★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
YouTube
Mela Muziqa - Teddy Yo (ቴዲ ዮ) - ወንበርሽ | Wenbersh New Ethiopian Music 2022 (Offical Video)
#ethiopiannewmusic2022 #teddyyo #melamuziqarecords https://zojak.lnk.to/wenbersh Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited. Copyright***©***2022: Melamuziqa Records LLC አዳዲስ እና ቆንጆ ስራዎችን ከቅርብ ጊዜ ወዲ ወደ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ገበያ ላይ ይዞ እየመጣ የሚገኘው…
ሰሞኑን እንጃልኝ
"""""""""" """""""""""
ሳማሽ እውላለሁ ሰው ባጣም ለራሴ ፣
መልክሽን ስስለው ፈገግ ይላል ጥርሴ ፣
አጃኢብ ያሰኛል
ተለዋውጫለሁ ተቀያይሬያለሁ ፣
ፍቅርሽ ገብቶልኛል ተረጋግቻለሁ ።
ሰሞኑን እንጃልኝ
ፈጣሪ ጠብቆኝ. ባይመታኝ እንቅፋት ፣
ፈረስ ቢያስጋልብም የጎዳናው ስፋት ፣
ጥጉን እሄዳለው..... አይኖቼን አቅንቼ ፣
ባገኝሽ እያልኩኝ
ባየሁሽ እያልኩኝ .........ልቤን አሞኝቼ ።
ሰሞኑን እንደዚህ ግራ እየተጋባው ፣
ሌቱን እያሰብኩሽ ሳልተኛ እየነቃው ፣
ሳገኝሽ ስታስሪው ያንደበቴን ድፍረት ፣
ስለይሽ በራሴ........ ሳዝንና ስፀፀት ፣
እናልሽ የኔ አለም
ከሀሳቤ ላወጣሽ ሞክሬ አቅቶኛል ፣
ማፍቀሬን ልነግርሽ ፈልጌ አቅቶኛል ፣
ሰሞኑን እንጃልኝ እንዲህ ያደርገኛል ።
ታዘበኝ ልጅነት
"""""""""""""""""""
ደግመን ብንገናኝ ከልጅነቴ ጋ ፣
አመታት አይበቁም የውስጤን ሳወጋ ፣
ስማኝ ልጅነቴ
በድሎኛል ማደግ ጨቁኖኛል እድሜ ፣
ተገፏል ከላዬ የልጅነት ህልሜ ፣
አወቅኩኝ መግፋትን ፍቅርን ታገልኩት ፣
ይቅር ባዩን ልቤን ቂመኛ አደረኩት ።
ስማኝ ልጅነቴ
ተነፍጓል ያ መልኬ ጎድፏል ንፁህ ልቤ ፣
እየሞትኩኝ አለሁ መኖርን አስቤ ፣
የእውነት ሳቅ የለኝም የልጅነት ደስታ ፣
መቦረቂያ እድሜዬ አልፏል ያኛው ለታ ።
ታዘበኝ ልጅነት ታሰርኩኝ በጊዜ ፣
ነፃነት ተነጠኩ.....ከበበኝ ትካዜ ፣
ተቀይሬያለሁኝ አሁን አታውቀኝም ፣
ለራሴ ደስታ እንጂ ለሰው ግድ የለኝም ።
ከተኛሁ ቆየሁኝ እንቅልፍ አጥቷል ቀልቤ ፣
ወጪ ወራጁን ሲያይ ይሸበራል ልቤ ፣
እይታዬ ሰፍቷል ማስተዋሌ ገዝፏል ፣
ግና ምን ያረጋል
ከደጀ ሰላሙ............. አካሌ ርቋል ።
ታዘበኝ ልጅነት
ጥለኸኝ ብትሄድም ላትመለስ ዳግም ፣
ምከረኝ ልጅነት ከህመሜ ላገገም ፣
ታምሜያለሁ እና በንዋይ መጠማት ፣
አድፌያለሁና
ሆዴን እያጠገብሁ ነፍሴን እያስራብኳት ፣
አኖራት እያልኩኝ.... ስን'ግዜ ገደልኳት ።
.
.
.
.
.
ታዘበኝ ልጅነት ፣
አሁን የለም እና ምታውቀው ማንነት ።
እርፍጃ
ላንች ያለኝን
የመውደድን ጥግ - 'ራሴን ጠይቄ፣
በእፍኟ ልቤ
የሰናፍጭ ቅንጣት - ፍቅር ሰንቄ፣
በመውደድ እርሾ
በትእግስት ቡሀ'ቃ - ህይወቴን አቡክቼ፣
ጋግሬ ስመጣ
በህሊና ምጣድ - ልቤን አስፍቼ፣
ምን ነበር ምላሽሽ?
የፍቅርን ማዕድ - ሳቀርብ ከፊትሽ?
" በህይወት ጎዳና - እንዳንተ ያረፈደ፣
ማፍቀሩን ለማወቅ - ጊዜ ያነጎደ
ፈጽሞ የለም - በዚች ምድር፣
መውደዱን ለመግለጽ
የህይወቱን ግማሽ - በከንቱ ሚገብር፡፡
እናም . . .
አንተ ስትጋግር - የፍቅርህን እንጀራ፣
ማዕድ ተቋርሻለሁ - ከሌላ ሰው ጋራ፡፡ "
ይሁና!!! . . . ይሁና እቴ
በልክ የበሰለ
የፍቅር ማዕድ - ይዤ መቅረቤ፣
በሌላ አስቀድሞ
አርፋጅ ካሰኘኝ - ፍቅር መደረቤ፣
ምን ይደረጋል
ምንስ ይባላል
የፍጥረት ፈጣሪ
ከፈቀደው ውጭ - መኖር መች ይቻላል፡፡
እቴ …
ያንችም ፈጥኖ - ማዕድ መጋራት፣
የኔም ማቅረብ - ያረፈደ እራት፣
ምክንያት ይኖረዋል
እኛ ባንረዳውም - ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡
ቢሆንም
አርፋጅ አትበይኝ - ውስጤ እንዳይጎዳ፣
ቢቻላት…
የፍቅሬን ፅናት - ልብሽ ትረዳ፡፡
እቴ …
ሰው መኖር አይችልም - በሰው ላይ ፈርዶ፣
ደግሞም አያውቅም
ፈጣሪ … በስራው አርፍዶ፡፡
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago