ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

Description
እኔና ቤቴ ግጥም የህያው ስሜት መግለጫ ከብቸኝነት ግዞት ማምለጫ መሆኑን እናምናለን፡፡ እኔና ቤቴ ግጥም ከቃላት ስደራ በላይ የእውነትና የእምነት ውጤት መሆኑን የነቆራ እና የምስጢር ዋሻ መሆኑን እናምናለን፡፡ አምነንም እነንፅፋለን!
አባላችን ይሁኑ!
°
°
°
@mr_trump_poems
ግጥሞትን ለመላክ እና ለማንኛውም አስተያየት
@termo_dynamics ን ይጫኑ።
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 months, 1 week ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

2 months ago

How beautiful to find a heart that loves you,without asking you for anything, but to be okay.

-Khalil Gibran

4 months, 4 weeks ago

*፨
እግሬ ወደ ጉድጓድ ፥ ነፍሴ ወደ አምላኳ ፥ ልቤ ወደ ሞቱ፥ ለመሄድ ሲቻኮል
እንደ እንቅፋት ሆኖ፥ መንገዴ ላይ አለ፥ መኖር ይሉት ተንኮል
ሞቴን እንዳልጨብጥ ፥ ለሙሉ እኔነቴ ነፍሴን እንዳልወክል
መኖር እግሬ ስር ፥ እንደ ታኮ አለ ፥ እንደ መስናክል

(ከመኖርም እሷ : ከህይወትም ፍቅሯ
እሷ እያለች ላልሞት የገባሁላት ቃል : እንዲሁም መኖሯ )

ልቤን ያደረገው...
ለሞት እንዳይጨክን ፥ እንዳይርቅ ከነፍሱ
ከቤቱ ግድግዳ ፥ ከልቡ አፀድና፥ ከፃፈው ደብዳቤ፥ በጉልህ አድምቆ ያስቀመጠው ጥቅሱ

(እንዲህ ይላል ጥቀሱ...)

''አንቺ ኖረሽ እንጂ ~ መኖር የጣፈጠ
አንቺን አይቶ እንጂ ~ ይህ ቀድሞ ሟች ልቤ ~ ህይወት የቋመጠ
መኖርማ እንደሆን !
የሟቾች እዳ ነው ~በለት ዕለት መቅለጥ ~ በጊዜ ሚከፈል
መኖርማ እንደሆን !
ልክ እንደ ጫጩት ነው ~ በትዕግስት የሚገኝ መሞት ሲፈልፈል ''

ይል ነበረ ጥቅሱ
(እውነቴን እኮ ነው...)
እሷ ኑራ እንጂ፥ ለነፍሴማ እንደሆን...
ይሻላት ነበረ፥ ሁሌ ከመታመም ፥ ያንድ ቀን ሙት መሆን ።

፦ ግዑዝኤል*

6 months, 1 week ago

*??⚰️?

አስር ሞት ቁሟል ከ'ደጄ ~
አይኔ ላይ ያንዣብባሉ ~ በርካታ ውል አልባ ቅርፆች
በቀየው ህይወት የለችም ~
ሚሰማው...
በሬሳ ያጥንት ትፍግፍግ ~ ሚወጡ የሙታን ድምፆች።

ላሽወይና ያሟሟቀ አፍ ~ ያወርዳል የዘመን ሙሾ
ሰዉ ከሰው ቂም ተቆጣጥሯል ~ አፍርቷል የበቀል እርሾ
ለሰርግ የጣሉት ዳስ ላይ ~ ሞት ወረደበት እስክስታ
አባት በልጁ ሞት አለቀሰ ~ እናት ወደቀች ራሷን ስታ።
ተስፋ መቁረጥ ንጉስ ሆነ ~ ተስፋ ራሱ ተስፋን አጣ
ደህና ውሎ ቤቱ አይገባም ~' ደህና አውለኝ ' ሲል የወጣ።
ቄስና ሼኩም አንድ ላይ ~ ፈጣሪ ላይ አኮረፉ
" ወይ ፍረድ፤ ወይ ስልጣን ልቀቅ "~ ሲሉ ጌታቸውን ወረፉ።

ይሄውልሽ እኔ ቤት ነኝ ~ ሰፈሩ በሞት ሲታጠብ
የሟቹ ቁጥር አይሎ ~ የቀብር ቦታ ሲጣበብ
አካሌን ቀቢፀ ተስፋ ~ የስጋት ደረመን ሲያጥር
በነፍሴ ትርትር እላለሁ ~ ዙሪያዬ ኮሽ ሲል ቁጥር።

ቆይማ...
( ምንድነው እዚህ ሚሰማኝ?)

መባርቅት ያጀቡት ክላሽ ~ የመሞት አዋጅ ለፈፈ
ይሄውልሽ...
በጎኔ ጥይት አለፈ።
(ደንገጥኩ )
መስኮቴን ከፍቼ ወጣሁ ~ መንገዱን በትኩረት ማተርኩ
ወዲያው ግን (አንድ ቀን የነገርሽኝን )
'' በሬ ሳላይ መጣሁ ከዛ'ስከዚ ድረስ "
ምትል ቅኔ አስታወስኩ።

ሰፈሩ እንዳለ ወድሟል ~  አንድ ቤት የለም
የቀረ (አንድ ሰዉ የለም የቀረ)
ያ ዋርካ (አድባራችንም )...
አንገቱን ደፍቶ ለሚያየው ~ ይመስላል ያቀረቀረ።

[ ወዳንቺ ልመጣ ወሰንኩ ]

መሬት ላይ መንፏቀቅ ጀመርኩ ~ በቁሜ መራመድ ፈራሁ
ከፊቴ ያለን ሬሳ ~ ቀስ ብዬ ወደ ጎን ገፋሁ
ታውቂያለሽ....
ቢበዛ ሰባት ዓመት ልጅ ~ ሰባቴ ጥይት መቶታል
[ መንግስት ላይ ተስፋ ብንቆርጥም ~ ነገር ግን እግዚሩስ የታል?]
ከኢየሱስ ስቃይ በማያንስ - ብዙ ሰዉ እዚህ ተሰቅሏል
ያውልሽ እዛ ጋ ደግሞ
የኢዮብን ቁስል በሚያስንቅ ~አንድ ሰዉ አካሉ ቆስሏል።

ይህንን 'የሞት ደብዳቤ ' ቢቀናኝ (በህይወት ብተርፍ)
ራሴው እነግርሻለሁ
አሊያ ግን ሞት ከቀደመኝ...
ራስሽ እንድተነቢው ~ ኪሴ ውስጥ አኖረዋለሁ።
ከደረት ኪሴ ስላለ -ስትቀብሩኝ መሬት ይወድቃል
ያን ጊዜ በፍጥነት አንሺው
{ አደራ እንዳትረሺው }

፦ ግዑዝኤል
28/12/16
ረፋድ 4:37

{መኖር ሲናፍቁ ሞት ለቀደማቸው በሙሉ...}*

6 months, 1 week ago

አሪቲ ጎፈሬ ፡ ቄጠማ ከመከም፣
ያስራ አንዱን ደዌ ፡ ዳብሼ ልታከም
ተውረግርጋ መጣች፡ ኮረዳ መስከረም።

የሰኔ ምንጣፍ ላይ
ሃምሌን ተንተርሳ
ነሀሴዋን ለብሳ
ባያት ደሜ ሞቀ፡
አምና መጣች ብዬ
ጥላኝ መኮብለሏ፡ ካቅሌ ላይ ተፋቀ።
ጣለኝ ያልኩት ገዴ፡ ቅኔ ቀን ሲያዝብኝ፡
ጭቃዋ ላይ ወደቅሁ፡ አደይ በቀለብኝ።

ኮረዳ መስከረም...

ይቺ በላዔ-ሰብ
ይቺ ድራኩላ...
ይቺ ድራ ኩላ
የዘመን መንትያ
ክራንቻዋን ስላ፡
ያረጁ ዐይኖቿን
እንደልጅ ተ´ኩላ
አምናና ካቻምና
ያስተረፈችውን
እድሜዬን ልትበላ፤.
መጣች እፍረት የላት
መጣች ረፍት የላት።
እሷ ምን ቸገራት?
ደንግላ ስትመጣ
አቅፌ የምለቀው
ቆዳዋ ይፋጃል...
እሷ እየታደሰች
እሷ እየደምቀች
የኔ ቀን ያረጃል።

መጣች ነጋ ደግሞ
መጣሽ ነጋ ደግሞ...
ኮረዳ መስከረም...

አወይ ጅል መሆኔ
ጡትሽን ማመኔ
ዳሌ ቅንፍሽን
ልታቀፍ ማለሜ፡
ለሚሸሸኝ ገላ
እድሜ መሸለሜ፡
ባከምሽኝ በወሩ
አርጅተሽ ስትሄጂ
ደግሞ መታመሜ፣
በያመት ስትደምቂ
በያመት መክሰሜ።
መስከረም ኮረዳ
ውበትሽ ሊከዳ
ሊሄድ ሊሸሽ ገላሽ
ለምን ይሞቀኛል
ደስ ደስ ይለኛል
አካለ ቢስ ጥላሽ?

ኮረዳ መስከረም
ምን አለሽ አደንዝዝ
ያምና ክዳትሽን
ካይምሮ የሚደልዝ
«ነበር!» የሚያስረሳ
የወደቀን ፍሬ
አብዝቶ ሚያስነሳ፤

ያበረድሽው ደሜን
ከራርሞ የሚያግል
ዝንትዓለም ተኝቼሽ
ያስመሰለሽ ድንግል።

አፍዝ ምን አለሽ?

መስከረም ኮረዳ፡
በአሮጊት እስትንፋስ
በልጅ ልስልስ ቆዳ፣
የሚያውረገርግሽ
ችክችካ ድለቃው
ሄደሽ ተደምስሶ
ትዝታ እስኪቀዳ፡
እንደ አምና ካቻምናው
እስክንከዳዳ፡
እድሜ ምናባቱ
ይሄው ረጲሳ
ይኸው ረገዳ።

(ቼቼ... ሼሼ... ቼቼ)

6 months, 1 week ago

ያሰኘኛል ደርሶ
አቅፌሽ ባልመሸ ጊዜ ባልቆጠረ
አይንሽን እያየሁ
ጠረንሽ ዘላለም በላየ በኖረ

የት እንደሰማው ያላስታወሰውን ግጥም ለራሱ ሲያነበንብ ነው የደረሰችበት። ሲያያት ፈገግ አለ። ሳቀች።

ይዋደዳሉ
እሱ ሲነሳ ስራው ስለእሷ ማሰብ ነው።
እሷ ስትተኛ ጸሎቷ እሱን ሰላም አንቃልኝ ነው።

ሲመጣላት በአክብሮት ጎንበስ ትላለች
ግንባሯን ይስማታል
እጁን ታስታጥበዋለች
ታጥቦ ያጎርሳታል
እሷ ጎርሳ እሱ ይጠግባል
እሱ ጠግቦ እሷ ታገሳለች

ይመሻል  ይተኛሉ  ይነጋል
ህይወት ይቀጥላል
እሷ ስትነሳ የእሱ ቀን ወገግ ይላል።
ሲነጋላት ይንጠራራል
ሲንጠራራ ትነቃለች
ስትነቃለት ቀኑን ይጀምራል
ቀኑን ሲጀምር ህይወት ይጣፍጣታል

እራሱ አስነጥሶ ይማርሽ ይላታል
ህይወት ይቀጥላል
ሲሰራ ትበረታለች
ስትበረታለት ጉልበት ይሆነዋል
ጉልበት ሲያገኝ ትደሰታለች
ስትደሰት ሳቁ ይዋባል
ሳቁ ሲዋብ የበለጠ ነገዋን ያስናፍቃታል
ነገን ሲናፍቁ...    ህይወት ይቀጥላል።

ፍቅሩ ይባላል። ፍቅርተ ትባላለች።

መኖሪያ አድራሻቸውን እንዲህ ብሎ መናገር ያስቸግራል። ለዚህም ነው አንድ ቀን በድንገት ወደፈሳሽነት የተቀየሩት።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ምርምር ጣቢያው ውስጥ ሦስት ነጭ ጋውን የለበሱ ሰዎች ይነጋገራሉ። ፀጉሯ መሀል ጥቁር ጣል ጣል ያለባት ፣ 50 አጋማሽ ላይ የምትገመት ትንንሽ ግን ንቁ አይኖች ያላት ሴት መናገር ጀመረች። የቡድኑ መሪ እንደሆነች ያስታውቃል።
"እንደተነጋገርነው አሁን ወሳኙ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። የምንፈልጋቸውን ሁለት ናሙናዎች አግኝተናል። አለችና 2 የናሙና መያዣ(test tube) ቀና አድርጋ አሳየቻቸው በቀኜ የያዝኩት ሴቷ ስትሆን የተቀየረችውም ወደ F8 ሞለኪውል ነው በግራ እጄ ያለው ደግሞ ወንዱ ሲሆን እሱንም ወደ B9 ቀይረነዋል። አሁን ቀጣይ ሂደቶችን መቀጠል እንችላለን አለችና ሁለቱንም ናሙናዎች አራርቃ አስቀመጠቻቸው።  ከዛም ሦስቱም ስለቀጣዩ ደረጃ እየተነጋገሩ ከክፍሉ ወጡ። ያስቀመጡበት ክፍል ግድግዳ ላይ በትልቁ የተቀመጠ ጽሑፍ እንዲህ ይላል

አቢይ አላማ : ፍቅርን በላብራቶሪ ማበልፀግ
ንዑስ አላማ : ስለ ፍቅር ባህሪያት ጥናት ማድረግ

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በየቀኑ እየተመላለሱ በናሙናዎች ላይ የሚፈጠሩ ለውጦች ካሉ ይመዘግቡ ጀመር

የመጀመሪያ ቀን : ምንም ለውጥ የለም
ሁለተኛ ቀን : ምንም ለውጥ የለም
ትንሽ አቀራርበዋቸው ሄዱ
ሦስተኛ ቀን : ምንሞ ለውጥ የለም
አራተኛ ቀን : የተለየ ትንሽ ለውጥ ያለ መሰላቸው። ሲያጠኑትም  B9 የነበረው B8 F8 የነበረው F9 ሆኗል። ይሄም አንድ ሽራፊ አካል ከB ወደ F ሄዷል ማለት ነው።

ከዚህ ምን አየን ተባባሉ።
ከሦስቱ ውስጥ ልጅ እግር የሆነው ሁለቱንም እጆቹን ከነጩ ጋዎን ኪስ ውስጥ ከትቶ እንዲህ አለ
"ይሄ ለመፈጠር ቀናትን ወስዷል። ትንሽ ነገሮቹ እስኪስተካከልለት ባለበት ሆኖ ጠብቋል። ከዚህም ተነስተን 'ፍቅር ይታገሳል' ማለት እንችላለን ብየ አስባለሁ"
"እሺ መልካም አንተስ"  አለችው ሴቷ የቀረውን ራሰ በራውን ሰውየ። እሱም መነጸሩን እያስተካከለ
"መገኛቸውን የፈለገ ብናራርቃቸውም ለመገናኘት አላስቸገራቸውም ከዚህ በመነሳት እኔ ደግሞ 'ፍቅር ርቀት አይገድበውም' እላለሁ"

"ጥሩ  የኔን ሀሳብ ለጊዜው እናቆየውና እንቀጥል።"

ጥናቱ ቀጠለ። F እስከ 10 B እስከ 7 ይደርሳሉ አንዳንዴ። ይገለባበጣሉ። ይቀባበላሉ። አንዳንዴ B ከነበረበት 9 ሲጎድል ሌላ ጊዜ ደግሞ F ከነበረበት 8 ያንሳል። ከዚህ ተነስተውም ተጨማሪ ሀሳብ አስቀመጡ
"ፍቅር የሁለቱንም ወገን ይሁንታ የሚፈልግ መስተጋብር(reaction) ነው።"

ማቀራረባቸውን በቀጠሉ ቁጥር የሞለኪውሎቹ ግንኙነት የበለጠ እየፈጠነም እየጨመረም ሄደ። አንድ ቀን ቦታ አቀያይረዋቸው ሄደው ሲመለሱ F7 B7 ሆነው ቆዩኣቸው። ይህ ማለት ከሁለቱም የወደቀ የጎደለ ቅንጣት አለ ማለት ነው። ሲፈለጉም ከናሙና ማስቀመጫዎቹ ውጭ ወድቀው አገኟቸው። ፈስሰዋል። ከዚህ ተነስታም ሴቷ የቡድን መሪ እንዲህ አለች
"ፍቅር ሁሌም የመሳሳብ የመፈላለግ ስሜት ነው። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ያንን አካል ከመናፈቅና ለማግኘት ከመጓጓት ስሜት ምንም ነገር ሊያርቅህ አይችልም።"
ራሰ በራውም በተራው
"ቦታ አቀያይረናቸው እንኳን የመገናኘት ሙከራቸውን አላቋረጡም። በየትኛውም ሁኔታ ሆነው ጥረታቸውን ቀጥለዋልና 'ፍቅር ተስፋ አይቆርጥም' ማለት እንችላለን ብየ አስባለሁ"

ልጅ እግሩን ባልደረባቸውን አንተስ ምን ትላለህ ሲሉት ፈገግ አለና "አይ ምንም" ብቻ ብሎ አለፈ። ያሰበውን ግን ማስታወሻ ደብተሩ ላይ አሰፈረ።
"ለመሄድ ቢፈልግም ያሰበው ቦታ አልደረሰም። መንገድ ተሳስቷል። መድረሻውን ስቷል በዚህ ተነስቼም 'Love is blind' ለማለት እገደዳለሁ።" ብሎ አስቀመጠ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ምርምሩ አለቀ።
አቢይም ንዑስ አላማውንም አሳክተናል ይላሉ ተመራማሪዎቹ። እነዛ ሞለኪውሎች ሽቶ ተሰርቶባቸው በውድ ዋጋ ይሸጣሉ። F&F ሽቶ የከተማዋን ገበያ እያጨናነቀው ነው። ሲመረት ጥንድ ጥንድ ሆኖ የራሱ መለያ ያለው ሲሆን አንዱ የወንድ አንዱ የሴት ሽቶ ነው። በዘፈቀደ ይበተናል ያንን ጥንድ ያገኙ ሰዎች በየትኛውም ሰበብ ሆነው ይገናኛሉ። ፍቅር ይጀምራሉ።
የሽቶው ካርቶን ስር በቀይ የተጻፈ ማስጠንቀቂያ እንዲህ ይላል።

ባል/ሚስት የማይደርስበት ቦታ ይቀመጥ።

አለቀ
       በአቤኒ የተጻፈ

ከዘመናት በአንዱ አመት በሆነ ወር የሆነች ቀን ላይ በሆነ ቦታ ይህ ተጽፎ ነበር።

6 months, 3 weeks ago

እዩዋት
መንግሥተ ሰማያት፡
በባሕር መካከል፡ በአጥማጅ የተጣለች
በዓይነት በዓይነት፡ ዓሣዎች የያዘች
መረብ ትመስላለች፤»
ብሎ በምሳሌ ፡ ነግሮን ነበርዝ ጌታ
እንኳንም የመጣሽ
ሚስጥሩ በሙሉ፡ ስናይሽ ተፈታ።

መንግስተ ሰማያት፡ በጻድቃን ልመና
ጅማትሽ ሳይደድር፡ ቋጠሮሽ ሳይፀና
እኛኑ ለማጥመድ፡ ገና ከመጣልሽ
ስንቱን መልካምና፡ የረከሰ ለየሽ?

ተውጦ ድምፃቸው
ለስልሶ ቆዳቸው
ዓሳ ከመሰሉን፡ ከእባቡ ከጊንጡ
ስውር መርዛቸው ፡ ሊነድፉሽ ሲያወጡ
ባንቺ የተነሳ ስንቱ ተጋለጡ?

መንግስተ ሰማያት ፡ ታናሺቱ መረብ
ደፋ ቀና እያሉ፡ በዓሦቹ ወረብ
ከሚያዜሙት መሀል፡ ያጠመድሽው ዓዞ
ሲበጥስሽ አይተን፡ በጥርሱ ገዝግዞ
ከአውሬነቱ ጋር ፡ ባንቺ ተዋውቀናል
የይምሰል ሀዘኑን፡ እንባውን ንቀናል
ከእንግዲህ በኋላ፡
ያንቺ እድል ቢጠምም፡ የዘርሽ ይቀናል።

መንግስተ ሰማያት ፡
Kingdom of heaven፡ የሰውነት ወንፊት
በክብር ስትቆሚ፡ ካበጀሽ ጌታ ፊት
በምኞት በሀሳብ፡ ድርጊት በወሬ
ላቆሰለሽ ፀላይ፡ ለነከሰሽ አውሬ
Heaven መንጓለያ ፡ መረብ ነሽ ለክሱ
የጣልሽው ነውና ፡ የሚፋጨው ጥርሱ።

6 months, 3 weeks ago

ያልፉልኛል ብዬ፣ ተማሪ ቀኖቼ
አስተማሪ ሆኜ ፣ ጀርባዬን ሰጥቼ
ሰሌዳው ላይ ፊቴን፣ ስቋጥር ስፈታ
ድንገት መንሾካሾክ ፣ ከጀርባ ሰምቼ፡ ዞር ስል ዝምታ...
«ማነው የሚያወራው? ወይስ ሁሉን ልምታ?»

ጥቂት ፀጥ አለና፡ ሹክሹክታው ቀጠለ 
በንዴት በግኜ፡ ዞር ስል አየሁት
«አንተ ነህ አይደለ? ...»
«የምትረብሸኝ?» ነደድኩኝ በቁጣ

«ና! ግጥም ና! ውጣ!»

(ጧ! )

ዘርጋ! ግጥም ዘርጋ!
በቀን`በር የኋሊት ፣ የታሰርኩኝ ፊጋ
ሳቢውን ጎትቼ ፣ ላሳልፍ ስፈጋ
ለምን ነው ጀርባዬ፡
ታሪክ እያነሳህ፡ የምትፈተፍተው?
ዞሬ ስሟገትህ ፡ የፊቴን እንድተው?
ኧረ ተው? ኧረ ተው... ?!

ያረድኩትን ፍስክ፡ ትናንት ቋጭቼ
ዛሬ ልፆም ብዬ፡ እህል ውሃ ትቼ
ማጣጣም ስጀምር፡ የረሀብን ጸጋ
አ'መህ ለመታወስ፡ ጥርስ የቀረህ ስጋ
'ካፍ አድረህ ለማግደፍ፡ ጥርስ የቀረህ ስጋ...!
ባደረ መጠዝጠዝ ፡
ባለፈ መነዝነዝ ፡ ዘርጋ ግጥም ዘርጋ...!
ዝቅ አርገው እጅህን፡ ወደኔ አታስጠጋ

(ጧ! ጧ! )

ያለፈን ለመጪው ፡ እንዳላስቆጥረው
የማላውቀውን ነው ፡ ልፅፍ የምጥረው
እድሜ ላንተ ግጥም፡ ልቅጣ ብዬ ቀረሁ!
ዝጋ ግጥም ዝጋ፣
ቆሽቴን አታጭሰው
ስትጮህ ስመታህ
ሲነደኝ ብደፋህ፡ ቤትህን ባፈርሰው
መመጠን የማይችል? ጀማሪ ሊለኝ ሰው?

ግጥም ተው! ግጥም ተው!
ሲቃህን ዋጥ አርገው
አፍንጫህን አብስ፡ እንባህን ጥረገው
ጥረግና ስማ...

ያልመጡ ቀናቴን፡ ላለፉት ልታማ
ጥበቃን በስንኝ፣ መቅረትን በዜማ
ለውሰህ ልትግተኝ፡ እረፍ አትታገል
ከአፈር ነው «እፍፍፍ» እንጂ ፣ አይወራም ከገል
ከሙት አትሟገት፡ ቀብረህ ተገላገል
ቀንጥሰው ሀረጉን፣ ስንኝህን ቀልጥም
እያልኩኝ ስዳረቅ...
ዞሬ ቀረሁ ባንተ፣ ዝጋ ዘርጋ ግጥም!

(ጧ! ጧ! ጧ! )

የፊቴ ጥቁር ነው፣ የጠፋ ሰሌዳ፡ ያልተደነገገ
ከሚሞቀኝ ትናንት፣ የማላውቀው ነገ
እፈጥራለሁ ብዬ፣ ሳወርድ ሳወጣ
በቃል ስታስቀረኝ፡ ሰይጣኔስ ቢመጣ?
በስሜት ስይዝህ
እጄ ላይ ብትሞትስ?
ውጣ ግጥም ውጣ!

(ጧ! ጧ ! ጧ! ጧ! )

Red-8

6 months, 3 weeks ago

ፃድቅ አያደርግም፡
በገዳይ መቀደም
ዝም በይ ያ'ቤል ደም!
ደርሰሽ አትጩኺ፡ እንደተበደለ
ለሁለት የጣሉት፡ ላንዱ እየታደለ
ፍቅር መተማመን፡ በእጣ ከጎደለ
የፉክክር ሜዳ፡ ከተደለደለ
ከዚያ በኋላማ፡ ሞት በዘር አይደለ?
ለሟች እና ገዳይ፡ ምን ይሰራል ድንበር
መጮህ አስቀድሞ፡
የደረሱበት ጋር፡ ላለመድረስ ነበር።

ፅጌሬዳ ቀንበጥ ፡ እሾኋ ሲወጋት
ብትጮህ እሪ ብትል፡ ተካይ ምን ያድርጋት?
እንዴት ትፀድቃለች?
እሷ ብትለሰልስ፡ ሌላውን ባትጎዳ
በዘሯ አይደለም ወይ ፡የመጣባት እዳ?

ፃድቅ አያሰኝም
በገዳይ መቀደም
ደርሰሽ አትጩኺ፡ዝም በይ ያ'ቤል ደም

እየበጠበጠ፡ ለጣለው ወላጁ
አንዴ እንደ ብርሌ፡ ከተበጀ ልጁ
ቢነቃም ባይነቃም፡ ለጠጅ የሚጋጭ
ሟችም ያው ገዳይ ነው፡ አልቀናውም እንጂ።

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 months, 1 week ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago