ዝጉ መንገድ ሚዲያ

Description
''ዝጉ መንገድ ሚዲያ '' የዚህ ቻናል ዓላም ተከታዮቹን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው፤ በግል ስብዕናቸው፤ በቢዝነስ ሕይወታቸው እና በሙያዊ ሕይወታቸው ላይ የሚያስፈልጋቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲሁም ጥበብ ለማጎልበት የሚሠራ ድንቅ ቻናል ነው።
የ ''ዝጉ መንገድ ሚዲያ''አስተማሪ ቪዲዮችን ለምትፈልጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ!!!
https://youtu.be/OIhbFJUy0Nw?si=6hhr3VOes5XEnZO
We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

1 year, 6 months ago

#ጾመ_ነነዌ

#ነነዌ «ታላቋ ከተማ»

ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ በአሁኗ ኢራቅ አከባቢ የምትገኝ፤ በኃያሉ ናምሩድ የተመሰረተች የአሥራውያን ዋና ከተማ ነበረች። (ዘፍ 10፡11) በጊዜው ዓለም ላይ ከነበሩ ታላላቅ ከተሞች አንዷ የነበረች ነነዌ፤ ውብ ቅጥሮች ያሏት፣ ኃያላን ነገስታትን የማረከች፣ ብዙ መንግሥታትን የተፈታተነችም ነበረች።  በሰለሞን ልጅ በሮበዓም ዘመን ሰሜን (እስራኤል) እና ደቡብ (ይሁዳ) ተብላ ከሁለት በመከፈሏ ብርታት ያጣችው የእስራኤልን መንግሥት ስትፈታተን እና ስትወጋም ቆይታለች።

ነነዌ 120ሺ ህዝብ የሚኖርባት የቅጥሯ ስፋት ወደ 12ኪ.ሜ ገደማ የሚሆን ከተማ ነበረች። ምንም እንኳን ነነዌ በዓለም ዘንድ ቁንጮ ብትሆንም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ኃጢያቷ የበዛ፣ ከአምላክ መንገድ የወጣች፣ ተመዝናም ቀላ የተገኘች ነበርች። ሳይመክር ሳያስመክር የማይጣላዉ እግዚአብሔርም ቃሉን ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል ላከ፤ «ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሒድ፥ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ» አለ። (ዮናስ 1፡1)

#ከእግዚአብሔር_የሸሸው_ነቢይ 

ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፤ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ከሞት ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃንም፣ ይህ ልጅ እንደ ሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል (1ኛ ነገ 17፥19)፡፡ የዚህ ነቢይ ስሙም «ዮናስ» ትርጓሜውም "ርግብ" ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃልም «ተነስተህ ወደ ነነዌ ሂድ፣ እንዲህም ብለህ ስበክ "ነነዌ እስከ ሦስት ቀን ትጠፋለች"» ሲል ወደሱ መጣ። (ዮና 1፡1) ዮናስ ግን «አንተ መሐሪ ነህ፣ በእሳቱ ፋንታ ምሕረትን ብታወርድ፤ አንተ መሐሪ፣ እኔ ደሞ ነቢየ ሐሰት እባላለው» ብሎ ከጌታ ፊት ሽሽት ጀመረ።

ነብዩ ዳዊት   «ከመንፈስህ ወዴት እሔዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።»   (መዝ 139፡7) ያለውን እግዚአብሔር፤  ከደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ዮናስ ግን እሱን ሽሽት ወድ ተረሴስ ኮበለለ። {ነቢየ እግዚአብሔር ዮናስ ሆይ? ከእግዚአብሔር ወዴት ትሸሻለህ? ተርሴስ ከእግዚአብሔር ትሰውረሃለችን? በእግረ ዳዊት የተተካህ ነቢይ ሆይ፣ ዳዊት «ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ» ያለውን አላስተዋልክምን?}። ምንም እንኳን ነቢዩ ከእግዚአብሔር ሽሽት ወደ ቴረሴስ በመርከብ ቢጓዝም፣ አምላክ ግን በዓሳ አንባሪ ሆድ ወደ ነነዌ ወሰደው። በዚህም በዓሳ አንባሪ ሆድ ዉስጥ ሦስት ቀን እና ሦስት ለሊት ቆይቶ ነነዌ ደረሰ። ይህም የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት የመቃብር ስለመቆየቱ እና  ከሙታን ተለይቶ ስለ መነሳቱ ምሳሌ ሆነን። (ሉቃ 11፡30)

#በሦስት_ቀን_ውስጥ_ነነዌ_ትገለበጣለች

ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገባ፤ ጮኾም፦ «በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች» አለ (ዮናስ 3፡4)። እንዴት የሚጨንቅ፣ የሚከብድ ቃል ነው? የዮናስ ስብከት ምህረት የለውም፣ 'ንስሃ ግቡ' ብሎ ለንስሃ አይጋብዝም።  እንድ ነቢዩ ኤርሚያስ «ስለ ሕዝብ ስለ መንግሥትም እነቅል አፈርስም አጠፋም ዘንድ በተናገርሁ ጊዜ፥ ይህ ስለ እርሱ የተናገርሁበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፥ እኔ አደርግበት ዘንድ ካሰብሁት ክፉ ነገር እጸጸታለሁ» ብሎ ተስፋ የሚሰጥ ቃልም  አይደለም።

የነነዌ ህዝብ ከአህዛብ ወገን ናቸው፣ ዮናስን አያቁትም የሱን አምላክ አያመልኩትም፤ ብቻ ለሃገሩ እንግዳ የሆነ አንድ ዕብራዊ ወደ ከተማዋ ገብቶ «ነነዌ ትገለበጣለች» አለ። የነነዌ ሰዎች እንዴት በኛ ላይ ታሟርታለህ ብለው ዮናስን አልሰቀሉትም (አይሁድ ሊያድናቸው የመጣውን መሲህን ሰቅለውታልና)፣ በመጋዝም አልሰነጠቁትም (አይሁድ የእግዚአብሔርን የምህረት ቃል ሊያቀብላቸው የመጣውን ልዑለ ቃል ኢሳይያስን በመጋዝ ሰንጥቀውታልና)። የነነዌ ሰዎች እንደ ኖህ ዘመን ሰዎች በኃጢአት ውስጥ ሆነው የቀራቸውን ጊዜ አልቆጠሩም፣ ይልቁንም በደላቸውን ለመቁጠር ተፋጠኑ እንጂ።

#የምህረት_አዋጅ

ነነዌ ከቤተ መንግስት እስከ ቤተ ከህነት፣ ከንጉስ እስከ አሽከር፣ ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከሰው እስከ እንስሳ ማቅ ለበሰች። ሃያላን መንግስታትን ያንበረከከች ነነዌ፣ በአንድ ዕባራዊ ተብረከረከች። ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊው እንዲህ ይላል ‹‹የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፣ ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን፡፡የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች፡፡ ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ››። ነነዌ ለሦስት ቀን ንስሃ ገባች። እግዚአብሔርም በምሕረት ከእሷ ተመለሰ በነቢዩ ኤርሚያስ እንደተናገረውም ሊያደርግባቸው ካሰበው ተጸጸተ።

#እኛስ

ወገኖቼ! እኛስ? በደላችን ከነነዌ ሰዎች አልባሰምን? ክፋታችን በእግዚአብሔር ፊት አልወጣምን? እግዚአብሔርስ እንደ ዮናስ ነቢይ አስነስቶ አልገሰጸንምን? እንደ ምሕረቱ ባይሆን ኖሮ እንደ ሥራችን ቢሆን ይሄኔ በእሳት አንጠፋም ነበርን?

ወዳጆቼ እንደ ነነዌ ሰዎች፣ እኛም ማረን እንበለው፣ መሐሪ ነውና ይምረናል፣ በእንባ ወደሱ እንመለስ። የቀረንን ዘመን ሳይሆን በደላችንን እንቁጠር። «የመዳን ቀን ዛሬ ነው» ይላል መጽሐፍ፣ ዛሬን ወድሱ እንመለስ። ወዳጆቼ! ይሄን ጾመ ነነዌ ስንጾም፣ በግብርም በኅሊናም ነነዌን እንምሰል።

1 year, 7 months ago

_ ” ተሰወረ እንጂ አልሞተም “በሚለው አስተሳሰብ ላይ ደግሞ የቅዱስ ያሬድን ሕይወትና ሥራዎቹን ያጠኑ ፪ ጸሐፍት እንዲህ ይላሉ።”ወአዕረፈ እግዚአብሔር እምኩሉ ግብሩ ዘአኅዘ ይግበር።ንዑ ኀቤየ ስሩኃን ወክቡዳን ፆር ወአነ አዐርፈክሙ ።ባለው መሠረት ከያዘው ከባድ ገድል ከማስተማር ድካም ከገድሉ ኹሉ ዐረፈ ተሰውሮ ቀረ ማለት ነው እንጂ አዕረፈ ማለት ትርጉሙ ሞተ አለመሆኑን በጠቀስነው ማስረጃ ገልጸናል።[፱]..ወከመዝ ነበረ ቅዱስ ያሬድ ካህን ዓቢይ ወብፁዕ እሰከ አመ አዕረፈ በክብር…በከመ ይቤ ዳዊት ነቢይ ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር ፤ነቢዩ ዳዊት የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ነው እንዳለ ንኡድና ክቡር የሆነው ቅዱስ ያሬድ ካህን በክብር እስከረፈበት ጊዜ ድረሰ …[፲]

⇛ የቅዱስ ያሬድ ዜማ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ብቸኛው ሰማያዊ ዜማ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺህ ሦስት መቶ ዘመናት በላይ ስትጠቀምበት ኖራለች ፣ ወደፊትም ትጠቀምበታለች ።የቅዱስ ያሬድ ዜማ አልፋ (የመጀመሪያው) እና ዖሜጋ (የመጨረሻው) ብቸኛው ሰማያዊ ዜማ ነው። ⇛ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሰማያዊ በመሆኑ ሕሊናን ወደ ሰማያት የመንጠቅ ፣ሥጋዊ ደስታንና ኃጢአትን ከማሰብ የመጠበቅ ሰማያዊውን ድንቅ የምስጋና ምሥጢር የማሳወቅ ታላቅ ኃያል አለው።

የቅዱስ ያሬድ ዜማ ከሌሎች ዜማዎች የሚለይበት ጠባይ አለው።

፩.በአዝማናት ተለይቶ በወቅት ተከፋፍሎ የሚዜም ነው።

፪.የተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር አለው።

፫.ዜማው አሳብን የሚገዛ ፣ከሥጋ ይልቅ በመንፈስ መመላለስን የሚያስተምር ነው።

፬.ዜማው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሥጢር የተሞላ ነው። ቅዱስ ያሬድ ” .ቅድስት ወብፅዕት ፣ከብርት ወልዕልት፣ አንቀጽ ብርሃን መዓርገ ሕይወት ወማኀደረ መለኮት በማለት የደረሰው ድርሰት ” አንቀጸ ብርሃን” (የብርሃን መውጫ) ተብሎ ይጠራል ።

✍️ ቅዱስ ያሬድ አንቀጸ ብርሃንን ሲያዜም ይነጠቅ (ከምድር ከፍ ይል )ነበር።

-ከሦስቱ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶች የወጣ ዜማ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊ መኾኑ እየታወቀ ፣በዜማው እየተጠቀምንበት ሳለን የሚገባውን ያኽል ከዓለም ኅብረተሰብ ጋራ ሳናስተዋውቅለት ቆይተናል።

✍️ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰጠው ጥቅም እጅግ ብዙ ነው ፦

፩.የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ ተችሏል ። ዜማው በየትኛውም አካባቢ የምትገኝ ኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ አይነት መዝሙር ፣አንድ አይነት ቅዳሴ፣አንድ አይነት ሥርዓት በአንድ ቀን ማቅረብና መፈጸም እንድትችል አስችሏታል፦

፪.ትምህርትና ሃይማኖትን ለማጠናከር ፦የሃይማኖት ትምህርቱን በዜማ አቀነባብሮ መድረሱ በጣም ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል ።

፫.በሥርዐተ ጸሎት ፦ከዓመት እስከ ዓመት ለሚከናወነው ማንኛውም ሥርዐተ ጸሎት ዋናው መሪው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ነው።

፬.በሀገር ሀብትነት እና በጎብኝዎች መስብሕነት

-በበዓላት ከሚቀርቡት ዝግጅቶች አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው።ገቢ በማስገኘት ትልቅ ጥቅም አለው።[ 👉፮ ]

አንዳንድ የውጭ ሀገራት ጸሓፊያንና የታሪክ መንታፊዎች ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊ አይደለም ለማለት ዳር ዳር ማለታቸው በተውሶ ልብስ ለማጌጥ እንደ መሞከር ነው ።

ኢትዮጵያውያን ሆይ! ዕንቁ የሆነውን ሀብታችን መጠበቅ ይገባናል። ከኤዶም ገነት ከእግዚአብሔር ተልከው ፫ ወፎች በሰው አንደበት “ብፁዕ ያሬድ ! ብፅዕት ከርሥ እንተ ጾረተከ ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናከ ፣የተመሰገንክና የተከበርክ ያሬድ ሆይ! አንተን የተሸከመች ማሕፀን የተመሰገነች ናትአንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው” በማለት ተናገሩት።[👉 ፯ ]

ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ የደረሳቸው የዜማ መጻሕፍት ፭ ሲሆኑ እነርሱም :ድጓ፣ጾመድጓ፣ምዕራፍ ፣ዝማሬና መዋሥዕት ናቸው።እነዚህ የዜማ መጻሕፍት በስንዷዋ እመቤት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዓመት እሰከ ከዓመት እንበለ አጽርዎዖ (ያለ ዕረፍትና ማቋረጥ ) እግዚአብሔር የሚመሰገንባቸው ድርሰቶች ናቸው።

✧ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከስድስተኛው ምዕት ዐመት የመጀመሪያ አጋማሽ እስከ ዘመናችን ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን የምትቀድስበት ፣አምልኮቷን የምትገልጽበትንና ለአማኞቿ መንፈሳዊ አገልግሎት የምትሰጥበትን ጣዕመ ዜማ ያዘጋጀ ታላቅ ሊቅ ነው።

ቅዱስ ያሬድ የዜማውን ድርሰት ያዘጋጀው ከብሉይ ኪዳንና ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ፣ከመጻሕፍተ ሊቃውንትና ከመጻሕፍተ መነኮሳት ፣እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገው ከተዘጋጁ ሌሎች አዋልድ መጻሕፍት እየጠቀሰ ፣ትርጉም እየሰጠና እያነጻጻረ እንደኾነ የታወቀና ኹሉም ሊቃውንት የሚስማሙበት ነው [👉 ፰]

☞ ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻ ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የቅዱስ ያሬድ ሕይወቱን እና ሥራዎቹን በሚዘክረው መርሐ ግብር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ (ዶ/ር) ተገኝተው “..ዛሬ በዓል ላይ ተገኝተን ስለቅዱስ ያሬድና ሥራዎቹ ስናወሳ ጊዜውም ሰዓቱም ስለማይበቃ በአንድ ቀን ተናግረን አንጨርሰውም ገና ጀመርነው እንጂ “ነበር ያሉት ።[👉 ፲፪ ]

✧ አንድ ጸሐፊ “ዛሬ በርካታ ወጣት የቤተ ክርስቲያን ልጆች በጸሎት ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒደው እንደ ሥርዓቱ ከቆሙ በኋላ ለሚቀርበው ጸሎት ባይተዋር ሁነው ሲደናገሩ ይታያሉ ።

↳ መንፈሳዊ ቅንዓታቸው ጎልምሶ እንሳተፍ ቢሉ እንኳን መሠረታዊውን የቅዱስ ያሬድን ዜማ ተከትለው መዘመር ስለሚቸገሩ በግላቸው የሚቀምሯቸውን ዜማዎች ያዜማሉ፤ካልሆነም በሰፈር በትምህርት ቤት ወደውም ሆነ በግድ በሚሰሟቸው ዓለማዊ ዜማዎች የታጀበ ሊያቀርቡ ይዳዳቸዋል (👉ሐመር መጽሔት _1994፥21) በማለት የሰነዘሩት አስተያየት የቅዱስ ያሬድ ዜማ ወደ ሚቀጥለው ትውልድ እንዳይተላለፍ ከፊቱ ትልቅ ጋሬጣ መኖሩን ይጠቁማል ። አበው “ባለቤት ካልጮኽ ጎረቤት አይረዳም” ይላሉ ። ስለዚህ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ተጠብቆ ወደሚቀጥለው ትውልድ እንዲተላለፍ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ምእመናን ድረስ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል።

#የማጣቀሻ መጻሕፍት፦

፩_የቅዱስ ያሬድ ዜና ሕይወት በተለያዩ ጸሐፍት

ሥራዎች -(ዲ/ን ሰሎሞን ወንድሙ፣መስከረም ፲፱፻፺፰ ዓ.ም)

#ያሬድና ዜማው ፦ሊቀ ካህናት ጥዑመ ልሳን ካሳ ፣(፲፱፻፹፩ዓ.ም )

፪_ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ፦_በግእዝና አማርኛ ፦መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ ጌታቸው ( ፳፻፲፭ ዓ.ም)

፬-ነገረ ቅዱሳን _፪ (ማኅበረ ቅዱሳን )፦፲፱፻፺፰ ዓ.ም ፦ገጽ_፳፰

፭_ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ__.፩(ቤክዕ_፫፻)፣ማኀበረ ቅዱሳን _፲፱፺፮ዓ.ም

_፮.የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ቅዱስ ያሬድ ፦ታደሰ ዓለማየሁ(መጋቢት ፣፳፻፭ ዓ.ም)

፯.መጽሐፈ ስንክሳር _ግንቦት ፲፩.

፰.የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት ቁ.፫ _ነሐሴ-፳፻፭ ዓ.ም ፤ (ማኅበረ ቅዱሳ)

፱.ጥንታዊ ሥርዐተ ማኀሌት ወአቡነ ያሬድ ሊቅ (ልሳነ ወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ) (፲፱፻፺፯ .፻፸፰);

_፲.መንግሥቱ ከበደ (ግራአዝማች) -ገድለ ቅዱስ ያሬድ፦፲፱፷፩ ገጽ_፲፩

፲፩.የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች ቅጽ ፩ -በሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት(ዲ/ን)፦፳፻፲፪”ዓ.ም

፲፪.ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከመስከረም ፲፭- ፴ ቀን ፳፻፩ዓ.ም

1 year, 7 months ago

ቅዱስ ያሬድ ፭፻፭ ዓ.ም ሚያዝያ ፭ ቀን በአክሱም ከተማ ተወለደ :ብሔረ ሙላዱ አክሱም ነው ። የቅዱስ ያሬድ ሐረገ ትውልድ ከካህተ አክሱም ወገን ነው።ከአዳም ፮ ኛ ትውልድ በሆነው በ፮ ኛ ሰው በመላልኤል ልጅ በያሬድ ስም “ያሬድ” ተብሎ እንዲጠራ አደረገ ።(ዘፍ.፭፥፲፭)

አባቱ አብዩድ(ይስሐቅ)፣እናቱ ክርስቲና ወይም ታውክልያ ይባላሉ ።[ 👉 ፩] በሌላም በኩል አባቱ እንበረም እናቱ ትውልያ ይባላሉ የሚል ታሪክም አለ።[፲፩] አባቱ የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር።በተወለደ በ ፯ ዓመቱ አባቱ ዐርፎበት ከአጎቱ አባ ጌዴዎን ጋር እየተማረ ለ፳፭ ዓመታት ተቀምጧል ።

☞ ያሬድ ማለት ንህብ ማለት ።ንህብ የማይቀስመው አበባ እንደሌለ ሁሉ ያሬድም ከመጻሕፍት የማይጠቅሰው የለምና። አንድም ያሬድ ማለት ረዐየ ምሥጢር ነጻሬ ኅቡዓት ማለት ነው።ረዐየ ምሥጢር አለ የመላእክት ምሥጢራት የነበረውን ጸዋትወ ዜማ አምልቶና አስፍቶ ይናገራልና ። ቅዱስ ያሬድ በተወለደ በ ፯ ዓመቱ አባቱ አብዩድ ስለሞተ እናቱ ክርስቲና የአክሱም ገበዝ ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እንዲያሳድገውና እንዲያስተምረው አደራ ብላ ሰጠችው።

⇛ ቅዱስ ያሬድ ቅዱሳት መጻሕፍትን በቃሉ ይዞ ሲያስተምር የትምህርቱን ጥራት ፣የሃይማኖቱን ጽናት ፣ደግነቱንና ትዕግሥቱ፣ትሕትናውና ተልእኮው በመምህሩና በካህናቱ ተመስክሮለት የአክሱም ጳጳስ አባ ዮሐንስ ሢመተ ዲቁና ሾመው። ቅዱስ ያሬድ በአክሱም ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዱቁና አገልግሏል። በቅዱስ ያሬድ ዘመን ከተለያዩ የሮምና የታናሿ እስያ አገሮች የተወጣጡ ተስዐቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አክሱም ከተማ ውስጥ ቤተ ቀጢን በተባለው ጉባኤ ቤት ሲኖሩ የቅዱስ ያሬድን ትምህርት ቤት ለግእዝ ቋንቋ ዕውቀታቸው ዋና ምንጭ ነበረ ።[ ፲፫ ]

⇛ በዘመኑ የመዝሙር አገልግሎት ይቀርብ የነበረው አይሁድ በምኩራባቸው ፣ቅብጣውያንም በቅዳሴያቸው እንደሚያሰሙት የማስተዛዘል አይነት ዜማ እንጂ ድምፅን ከፍ አድርጎ የሚያሰሙት ዜማ አልነበረም ( 👉 ጥዑመ ልሳን ካሳ1981፤#የቅዱስ ያሬድ ዜና ሕይወት በተለያዩ ጸሐፍት ሥራዎች ገጽ_፲)

_ከአጎቱ ዘንድ ገብቶ መዝሙረ ዳዊት በሚማርበት ጊዜ ትምህርት አልገባው አለ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ተአምራቱን ለመግለጥ ሲፈልግ የተለያዩ ሥራዎችን ስለሚሠራ ነው ።በዚኽም ምክንያት መምህሩ ጌዴዎን ብዙ ጊዜ ስለሚቆጠውና ስለሚገርፈው ያሬድ መታገስ ተስኖት ከወላጆቹ ቤት ወጥቶ #ማይኪራሕ ወደምትባል ቦታ ሂዶ ተደበቀ [፪]

⇛ ያሬድ ወደ አንዲት ዛፍ ሥር ተጠግቶ ዐርፎ እያለቀሰ ሳለ አንድ ትል አየ ትሉም ወደ ላይ እወጣለሁ እያለ ከመካከሉ ሲደርስ ይወድቅ ነበር።በዚኽ ሁኔታ ለ ፮ ጊዜያት በተደጋጋሚ ሲወጣና ሲወርድ ከቆየ በኋላ በ ፯ኛው ትሉ ከዛፉ ላይ ወጥቶ የዛፉን ፍሬ ወይም ቅጠል ሲበላ ተመለከተ ።ቅዱስ ያሬድ የትሉን ተስፋ አለመቁረጥ ተማረበት። አበው “የሰይጣን ክፋቱ ተስፋ ማስቆረጡ “ይላሉ።[፬]

☞ በመጨረሻም ወደ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደቀደመውአስተምረኝ አለው።መምህሩም እሽ ብሎ ተቀብሎ ያስተምረው ጀመረ።ከዚያ በኋላ በአንድ ቀን ፻፶ መዝሙረ ዳዊት መኃልየ ነቢያትንና መኃልየ ሰሎሞን እንዲሁም ትርጓሜ መጻሕፍትን ቁጥራቸውን ዐወቀ።

-ጥንታዊ ታሪኩን ጨርሶ በመፋቅ ወይም በመሠረዝ ዜግነቱንም የራሳቸው አድርገው በመቁጠር የዜማውን ትምህርት የተማረው በውጭ ሀገር ነው ይላሉ ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ” ወሪድየ ብሔረ ሮሜ” የሚለውን ቃል ነው። [፫]

☞ በኢትዮጵያ በስድስተኛው ምዕት ዓመት ቅዱስ ያሬድ ተወልዶ ልብ የሚመስጥ እጅግ ድምፀ መልካም የዜማ ደራሲ ሊቅ፣የቅኔ ጀማሪ ፣የጸዋትወ ዜማ ደራሲ ፣የትርጓሜ መጻሕፍት ወጣኒ፣የነገረ መለኮት ሊቅ ፣ሰባኬ ወንጌል ፣የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ መሠረት እናማኅደረ ጥበብ ነው።አንድ የጎጃም ባለቅኔ ይኽንን በማስመልከት

_☞አእመርነሂ ከመ ሀሎ በቀራንዮ ገነት፣

ያሬድ ዘወለዶ ሄኖክ ማኅሌት ብሎ ተቀኘ ይባላል ።ይኽ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ያሬድ የወለደው ሄኖክ ማኅሌት በቀራንዮ ገነት እንዳለ አወቅን፣ተረዳን ማለት ነው። ውስጠ ምሥጢሩም ሲብራራ ሄኖክ እንደ ኤልያስ በሥጋ ወደ ሰማይ ዐርጎ እንደሚኖር ሁሉ ማኅሌትም የተገኘው ከሰማያውያን መላእክት ዘንድ መሆኑን ለማነጻጸር ነው።

☞ ከዕለታት አንድ ቀን ቅዱስ ያሬድ በንጉሡ በዐፄ ገብረ መስቀል እግር አጠገብ ቆሞ ሲዘምር ከማኅሌቱ ጣዕም የተነሣ ንጉሡ ዐፄ ገብረ መስቀል አእምሮአቸውን ሳያውቁ የቅዱስ ያሬድን እግር በያዙት ጦር ወጉት። ቅዱስ ያሬድ ግን ማኅሌቱን እስኪፈጸም ድረስ ሕማመ ኩናቱን ታግሦ እየዘመረ ቆየ :ምክንያቱም ማኅሌቱ ምድራዊ ሳትሆን ሰማያዊት ናትና ።

☞ ቅዱስ ያሬድ የቅዱሳን መላእክትን ዜማ ከመላእክት ተምሮ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንድትገለገልበት ዜማውን ከድርሰት ጋር አበርክቷል ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ያሬድን ዜማ ” የቤተ ክርስቲያን መክፈቻ ቁልፍ ፣ የውስጥ ማኅቶት ፣የውጭ (አፋ) መብራት ፣ የቤተ ክርስቲያን ዓረፍት መሠረት በጠቅላላው የቤተ ክርስቲያን መንቀሳቀሻ ሕይወት ነው” በማለት የዜማውን ታላቅነት ይገልጻሉ ።[፭] ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ አባት ነው።

☞ ቅዱስ ያሬድ ዙር አባ ወይም አምባ ተራራ ላይ ለ፫ ዓመታት ዝማሬ መዋሥዕት አስተምሯል ።ይኽ ቦታ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬድረሰ የዝማሬና የመዋሥዕት ማስመስከሪያ ቦታ ሁኖ ይገኛል ።በወገራ በኩል አድርጎ ወደ አክሱም ተመልሶ ፲፬ቱን ቅዳሴዎች በዜማ አዘጋጀ ፤ የቅዳሴውንም ዜማ ያዘጋጀበት ቦታ መደባይ ታብር ይባላል። ወደ ሰሜን ተራሮች ወደ ጠለምት ሄዶ ምዕራፍ የተባለውን ድርሰት ከዳዊት መዝሙር ጋር በማቀናበር በዜማ የደረሰው ቅዱስ ያሬድ ነው።

☞ ነገረ ቅዱሳን _፪ በማኅበረ ቅዱሳን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ማስተማሪያ በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም የተዘጋጀው መጽሐፍ ገጽ_፳፱ በሰሜን ምሥራቅ ባለ ዋሻ ውስጥበ፭፻፸፩ ዓ.ም ግንቦት ፲፩ ቀን ፷፮ ዓመቱ ደብረ ሐዊ በተባለው ተራራ ተሰውሯል ሲል “ያሬድና ዜማው” መጽሐፍ በሊቀ ካህናት ጥዑመ ልሳን ካሳ በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም የታተመው ገጽ_፴፬ ደግሞ ዐረፈና ተቀበረ ይላል። “መጽሔተ ጥበብ ድጓ” #መቅድም ላይ የምናገኘው ጥቅስ አሻሚ አስተሳሰቦች እንዲፈጠሩ ያደረገ ነው ።ስንክሳሩ እንዲኽ ይላል”..ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ ያሬድ ማኅሌታይ አምሳሊሆሙ ለሱራፌል….ወእምዝ ሖረ ኅበ ገዳመ ስሜን ወነበረ በህየ በጾም ወበጸሎት ።ወአፃመወ ሥጋሁ ፈድፋደ ወፈጸመ ገድሎ በህየ ።..ወእምዝ አዕረፈ በሰላም ።ወመቃብሪሁሰ ኢተዐውቀ እስከ ዮም..።”በዚች ቀንም የሱራፌል አምሳያቸው የኾነው ማኅሌታይ ያሬድ ዐረፈ።…ከዚያም ወደ ስሜን ገዳም ኼደ።በዚያም በጾምና በጸሎት ተቀመጠ።ሥጋውንም እጅግ አደከመ ፤ ገድሉንም በዚያው ፈጸመ።…ከዚያም በሰላም ዐረፈ።መቃብሩ ግን እስከ ዛሬ አልታወቀም” ( 👉 ግንቦት ፲፩ ስንክሳር )

1 year, 9 months ago

የሕዳር ጽዮን እና የአክሱም ጽዮን ማርያም ታሪክ።

★ አክሱም፦

የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን መሠረት፣ የሥነ ህንፃ፣ የሥነ ዜማ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የሥርዓተ መንግሥት፣ የፊደል፣ የቋንቋ፣ የስልጣኔ ምንጭ፣ የሕገመንግሥት መገኛ፣ የጥንታዊ ቴክኖሎጂያችን አሻራ፣ የአስደናቂ ቅርጻቅርጾቻችን መገኛ፣ የታቦተ ጽዮንም ማረፊያ ናት።

በዛሬው ዕለት በሰሜን ኢትዮጵያ በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ሀገራችን መናገሻ በነበረችው በአክሱም ከተማ "በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን " ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ታላቅ የሆነ ሃይማኖታዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል።

የዛሬው የሕዳር ጽዮን ማርያም በዓል ስለ 8 ዓበይት ምክንያቶች ይከበራል።

፩፦ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ። 1ኛ ሳሙ 1–6።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ታቦተ ጽዮን በፍልስጥኤማውያን ተማርካ ቤተ ጣዖት ወስደው ከጣዖታቸው ከዳጎን በታች አስቀምጠዋት እንደነበር ነው። ነገር ግን ታቦተ ጽዮን በላይዋ እንዲቀመጥ ተደርጎ የነበረውን ዳጎንን ገልብጣና ጥላ እርሷ ከላይ ከዳጎኑ ከበላይ እንደተተቀመጠች ይነግረናል። ይህ የሚያሳየን ደግሞ በታቦት የሚገለጠው የእግዚአብሔር ኃይል መሆኑን ነው። ምክንያቱም በታቦቱ ላይ ያለው ሕገ እግዚአብሔርና ስመ እግዚአብሔር ነውና። ምንም እንኳ ታቦተ ጽዮን ስትማረክና በአህዛብ እጅ በወደቀች ጊዜ ለጊዜው ደካማ ብትመስልም መማረኳ ግን ኃይሏን ለመግለጥ፣ ለአሕዛብ የጣዖትን ከንቱነት የታቦትን ክቡርነት ለመግለጥ ነበርና መማረኳ ግድ ነበር፡፡ በዚህም ዘመን ታቦታት ይማረካሉ፣ ይሰረቃሉ፣ ነገር ግን በተአምራት በክብር ይመለሳሉ።

፪፦ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተ መቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ ።1ኛ፣ ነገ 8 ፣1–66።

፫፣ ታቦተ ጽዮን በንግሥት ሳባ ልጅ በቀዳማዊ ንጉሥ ምኒልክ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ምድር የገባችበትና እናቱ ንግሥት ሳባም ታላቅ በዓል አድርጋ የተቀበለችበትም ዕለት ነውና እሱን በማሰብ፦

በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ መሠረት ታቦተ ጽዮን በኢየሩሳሌም ከሚገኘው ከሰሎሞን ቤተ መቅደስ የታጣችውና ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው በራሱ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመነ መንግሥት እንደሆነ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት እንዳካሄደ የሚነገረው እንጊሊዛዊው ደራሲና ተመራማሪ ግርሃም ሐንኮክ ግን ታቦቷ የተሰወረችው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ዐራት መቶ ዓመታት በኋላ በ687 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጎ ይናገራል። ይህም ዘመን ሲስላ በንጉሥ ምናሴ ዘመነ መንግሥት መሆኑ ነው።

ቀጥሎም ግርሃም ሐንኮክ ታቦቷን ወደ ኢትዮጵያ ያመጧት፣ ክብረ ነገሥት እንደሚለው እነ ቀዳማዊ ሚኒልክ ሳይሆኑ፣ በዚያን ዘመን ንጉሥ የነበረው ምናሴ በጣዖት አምልኮ በመጠመዱ ምክንያት ለእምነታቸው ቀናዒ የሆኑ እስራኤላውያን ታቦቷን ከመቅደስ አውጥተው ወደ ግብፅ ይዘው ሳይሰደዱ እንዳልቀሩና..... በዚያም ሁለት መቶ ዓመታትን ከኖሩ በኋላ፤ ከግብፆች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ወደ አገራቸው ወደ እስራኤል ከመመለስ ይልቅ ወደ ደቡብ ግብፅ በመጓዝ አትባራን እንደገቡ ይነግረናል።

ከአትባራ ተነስተው የተከዜን ወንዝ በመከተል ወደ ኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች በመዝለቅ ጣና ሐይቅ (ያሁኑ ጣና ቂርቆስ ደሴት) ደረሰዋል። በጣና ሐይቅም ታቦተ ጽዮንን 800 ዓመታትን ይዘው ከቆዩ በኋላ፤ በ330 ዓም ክርስትናን ለንጉሥ ኢዛናና ለመላው አክሱም ያስተዋወቁት ሶሪያዊ ሊቀ ጳጳስ ፍሬምናጦስ ኋላ አባ ሰላማ ወደ ጣና ሐይቅ በመምጣት በዚያን ጊዜ በጣና ሐይቅ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎችና ገና ክርስትናን ያልተቀበሉ የታቦቷን ጠባቂ አይሁዶችን በማግባባትና በማናገር፤ በጣና ቂርቆስ በድንኳን ትኖር የነበረችውን ታቦተ ጽዮን በአክሱም ቤተ መቅደስ በማሠራት ወደአክሱም ወሰዷት።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዮዲት እስከ ተነሳችበት(10ኛ መ.ክ.ዘ) ድረስ በዚያ ኖራለች። በ959 ዓ.ም ግን ዮዲት የተባለች ፀረ ክርስትና ንግሥት በመነሳቷ ታቦቷን ከአደጋ ለማዳን ሲባል መጀመሪያ ወደ ሰሜን ሸዋ መርሃ ቤቴ፣ ከዚያም ምሥራቅ ሸዋ ወደ ደብረ ጽዮን (ዝዋይ ሐይቅ) በመውሰድ 72 ዓመታትን በዚያው ካሳለፉ በኋላ መልሰው ወደ አክሱም በማምጣት በዚያ አኑረዋታል።

ታቦተ ጽዮን ከዘመነ ዮዲት ጉዲት በኋላ በ15ኛው መ.ክ.ዘ ከተነሳው ከግራኝ አህመድ ወረራ ለመደበቅ ሲባልም በምዕራብ ኤርትራ በረሃ ለአስራ ሰባት ዓመታት ከአክሱም ወጥታ እንደቆየችና ከዚያ በኋላ ግን እስካሁን ድረስ በአክሱም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደምትገኝ ይታመናል።

ስለ ዮዲት ጉዲት አነሳስና ውድመት " ቅዱሳት መካናት በኢትዮጵያ " ከሚለው መጽሐፍ ይገኛል።

  1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በአብርሀ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት መሆኗ የታወጀበት ዕለትም ነው ዛሬ ህዳር 21።

፭፦በብሉይ ኪዳን መስዋዕተ ኦሪት /የእንሳት ደም ከሚሰዋባት ሙኵራብ / ወደ ሐዲስ ኪዳን/ አማናዊው በግ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት /" ጽዮን ማርያም ተብላ ወደ ቤተ ክርስቲያንነት የተቀየረችበት ዕለት ነው።

፮፦ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ ህብረ አምሳል ያዩበት፤ ለምሳሌ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት ፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ።

፯፦ በአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት ከመፍረሱ በፊት፤ በሁለቱ ደጋግ ወንድማማች የኢትዮጵያ ነገሥታት በነበሩት በዘመነ አብርሀ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ የተሠራው ባለ አሥራ ሁለት ክፍሉ ቤተ መቅደስ ሥራው ተጠናቅቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትን ዕለት በማሰብ።

፰፦ በአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት መነሳት ምክንያት ለብዙ ዓመታት ያህል ወደ ዝዋይ ገዳም ተሰድዳ የነበረችው ታቦተ ጽዮን የስደት ዘመኗን ፈጽማ ወደ መንበረ ክብሯ አክሱም ጽዮን የተመለሰችበት ዕለት በመሆኑ፤ ይህንና ይህን በመሳሰሉ ምክንያቶች የህዳር ጽዮን በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

9 ፦ ነቢዩ ዘካርያስ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ፣ የዘይት ማሰሮ በራሱ ላይ የነበረበትንና ሰባት መብራቶች ያሉትን መቅረዝ ሲያበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡ ዘካ. 4፤1-2፡፡
ዘካርያስ ያየው ብርሃን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ፡፡ ዮሐ 8፣12 ፡፡ ይህ ብርሃን የታየባትና የተገለጠባት መቅረዝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ ብርሃን መቅረዝ እንዲያዝና እንዲገለጥ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ተገልጦልናል፡፡ ጨለማ ዓለምን አብርቷል፡፡ ብርሃን ክርስቶስን ወልዳለችና እርሷም እመ ብርሃን / የብርሃን እናት/ ትባላለች፡፡
ባልገኝም

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ከአማናዊቷ ታቦት አምላክን ከወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ከፀናች ከክብርትና ቅድስት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከቷን ያሳድርብን። አሜን
https://t.me/dn_mez

1 year, 9 months ago

✍?✍?✍?✍?✍?✍?

ማሙሽ ሳንቲም የሚያጠራቅምባት ትንሽ ባንክ አለችው::
አንድ ጠዋት ከወላጆቹ ጋር ቤተ ክርስቲያን አርፍዶ ሲመለስ  ባንኩን ዘርግፎ ሳንቲሙን መቁጠር ጀመረ:: ይህንን ሥራውን ያየው አባቱ ምን እያደረገ እንደሆነ ሲጠይቀው እንዲህ ሲል መለሰ :-

"ዛሬ ቤተ ክርስቲያን አባ ሲያስተምሩ ክርስቶስ በቶሎ ይመጣል ብለዋል:: የሚመጣ ከሆነ ደግሞ ይህንን ሁሉ ሳንቲም ደብቄ ይዤ እንዲያገኘኝ ስለማልፈልግ በቶሎ ለድሆች ልሠጠው አስቤ ነው"

ዲ/ን መዝሙር
17-03-17 ዓ.ም

1 year, 9 months ago
2 years ago

#የሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ_ማብራሪያ

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው #“ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭ ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
#ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪ. ዘፍ ፫፥፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡ አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Genesis/፡፡
#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም #በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤ አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው? አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily Readings of St. John Chrysostom/፡፡
#ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ #“ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡ ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው #ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· #ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· #ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· #ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡
#“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡ አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
#“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡ “ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል” የሚሉም አሉ፡፡
https://t.me/dn_mez

2 years ago

#ቅድስት_ፀበለ_ማርያም_ማለት

☞ወር በገባ በ18 ከሚታሰቡት መካከል ክብሯ ቅድስት ፀበለ ማርያም ይቺውም በፀሎቷ ብዛት በወገቧ በታጠቀችው ሰንሰለት በስግደቷም ስጋዋ ከአካሏ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ የጌታዋን መከራ እያሰበች ትሰግድ ነበር

☞ማንም ከቶ እንዳያውቅባት ከአካሏ የወደቀውን ስጋዋን መሬት ቆፍራ ትቀብረው ነበር በዚህም የተነሳ የገዳሟ መሬት ሁለተኛ አካሏ ሆነ ከእንባዋም ብዛት የተነሳ ዝናብ የጣለ መሬት ይመስል መሬቱ በእንባዋ ይረሰርስ ነበር እርሷ ግን ሰው እንዳያውቅባት በደረቅ አፈር ትለውሰው ነበር።

የዓለም መዳኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በደሀ ሰው ተመስሎ ምግብ ለመናት እርሷም
ጌታዋን መገበችው ደክሞኛል እዘይኝ ባላት ጊዜ እርሷ አዛኝ ናትና በጀርባዋ አዝላ
የዲንጋይ መወርወሪያ ያህል ተሸክማ ወሰደችው በዚህ ክብርት የምትሆን
እናታችን ፀበለ ማርያም ስለንፅህናዋ ፀበል አፈለቀላት እመቤታችንም ከሰማይ
ወርዳ ስሜን የተሸከምሽ ፀበለ ማርያም ሆይ ነይ ብላ አቅፋ ሳመቻት።
☞የክርስቲያን ወገኖች ስሙኝ የገዳሟን አፈር የወሰደ የስጋዋን ቁራሽ
ለመዳኒትነት
እንደወሰደ ይወቅ ይረዳ የእምነት አፈሩ ክርስቶስን ተሸክሟልና የእንባዋን ፀበል
የወሰደ ፍፁም ፈውስ ያገኛልና ከቶ እናቴ ፀበለ ማርያም እያላችው ተማፀኗት።
☞ገና ዓለም ሁሉ ገዳሟ እንደሚጎርፉ ዝናዋ የዓለም ጫፍ እንደሚደርስ የማታ
የማታ የከተማ ልጆች ቤቴን ይሰሩታል የተባለው ትንቢት መድረሱን የገዳሙ
አባቶች ይናገራሉ።
የገዳሟ አድራሻ ፦ በደቡብ ወሎ ጃማ ዳጎሎ አህያ ፈጂ የሚባል ቦታ ልዩ ስሙ
ንህበት የሚባል ቦታ ነው ።
☞የጻድቋ እናታችን የጸበለ ማርያም የጸሎቷ በረከት አይለየን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

2 years, 3 months ago

አንብቡት ይጠቅማችኋል እራሳችሁን ታዩበታላችሁ

We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik