የግጥም መድበል

Description
እናንተ ለግጥም ጆሮ የሰጣችሁ
እናንተ ለግጥም የበራ አይናችሁ
እናንተ ግጥምን ያከበራችሁ
ይሔው ማረፊያ ቤታችሁ።

ኑ! ጉልበታችሁን እጠፉት።

ግጥም

አስተያዬት ካላችሁ

@tilahun5 ላይ ማድረስ ተፈቅዶአል።
Tags
We recommend to visit

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 6 months ago

?? የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ ??

For promotion and Advertisements
? @Mussegirma

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo

1 month, 3 weeks ago

ሰው እንደ አሸን በዝቶ በሞላበት ምድር
አፌ ሳይናገር ቃላት ሳልደረድር
የሰው ዘር መራቤን የአይኖቼን ናፍቆት
ካንድ አንቺ በስተቀር ማን አይቶኝ ማን አውቆት
ምክንያት ስፈልግ እንባዬን ለመዝራት
የትም ትቢያ ሲሆን የወንድነት ኩራት
ከማኩረፍ ስላመድ
ከሀዘን ስዛመድ
ህይወት ተስፋ ሲያጥረኝ ሞቴን ስደግሰው
ካንድ አንቺ በስተቀር
ማን ነበረ ያለኝ 'አይዞህ' ቀርቦ እንደሰው

የፊቴን ጨለማ ግንባርሽ ደገመው
የእንባየ መስመር ጉንጭሽን አመመው
ሲከፋኝ ተከፋሽ
ስወድቅ አብረሽ ጠፋሽ
መሠልሽ እና እራሴን ጠበበቺኝ አለም
ካንቺ ወርድ ቁመት የሚበልጥ የለም።

የፍቅር መለኪያው
የሠላም መስበኪያው
ከዚህ እስከ አንቺ ነው የደግነት ዙፋን
ታዲያ
እኔና ምስሌ ዛሬ ለምን ከፋን
ለምደን ብትርቂን አቋቋምም ጠፋን።
ቢሆንም ሔደሻል

2 months ago

ወጋገን ራቀህ
ከፊት ለፊትህ ላይ ጨለማ ተጣለ?
መጓዝ ስትጀምር
ሀሞትህ ፈሰሰ ጉልበትህም ዛለ?
እንዳው የሱስ ነገር የሚልህ ሰው በዛ
ንግግርህ ሁሉ አጧል አይደል ለዛ
ደከመህ
ታከተህ ሰለቸችህ አለም?
አይዞህ ቀና በል ግድ የለም
መንገዶቹ ሁሉ
በተዘጉ ጊዜ ከተስፋህ ተሟገት
ወትሮስ
ፋሲካ ለመድረስ
ያደክም የለም ወይ መስቀሉን መጎተት
ካደረጉበት ግፍ ከፈተኑት አንጣር
ምን አላት እና ነው ለመነሳት መጣር
የልቅ
ወደ ነገ መንገድ
ዝም ብለህ ተራመድ

2 months, 1 week ago

መንገድህ አልቀናም
ዳግም ስትራመድ ፤ መንገዳገድ በዛው
ሺ ላብ ጠብ አድርገህ
ለቁርስህ አይበቃም ፤ ድካምህ የገዛው።

ለውጥ ልብህ አለ ፤ ውሉን አትጨብጥም
የነካኸው ሁሉ
ያተርፈኛል ስትል ፤ አይነቱን አይሰጥም።

ሰው ሁሉ የሚልህ ፤ መጓዝህን አታቁም
ግን~~~
ታግለህ ከዛሬ ጋር ፤ ጥለኸው አታውቅም።

ገፍ ጨብጠህ ነፋስ ፤ ወርቅ ስታፍስ አመድ
አሁን ደረስኩ ስትል ፤ ሌላ ቀጣይ መንገድ
ይሄን ሁሉ ትጋት ፤ ያልተረዳ ዘመድ
ከበበህ ዙሪያህን ፤ ማረፊያ ጥላ አጣህ
እንደ ትላንትናህ
ለነገ የሚሆን ፤ ተስፋ ሳቲዝ ወጣህ?

በቃ ባለህ እርጋ ፤ ወደ ውስጥህ ተንፍስ
ወዝህን በምንም ፤ ሜዳ ላይ አታፍስ
ለውጥ ካልተፃፈ
ወይም ከዘገዬ ፤ ካሰብከው ላይ ማረፍ
ያለህን አትጣል ፤ ከያዝከው ነው ማትረፍ።

እኔን ባይ

2 months, 3 weeks ago

በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

2 months, 3 weeks ago

እፈራለሁ
[ ምካኤል ምናሴ]

ቆይ፥
መንፈስ ብትሆኚስ?
ለእኔ ብቻ የሚታይ ፥ ከህልም የተሰራ፥
'ዴልዩዥን' ብትሆኚስ?
የምኞት መዶሻ ፥ ጠራርቦ ያቆመሽ ፥ የልቤ ፈጠራ፤

ከጨዋታ መሐል ፥ ድንገት ብትጠፊብኝ፤
'የታለች?' ስላቸው፥
'ማን ናት ደሞ?' ብለው ፥ ሰዎች ቢስቁብኝ፤

ህልም ብትሆኚስ?
ስነቃ ብትቀሪስ?
ቆይ አሁን፥
ጭራሹን ባትኖሪስ?

ሞልተሽኝ በእቅፌ፥
እጆቼን ቀንፌ፥
ደስታዬ እንደድመት ፥ ልቤን እየላሰው፥
ሳቅ ሆዴን ሲያምሰው፥
ባዶዬን ቢሆንስ፥
ብቻዬን እንደእብድ ፥ የምታየው ለሰው?
እንደንፋስ ነክቶኝ ፥ ሲያልፍ ሰቀቀኔ፥
ከተዳከምሁበት ፥ ከውብ ሰመመኔ፥
'ቢሆንስ?' እያልሁኝ፥
ድንገት እየባነንሁ ፥ እፈራለሁ እኔ፥

መቼም፥
ነፍሱን መርጦ አጥቦ ፥ ውድ አካል ቢያለብሰው፥
ምን ያህል ቢወደድ ፥ ፍቅር ቢያንተርሰው፥
እንዲህ ሁሉ አምሮለት፥
በስጋና በደም ፥ አይገለጥም ሰው።

2 months, 3 weeks ago

እንደ እርግማን ሲሆንብን
አሜን ብለን የደረሰን ገፍ ምርቃት
እየፈጩን አስገብተው በዘመን ቋት
ስንሳቀቅ
ስንጨነቅ
ስንወረር በመከራ ስንከበብ በጥላሸት
ሲሆንብን ሰላም ውሎ ብርቅ ማምሸት
አይዞን ያለን ማን ነበረ
የልቅ እንድህ
የደገፍነው ቀን ሲያነሳው ፊት አዞረ።

5 months, 4 weeks ago

ፀንቶ እንድቆም ሁለት እግሯ
ራስ መቻል
መጠንከር ነው ንጎጎሯ
እንደ ዋዛ ሞት አይጥለው የበረታን
ስቀንባት ልታስቆጨን በጥረቷ ልትረታን
ትወጣለች በተስፋ ቃል
ሰው ለመሆን
ራስ ችሎ ለመራመድ ስንት ድካም ግን ይበቃል?።

5 months, 4 weeks ago

''ዐገቱኒ'' አለ ዳዊት ወንድማገኝ።

ዐገቱኒ

እኔ ራሱ ጥያቄ ከበበኝ።

@yegtmmedbl

6 months ago

ያለሁት ምድር
ለዛውም ደግሞ መኖሬ ምንም
ምኞቴ ሰማይ
አንድ ሰው ቅሉ ሁለት ባይሆንም
እየተጋጨሁ
በራሴ ሜዳ ከራሴ ትግል
ግማሽ ውስጠቴ
ሌላኛው ጎኔን ሲነካኝ ፍንግል
ጣር ሁኖብኛል
በወጀብ መሐል ፀንቶ እግር ማቆም
እኔው አጥፍቼ
ደግሞ በፀፀት ጣቴን መጠቆም።

6 months ago

ስትፈልግ አሁን ማረኝ
አይኔን ዳብሰህ አነጋግረኝ
ተስፍ ስጠኝ ስንቅ ለነገ
መኖር ህልሜን
አይመፅውተኝ የፈለገ
ከነ አልጋዬ ስበህ አንሳኝ
አለሁ ልበል
በሰው መሐል ሰው አይርሳኝ።
ካስፈለገም
አሁን ለያት ስጋ ነፍሴን
አልወደውም በተስፋ ቃል ምልልሴን
ጢንጥዬ ሙቅ ብርሃን ሳያገኙ
ጨለማ ውስጥ እየዋኙ
ሌላ ቀን ነው በሚል ተስፋ
ለምን ዛሬ ኑሬ ልጥፋ።

We recommend to visit

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 6 months ago

?? የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ ??

For promotion and Advertisements
? @Mussegirma

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo