ፅናቴ " አለ ሰሞኑን በተከታታይ የጠጣው መጠጥ
ባደከመው ድምፁ " ሚኪዬ ዝርዝሩን አሁን አትጠይቀኝ ሀዋሳ ነው
ያለነው ። ወንድሜ በፀብ ምክንያት ተጎድቶ እሁን ከሀኪም ቤት
መውጣታችን ነው ብሩኬ እዚህ ታስሯል።
የሚለቁት ይመስለኛል ነገሩን ካከበዱበትና ዋስ የሚያስፈልገው
ከሆነ መልሼ እደውላለሁ ቻው "ስትለው •••
ሚኪ በመደናገጥ " እንዴት በምን ምክንያት እዛ እንዴት ሄደ"
በማለት የሸሸችውን መልስ የሌለው ጥያቄ አክተለተለባት።
እደውልልሀለው ብቻ ብላ ስልኩን ከመዝጋት ውጪ መልስ
አልነበራትም ። ብሩኬ ወንድሟ ሲጣላ ፀቡ ውስጥ ድንገት
ከመከሰቱ ውጭ ሌላው ለሷም እንቆቅልሽ ነበርና።
ሚኪ ወድያው ከተኛበት በመነሳት ለጓደኛው ሊደርስለት
በመዘጋጀት የፅናትን ስልክ ቢጠባበቅም እስከ ማታ አልደወለችም
ቢደውልም ስልኳ ጥሪ አይቀበልም። ለጓደኛው እጅግ ከመጨነቁ
የተነሳ እስከማታ የመፈታቱን ዜና ካልሰማ በጥዋት ሊሄድ ወሰነ።
ፅናት እሥር ቤት ብሩኬን እንዳገኘችው እንዴት ሀዋሳ መጥቶ እዛ
ሆቴል ውስጥ ሊከሰት እንደቻለ በጥያቄ ታጣድፈው ጀመር....

............ይቀጥላል..........

3 years, 3 months ago

​​​​?ምኞት?

ክፍል 12
.
.
ከመደንገጡ የተነሣ ሥልኩን እንሥቶ እየደወለ ልብሡን
ሣይለብሥ ከቤት ሊወጣ ዳዳው ልጅታ ሥልክ አ አታነሣም
ደግሞ መከረላት አነሳችው.....
"በሂወት መኖር ካልፈለግሽ በሥተቀር የራሥሽን ቪድዮ አጥፍተሽ
ሚሞሪውን ብትመልሺ ይሻላል!" አላይ•••
ግራ ገባት "የምን ሚሞሪ" አልችው እምታላግጥበት መሠለው
በሷ ባህሪ ማሥፈራራቱ እንደማያዋጣው እሥቦ " እየውልሽ የኔ
ወፍ እኔ በፍፁም አንቕችን የመጉዳት ሀሳብ የለኝም በቃ የራሥሽን
አጥፊና ሌሎቹን ግን በጣም የምፈልጋቸው የግል ነገሮች ሥለሆኑ
እባክሽ መልሽልኝ አንቺ አድርግ ወይም ክፈል በይኝ ብቻ ደሥ
ያለሽን ነገር እቀጣለሁ"
ሢላት..
የበለጠ ግራ ብትጋባም ከሁኔታው ግን የሆነ ነገር እንደተፈጠረ
እየተጠራጠረች " እኔ ሥለ ምን እንደምታወራ አላውቅም ብላ
ሥልኩን ዘጋችና ምናልባት ከኔ ለመደበቅ ኪሡ አሥቀምጦት
ወድቆ ጠፍቶበታል ምለት ነው" "ጠፍቶ በቀረ!" አለች።
"ሠውየው ግራ ተጋባና ማታ ሠክሬ ሥለነበር ቦታውን ተሣሥቼ
ይሆን እንዴ? " ብሎ ምንጣፉን እየገላለጠ መፈለግ ጀመረ የለም።
ቀጭና ልጅ አንድ የሴት ጒደኛዋ ጋር ለመሄድ ታክሢ ውሥጥ ነች
ሂሣብ ለመክፈል ዝርዝር ፈለጋ የቦርሳዋን ኪሶች ስትበረብር
በወረቀት የተጠቀለለውን ነገር አገኘችና ግራ በመጋባት ገላልጣ
ሥታየው ወይኔ ጉዴ ብላ ጬኸቷን አቀለጠችው ታክሲ ውስጥ
ያሉት ግራ በመጋባት ሲገላምጧት ወራጅ አለችና ሳትደርስ ወርዳ
ወደ አንድ ካፌ ገባችና ሚሞሪውን ስልኲ ውስጥ በማስገባት
የሷን ጨምሮ ብዙ ሚስጥሮችን ተመለከተችና ጭንቀታ ሁሉ
እንደጉም በኖ ሲሄድ ታወቃት በሱ ቤት ምናልባት ጥዋት በግዜ
አትነሣም ብሎ እኔ እማልጠረጥርበት ቦታ ደብቆ ጥዋት ጥዋት
ሊወሥድ እሥቦ ነበር አለችና ሥልኲን አንሥታ ደወለችለት።
ስልኩን ወድያው ነበር ያነሳው አንተ ዝሆን ፈጣሪ ሀያል ነው እጄ
ላይ ጣለህ ደሞ ሚጣ ትሙት ትላለህ ልጅህን ብትወድ ኖሮ
የልጅህ እኩያ ከምትሆን ሴት ጋር እያስፈራራህ ባልተጋደምክ ነበር
እሄን ጉድህን ለዛች ብሯን አይተህ ለምታገባት እጮኛህ በስጦታ
መልክ እልክላታለሁ ብላው ስልኩን ዘጋችው ።
እባክሽ አትዝጊው ቆይ እንነጋገር እያለ በሩን ቆልፎ እየተጣደፈ
ሢሄድ ምኛት ሚሞሪውን ወሥዳ ጥላው ቢሆን ኖሮ ልጅታ
መጥፋቱን ብትሰማም ከሠቀቀን እንደማትድን አሥባ ቦርሳዋ
ውስጥ ለመክተት በወሠነችው ውሳኔ እንደ ህፃን ልጅ በመዝለል
ጮቤ ረገጠች••
ደስታዋን አጣጥማ እንደጨረሰች ወጣ ብላ ቁርስ ቢጤ
በመግዛት ከቀማመሠች ቡሀላ ለሊቱን ሣትተኛ ሥላደረች ገላዋን
ታጥባ ተኛች።
ከቀኑ 11 ሰአት ከ 40 ደቂቃ ሆኗል ንፋስ ለመቀበል ከቤት
ወጣች ከኮንደሚንየም የሚያሥስወጣውን ዋና አሥፓልት በመያዝ
ቁልቁል ወደ ቀለበት መንገድ ሄደችና ፊቷን ወደ ደብረዘይት
መውጫ አድርጋ ብዙ ከተጓዘች ቡሀላ ስትመለስ ዛሬም እዛ ቤት
ሌላ ባለታሪክ እንዳይይመጣና በሰላም እንድትተኛ ፈጣሪዋም
እየተማፀነች ሰፈሯ እንደደረሰች ድሬ ድሬ በማለት የሚጣራ የሰው
ድምፅ ሰምታ ዘወር ከማለታ የሆነ ባጃጅ አጠገባ ደርሶ ቀመ
ወድያው ነበር ያወቀችው ባለፈው እቃ ለመግዛት የወሰዳት ባጃጅ
ሹፌር ነበር አንተ እንዴት ነክ አለሁልሽ ጠፋሽ እኮ የገዛሽው
አስቤዛ ካላለቀ ከቤት አትወጭም እንዴ አላት ፈገግ አለች
ሰላምታ ከተለዋወጡ በሃላ ኬት እየመጣች እንደሆነ ጠየቃት ኬት
እንደምትመጣና አሁን ግን ወደ ቤት ልትግባ እንደሆነ ስትነግረው "
በይ ነይ ግቢ እሷን አድርሰናት እሸኝሻለሁ አላት አንድ ወፈርራምና
ክብ ፊት ያላት እጭር ወጣት ሤት ጭኗል ምኛት ባጃጁ ውስጥ
ገባች።
ተሳፋሪዋ መውረጃዋ ደርሶ ወረደችና ከያዘችዉ ትልቅ ቦርሳ
ውስጥ የመጣችበትን ሂሳብ ለመክፈል ብር በመፈለግ
ስለቆየችበት " አልታይ ካለሽ ለምን መብራቱን አታበሪውም?"
አላት "የምኑን?" አለች ተሳፋሪዋ "የቦርስሽን ነዋ መብራቱ ጠፍቶ
ነው ዛሬ ተረኛ ነሽ እንዴ "? የምን ተራ ? አለች ይበልጥ ግራ
በመጋባት ማለቴ መብራት በፈረቃ አደል ከዚህ ቤት ከሚያህል
ቦርሳሽ ብር ፍለጋ ስትደናበሪ ተረኛ ሆና መብራት ጠፍቶ ካልሆነ
ለምን አታበራውም ብዬ ነው ወይ ባትሪ ልስጥሽ እንዴ ሲላት
እንኳን ለኔ ቦርሳ ላንተም ኩርኩር መብራት አላስፈለጋት እቤት
ውስጥ የተሰቀለው መብራት ንፋስ ውስጥ እንደለኮሱት ሻማ
እየተስለመለመ ተቸግረናል! ጭራሽ ቦርሳሽ መብራት የለውም
ይላል እንዴ ! ቀልደኛ !ለከፋ መሆኑ ነው? ብላ ስትንጣጣበት ።
አረ የምን ለከፋ ለጎፋ ነው ስሚ እኔ ጥዋት ካላየኋት ቀኑን ሙሉ
የሚያፋሽገኝ ምርጥ ፍቅረኛ አለችኝ እሷን በሳምኩበት አፌ አንቺን
መልከፍ አይከብድም ሲላት •••
ወሬ አለብህ ዝም ብለህ የጫንካትን ሸኝ "ሆሆ..." ብላ ሂሳቡን
ወርውራለት ስትሄድ ምኛት ያፈነችውን ሳቋን ለቀቀችው•••
"አንተ ምን አርጊ ነው ምትላት?" አለችው ሳሳቋ መሀል
"አላየሽውም እንዴ የያዘችውን ቦርሣ ከመሸ ቡሀላ ከውሥጡ ብር
ለማውጣት እኮ ወይ መብራት ወይ ባትሪ ያሥፈልግዋል ለመሆኑ
እሄ ቦርሣ ምን እንደሚባል ታውቂያለሽ?" አላት ወደ ምኛት ፊቱን
አዙሮ "ያው የሴት ቦርሣ ነዋ ደሞ ሌላ ምን ይባላል" አለች ምኛት
እየሳቀች " ስንት አይነት የሴት ቦርሳ አለ አንዳንዶቻቹማ ቤቱን ከነ
ሙሉ እቃው አይደል እንዴ ይዘው የሚንቀሳቀሱት ለማንኛውም
እሄ አሁን ልጅታ የያዘችው አይነት ቦርሳ ባለ ባለሶስት መኝታ ቤት
ኮንደሚንየም ይባላል" ሲላት" አቦ አታብዛዋ አንተ ደሞ !
እየሳቀች። እስቲ ድገሚው አሁን ያልሽውን አፍሽ ሲጣፍጥ አላት።
ሂድ ወደዛ ሀይይ! አለችው።
ምኛትን ሢሸኛት ሠአቱ 2: 20 ሆናል ተደብቃ ወደ ምትኖርበት
ኬንደሚንየም ለመግባት ቁልፏን አንገቷ ላይ ጣል ከረገቻት ሻርብ
ጫፍ ላይ ነበርና ያሰረቻት ቋጦሮውን እየፈታች በሩ ላይ ደርሳ
ለመክፈት ስትሞክር ቤቱ ከውሥጥ ተቆልፎ ቁልፍ ሥላልተነቀለ
አልከፈት ብሏት ስትታገል ማነው የሚል የተኮላተፈ የወንድ ድምፅ
ከውሥጥ ሠማች አመዳ ቡን እለ ወድያው በሩ ከመከፈቱ በፉት
ጫማዋን አውልቃ በእጃ በመያዝ ቁልቁል ከነፈች..

?ክፍል 13 ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like? ማድረግ አይርሱ።

3 years, 3 months ago

​​​?ምኞት?

♠️ክፍል 11

.
.
.
ሚሞሪውን ከደበቀ ቡሀላ በፍጥነት ወደ ቦታው በመመለሥ
"እሄው አጥፍቼልሻለሁ አንቺ ነዝናዛ ወፍ " አላት ሻወር ቤት በር
ላይ ሆና ገላዋን እያደራረቀች " እሥቲ ማል"? አለችው " ሚጣ
ትሙት አጥፍቼዋለሁ" ሚጣ ፈረንጆቹ አገር እያለ የውለዳት ሤት
ልጁ ነች። እሥቲ አለችና ሞባይሉን ተቀብላ ያሉትን ቪድዮዋችና
ፎቶዋች በየተራ እያየች ምንም እንኳን ውጪ ብዙ ግዜ ብትቆይም
ኢትዮጲያዊ ነህ እሄ ነገር በኖርክበት አገር ምንም ማለት ላይሆን
ይችላል እዚህ ግን ኢትየጲያ ነው ሰው ከምንም ነገር በላይ
ለራሡ እና ለሀገሩ ክብር አለው እንደዚህ አይነት ነገር ደግሞ
የአንድን ሠው ክብር ብቻ አይደለም የሚያቆሽሸው" ሥትል እፍፍፍ
ፍልሥፍናሽን ተይን እንግዲህ" አለና ወደ ሽንት ቤት መሄድ
ሲጀምር እውነቴን ነው እናንተም ብትሆኑ የክብርን ጣእም
የምታጣጥሙት በሀገራችሁ ነው ከምንም ነገር በላይ ደግሞ
አባቢ እሄን ነገር ቢያውቅ አንተንም እኔንም ከመግደል ወደ ሃላ
አይልም ነገሩ እሡ በዚህ ነገር ቀሥሙ ሢሠበር ከማይ ሞቴን
እመርጣለሁ" አለች በሚያሣዝንና በሚያባብል የንግግር ቃና።
ምኛት ሠውየው ወደ ሽንት ቤት ሢገባ ተክለ ሠውነቱን በደንብ
አየችውና "እሄ አሣማ " አለች ከተደበቅሽበት ውጭና እነቂው
እነቂው የሚል ሥሜት እየተናነቃት ሢመለሥ ልጅታ አሁንም
ሞባይሉ ላይ ነች በቃ እንተኛ ግን ዛሬ ባለፈው እምቢ ያልሽኝን
ነገር ማረግ አለብን አለብን" ሢል
እባክህ እንድዛ አይነት ነገር አድርጌም አላውቅም ማረግም
አልፈልግም አታሥገድደኝ" አለች አይን አይኑን እያየች " ምንድን
ነው ቆይ ያ አፈቅረዋለሁ አገባዋለሁ የምትይው ፍቅረኛ ተብዬሽ
ወጣ ያለ ነገር አያሣይሽም እንዴ"? አላት እያላገጠ
እሱ ለሤት ልጅ ፍቅርም ክብርም ያለው ንፁህ ኢትዮጲያዊ ነው
እንደ አንተና መሠሎችህ በባእድ ሀገር እሥነዋሪ ድርጊቶች
አልተመረዘም "
አገጯን ይዞ ቀና እያረገ ምን ምን ፍቅር ክብር ደሞ እሄ ወይ
ገንዘብ የለው ወይ ንቃት የለው ደሀ ደሞ እሡ ለምን ተነካ ነው
እምታፈጭብኝ " አለ በውሥጡ ቆይ ያንን ቪድዮ ልኬ
እገላግልልሽ የለ አለና የፌዝ ሣክ ሣቀባት
ተብከነከነች የቪድዮው ነገር ይዛት እንጂ ልጅታ በቀላሉ
እምትበገር እይደለችም "እናንተ ብር ያላችሁ ምን አረጋችሁ
በብራችሁ ሀይል በሚሥኪኖች ሥቃይ ከመደሠትና የሠይጣንን
ፍላጎትና እቅድ ከማሥፈፀም ውጪ "
ሥትለዉ "አንቺ ያባቷ ልጅ !! አለና ባንድ እጁ አንገቷን ባንድ እጁ
ሁለት እግሯን በመያዝ ከተቀመጠችበት ብድግ አድርጎ
ከተሸከማት ቡሀላ ወደ ምኝታ ቤት ይዟት በመግባት ንዴት እና
እልሁን ይወጣባት ጀመር።
ምኛት ሠውነታን ውርር አደረጋት ሠውነታቸው ከፍራሽ ጋር
ሢፋተግና ትንፋሻቸው ሢቆራረጥ ይሠማታል ልጅታ ከአቅሟ በላይ
እንደሆነባት የምታወጣው የታፈነና የተጨነቀ ድምፅ ይመሠክራል
ምኛት ከዛ በላይ ቆማ መሥማት አልቻለችም ወደ ፍራሻ በመሄድ
ጆሮዋን ይዛ ተቀመጠች ።
መሥማት የሌለባትን ነገር በመሥማታ የጥፋተኝነት ሥሜት
ተሠማት ግን እዛ ቦ ታ ላይ የተገኘችዉ ተጥላ እና ተገፍታ እንጂ
ፈልጋ አልነበረም መርጣ ሣይሆን አማራጭ ሥላልነበራት ነበር
ተከፍቶ በማያውቅ እና በተረሣ ጭለማ ቤት ውሥጥ የምትኖረው

ከለሊቱ 8: 30 ሆኗል የቀጭና ልጅ ትንፋሽ ባይሠማም ሰውየው
ግን እያንኮራፋ ነው ምኛት ከተደበቀችበት እቃ ቤት በጥንቃቄ
ወጣች የሳሎኑ መብራት አልጠፋም ቀጥታ ሚሞሪው ከተደበቀበት
ካነሣች ቡሀላ ቆም ብሏ በማሠብ በሠከንዶች ውሥጥ ምን
ማድረግ እንዳለባት ወሠነችና ሶፋው ላይ የተቀመጠውን የልጅታን
ቦርሳ ከፍታ ሚሞሪውን ውሥጡ በማረግ ብ
በጥንቃቄ ወደ ክፍላ በመመለሥ ተኛች።
ሰውየው ማታ መጠጥ አብዝቶ ሥለነበር ለመሽናት ተነሥቶ ወደ
ሽንት ቤት ሢሄድ..
ተነሥቶ ወደ ሽንት ቤት ሢሄድ ምኛት ወድያው ነበር የሠማችው
ፍርሀት ሥላለበት በደንብ እራሣን ጥላ አልተኛችም "አምላኬ ሆይ
አውጣን አለች ሢመለሥ ሚሞሪው አለመኖሩን ካየ ምን ሊፈጠር
እንደሚችል እያሠበች።
ቀስ ብላ ተነሣችና ለማንኛውም ብላ ያሥቀመጠችውን ርዝመቱ
አንድ ሜትር የሚሆን ወፍራም ዱላ አንሥታ በመያዝ ወደ በሩ
ተጠጋች ሢያጣው አምጪ ይላታል፡ አልወሠድኩም ሥትለው
ቢያንቃት ማንም እንደማይደርሥላት አሠበችና "መቸሥ ሢገላት
ዝም አልልም ለሁለት አያቅተን" እያለች ወደ እቃ ቤቱ በር
ተጠጋች።
ሠውየው አይኑን እንኲን በአግባቡ ሣይገልጥ ነበር ሽንቱን ሸንቶ
ወደ መኝታው የተመለሠው ወድያው ማንኮራፋቱን ቀጠለ።
ቀጭና ልጅ ጥዋት መነሣት እንደማትወድ ሥለሚያውቅ ሢነሣ
እንደሚያገኛት እርግጠኛ ቢሆንም ልጅታ ግን ቀድማ የሥልኲን
ማንቂያ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ድምፅ ከጥዋቱ 12፡30
እንዲቀሰቅሳት ሞልታው ሥለነበር ገና ማቃጨል ሢጀምር ተነሥታ
ማንቂያውን ካጠፍች ቡሀላ ማታ የሠውየውን ሥልክ ሥትፈትሽ
ሚሞሪ እንዳልነበረው አሥተውላ ሥለነበር "እሥቲ ዝም ብዬ
ከምወጣ ምናልባት ብላ" የሠውየው ልብሶች ኪሥ ውሥጥና
የሶፋውን መቀመጫዎች እያነሣሣች ብትፈልግም ሥላጣች " በቃ
የለውም ይሆናል ሣይነሣ ብሄድ ይሻላል" አለችና ቦርሣዋን
አንሥታ በሩን ቀሥ ብላ በመክፈት ተፈተለከች።
ምኛት ሠውየው ሢያንኮራፋ ሥለሚሠማት የወጣችው ልጅታ
እንደሆነች እርግጣኛ በመሆኗ ጋደም ካለችበት ቀና ብላ
በመንበርከክ ፈጣሪዋን አመሠገነች።
ከእንቅልፉ ብንን ሢል ከጥዋቱ 2:30 ሆኗል አጠገቡ አለመኖሯን
አሥተዋለና ቀና ብሎ ማታ እያወለቀ ያሽቀነጠረውን የልጅታን
ልብሥ መሬት ላይ ፈለገ ልብሣም የለም እንዴት ነው ዛሬ
በጥዋት የነቃችው እያለ ተነሥቶ ወደ ሣሎን ሚሞሪውን ወደ
አሥቀመጠበት በመሄድ ምንጣፉን ገለጠው በድንጋጤ አድሮበት
የነበረው ሥካር ለቀቀው....

..........ይቀጥላል........

3 years, 3 months ago

​​?ምኞት?

♠️ክፍል 10

.
.
.
ሚኪ ከትንሹ አጠገብ ወዳለው መሥስኮት ሄደና ወደ ውጪ
እየተመለከተ እኔኮ እማረባና እራስ ወዳድ ሠው ነኝ አለና አቀረቀረ ።
ትንሹ ሚኪ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ምኞት ደብዳቤ
ልካ እንደነበርና ብሩክ ጋር እንደሆነ መናገር ፈራና ቁልፉን
ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦለት ወጣ። እቤት ገብቶ ቢተኛም ሚኪ
ሥለ ምኞት የጠየቀውን ጥያቄዎችና፡ ፊቱ ላይ ያየውን የፀፀትና
የጥፋተኝነት ስሜት ግን መርሳት አቃተው።
ምኞት እሥከ ቅዳሜ ጠዋት ብትጠብቀውም ሚኪ አልደወለም
ተሥፋ ቆረጠች ሞባይላን በመውጣት
ያቀደችውን በሙሉ አደረገችው።
ዛሬ ቅዳሜ ሥለሆነ ሠው ሊመጣ እንደሚችል እያሠበች እቃ
ቤቱን በመዝጋት እዛው ቤት ውድጥ
የነበረ አንድ ተጀምሮ ያላላቀ ግማሽ ከረጢት ስሚንቶ ጎትታ
በማሥደገፍ ቀኑን ሙሉ የሰው ኮቴ እያዳመጠች ሥትጨነቅ
ብትውልም የመጣ ሰው የለም ።
መሸ ልክ ከምሽቱ 5፡15 ሲሆን እንቅልፍ ሸለብ እንዳረጋት በሩ
ውስጥ ቁልፍ ሲገባ ድምፅ ሰማችና ተመንጭቃ በመነሳት
በጭንቀት እቃ ቤቱ በር ላይ ተለጥፋ ስታዳምጥ አንድ ጎርነን ያለ
ድምፅ ያለው ወንድ ሲያወራና አብራው ያለችው ሴት ስትስቅ
ሰማች ወድያው በሩን ከፍተው ወደ ሳሎን ሲገቡ በቀዳዳ እንዲት
ቀጭን ወጣት ሴት የሰማይ ስባሪ ከሚያክል ወፍራም ወንድ ላይ
እንደ ጨርቅ ተለጥፋ እየተጓተቱ ሲገቡ አየችና የልቧ ትርታ
ድምፅ ለሠዎቹ የሚሰማ እስኪመስላት ድረስ ፍርሀት ወረራት።
እንደገቡ ትልቁ ሶፋ ላይ ጎን ለጎን ተቀመጡና የያዙትን ውስኪ
መጠጣት ጀመሩ "እዚህ ቤት በቅርብ መተሀል እንዴ "? አለችው
ለምን ጠየቅሽኝ"? አላት ጎርነን ባለ ድምፁ" ልክ ባለፈው ስመጣ
እንደነበረው የተዘጋ ቤት ጠረን የለውም " ስትለው " እዚህ ቤት
እኮ የሚመጣው ሠው አይታወቅም ቁልፍ ያለው አራት ሠዎች ጋር
ቢሆንም ሁሉም በየፊናዉ ለተለያየ ሠው እየሰጠ ለተለያዩ የግል ጉዳዮች ይጠቀሙበታል" አላት።
"ካንተ እና ከዛ አረመኔ ጓደኛህ ዉጪ የሚመጣ አለ ማለት ነው
ደሞ ምን ጉዳይ ኖሯቸው ያውቃል ዲያስቦራው ከውጪ ወደ ሀገሩ
ገብቶ ለአገር በሚጠቅም ነገር ላይ ኢንቨሥት ያረጋል ያ ጓደኛህና መሰሎቹ የሀገራቸውን ሴቶች መጫወቻ ያደርጋሉ"
ስትለው•••
አሁን አንቺ ምንሽ ተነካ ነው ለዛች በረሮ ጓደኛሽ መቆርቆርሽ ነው
ምላሷን እና እግሯን ብትሰበሰብ ኖሮ እዚህ አምጥተው እንደ ህፃን
ልጅ አይገርፏትም ነበር" አለ ።
አረመኔዋች ናቸው በእዉነት ለሳምንት ያክል ቁጭ ለማለት እኮ
እስክትቸገር ነው የገረፏት እኔኮ ሚገርመኝ እንደዛ ስትጮህ ሰው
የሚባል ሊያስጥላት አለመምጣቱ ነው" እለች ።
"ቤቱ ኮ ኮንደሚንየም ነው ረሳሽው እንዴ ሁሉም ቤቱን ዘግቶ
የራሱን ኑሮ ነው እሚኖረው እሄ መንደር ውስጥ ያለው ማህበራዊ
ኑሮ እዚህ የለም ጉርብትና ብሎ ነገር ታሪክ ሆኗል መንግስት
በቋንቋ ላይ ከተመሰረተው ፌደራሊዝም ቀጥሎ ህዝቡን የከፋፈለው በኮንደሚንየም ይመስለኛል ሳስበው። አጠገብ ለአጠገብ እየኖሩ ሰላም አይባባሉም ።
በተለይ ብዙ ግዜ በሩ የሚዘጋ ከሆነ እሚኖረውና እንግዳ ሆና
የመጣው ተለይቶ አይታወቅም በዛ ላይ ከዚህ ቤት ቀጥሎ ያሉት
ተከታታይ ሁለት ቤቶች ጒደኞቻችን ናቸው የያዙአቸው ታዲያ
እንጥሏ እሥኪወርድ ብትጮህ ማን ይደርስላታል" አለ።
ምኞት የለሊቱ ፀጥታ የሚያወሩት በሙሉ በደንብ እንዲሰማት
ረድቷቷል "ወይ ጉድ ለካ እነዚህ ሁለት ቤቶች ተከፍተው የማያውቁት ለዚህ ነው እነዚህ አውሬዎች" አለች
ነገሩ አንተም የጓደኛህ በህሪ አየተጋባብህ ነው አለች ቀጭኗ
ወጣት "እንዴት እኔ እና እሱን ምን አንድ አረገን " አለ ቆጣ ብሎ
" በቃ ተወው" አለች ፈርታ " ተናገሪ ስለ ቪድዮው ለማውራት ነው አይደል እኔ ሆነ ብዬ ነው እንዴ ያንን ቪድዬ የቀረፅኩት እኔም አንቺም በጣም ሰክረን ነበር ግንኙነት እያደረግን ዝም ብዬ
እንደቀልድ ሪከርድ አረኩት አለቀ ያለፈ ነገር ነው" አለ እያፈጠጠባት።
"አስበህበት ካልሆነ እንደ ቀልድ ከተቀረፀ እንዴት የኔ ሁለመናዬ እየታየ የአንተ ከወገብ በታች ብቻ ሊገባ ቻለ ደሞ ዛሬ ለመገናኘት እንደማይመቸኝ ስነግርህ ያንን ቪድዮ ዩቲዩብ ወይም ፌስቡክ ላይ
ላይ እንድለቀው ትፈልጊያለሽ ብሎ ማስፈራራቱ ለምን አስፈለገ"
አለች።
አሁን ማልቀስሽን አቁሚ በቃ ካሁን ቡሀላ እኔም ላገባ ስለሆነ
እሄ የመጨረሻችን ነው ቩድዮውንም አጠፋዋለሁ" አላት
ምኞት ፡ ወይ ፈጣሪዬ በቀረፀው ቪድዮ እየስፈራራ ነው እቺን አንድ ፍሬ ልጅ እሚጫወትባት " አለችና ፍርሀቷ ወደ እልህ እና ንዴት ተቀይሮ በቆመችበት መንቀጥቀጥ ጀመረች።
"አሁን ማላዘንሽን አቁሚና ጠጪ" ሲላት " እኔ በራሴ እጅግ አፍራለሁ ያንን ቪድዮ ሳስበው ቆሻሻነት ይሰማኛል ያን ቀን ምን
አዳስነካከኝና እዚህ ቅሌት ውስጥ እንደገባሁ አላውቅም ያባዬ
የቅርብ ጓደኛና ባለውለታው ነክ ብዬ ነበር ግብዣህን የተቀበልኩት•••
እባክህ አጥፋው እኔ ከዛ ውጪም ቢሆን እንደፈለከው እሆንልሀለሁ
ካለበለዝያ ግን በዚህ ምክንያት ምንም ነገር ለማድረግ ብትሞክር እራሴን እንደማጠፋ እወቅ " እለችው እና አይኗን እየጠራረገች ሻወር ለመውሠድ ገባች።
[የሻወር ቤቱን በር መዝጋቷን ካረጋገጠ ቡሀላ ቪድዮው ያለበትን
ሚሞሪ ካርድ ከሞባይሉ በማውጣት ኮርነር ላይ የመሬት
ምንጣፉን በመግለጥ ሲደብቅ ምኛት አየችው•••

ይቀጥላል ........

3 years, 3 months ago

"ስንወለድ ሰዎችን ሁሉ አውቀን አይደለም፡፡ ከሰዎች ጋር በብዙ መንገዶች እንተዋወቃለን፡፡ ለሁሉም ሰው ተገቢውን ቦታ ስንሰጥ ለህይወታችን ትክክለኛውን ሰው እናገኛለን፡፡"

?????????????

???? ??? @yekeberedaha

?????????
? @mood_zeki

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion ? @Share_Home

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 6 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 8 months, 3 weeks ago