ዝጉ መንገድ ሚዲያ

Description
''ዝጉ መንገድ ሚዲያ '' የዚህ ቻናል ዓላም ተከታዮቹን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው፤ በግል ስብዕናቸው፤ በቢዝነስ ሕይወታቸው እና በሙያዊ ሕይወታቸው ላይ የሚያስፈልጋቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲሁም ጥበብ ለማጎልበት የሚሠራ ድንቅ ቻናል ነው።
የ ''ዝጉ መንገድ ሚዲያ''አስተማሪ ቪዲዮችን ለምትፈልጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ!!!
https://youtu.be/OIhbFJUy0Nw?si=6hhr3VOes5XEnZO
Advertising
We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc

3 weeks, 4 days ago

የሕዳር ጽዮን እና የአክሱም ጽዮን ማርያም ታሪክ።

★ አክሱም፦

የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን መሠረት፣ የሥነ ህንፃ፣ የሥነ ዜማ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የሥርዓተ መንግሥት፣ የፊደል፣ የቋንቋ፣ የስልጣኔ ምንጭ፣ የሕገመንግሥት መገኛ፣ የጥንታዊ ቴክኖሎጂያችን አሻራ፣ የአስደናቂ ቅርጻቅርጾቻችን መገኛ፣ የታቦተ ጽዮንም ማረፊያ ናት።

በዛሬው ዕለት በሰሜን ኢትዮጵያ በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ሀገራችን መናገሻ በነበረችው በአክሱም ከተማ "በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን " ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ታላቅ የሆነ ሃይማኖታዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል።

የዛሬው የሕዳር ጽዮን ማርያም በዓል ስለ 8 ዓበይት ምክንያቶች ይከበራል።

፩፦ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ። 1ኛ ሳሙ 1–6።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ታቦተ ጽዮን በፍልስጥኤማውያን ተማርካ ቤተ ጣዖት ወስደው ከጣዖታቸው ከዳጎን በታች አስቀምጠዋት እንደነበር ነው። ነገር ግን ታቦተ ጽዮን በላይዋ እንዲቀመጥ ተደርጎ የነበረውን ዳጎንን ገልብጣና ጥላ እርሷ ከላይ ከዳጎኑ ከበላይ እንደተተቀመጠች ይነግረናል። ይህ የሚያሳየን ደግሞ በታቦት የሚገለጠው የእግዚአብሔር ኃይል መሆኑን ነው። ምክንያቱም በታቦቱ ላይ ያለው ሕገ እግዚአብሔርና ስመ እግዚአብሔር ነውና። ምንም እንኳ ታቦተ ጽዮን ስትማረክና በአህዛብ እጅ በወደቀች ጊዜ ለጊዜው ደካማ ብትመስልም መማረኳ ግን ኃይሏን ለመግለጥ፣ ለአሕዛብ የጣዖትን ከንቱነት የታቦትን ክቡርነት ለመግለጥ ነበርና መማረኳ ግድ ነበር፡፡ በዚህም ዘመን ታቦታት ይማረካሉ፣ ይሰረቃሉ፣ ነገር ግን በተአምራት በክብር ይመለሳሉ።

፪፦ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተ መቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ ።1ኛ፣ ነገ 8 ፣1–66።

፫፣ ታቦተ ጽዮን በንግሥት ሳባ ልጅ በቀዳማዊ ንጉሥ ምኒልክ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ምድር የገባችበትና እናቱ ንግሥት ሳባም ታላቅ በዓል አድርጋ የተቀበለችበትም ዕለት ነውና እሱን በማሰብ፦

በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ መሠረት ታቦተ ጽዮን በኢየሩሳሌም ከሚገኘው ከሰሎሞን ቤተ መቅደስ የታጣችውና ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው በራሱ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመነ መንግሥት እንደሆነ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት እንዳካሄደ የሚነገረው እንጊሊዛዊው ደራሲና ተመራማሪ ግርሃም ሐንኮክ ግን ታቦቷ የተሰወረችው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ዐራት መቶ ዓመታት በኋላ በ687 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጎ ይናገራል። ይህም ዘመን ሲስላ በንጉሥ ምናሴ ዘመነ መንግሥት መሆኑ ነው።

ቀጥሎም ግርሃም ሐንኮክ ታቦቷን ወደ ኢትዮጵያ ያመጧት፣ ክብረ ነገሥት እንደሚለው እነ ቀዳማዊ ሚኒልክ ሳይሆኑ፣ በዚያን ዘመን ንጉሥ የነበረው ምናሴ በጣዖት አምልኮ በመጠመዱ ምክንያት ለእምነታቸው ቀናዒ የሆኑ እስራኤላውያን ታቦቷን ከመቅደስ አውጥተው ወደ ግብፅ ይዘው ሳይሰደዱ እንዳልቀሩና..... በዚያም ሁለት መቶ ዓመታትን ከኖሩ በኋላ፤ ከግብፆች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ወደ አገራቸው ወደ እስራኤል ከመመለስ ይልቅ ወደ ደቡብ ግብፅ በመጓዝ አትባራን እንደገቡ ይነግረናል።

ከአትባራ ተነስተው የተከዜን ወንዝ በመከተል ወደ ኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች በመዝለቅ ጣና ሐይቅ (ያሁኑ ጣና ቂርቆስ ደሴት) ደረሰዋል። በጣና ሐይቅም ታቦተ ጽዮንን 800 ዓመታትን ይዘው ከቆዩ በኋላ፤ በ330 ዓም ክርስትናን ለንጉሥ ኢዛናና ለመላው አክሱም ያስተዋወቁት ሶሪያዊ ሊቀ ጳጳስ ፍሬምናጦስ ኋላ አባ ሰላማ ወደ ጣና ሐይቅ በመምጣት በዚያን ጊዜ በጣና ሐይቅ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎችና ገና ክርስትናን ያልተቀበሉ የታቦቷን ጠባቂ አይሁዶችን በማግባባትና በማናገር፤ በጣና ቂርቆስ በድንኳን ትኖር የነበረችውን ታቦተ ጽዮን በአክሱም ቤተ መቅደስ በማሠራት ወደአክሱም ወሰዷት።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዮዲት እስከ ተነሳችበት(10ኛ መ.ክ.ዘ) ድረስ በዚያ ኖራለች። በ959 ዓ.ም ግን ዮዲት የተባለች ፀረ ክርስትና ንግሥት በመነሳቷ ታቦቷን ከአደጋ ለማዳን ሲባል መጀመሪያ ወደ ሰሜን ሸዋ መርሃ ቤቴ፣ ከዚያም ምሥራቅ ሸዋ ወደ ደብረ ጽዮን (ዝዋይ ሐይቅ) በመውሰድ 72 ዓመታትን በዚያው ካሳለፉ በኋላ መልሰው ወደ አክሱም በማምጣት በዚያ አኑረዋታል።

ታቦተ ጽዮን ከዘመነ ዮዲት ጉዲት በኋላ በ15ኛው መ.ክ.ዘ ከተነሳው ከግራኝ አህመድ ወረራ ለመደበቅ ሲባልም በምዕራብ ኤርትራ በረሃ ለአስራ ሰባት ዓመታት ከአክሱም ወጥታ እንደቆየችና ከዚያ በኋላ ግን እስካሁን ድረስ በአክሱም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደምትገኝ ይታመናል።

ስለ ዮዲት ጉዲት አነሳስና ውድመት " ቅዱሳት መካናት በኢትዮጵያ " ከሚለው መጽሐፍ ይገኛል።

  1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በአብርሀ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት መሆኗ የታወጀበት ዕለትም ነው ዛሬ ህዳር 21።

፭፦በብሉይ ኪዳን መስዋዕተ ኦሪት /የእንሳት ደም ከሚሰዋባት ሙኵራብ / ወደ ሐዲስ ኪዳን/ አማናዊው በግ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት /" ጽዮን ማርያም ተብላ ወደ ቤተ ክርስቲያንነት የተቀየረችበት ዕለት ነው።

፮፦ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ ህብረ አምሳል ያዩበት፤ ለምሳሌ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት ፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ።

፯፦ በአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት ከመፍረሱ በፊት፤ በሁለቱ ደጋግ ወንድማማች የኢትዮጵያ ነገሥታት በነበሩት በዘመነ አብርሀ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ የተሠራው ባለ አሥራ ሁለት ክፍሉ ቤተ መቅደስ ሥራው ተጠናቅቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትን ዕለት በማሰብ።

፰፦ በአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት መነሳት ምክንያት ለብዙ ዓመታት ያህል ወደ ዝዋይ ገዳም ተሰድዳ የነበረችው ታቦተ ጽዮን የስደት ዘመኗን ፈጽማ ወደ መንበረ ክብሯ አክሱም ጽዮን የተመለሰችበት ዕለት በመሆኑ፤ ይህንና ይህን በመሳሰሉ ምክንያቶች የህዳር ጽዮን በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

9 ፦ ነቢዩ ዘካርያስ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ፣ የዘይት ማሰሮ በራሱ ላይ የነበረበትንና ሰባት መብራቶች ያሉትን መቅረዝ ሲያበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡ ዘካ. 4፤1-2፡፡
ዘካርያስ ያየው ብርሃን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ፡፡ ዮሐ 8፣12 ፡፡ ይህ ብርሃን የታየባትና የተገለጠባት መቅረዝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ ብርሃን መቅረዝ እንዲያዝና እንዲገለጥ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ተገልጦልናል፡፡ ጨለማ ዓለምን አብርቷል፡፡ ብርሃን ክርስቶስን ወልዳለችና እርሷም እመ ብርሃን / የብርሃን እናት/ ትባላለች፡፡
ባልገኝም

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ከአማናዊቷ ታቦት አምላክን ከወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ከፀናች ከክብርትና ቅድስት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከቷን ያሳድርብን። አሜን
https://t.me/dn_mez

4 weeks ago

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

ማሙሽ ሳንቲም የሚያጠራቅምባት ትንሽ ባንክ አለችው::
አንድ ጠዋት ከወላጆቹ ጋር ቤተ ክርስቲያን አርፍዶ ሲመለስ  ባንኩን ዘርግፎ ሳንቲሙን መቁጠር ጀመረ:: ይህንን ሥራውን ያየው አባቱ ምን እያደረገ እንደሆነ ሲጠይቀው እንዲህ ሲል መለሰ :-

"ዛሬ ቤተ ክርስቲያን አባ ሲያስተምሩ ክርስቶስ በቶሎ ይመጣል ብለዋል:: የሚመጣ ከሆነ ደግሞ ይህንን ሁሉ ሳንቲም ደብቄ ይዤ እንዲያገኘኝ ስለማልፈልግ በቶሎ ለድሆች ልሠጠው አስቤ ነው"

ዲ/ን መዝሙር
17-03-17 ዓ.ም

3 months, 4 weeks ago

#የሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ_ማብራሪያ

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው #“ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭ ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
#ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪ. ዘፍ ፫፥፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡ አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Genesis/፡፡
#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም #በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤ አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው? አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily Readings of St. John Chrysostom/፡፡
#ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ #“ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡ ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው #ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· #ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· #ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· #ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡
#“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡ አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
#“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡ “ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል” የሚሉም አሉ፡፡
https://t.me/dn_mez

4 months ago

#ቅድስት_ፀበለ_ማርያም_ማለት

☞ወር በገባ በ18 ከሚታሰቡት መካከል ክብሯ ቅድስት ፀበለ ማርያም ይቺውም በፀሎቷ ብዛት በወገቧ በታጠቀችው ሰንሰለት በስግደቷም ስጋዋ ከአካሏ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ የጌታዋን መከራ እያሰበች ትሰግድ ነበር

☞ማንም ከቶ እንዳያውቅባት ከአካሏ የወደቀውን ስጋዋን መሬት ቆፍራ ትቀብረው ነበር በዚህም የተነሳ የገዳሟ መሬት ሁለተኛ አካሏ ሆነ ከእንባዋም ብዛት የተነሳ ዝናብ የጣለ መሬት ይመስል መሬቱ በእንባዋ ይረሰርስ ነበር እርሷ ግን ሰው እንዳያውቅባት በደረቅ አፈር ትለውሰው ነበር።

የዓለም መዳኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በደሀ ሰው ተመስሎ ምግብ ለመናት እርሷም
ጌታዋን መገበችው ደክሞኛል እዘይኝ ባላት ጊዜ እርሷ አዛኝ ናትና በጀርባዋ አዝላ
የዲንጋይ መወርወሪያ ያህል ተሸክማ ወሰደችው በዚህ ክብርት የምትሆን
እናታችን ፀበለ ማርያም ስለንፅህናዋ ፀበል አፈለቀላት እመቤታችንም ከሰማይ
ወርዳ ስሜን የተሸከምሽ ፀበለ ማርያም ሆይ ነይ ብላ አቅፋ ሳመቻት።
☞የክርስቲያን ወገኖች ስሙኝ የገዳሟን አፈር የወሰደ የስጋዋን ቁራሽ
ለመዳኒትነት
እንደወሰደ ይወቅ ይረዳ የእምነት አፈሩ ክርስቶስን ተሸክሟልና የእንባዋን ፀበል
የወሰደ ፍፁም ፈውስ ያገኛልና ከቶ እናቴ ፀበለ ማርያም እያላችው ተማፀኗት።
☞ገና ዓለም ሁሉ ገዳሟ እንደሚጎርፉ ዝናዋ የዓለም ጫፍ እንደሚደርስ የማታ
የማታ የከተማ ልጆች ቤቴን ይሰሩታል የተባለው ትንቢት መድረሱን የገዳሙ
አባቶች ይናገራሉ።
የገዳሟ አድራሻ ፦ በደቡብ ወሎ ጃማ ዳጎሎ አህያ ፈጂ የሚባል ቦታ ልዩ ስሙ
ንህበት የሚባል ቦታ ነው ።
☞የጻድቋ እናታችን የጸበለ ማርያም የጸሎቷ በረከት አይለየን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

6 months, 2 weeks ago

አንብቡት ይጠቅማችኋል እራሳችሁን ታዩበታላችሁ

6 months, 3 weeks ago

#ሰውን ለመርዳት ጥሩ ነገር ማሰብ ብቻ በቂ ነው።

ሰዎችን የምንረዳባቸው መንገዶች እጅግ ብዙ አማራጮች አሉን።
ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡

እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን?

ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡

@deacon mezmur niguse

We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc