የአባቶች ምክር

Description
አስተማሪ የሆኑ የአባቶች ምክሮችን ÷መንፈሳዊ ፅሁፎችን እና ትምህርቶችን የምናጋራበት ቻናል ነው። ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ! የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!@Father_advice
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 month ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 6 months, 2 weeks ago

1 week, 1 day ago

ምን የማያልፍ ነገር አለ

ቀኑን ወስዶ ጨለማን ያመጣ ጨለማውን ወስዶ ቀኑን ያመጣል
የውርደት ዘመን በክብር ዘመን ይተካል
የማጣት ዘመን በማገኜት ዘመን ይተካል
ደግሞ ሁል ጊዜ ደስታ ቢሆን እግዚአብሄር ይረሳል
ሁል ጊዜም መከራ ቢሆን ሰው በሞት ያልቃል
እግዚአብሄር ግን እያፈራረቀ ህይወትን ቀጣይ አድርጓአል

መ/ር ሳሙኤል አስረስ

1 week, 1 day ago

"ክፉ ዘመን ቢመጣና በቤተክርስቲያን መገልገል ባንችል ቀድሰን የምናቆርበዉ እናንተ ቤት ስለሆነ ክርስቲያኖች ሆይ የምትኖሩበትን ቤት በቅድስና ና በክብር
ያዙት
፤ ጠብቁት"
(ሊቀ ሊቃዉንት ስምዐኮነ መልአክ)

ክርስቲያን ማለት ቤቱን ቤተክርስቲያን
ቤተክርስቲያንን ደግሞ ቤቱ የሚያደርግ ነው!

1 week, 2 days ago
2 weeks, 1 day ago

ግትርነት ውስጥ ምህረት የለም!!

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ60 ዓ.ዓ የኖረው ጠቢቡ #ሲሴሮ ስለቁጣ ሲናገር ፦ << በንግሥና ዙፋን ተቀምጦ በቁጣ ቀንበር ስር እንደሚሰቃይ ንጉስ የሚያሳዝን የለም።>> ይላል፡፡

ንጉስ ግኔስ ፒሶ ፦ ቁጡ ፣ ግትር እና ማስተዋል የጎደለው ንጉስ ነበር ። #ፒሶ :: አንድ ቀን አንድ ወታደር ለአሰሳ ከወጣበት ሲመለስ አብሮት የወጣውን የመቶ አለቃ ትቶት ብቻውን ይመለሳል ። ይህን የሰማው #ንጉስ ፒሶ ወታደሩ እንዲገደል ትእዛዝ ሰጠ ። ለሞት ፍርዱም ምክንያት ፦ " ወታደሩ መቶ አለቃውን ገድሎት ሊሆን ይችላል ፤ ባይገድለውም ደግሞ አለቃው ትቶ መምጣቱ በራሱ ብቻ ያስገድለዋል " የሚል ነበር ።
ሞት የተፈረደበትን ወታደር የሚገድል ሌላ ወታደር ታዘዘና ወደ አንድ ከፍታ ይዞት ይወጣና ሰይፉን መምዘዝ ሲጀምር። መቶ አለቃው ድንገት ከተፍ ይላል ። ገዳዩ እና ተገዳዩ በዚህ ደስ ተሰኝተው ከመቶ አለቃው ጋር ሦስቱም ወደ ቤተ መንግስቱ ይመጣሉ ። ይህን ጊዜ በቤተ መንግስቱ ደስታ ይሆናል ። ነገር ግን #ፒሶ ሶስቱን ወታደሮች በአንድ ላይ ሲመለከት በቁጣ ነደደ ። ወዲያው ሦስቱም እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠ።

የፒሶ ምክንያት ደግሞ ፦
<<የመጀመሪያው እንዲሞት እስቀድሜ ስለፈረድኩበት ይሞታል
ሁለተኛው ወታደሩን እንዲገድል ትእዛዝ ከሰጠሁት በኃላ ትእዛዜን ባለመፈፀሙ ይሞታል ፣
ሦስተኛው የመቶ አለቃ ደግሞ ለወታደሩ መሞት ምክንያት ስለሆነ እሱም ይሞታል>> በማለት ፈረደ ።

#ግትርነት_ውስጥ_ምህረት_የለም!!!
እኔ ያልኩት ብቻ ይሆናል ከሚል ግትርነት ራቅ አንዳንዴ መሸነፍ መልካም ነውና!

✦_  @father_advice  _✦ ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

2 weeks, 1 day ago

ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።

ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ፣
ጀርባዉ በጅራፍ ስለእኔ ደማ፣
የእኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ፣
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ፣ ( ×፪ )

በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ
ጌታ ተያዘ ሕይወቴን ፈቅዶ
ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ
ለእኔ ግን ሆኗል መውጫ መንገዴ ( ×፪ )

ታስረሃል ስለእኔ ኢየሱስ መድኅኔ
     ታስረኃል ስለኔ ኢየሱስ መድኅኔ
አገቱኒ ከለባት ብዙኀን
ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን
አገቱኒ ከለባት ብዙኀን

ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ
በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ
እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ ( ×፪ )

ታርደሃል ስለእኔ ኢየሱስ መድኅኔ
     ታርደሃል ስለእኔ ኢየሱስ መድኅኔ

ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ወኈለቁ ኩሎ አዕጽምትየ
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ

ሕይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑ
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ
እጅ እግሩን ሚስማር ሲቸነክርው
የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለው ( ×፪ )

ተወጋ ስለእኔ ኢየሱስ መድኅኔ
     ተወጋ ስለእኔ ኢየሱስ መድኅኔ

ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ
ወአስተዩኒ ብሒዓ ለጽምዕየ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ

እርቃኑን ሆኖ ፈተለው ልብሴን
አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ኾምጣጤ
በምሕረቱ ጠል ነፍሴን አርክቶ
አለመለመኝ እርሱ ተጠምቶ ( ×፪
)
ተጠማ ስለእኔ ኢየሱስ መድኅኔ
    ተጠማ ስለእኔ ኢየሱስ መድኅ

3 weeks ago

"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

3 weeks, 1 day ago
3 weeks, 1 day ago

"እምነት የማናየውን ማመን ማለት ነው
የእምነታችን ሽልማት ያመነውን ማየት ነው::"
ቅዱስ አውግስጢኖስ

4 weeks ago

+ ከመሞትህ በፊት ተናገር ብትባል +

ዝንጀሮ ዕድሜ ጠግቦ ሊሞት እያቃሰተ ነው፡፡ ልጆቹ ከብበውት የመጨረሻ ቃሉን እየሰሙ ነው ፦

‘እንግዲህ ልጆቼ አደራ ... ስሞት በክብር ቅበሩኝ ... ቀብሬን አክሱም ጽዮን አድርጉልኝ ... ፍትሐቴን ደግሞ ጎንደር አድርጉት ... ተዝካሬን ደግሞ ላሊበላ አድርጉት ...’ አለ እያቃሰተ፡፡

ልጆቹ ደንግጠው ተያዩ  በመጨረሻ ግን የተናገረው ዐረፍተ ነገር ግን ከድንጋጤአቸው አረጋጋቸው ‘... ልጆቼ ይህንን የምናዘዘው ችላችሁ ታደርጉታላችሁ ብዬ ሳይሆን ... አያ ዝንጀሮ እንዲህ ብሎ ሞተ ተብሎ እንዲወራልኝ ፈልጌ ነው ...’’ ብሎ አረፈው፡፡ ይህችን አስቂኝ ወግ ያነበብኳት ነፍሱን ይማረውና ጋሽ ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር ከጻፋቸው መጻሕፍት በአንዱ ላይ ነበር፡፡

እውነትም ባይፈጸምም ደህና ነገር ተናግሮ መሞት ጥሩ ነው፡፡ ሌላው በጣም ያሳቀኝ ደግሞ የአንድ ወንጀለኛ የመጨረሻ ቃል ነው፡፡ ሀገር የበጠበጠ ወንበዴ ነው አሉ፡፡  በአንገቱ ገመድ አስገብተው ‘በል እስቲ የመጨረሻ ቃል ካለህ ተናገር’ አሉት፡፡ የተናገረው ቃል ግን ሰቃዮቹን በሳቅ ያፈረሰና እሱንም በሳቅ ታጅቦ እንዲሞት ያደረገ ነበር ፦ ‘ይብላኝ ለእናንተ እኔስ ትምህርት ወስጃለሁ!’

እውነት የዛሬዋ ቀን በሕይወት ለመቆየት የመጨረሻዋ ቀንህ ብትሆንና የመናገር ዕድል ቢሠጥህ ምን ብለህ ትሞታለህ? የግድ ትሞታለህ ባትባልም እንኳን የዛሬዋ ቀን የመጨረሻ በሕይወት የምትቆይባት ዕለት ልትሆንም ትችላለች፡፡ ከቤት ስትወጣ ምን ብለህ ወጣህ? አብረውህ ለሚውሉትስ ምን አልካቸው? ክርስቶስ መሳደብን ከመግደል ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በቃልህ ማንን ገደልህ? ማንንስ አዳንህ? በብዕርህ ማንን ወጋህ? ማንንስ ጠገንህ? ይህን ጽሑፍ ከማንበብህ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የተናገርከው ቃል ምን ነበር? አሁኑኑ ብትሞት ተናግረህ በነበረው ቃል ትኮራበታለህ? ያንተ ንግግር እንደ ዝንጀሮው እንዲህ ብሎ ሞተ የሚያሰኝ ነው ወይስ የሚያስቅ?

በጣም ይገርማል በዓለም ታሪክ ከመሞታቸው በፊት የማይረሳ ቃል የተናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሊሞቱ ሲሉ እየተሳደቡ ፣ የተወለዱበትን ቀን እየተራገሙ ፣ ገዳዮቻቸው ላይ እየዛቱ የሞቱ ብዙ ናቸው፡፡ ሊሞት ሲል የተናገረውን ብቻ ሰምተህ ሰውዬው ምን ዓይነት ሰውዬ እንደነበረ ትረዳለህ፡፡ ታሪክ የማይረሳው ድንቅ ንግግር ከመሞታቸው በፊት ያደረጉ በእኛም በሌሎችም ሀገራት አሉ፡፡

ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ስንመለስ ‘’ፍልስጤማውያንን እንድበቀል አንድ ጊዜ ብቻ አበርታኝ’’ ብሎ ጠላቶቹን ገድሎ የሞተውን ሶምሶንንም እናገኛለን፡፡ ሶምሶን ሲሞት የገደላቸው ሰዎች እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡

ሮማውያን ወንጀለኞችን ሲሰቅሉ በጣም ለጆሮ የሚቀፍፍ ስድብ ከሟቾቹ አፍ ይወጣ እንደነበር ሲሴሮ ጽፎአል፡፡ የአንዳንዶቹ ስድብ ከማስጸየፉ ብዛት ምላሳቸው ተቆርጦ የሚሰቀሉም ነበሩ፡፡

ዐርብ ዕለት የተሰቀለው ናዝራዊ ግን የተናገረው ከአፉ  የተሰማው የመጨረሻ ቃል የሮም ወታደሮችን ግራ ያጋባና ተሰምቶ የማይታወቅ ነበር፡፡ እርሱ ሁሉ በጠላትነት የተነሣበት ሳር ቅጠሉ የጠላው የሕማም ሰው ነበር፡፡ እንጨት መስቀል ሆኖ ተጫነው ፣ ብረት ሚስማር ሆኖ ጨከነበት ፣ አበቦች እሾህ ሆነው ወጉት ፣ ሰዎች እንደማያውቁት ከዱት ፣ ተማሪዎቹም ጥለውት ሸሹ፡፡ ይህ ሁሉ መከራ ወርዶበት ግን በዓለም ተሰምቶ የማያውቅ የጸሎት ቃል ከአፉ ፈሰሰ  - የሚያደርጉትን አያውቁና ይቅር በላቸው፡፡ እርሱ እንደሶምሶን በሞቱ ሰዎችን አልገደለም:: በሞቱ ያስነሣቸው ግን ብዙ ነበሩ::
ሞቱ ለብዙዎች መነሣት ምክንያት የሆነው እርሱ የመጨረሻ ቃሉን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው በማለት ጀመረ::

ጌታ ሆይ የማደርገውን አላውቅምና እባክህን እኔንም ይቅር በለኝ፡፡ አዎን በኃጢአቴ ቸንክሬሃለሁ ፣ በበደሌም አቁስዬሃለሁ ነገር ግን የማደርገውን አላውቅምና ይቅር በለኝ፡፡ ባውቅህ ኖሮ የክብርን ጌታ እሰቅልህ ነበር? ጌታ ሆይ ባላውቅህ ነው፡፡ ያስከፋሁህ አይሁድ ሆኜ ነው ፤ ያደማሁህ ሮማዊ ሆኜ ነው፡፡ የማደርገውን አላውቅምና ይቅር በለኝ፡፡

ጌታ ‘የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው’ ሲል አይሁድ ከሥር ቆመው ‘ተአምርህን አሳይ ከመስቀሉ ውረድ’ ይላሉ፡፡ ለጠላቶቹ ከመጸለይ በላይ ፣ የሚጠሉትን ከመውደድ በላይ ፣ ምን ተአምር ያሳያችሁ?

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 month ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 6 months, 2 weeks ago