★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
ቤተሰብም ላማክር ነገ ወደ ባህርዳር እመለሳለሁ አልኩት ፡፡ እነ ሀፍ ንግግራችንን ተጠባብቀው መጡ ቴክስት አድርጎላቸው ነበር ትንሽ ቆይተን ወደ ደሴ ተመለስን ለነገ ወደ ባህርዳር የ አውሮፕላን ትኬት ቆርጠን ወደ ቤት ተመለስን ....አየር ማረፊያዉ ኮምቦልቻ ሲሆን የሚጠቀምበት ግን የደሴ ከተማ ነዋሪ ናቸዉ የአዉሮፕላን ትኬቱ የሚቆረጠዉ ደሴ ላይ ነዉ፡፡ደሴ እና ኮምቦልቻ የተያያዘ የሚወደዱ በትዳር የተጣመሩ…
ቤተሰብም ላማክር ነገ ወደ ባህርዳር እመለሳለሁ አልኩት ፡፡ እነ ሀፍ ንግግራችንን ተጠባብቀው መጡ ቴክስት አድርጎላቸው ነበር ትንሽ ቆይተን ወደ ደሴ ተመለስን
ለነገ ወደ ባህርዳር የ አውሮፕላን ትኬት ቆርጠን ወደ ቤት ተመለስን ....አየር ማረፊያዉ ኮምቦልቻ ሲሆን የሚጠቀምበት ግን የደሴ ከተማ ነዋሪ ናቸዉ የአዉሮፕላን ትኬቱ የሚቆረጠዉ ደሴ ላይ ነዉ፡፡ደሴ እና ኮምቦልቻ የተያያዘ የሚወደዱ በትዳር የተጣመሩ የ25ደቂቃ መንገድ የሀገረጎ መንገድ ነዉ የሚለያቸዉ፡፡ የአዉሮፕላን ትኬቱን ሳዳም ነው የከፈለልኝ የዛሬዋን ቀን አድሬ ጠዋት ላይ ሳዳም እና ሀፍ ኮምቦልቻ አየር መንገድ ሸኝተዉኝ ወደ ባህር ዳር ተመለስኩ
ባህርዳር ከደረስኩ ቡሀላ ሳዳም ያለኝን በሙሉ ከልቤ ሁኜ መተግበር ጀመርኩ ግን ይቅርታ ለማድረግ ተቸገርኩኝ ግን ቀስ በቀስ ለአላህ ብየ ሁሉንም ነገር ስተውና ማድረግ ስጀምር ነገሮች እየቀለሉልኝ መጡ፡፡ አሁን ከደሴ ከተመለስኩ ዛሬ ስድስተኛ ወሬ ነው ከሳዳም ጋር ሁሌም ነው የምናወራው በጣም በሳል ልጅ ነው ፡፡
አንድ ቀን መጥፎ ሽታ ሸቶኝ አፍንጫየን ጥቅጥቅ ልቤን እፍን አደረገኝ፡፡ ህመሙን መቋቋም አልቻልኩም አባቴ ባህርዳር የሚገኘዉ ሪፈራል ሆስፒታል ወሰደኝ፡፡ ሁለት ቀን መተኛት አለብሽ ተብየ ተኝቼ መታከም ጀመርኩ .መድሀናቴን እየዋጥኩ ነዉ....
....ዶክተሩም ሙሉ ምርመራ አደረገልኝ፡፡ ከዛም ምን እንደተሰማኝ አላቅም እንደገና የHIV ምርመራ ማረግ እፈልጋለሁ አልኩት
....አባቴም አይ ሀሊማ ለምን ትጨነቂያለሽ አትሰቢ አላህ ያለዉ ሁኗል አለኝ
....እኔም እንደዉ ዝም ብየ ልመርመር ብየ ነዉ አልኩት
.......ዶክተሩም እሺ ብሎ የHIV ለመመርመር ደም ወሰደ
ዉጤቱ ሲመጣ ግን ያልታሰበ ነገር ሆነ የሚአጅብ ነዉ ሀላሊ HIV በደምሽ የለም አለኝ ዶክተሩ
....ማመን አቃተኝ በጣጣም የደስታ ጩኸት ጮህኩኝ
......እርግጠኛ ነህ?? አልኩት
......አዎ የለብሽም አለብሽ ያለዉ ሆስፒታል ዉጤት ተሳስቶባቸዉ ይሆናል አለኝ
.....ማመን አልቻልኩም በደስታ ልቤ ሊፈነዳ ሲወጣ ሲገባ ይታየኛል፡፡ ከዛም አባቴ ነገ ስንወጣ አለብሽ ያሉኝ ሆስፒታል ሄጄ እመረመራለሁ ብየ አንገቱ ላይ ጥምጥም አልኩበት፡፡ የደስታ እንቅልፍ አልወስደኝ አለ
የማይነጋ የለም ነጋ ቀጥታ HIV አለብሽ ወዳሉኝ ሆስፒታል ሄድኩ ፡፡ ሌላ ሀኪሞች አገኘሁ ...ከዛም ስመረመር ዉጤቴ ሲመጣ HIV የለብሽም አሉኝ....
.....ደስታየን መቆጣጠር አቃተኝ ተደሰትኩ አባቴ ጋር ተቃቅፈን ማልቀስ ጀመርኩ፡፡
አባቴ ተናዶ እንዴት በስነስርአት አይመረምሩም ብሎ የሆስፒታሉ ሀላፊ ጋር ሂዶ ተናገረዉ ሁሉንም አስረዳዉ፡፡
የሆስፒታሉ ሀላፊም ይቅርታ እንደዚህ ያለ የህክምና ስህተት አንዳንዴ ይፈፀማል ..ግን ይሄ ከባድ የህክምና ስህተት ነዉ ይቅርታ አለዉ
....ለሀፍ እና ለሳዳም ደዉየ ነገርኳቸዉ ደስታ፡በደስታ ሆኑ ...ሳዳም ግን ከነማንነቴ ተቀብሎኝ ነበር
ለማማና ባባም ስለሳዳም ነግሪያቸው ተስማምተውልኛል ፡፡ ሀምዛም ወደ ደሴ የሚሄድበት የጀመአ ፕሮግራም ነበር ሳዳም ጋር ተዋዉቀዉ ተግባብተዉ እነሱን መረጠልኝ፡፡ በዚ መሀል አንድ ቀን አዩብ ሱቅ ድረስ መጣ በተናገረው ንግግር እንደተፀፀተና መልሶ ሊያገባኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ
..... ለ ማይረባ ደም ብሎ እኔንና ቤተሰቤን አቁስሎን የሄደ ሰው መልሼ ላግባ ማለቱ ምን ያለ ድፍረት ነው?? ሰው እንዴት ተፍቶና ጥሎት የሄደውን ያውም ተጠይፎት የሄደውን እንዴት ሊመልሰው ይሻል??
የሳዳም ቤተሰብና የኔ ቤተሰብ ተነጋግረው ፈቲ በሁለተኛ አመቷ ህክምናዋን ጨርሳ ለኔ ሚዜ እንድትሆነኝ እፈልጋለሁ ስላልኩኝና መውጫዋ ጊዜ አራት ወር ስለቀረው በዛ ተወሰነ
አልሀምዱሊላህ ፈቲ ከአእምሮ ማገገሚያ ሆስፒታል ህክምናዋን ጨርሳ ከአዲስ አበባ መጣች፡፡ ፈቲ ስትወጣ አምሮባት የፈቲ ወዝ ተመልሷል፡፡ ፈቲም የተወሰነ ግዜ ተቸግራ እንደነበርና አሁን ከበፊቱ ለውጥ አምጥታ የማእከሉ ሁሉ ተሸላሚ ነበርኩ..ቁርአን መቅራት ሶላት መስገድ ጀምሪያለሁ አለችኝ
የእኔ እና የሳዳም ሰርግ ቀን ደረሰ ....ድል ባለ ሰርግ ደሴ ላይ ተደግሶ ዘመድ አዝማድ ከባህርዳር ደሴ ድረስ መጥተዉ ተጋባን ... ልቤ ሲመኘው ..የነበረን ልጅ አገኘሁ አልሀምዱሊላህ
ሙሸራችንን ከጨረስን ቡሀላ እኔ ፈቲ እና ዉዱ ባለቤቴ ሳዳም ሁነን ማማየን ልንዘይር ወደ አዳማ ከተማ ሄድን ፡፡ ማማየ ቤት ስንሄድ ደስታ አልጠበቀንም ማማየ ሙተው ነበር ያገኘናቸዉ አለቀስን ፈቲም ብታለቅስ ብታለቅስ ሊወጣላት አልቻለም ማማየ አሁን አንቱ የምፈልጓት ሰዉ ሁኛለሁ ተቀይሪያለሁ ብትል ማን ሰሚ አለ ወደ ማይመለስ አኼራ ሂደዋል፡፡ በጣጣም አዘን ለዚች ተራ ህይወት ነበር እንደዚህ የምንሆነው...ማማየ ሁሌም ቢሆን በልባችን አሉ ...ጥሩ የሰራ መቼም ቢሆን ከልብ አይወጣም አጂብብብብብብብብብብ
#መከረኛው_ድንች_ቤት
......#ተ....... #ፈ..........#ፀ........ #መ
❤️〰〰አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ〰〰❤️
የታሪኩ ርዕስ
😔 #መከረኛዉ_ድንች_ቤት
የመጨረሻዉ ክፍል
የማይታመን ተአምር ይሆናል ብየ ያልጠበኩት በፍፁም ያላሰብኩት ነገር ከመሸ ስለሆነ የገባነው ደክሞኛል ውስጤን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ዋጠኝ ድንጋጤ,ደስታ,እቀፊው እቀፊው እቀፊው የሚል ስሜት እቅፉ ግቢና መልካም ጠረኑን አሽቺ ናፍቆትሽን አስወጪ የሚል የልብና አእምሮ ትዛዝ ብዙ ሰአት በድንጋጤ ደርቄ ቁሚያለሁ.... በስስት አይን አይኑን አያለሁ
.... ሀፍ ሀሉ ምን ሁነሽ ነው?? ንቂ እንጅ አንቀላፋሽኮ ብላ በኔና በሱ ሳቅ ብላ ይዛኝ ሄደች
ግን እንዴት ሳዳም እዚህ ቤት ተገኘ ለምን ዘመድ ነው?? ወይስ የሀፍ ወንድም ነው?? ምን ይሰራል እዚህ?? ቆይ ግን ያኔ ምንድን ነበር መልክቱ ሊሰጠኝስ የነበረው ??ወረቀቱ ምን ነበረ ??ቆይ ያልተፈታልኝ ሚስጥር ምንድን ነው ??ከኔ የተደበቀው ነገርስ ምን ይሆን ??ግራ በመጋባት ውስጥ ሆንኩኝ
ሀፍስን ስለ ሳዳም ልጠይቃት ፈለኩኝ ግን ገና ከመግባቴ ምን ይባላል ብየ ዝም አልኩኝ ..ሻወር ወስጄ ሰግጄ ራት ተብለን ሳሎን ገባን ሁሉም ተሰብስቧል ፡ታላቅ ወንድሟ አባቷ እናቷ ሁሉም አሉ
ሳዳም ግን ከእነሱ መሀል የለም ለምን የለም?? የዚህ ቤተሰብ አካል ከሆነ አሁንስ የት ሄደ?? ስለሱ ብቻ ማሰብ ጀመርኩ
ትንሽ ቆይተን በራፍ ተቆርቁሮ አሰላሙ አለይኩም ብሎ ገባ ሳዳም ነበር ... እናቷና ሀፍ ለኔ ሲሉ ለብቻችን ሱፍራ አድርገን መብላት ጀመርን ...ቀና እያልኩ ሳዳምን ሳላስባንን አይዋለሁ... ሁለታችንም ፊት ለፊት ተገጣጠምን ልቤ ስንጥቅ ልትል ደረሰች... የያዝኩትን የእንጀራ ጉርሻ ለቅቄው ትሪው ላይ ወደቀ እኔ ምን እየሆንኩ ነው እጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ ...ሀፍሳ ለኬ ምሰራውን ነገር በደንብ እያየች ነበር ሌላ ጥፋት ሳላጠፋ በቃኝ ብየ ብነሳ የተሻለ ሀሳብ ነው ብየ ልነሳ ስል... የደሴ ሰዎች እንድትበሉላቸው ያላቸው ፍላጎት ልዩ ነው እነሱ ሳይበሉ ቢቀርባቸውና እንግዳቸው እንዲበላ ያላቸው ፍላጎት ልዩ ነው የምር የሆነ ፍቅርና ርህራሄ ነው የሚያሳዩት በሞተ ብላ አይሆንም አትነሺም አሉኝ እኔም ትንሽ በልቼ ተነሳሁ በቃ ፍቅር ናቸው
እኔም ደክሞኝ ስለነበር ተኝ አሉኝ ተነስቼ መኝታ ቤት ገባሁ ከ ሀፍ ጋር የሌለ ወሬ አወራን፡፡ ስለ አዩብም ነገርኳት ...በዛውም ትልቅ ሚስጥሬን የተፈጠረዉን Hiv እንዳለብኝ ነገርኳት፡፡ ሁለታችንም ተላቀስን በጣም ስለመሸ ተኛን፡፡ መተኛት ግን አይደለም የተኛሁት ሳዳምን አንድ ቤት ቁጭ ብለን በደንብ አየሁት እሱን እያልኩ እያሰብኩ ያላሰብኩት እንቅልፍ ወሰደኝ ፡፡ ሱብሂ ተነስተን ሰግደን አርፍደን ስለተነሳን ቁርስ በልተን ከቤት ወጣን እንደተለመደው አብረን ስንዞር ውለን የደሴን ናፍቆት አስወጥቼ ሀፍ የምትማርበትን ትምህርት ቤት ካየሁ ቡሀላ አሱር አካባቢ ተቋም የሚገኘዉ ኡስታዝ ጠልሀ መስጊድ ሰግደን .....ሻይ እንጠጣ ተባብለን ወደ ደሴ መውጫ አካባቢ ወዳለ መዝናኛ ወስዳኝ የደሴን ንፁህ አየር እየተቀበልን በመናፈሻው ውበት ተገርሜ የምታወራኝ ትልቅ ነገር እንዳለ አስረዳችኝና በ ትግስት እንዳዳምጣት ነገረችኝ
......በመስማማት በሚመስል መልኩ ራሴን ነቅነቅ አደረኩላት
......ከዛ በፊት ግን ስለ ሳዳም ጠየኳት ምንሽ ነው??? አልኳትከት
ከት ብላ ስቃብኝ እኔም ስለሱ ነው ማወራሽ እና አዳምጭኝ አለችኝ //////ሳዳም ታላቅ ወንድሜ ነው በጣም እወድዋለሁ ሚስጥሩን አይደብቀኝም እኔም አልደብቀውም እናም አንድ ቀን ያኔ ህመሜ ብሶብኝ ከግቢ የተመለስኩ ግዜ ፎቷችንን እያየሁ የአንችን ፎቶ አሳየሁትና ስለ አንች ብዙ ጠየቀኝ ፡፡ ቆንጆ እንደሆንሽና እንደወደደሽ ነገረኝ ....ከዛም ወደ አዳማ መቶ ሊያገኝሽ እንደሚፈልግ ነገረኝ
እኔም ራሴ የፃፍኩትን የጓደኝነት ደብዳቤ ሰጠሁት፡ አዳማ ሲገባ በስልክ እናወራ ነበር እና ድንች ቤቱ አካባቢ እንዲሄድ ስነግረው ቀጥታ ሄደ አንች ዜብራ ላይ መኪና ልትገጭ ብለሽ ራስሸን ስተሽ ስትወድቂ ወደ ሆስፒታል ወሰደሽ
....ከዛ ቡሀላ ያረገልሽና ያወራቺሁትን ነገር ይነግረኝ ነበር ....ያኔ ለኮንግራሽ የመጣን ቀን ሆቴል እንያዝ ሲባል ሳዳም የጋበዘሽ ሆቴል እንደምትጠሪልኝ ተስፋ አድርጌ ነበር ፡፡
ከዛ ቡሀላ አንች እኔንና ሴቱን ሁላ ከጥቅም ውጭ ስላደረገን ሄኖክ ነግሬው ነበር ተከታትሎ ደበደበውና ታሰረ...... ከዚ ቡሀላ የምትነግረኝን ነገር በ እንባ አጅቤው ነበር ማዳምጣት እሱ ለኬ ያውቀኝ ነበር ከዛ ታላቅ ወንድሜ ዋስ ሁኖ አስወጣው ለሄኖክ መታከሚያ ብርም ከፈልን ከዛw ቡሀላ በቃ ወሬው ሁሉ ስለ አንች ሆነ ፡፡ እናም ከፈቲ ሁሉንም መረጃ አግኝቷል በሄኖክ መደፈርሽን ጭምር ያውቃል፡ ፈቲን አሳምኖ በሱሷ ሰአት ሚስጥር አስወጥቷት ነበር ከዛ ቡሀላ ሊያገባሽ ወሰነ፡፡
እናም አሁን ያስመጣውሽ ልመረቅ ሳይሆን ከ ሳዱ ጋር እንድታወሩ ብየ ነው አለችኝ
......በፍፁም ምንም ማውራት አልፈልግም፡ እኔ ስንት ሚስጥሬን ነግሬሻለሁ በሽተኛ ነኝ ላገባው አልችልም አልኳት ፡፡ ያንች ወንድም መሆኑን ባውቅ ለራሱ አላወራም ነበር ወላሂ ወድጄዋለው ግን አይሆንም ብየ ለቅሶየን አባስኩት ቆይ እኔ ሚስጥሬን እየነገርኩሽ በሽተኛ መሆኔን እያወቅሽ እንዴት ለምትወጂው ወንድምሽ ትመኝኛለሽ ??በፍጹም አላደርገውም ሳዳምና አንችኮ ለኔ ከምንም በላይ ናችሁ ስለዚህ አላስበውም ህይወቴን ያተረፈልኝን ያንችን ወንድም ለኔ ደግሞ ልዩ የሆነን ወንድ አግብቼ ህይወት ማበላሸት አልፈልግም ለአላህ ስትሉ ተውት ይህንን ሀሳብ ሳዳምም ከኔ የተሻለች በጤናዋ ንፁህ እና ቢክራ ሴት ትገብዋለች እኔ ከምኑም የለሁበትም ከጤናየም በሽተኛ ከንፅህናየም ዝርክርክ ሰይባ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ ለሳዳም አልገባም ብያት ተነስቼ መኪናው ውስጥ ገባሁ
ሰአቱ መሸ መግሪብ አካባቢ ወደ ቤት ገባን ምንም እንዳልተፈጠረ አስመስለን አመሸን ፡፡ሳዳም ኢሻ ሰግዶ ነው የሚገባው ቤት ገብቶ ሁላችንም ትንሽ አውርተን ተኛን፡፡ መኝታ ቤት ሁኜ ነገሮችን ማሰብ ጀመርኩ አዳሬን ሁሉ ስለ ሳዳም ብቻ ማሰብ ሆነ ስለ ሀፍ ንግግርና ህመምተኛ መሆኔን እያወቀች ለወንድሟ እኔን መምረጧ ገረመኝ ፡፡ ብቻ ባህር ዳር ሱፐር ማርኬቱን ዘግቼ ስለመጣሁ መመለስ አለብኝ አልኩኝ በተጨማሪም ማራዘሚያ መድሀኒቴ ሊያልቅብኝ ስለሆነ መመለስ አለብኝ ብየ አሰብኩ
ጠዋት ተነስተን ቁርስ በልተን ከቤት በሳዳም መኪና ወጣን ሀይቅ ዳር ወይም ኮንቦልቻ እንሂድ ሲባል ኮንቦልቻ ተመርጦ ሄድን ሀፍና ወንድሟ እኔና ሳዳምን ትተውን ሄዱ
...ኮምቦልቻ የሚገኘዉ ግሪን መስክ የተባለበት ቦታ ነበር ፡፡ ሳዳም ጋር ሰላምታ ተለዋውጠን ብዙ ነገር አወራን ስለአለብኝ በሽታ ጭምር
.....አንች በዱአ በርች ሲከፋሽና ስትቸገሪ ብቻ ሳይሆን መስገድ ያለብሽ በማንኛውም ቀን የለሊት ስግደትሽን ቀጥይ የበደሉሽን ሰዎች ሁሉ ይቅር በያቸው ለአላህ ብለሽ አውፍ በያቸው ሄኖክ ፈቲያ ባለ ድንች ቤቷ ሌሎቹንም ከልብሽ ይቅር በይ ሲቸግርሽ ብቻ ለይል አላህ ፊት አትቁሚ በሽታዉ ቢኖርብሽ ዋናዉ፡ፍቅሩ ነዉ እኔ blood O ነኝ ብቻ ወደምንወልደዉ ልጅ እንዳይተላለፍ ክትትል እናረጋለን.... ከዛ በፊት ግን ብንጋባና በአላህ መንገድ ላይ ብንጓዝ የተሻለ ይመስለኛል ብሎ ዝም አለ
ንግግሩ እንዴት ቀልብ ይስባል እይታውና ምክሩ እንዴት ይማርካል ምን አይነት ስብእናን ነው የተላበሰው?? አጂብ ይህ የንግግር ቺሎታ ግን በዘር የተላለፈ ይመስለኛል ከሀፍ ጋር ያመሳስላቸዋል
እኔም ሳዳም ፍቀድልኝ 👇
የአለህ ሰላም እዝነት ራህምት እና በረከት ለነዛ ቀን ከሌት የሙስሊሞቹ ጉዳይ በሚያሳስባቸው ላይ ይሰፈን
እነሆ ከ 300 ቀናት በላይ ግፍ መከራ ረሀብ ስቃይ የዘር ማጥፋት የተፈራረቀባቸው የጋዛ ህዝባ አሁን ፀንተው ቆመዎል ።
#አሁንም_ተርበዎል_አሁንም_እየተገደሉ_ነው።
የነሱን ስቃይ እያየን ማይት ብቻ ለምን? በገንዘብ እንድንረዳ መንገዱ ተመቻችቷል .....
10 ነው 20 ነው ሳትሉ የምትችሉትን እንድታስገቡ በአላህ ስም እጠይቃለው።
Account no:- 1000644941284
ስም SUDEYIS & ABDUSELAM & SEBRIN
ስትልኩ ስሙን አረጋግጣቹ ላኩ...
አንድ ኸይር ስራ ስትሰሩ የስራውን ትንሽነት አትዩ ለማን ብላቹ እንደምተሰሩ እንጂ
ለኸይር ማነቃቂያ ይሆን ዘንድ የላካቹትን በ @Strong_iman_bot screenshot አርጋቹ ላኩልኝ
ወሰላም አለይኩም ወራህመተላሂ ወበረካትሁ
አሰላም አለይኩም ወራህመተላህ....ወበረካትሁ
ከዚህ በፊት ያወራንብት ሀሳብ ማለትም ፍልስጤምን በሚረዱ ድርጅቶች ላይ ገንዘብ አሰባስበን... እነሱን ለመርዳት በሚለው ላይ ዛሬ እንሻኣለህ አንጀምረዎለን
ሰለ ሁኔታው ግልፅ ላርግላቹ በመጀመሪያ አዲስ አካውንት መክፈት ነበር አዲስ ያስፈለገው ብሩ ሲሰባሰብ በአንድ ሰው አካውንት መሆን የለበትም ስለዚህ በ3 ሰው ስም አካውንቱን ከፍተናል አንድ በኔ እና ሁለት እዚው ቻናል በሚገኙ ሜምበሮች...
የሚከፈትበትን ብዛት 4 ለማረግ አስበን ነበር 3 ነው ሚቻለው ተብለናል....
እና አሁን ብሩ ከተሳባሰበ ቡኋላ ብብሩ dollar ተገዝቶበት በ MasterCard ወደ ድርጅቶቹ ማስገባት ነው
ነገሩን ትልቅ ሰው ላስገባበት ሞክሬ ነበር abdi ikhlas ኢብኑ ጀራህን ላናግር ሞክሬ ነበር መልዕክቴን ሊያዩት አልቻሉም ስለዚህ i got my self
ኢንሻአለህ አሪፍ ገንዘብ እናስገባለን አካወንቱን ከሰር እልከዎል?
?የዛሬው የቁርዓን ግብዣ?
ከጋበዝኩ ቆይቼ ነበር ስለዚህ ታኪሲ ላይ ስትሄዱ ብቻ በሁሉም ቦታ ምትሰሙት ረዥም ቁርዐን በ አቡበከር ሻጥሪ
Surah Baqarah | Abu Bakr Shatri |
@STRONG_IMAN
እርግጠኛ ሆኜ ምናገረው ሰዎች ወንጀል ሲሰሩ እናንተ ምትሳለቁ ከሆነ ያን ወንጀል ሳትሰሩት አትሞቱም
@STRONG_IMAN
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago