Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

Description
ወሳኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የሚነኩ አገራዊ ጉዳዮችን የውይይት አጀንዳ እንዲሆኑ በማቅረብ አስተያየትና የመፍትሔ ምክረ ዐሳብ ይቀርቡበታል። የሚያወያዩ የቤተክርስቲያንና ስለአገር የሚቆረቆሩ ወገኖች የሚያቀርቡትን ሀሳብ እንጋራታለን።

https://www.facebook.com/fwakie

Join me also here https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_Fant
Advertising
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 5 days, 7 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago

3 months ago

https://youtu.be/cUx8ZIZ9Rn8
አጥፊያችንን የብሔርተኝነት ፖለቲካ የክፋት ሕንጻ የምናፈርስበት ውይይት ይኖረናል። አስከዚያው ይህ የግል አተያይ እሁድ ከቀቡ 8 ሰዓት ጀምሮ ይቀርባል። ቀጠሮአችንን ይዘን አንጠባበቅ፥ አስተያየት እንጻፍ፥ አንጋራ፥ ላይክና ሰብስክራይብ እናደርግ። አግባብነት ያላቸው ጠቃሚ ወረቀቶቸን ላኩልኝ
እግዚአብሔር በቸርነቱ ለሰዓቱ በያለንበት ይጠብቀን፥

3 months ago
3 months ago
Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ
3 months, 1 week ago

ተቋሟዊ የሆነ የተደራጀ ሌብነትን በኮሚቴ ማጥፋት አይቻለም። መፍትሔው ሌላ ነው። ሌላ ጊዜ እንወያይበታለን።

3 months, 1 week ago
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ …

https://www.facebook.com/share/QEdcUjcsiNYqeT15/?mibextid=xfxF2i

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ ሰጡ።

"ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።"
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

መስከረም ፳፫ ቀን፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም.
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የሙስናና ብልሹ
አሰራር በዝርዝር በማጥናት የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው አጥኚ ኮሚቴ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትና ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የሠራቸውን ሥራዎች ሪፓርት በማቅረብ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ በመወያየት የሥራ መመሪያ ተቀብሏል።

ኮሚቴው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር ከውስጥ አልፎ በአደባባይ መነጋገርያ በመሆኑ በጥናት ላይ በተመሠረተ አግባብ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችልና የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲደራጅ የሚያደርግ የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶር)
እና ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርኩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት አባታዊ የሥራ መመሪያ "ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም። ያሉ ሲሆን ስለሆነም ሕግና ሥርዓትን አክብራችሁ፣ በእውነተኝነት ለቤተክርስቲያን፣ለእግዚአብሔርና ለራሳችሁ ብላችሁ ሳታፍሩና ሳትፈሩ ሥራችሁን ሥሩ። ሥራው ታማኝነት"ጥብዓት" ያስፈልጋል ብለዋል።

ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ሆናችሁ በጋራ ሥሩ ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ጠንከር ያለ መድኅኒት ሊሆን የሚችል ጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደምታቀርቡ እምነቴ የጸና ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም የተላካችሁበት ሥራ ያለ ውጤት የሚቀር መሆን የለበትም። ቤተክርስቲያን የተዋረደችበት ጊዜ ማብቃት አለበት ያሉት ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያናችን ራሷን አንጽታ ለሌሎች መልካም አብነት መሆን አለባት ካሉ በኋላ ዓለማዊያን የሚሰሩት ሥህተት እንዳይኖር በተግባር የምታስተምር ተቋም እንጂ በሙስና የምትታማ መሆን የለበትም ብለዋል።

ልጆቼ እውነቱን ለማውጣት ታጥቃችሁ ሥሩ በሙስና ህመም ለምትሰቃየው ቤተክርስቲያን መድኃኒት ፈልጉላት በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንመረመርም ማለት ራሱን ችሎ ወንጀል ነው ካሉ በኋላ ይህ ሥራ ለእናንተም ታሪክ ነው። እውነትን መሰረት አድርጋችሁ በመሥራት ታሪክ አስመዝግቡ ብለዋል።

በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይም ወደ እዚህ ተቋም የሚገቡ ሁሉ ይህን ያህል ጊዜ ቆይተን ይህን ያህል ይዘን እንውጣ የሚሉ እንጂ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩና የሚያስቡ እንዳልሆኑ ይታወቃል ካሉ በኋላ የተሰጣችሁን ኋላፊነት በትጋት ፈጽሙ ብለዋል።
በመጨረሻም ሥራችሁ ሁሉ የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን እንጸልያለን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

3 months, 3 weeks ago

በዐመሓራ የሕልውና ትጋድሎ ውስጥ የሚዋጉት "ብሔሮች" ተብለው በሕወሃትና ኦነግ ሕገ-መንግሥት የተፈጡሩት፣ ቡድኖች ናቸው። እነዚህ "ብሔሮች" የቅኝ ገዥዎች የሤራ ትምህርት ያሳወራቸው ልሂቃን የአእምሮ ውጤት የሆነው ሥርዓት መንጋዎች እንጂ እግዚአብሔር አልፈጠራቸዉም።

እግዚአብሔር የፈጠረው ሰውን ነው። ሰው ቤተሰብና ጎሣ ሆነ፤ ጎሣዎች ሰፍተው አገርና መንግሥት ፈጠሩ።

ሕወሃትና ኦነግ ግን ሰውን አጥፍተው የሚጠፋፋ ቡድን ፈጠሩ። ቡድኖችን ሁሉ በአማራና ኦርቶዶክስ ላይ አዘመቱት።

የብልጽግና ወንጌሉ አብይ አህመድ አሊ የሁለቱ የኢትዮጵያ ካንሰር ድርጅቶች የአስተሳሰብ ድቅል ልጅ የሆነ።
ሰውዬው ብልጽግናን መርቶ ወላጆቹን ሳይቀር የሚያጠቃ ተራጋጭ መካን ኢሰብአዊ እንስሳ በቅሎ ሆኖ ተከሰተ።

ታላቋ ኦሮሚያ፣ የኩሽ ኢፓየር፣ የቀይባሕ ኢሬቻ፣ የምሥራቅ አፍሪካ ንጉሥ ወዘተ ቅዠቱን ለማሳካት በደም ጎርፍ እየዋኘ ነው።

ዐመሓራ ሰውነቱን ለማትረፍ፣ ፍትሕን ለማግኘት፣ እውነትን ከቅዠታም የፖሊተካ-ሥር ብሔርተኝነት ለመከላከል ቆመ። አስገዳጅ የህልውና ጦርነት ውስጥ ገብቷል። ታዲያ ዐመሓራ እንዴት ዐሓራነት ለማጥፋት የተፈጠረ የብሔርተኝነት ጽንሰ ዐሳበን ለመውረሰ ከጅሎ፣ የሚጠላውን ለመሆን
"የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም" ወደማለት አዘነበለ?

ታዲያ ይህንን "ዐመሓራነት" የተባለ እሤት ሕወሃትና ኦነግ በተጠሩበት ግብሩ የከፋና ከፋሺዝም ሊለይ የማይችል ስም በ"ብሔርተኝነት" የሚሰይሙ የብአዴን እንግዴ ልጆች ብቅ አሉ እና "ዐመሓራነት" ማለትም ክብረ-ሰብእ፣ ክብረ ሀገር፣ ፍትሕ፣ እውነተኝነትን ደፍጥጠው "ያማራ ብሔርተኝነት ይለምልም" ወይንም "ፋሽዝም ይንሥ" አሉ። 50 ዓመት ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐመሓራነትን፣ ኦርቶዶክሳወዊ ክርስትናን ለማጥፋት በታተረው "ብሔርተኝነት" ሥር "ዐመሓራነትን" ጭዳ ሊያደርጉ ተነሱ።

በእርግጥ ዐውቀዉት አይመስለኝም ይህን ከቅዱስ አስተሳሰብና ማንነት ወደ አጥፊና ርኲስ ፖለቲካ-ሥር ብሔርተኝነት የተንደረደሩት። የዐመሓራ ማኅበረሰብ ስብስብ ብሎ ጠንክሮ በአንድነት ብሔርተኞቹ የደቀኑበትን የህልውና አደጋ መቀልበስ የሚችለው እንደ ሕወሃትና ኦነግ ያለ ድርጅት የሚፈጥራቸው ከሰውነት የወጡ አራጅና አጥፊ መንጋ ፈጥሮ መልሶ ሲዋጋ ነው ከሚል አማራጭን ያለመመልከት እጥረት ይሆናል።

ዐመሓራ ሆይ የሰው ልጅ አራዊትን ለመከላከል አራዊት ልሁን ብሎ አያውቅም። እንደዚሁ በተለያዩ ማኅበረሰቦች ስም ራሳቸው ነጻ አውጭና አዲስ አገር አዋላጅ አድርገው ከሰብእና ውጭ በሆኑ ልሂቃን መሪነች ህልውናህን ሊያጠፋ የሚወገህን አካል ለማሸነፍ የግድ ጠላትን መምሰል ከያሻህም። ዐመሓራነት በቂ ነው።

3 months, 3 weeks ago

ከላይ የለጠፍኩትን የዐመሓራነትና የብሔርተኝነት ጉዳይ ማብራራት ይኖርብሃል የሚል ግብረ-መልስ ስላገኘው 2 ክፍል ያለው ቪዲዮ ሠርአቼአለሁ። ከ1፡30 ሰዓት በኋላ አቅርባለሁ https://youtu.be/Vy1T26T2z7U?t=932

We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 5 days, 7 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago