Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

Description
ወሳኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የሚነኩ አገራዊ ጉዳዮችን የውይይት አጀንዳ እንዲሆኑ በማቅረብ አስተያየትና የመፍትሔ ምክረ ዐሳብ ይቀርቡበታል። የሚያወያዩ የቤተክርስቲያንና ስለአገር የሚቆረቆሩ ወገኖች የሚያቀርቡትን ሀሳብ እንጋራታለን።

https://www.facebook.com/fwakie

Join me also here https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_Fant
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 5 days, 11 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month ago

ጥራት ያላቸው የቤት ዕቃዎችንና የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ከእኛ ይግዙ። አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ 376 ያገኙናል። ባሉበት ሆነው ማዘዝ ይችላሉ። 0944222324

Last updated 23 hours ago

2 weeks, 5 days ago

ገጣሚ ገ እና አንባቢ ሳ
እግዚአብሔር ጸጋችሁን ያብዛላችሁ ብላችሁ መርቁልን። https://vm.tiktok.com/ZMM9Wkmdg/

2 weeks, 5 days ago

ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ችግር ተጠያቂው ማነው?

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

2 weeks, 6 days ago

👆🏾👆🏾
ይህን ጥያቄ በዝግታ፥ በማስተዋል፥ በትኩረት ቢያንስ ፭ እና ፯ ጊዜ ለምን? ለምን? —- እያልን እንመልስ፥ እንወያይ፥ እንንቃ፥ እንለወጥ፥ እንለውጥ!
======== ================================
✔️የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ኦርቶዶክሳዊው ክርስቲያን ለምን ከፈቃዱ ውጪ በጥቂት ከአገራዊና ሃይማኖታው ፍላጎቱ ውጭ በሆኑ ሰዎች የሚነዳ ሆነ?

✔️ለምንስ እንደ ስልጤ ዞንና ሀረሪ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አነሳና ጥቂት የዉሀብያ ጽንፈኞች ብዙሀኑን ክርስቲያኖች እንደልባቸው እያጠቁ መቀጠል እንዲችሉ ክርስቲያኖች ፈቀዱ?

✔️ዛሬ የመጥፋት አደጋ ይደርስብኛል ብሎ የሚሰጋውና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ ተከታይ ወደ ፷ሚሊዮን የሚገመት ሆኖ፥ ፹በ፻ ሚሊታሪ፥ ፷በመቶ ገበሬና ምሁር ኦርቶዶክስ ይዞ እንዴት የህልውና አደጋ ሥር መኖርን ፈቀደ?

✔️የአዲስ አባባ ሕዝብ ለምን አራጁን የአብይ መንግሥት መዋቅር ተሰልፎ አንገቱን ለመስጠት ይጠብቃል?

✔️ለምን አናሳዎች (በቁጥር) እንዲህ ልብ ልብ ተሰማቸው? ለምንስ ትላልቆቹ ደግሞ መንፈሳቸው ተሰለበ?

✔️አናሳዎች አጥቂ ትላልቆቹ ደግመው ተሰልፈው የሚታረዱና በቴሌቭዥን ላይ የሚያለቅሱ የሚቃጠል ሻማ በፌስ ቡክ የሚለጥፉ እንጂ ምንም አይነት እርምጃ የማይወስዱ እንዴት ሆኑ?

----- እነዚህን ጥያቄዎች ከ፭ እስከ ፯ ጊዜ ደጋግመን “ምን?” እያልን በመጠየቅና ምላሽ በመፈለግ ራሳችንን በግልና በወል ፈትነን መታረም ይጠበቅብናል። ለዚህ ነው ሰባት ግዜም ቢሆን ለምን ለምን እያልን እራሳችንን መጠየቅ ግድ የሚለን።

ለዚህ ዋናኛ መልሱ የአሜሪካው ቀልደኛ ማርክ ትዌን “ ዋናው ነገር የውሻው ትልቅነት ሳይሆን በውሻው ውስጥ ያለ ተናካሽነት ስሜት ነው” እንደሚለው (“It's not the size of the dog in the fight, it's the size of the fight in the dog” Mark Twain) የአቅም ማነስ ሳይሆን የስነልቦና መሰለብ አሉታዊ ያልተጣሩና ከኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ጋር የሚጋጩ የግለሰቦችና የቡደን እሳቤዎች የተሸከመ፥ ቀኖናውና ዶግማውን ታሪኩንና አገራዊ መብቶቹን ጠንቅቆ ሳያውቅ በመንጋነት የመረጠውን ቡድን፥ ግለሰብ ጀግና፥ “አባት” ተብዩ ምንደኛ በጭፍን እየተከተላ የጋራ ሀሳብ ላይ መሰባሰብ ስለተሳነው ነው።

በመንግሥቱ ኃ/ማርያም፥ በመለስ ዜናዊ፥ በኃ/ማርያም ደሳለኝ፥ በአብይ አህመድና የክልል አሽከሮቹ የሚመራ ክርስቲያን እነዚህን ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ኦርቶዶክስ መሪዎችና የሚመሩበትን አስተምህሮ፥ ያላቸውን አገራዊ ርዕይና ግብ ለመገንዘብ እጅግ የተሳነው ብቻ ሳይሆን ራሱን ለሌላ ወገን ነፃ አውጭነት በባርነት ያስረከበ መንጋ ያስመስለዋል።

ከ፷ ሚሊዮን የማያንስ ክርስቲያን ራሱን እና ጠላቶቹን ተረድቶ ለሚጠቅመው ለውጥ በአንድነት እንዳይቆም ከተመሪዎቹ እጅግ በባሰ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቱ፥ ዘመናውያኑ ከርስቲያን ምሁራን፥ ጳጳሳቱ፥ ሰባክያኑና ካህናቱ ሁሉ ለዚህ አጥፊ ፖለቲካና ሥርዓት መእምናን እንዲገዙ ላለፉት ፶ ዓመታትበባርነት ስነ ልቦና የተጠቁ አስጠቂዎች ሆነው መገኘታቸው አንዱ መንስዔ ነው።

ዛሬም በጠላታቸው ቤተ መንግሥት ተገኝተው “ለችግራችን መፍትሔው አንተ ብቻ ነህ፥ አሁን ተመችቶናል፥ ስለ አንተ ጤንነትና ዕድሜ እንጨነቃለን” ሲሉ መሰማታቸውና ጠላታቸውን አውቀው ለመከላከል የሚሰባሰቡ ልጆቻቸውን እውቅና ከመንፈግ አልፈው ወደ ማሳጣትና ወደ ማሳደድ ያዘነበሉ መነኮሳትና ጳጳሳት እንዴት ተፈጠሩ?

የባርነት ስነ ልቦና የሕዝብ ብዛትን፣ ታሪክን፣ እምነትን፣ እውነትን፣ ባለአገርነትን ሁሉ ዋጋ ያሳጣል። የባርነት ስነ ልቦና ነፃ አውጭ መፍትሔ ሰጭ 3ኛ ወገን ያስጠብቃል፣ ሽባ ያደርጋል፤ ለስደት ያተጋል።

የባርነት ስነ ልቡና ትንቢት፣ ተአምር ያስጠብቃል። ፈሪና ከሰማዕትነት የመሸሽ ባህልን ጥበብ አስመስሎ በትውልድ ላይ ያሰፍናል።
ህዝብ ካላሰበ እራሱን የጨካኞች ማገዶ አድርጎ ያቀርባል። የሩቁን ከ1960ዎቹ ወዲህ የሆነውን ለግዜው ትተን በቅርቡ በትግራይ ወጣቶች መሣሪያነት፥ በሕወሃትና በኦነግ-ኦሮሙማ መንግሥት ሾፋሪነት ያለቀው መከላከያ፥ የአፋር፥ የአማራ፥ የኦሮሞ ወዘተ ሕዝብ ብዛት ይኼው በማገዶነት ራስን የማቅረብ ውጤት ነው።

ህዝብ የእያንዳንዱን ዜጋ የማሰብ መብት ካላከበረ፥ በጭፍን ተከታይነት የቡድን እሳቤ ሰለባና መንጋ ከሆነ —- ሁሉም ፈሪ ተከታይ ይሆናል። በራሱ ላይ ስለማይወስንና የቡደን መሪዎቹ መገልገያ ስለሚሆን እራሱን ባርያ ያደርጋል።

ስለዚህ ህዝብ የግለሰቦች ጥርቅም ስለሆነ ውጤቱም የግለሰቦች ጥርቅም ስህተት ወይንም ስኬት ድምር ነውና ህዝብ ይተቻል። ራሱን ለቡንን ፖለቲካ ባርነት የሚያስገዛ ግለሰብ ጥርቅም የሆነ ሕዝብ ባርያ ነው። አገሩንና ሃይማኖቱን፥ ሰብእናውን፥ ፍትህና እውነትን ሁሉ ነፃ አወጣሀለሁ፥ መርሃለሁ ብሎ በቡድንነት ላደራጀው ብልጣብልጥ ፖለቲከኛና ድርጅቶቹ ባርያ ይሆናል።

አሁን ያሉት በብሔር ቡድንነት አንጂ በሙሉ ነፃ ሰውነት ራሳቸውን ያልተቀበሉ ዜጎች ሁሉ የየቡድኖቻቸው መሪ ድርጅቶች አስተሳሰብና የተወሰነላቸው አኗኗር ባሮች ናቸው። ስለዚህ "ብሔረሰቦች" የነፃ አውጭዎቻቸው እሥረኞችና አገልጋዮች ከመሆናቸው የተነሳ በሚሉዮኖች በጦርነት ተማግደው ሌላውን ወገናቸውን እስከማጥፋት እንሚሰለፉ የሕወሃትና የኦነግ-ኦሮሙማ ሠራዊቶች ተጨባጭ ድርጊትና እልቂት አረጋግጦልናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ለግማሽ ምዕተ ዐመት በባርነት ለመማቀቁ ተጠያቂው ራሱ ነው። በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ለዚህ የታሪክም የእግዚአብሔርም ፍርድ ይጠብቃቸዋል። ብርሃንና ጨው ናችሁ ተብለው ጨለማና አልጫ ከመሆን አልፈው ለጥፋት ራሳቸውን አመቻችተውና ተከፋፍለው በማጋለጣቸው፥ እንዲሁም መነኮሳትና ካህናት ሳይቀሩ ልጆቻቸውን ለሚያጠፋ ሥርዓተ መንግሥትና የዘረኛ ፖለቲካ ርእዮት አገልጋይ ሆነው በመገኘታቸው ከገሀነም ፍርድ አያመልጡም።

ምክንያቱም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸውን "በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።"(የሐዋ ፳፥፳፰) የሚለውን አደራ በልተዋልና፤

እንዲሁም አግዚአብሔር በነብዩ ሕዝቅኤል አድሮ፡- " የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን? —— (ሕዝ ፴፬፥ ፪)፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና (ሕዝ ፴፬፥ ፰)፤ —— ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያሰማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።(ሕዝ ፴፬፥ ፰)፥ ——ራሳቸውንም አይላጩ የራሳቸውንም ጠጕር ይከርከሙ እንጂ ጠጕራቸውን አያሳድጉ። (፵፬፥፳) እያለ አዳኝቶባቸዋልና።

3 weeks, 4 days ago

https://www.facebook.com/share/r/4sKjnDisXpxt5dn5/?mibextid=4UDYQr

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

3 weeks, 6 days ago

እንዚህ መሆኑን ካወቅን በአሜሪካ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ (ሩሲያ፥ ግሪክ፥ ግብጽ፥ ኢትዮጵያ ወዘተ) ተባብረው ይህንን ግለሰብ ብቻ ሳይሆን በአሜሪካ ውስጥ ያለውን አስተሳሰብ የመዋጋት ኃላፊነታቸውን አንዲወጡ እትዮጵያኖች ቅድምያ ወስደው ቢሠሩ መልካም ነው።

#አብይ አህመድ በግልጽ እንዲያጠፋን ድጋፍ የሚሰጠው፥ ዘር በማጥፋት 36 ዓመታት የሠሩት ሕወሃትና ኦነግ ከፖለቲካ አውዱ አንዳየወገዱ በምእራባውያን ጥበቃ የሚደረግላቸው ኦርቶዶክስን ስለሚያጠፉ ይመስላል። ድረኖንና ብድርም የሚቀርበው ለዚህ ሊሆን ይችላልና ሁሉም ከእንቅልፉ ይነሳ!!

👇🏾👇🏾👇🏾

3 weeks, 6 days ago

https://www.facebook.com/groups/1034587796694448/permalink/2847118685441341/?ref=share&mibextid=NOb6eG

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

2 months, 3 weeks ago

https://sites.tufts.edu/reinventingpeace/2024/02/01/starving-in-silence-and-dizzy-with-excess-china-then-ethiopia-now/

Reinventing Peace

Starving in Silence and Dizzy with Excess: China then, Ethiopia now - Reinventing Peace

Between 1958 and 1961, the people of China suffered the greatest famine on record. Perhaps 36 million people perished. Astonishingly, this famine was concealed from the world and only became known more than 20 years later. The Article 19 Report on famine…

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ
2 months, 3 weeks ago
Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ
2 months, 4 weeks ago

ቤተክርስቲያናችን ከውጭ ከከበባት ጠላት ብዛትና የጥቃት ሁለገብነት አንጻር ሁሉም ምእመን ቆሞ ማየት ሳይሆን መፍትሔ በመፈለጉ መሳተፍ ግዴታው ነው።
በተጨማሪ ከውስጥ ያለው ኃላፊነትን አለመወጣት ጥያቄ ሊነሳብት ይገባል። የነፍሳችን ዋና መርክብ ቅድሰት ቤተ ክርስቲያንን በጠባቂነት ተሰይመውበት ሳለ የእረኝነት ተግባራቸውን የማይወጡ መኖራቸውን አውቀንም መፍትሔ መሻትም የሁሉም ግዱታ ነው። እኔ በአእምሮዬ የሚመላለሱ 6 ጥያቄዎችን አቅርቤአለሁ።
ምላሽም ሆነ የመፍትሔ ሐሳብ ያላችሁ መምህራንና ሊቃውንት ለውይይት አቅርቡት። እንደ ሰጎን አንገታችንን አሸዋ ውስጥ በመቅበርና ከእውነት በመሸሽ እንደማንድን አሁን በቤተ ክርስቲያንና በአገር ጠላት የሚፈጸምብት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምስክር ነው።

3 months ago

https://us06web.zoom.us/j/83732040233?pwd=mGaPandYf7211DbwmuSmgwZrajIUyS.1

It is live now and you can get in I you have the time

Zoom Video

Join our Cloud HD Video Meeting

Zoom is the leader in modern enterprise video communications, with an easy, reliable cloud platform for video and audio conferencing, chat, and webinars across mobile, desktop, and room systems. Zoom Rooms is the original software-based conference room solution…

We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 5 days, 11 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month ago

ጥራት ያላቸው የቤት ዕቃዎችንና የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ከእኛ ይግዙ። አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ 376 ያገኙናል። ባሉበት ሆነው ማዘዝ ይችላሉ። 0944222324

Last updated 23 hours ago