Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ

Description
፦ እንዴት relationship ን ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር እናስኪድ💏💏

💑ተከታታይ ጾታዊ ትምህርቶች
💑ማንን ላግባ?
💑 እንዴት r/ship በቅድስና እንያዝ
💑 pornography እና ሴጋ ጉዳቶቹ

በሌሎችም ወሳኝ ርዕሶች ላይ እንማማራለን

for any comment
@edbornagain

@relationship4christ
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month, 2 weeks ago

በቻናላችን ፦ እንዴት relationship ን ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር እናስኪድ💏💏

💑ተከታታይ ጾታዊ ትምህርቶች
💑ማንን ላግባ?
💑 እንዴት r/ship በቅድስና እንያዝ
💑 pornography እና ሴጋ ጉዳቶቹ

በሌሎችም ወሳኝ ርዕሶች ላይ እንማማራለን

for any comment
@edbornagain

@relationship4christ

1 month, 2 weeks ago

Loving the wrong person🥺,""*

So many people are suffering in relationships today because they refuse to let go of the person they are currently in a relationship with.

They know the relationship isn't working, but they refuse to leave because they feel they might be able to change the person.

They believe they are willing to go to any length to ensure that the person continues to "love them".

The hardest aspect is that they are doing everything in the hopes that the person would change, even when the person has no intention of changing in the first place.

If you're in a relationship right now where the person is causing you more grief than happiness, then it's time to let them go.

Accepting that things aren't working is the best approach to avoid getting hurt more in this type of relationship.

It's crucial to admit to yourself that the relationship is in disrepair.

I see so many people that are suffering in their current relationships because they refuse to face the reality of its true nature.

If your current relationship isn't working, do me a favor and don't force it, the more you force it, the more you will end up hurting yourself in the long run.

Nobody can take your happiness away if you don't want it taken away. Your happiness is in your hands; your happiness is dependent on you.

If you don't want others to continue to mistreat you......you have the power to stop them.

Take my advice and have the courage to leave the table when respect is no longer being served.🙏
Let's share to educate others 🙏🥺🫂

Fb.com

1 month, 4 weeks ago

ሚዛን ያልጠበቀ የአንድዮሽ ግንኙነት ምልክቶች (By Sara Kubburic)

ማንኛውም ግንኙነት ትክክለኛና ሚዛናዊ እንዲሆን ሁለትዮሽ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህም ማለት የሁለትን ሰዎች የጋራ መቀራረብ፣ መሰጠትና ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በሁሉ ነገር የሚጦዘው አንደኛው ወገን ብቻ ሲሆን የሆነ የተዛባ ነገር እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡

  1. በስልክ፣ በአካልም ሆነ በቻት እናንተ ካላናገራችኋቸው እነሱ ንግግርን የማያነሳሱ ሰዎች . . .

  2. አብሮ የማሳለፍን ጥያቄ እናንተ ካልጠየቃችሁና ካላነሳሳችሁ እነሱ በፍጹም ፍላጎት የማያሳዩና የማያነሳሳ ሰዎች . . .

  3. አለመግባባት ሲፈጠር እናንተ ብቻ ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ጥፋታቸው ሆኖ እንኳን በፍጹም ይቅርታ የማይጠይቁ ሰዎች . . .

  4. ለሁሉም ሁኔታ መስዋእትነት ከፋዮች እናንተ እንድትሆኑ የሚጠብቁ ሰዎች . . .

  5. ለግንኙነቱ ጤናማነት ሲባል መስዋእትነትን እናንተ ብቻ እየከፈላችሁ እነሱ ግን የማይከፍሉ ሰዎች . . .

  6. እጅግ በጣም አስቸጋሪ የሆነውን ባህሪያቸውን ዝም ብላችሁ እንድትሸከሙ የሚፈልጉ ሰዎች . . .

  7. ሆን ብለው በማንኛውም ጊዜ ትተዋችሁ ሊሄዱ እንደሚችሉ አይነት ስሜትን የሚሰጧችሁና ሰዎች . . .

  8. የእናንተ ፍላጎትና ዓላማ ሙሉ በሙሉ በእነሱ ፍላጎትና ዓላማ ስር እንዲጠቃለል የሚፈልጉ ሰዎች . . .

  9. ሁሉንም ነገር (ስራ፣ ጓደኛ፣ መዝናናት …) ከእናንተ የሚያስቀድሙ ሰዎች . . .

  10. እናንተ እቅዳችሁን ከእነሱ አንጻር ስታወጡ እነሱ ግን ከራሳቸው አንጻር ብቻ የሚያወጡ ሰዎች፡፡

ሚዛኑ ይጠበቅ!

Dr eyob

4 months, 2 weeks ago

“ሕፃን ተወልዶልናልና"
          — ኢሳይያስ 9፥6

አንድ ሕፃን ልጅ በመወለዱ የቤተሰቦቹ ደስታ ነው። ጌታ ኢየሱስ በመወለዱ የዓለሙ ሁሉ ደስታ ነው። ሕፃናት የዋህ ናቸው። ጌታ ኢየሱስ ትሁት ደግሞም የዋህ ነው። መወለዱ ሰዋዊ ማንነቱን ያሳየናል። እጅግ ትሁት በመሆኑ ከምድራዊ እናት ተወለደ።

የተወለደ ልጅ ለቤተሰቡ ደስታ ቢሆንም፣ ለወለዱት አደራ ቢሆንም ህይወቱ ግን የራሱ ናት። የተወለደው የራሱን ህይወት ሊኖር፣ ዓላማውን ሊያሳካ ነው። ጌታ ኢየሱስ የተወለደው እንደማንኛውም ሰው በልቶ ጠጥቶ፣ አድጎ ስራ ይዞ፣ አግብቶ ወልዶ ለመኖር ሳይሆን ስለእኛ ብሎ ለእኛ ተወልዷል። ዓላማው ለራሱ መኖር ሳይሆን ለእኛ መሞት ነበር።

ለእኛ ሲል በዚህች ጎስቋላ ምድር ላይ ሰላሳ ሶስት አመት ኖረ። እንደ ሰው እየተራመደ፣ እንደ ሰው እያሰበ፣ እንደ ሰው እየተናገረ፣ እንደ ሰው እየበላ እየጠጣ፣ እንደ ሰው እየተጠማ እየተራበ፣ እንደ ሰው እየደከመ፣ እንደ ሰው መከራ እየተቀበለ፣ እንደ ሰው ሞተ፣ እንደሰው ተቀበረ።

የሰውን ስጋ ሲለብስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እኛ ምን እንደሚሰማን፣ በምን ውስጥ እንደምናልፍ ስቃያችንን ያውቃል። ከኃጢአት በቀር ሊኖረን የሚችለው ስሜት ሁሉ ነበረው። “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።” — ዕብራውያን 4፥15

ይህ የተወለደው ህፃኑ ኢየሱስ ምድራዊ መኖሪያ ስላልነበረው ዛሬም ለሚፈናቀሉት፣ ቤት አልባ ሆነው በአደባባይ ለተጣሉት መኖሪያ ሊሆናቸው ተወልዶላቸዋል። ይህ ህፃኑ ኢየሱስ ብዙዎች የተውትና ያገለሉት ነበር። ዛሬም ሰው ጀርባ ለሚሰጣቸው ብቸኝነት ለሚሰማቸው ሊረዳቸው ተወልዶላቸዋል። ይህ ኢየሱስ በስጋ ወራቱ የሚወዳቸውን እንደ አልዓዛር አይነቶቹን በሞት አጥቶ አዝኗል አልቅሷል። ወንድማቸውን በሞት ላጡት እህቶቹም ደርሶላቸዋል። ይህ ህፃኑ ኢየሱስ ዛሬም በሞት ልጃቸውን አጥተው በሀዘን ለተኮራመቱ፣ በሞት ወላጆቻቸውን አጥተው ሀዘን ለወረሳቸው መጽናኛ ሊሆን ተወልዶላቸዋል።

በጉድለታችሁ ሁሉ ሙላት ሊሆናችሁ ጌታችን ኢየሱስ ተወልዶላችኋል። እንኳን ደስ አላችሁ። መልካም በዓል ይሁንላችሁ!!

በአዶኒ

4 months, 3 weeks ago

ሰላም እንዴት ናቹ  ሁሉ ሰላም ነው? ስሜን ለጊዜው ላቆይና በህይወቴ የገጠመኝን ነገር ላካፍላችው መጥቻለው

እኔን ያጋጠመኝን ነገር ማንንም እንድያጋጥም አልፈልግም እና በመጀመሪያ እኔ በጌታ ነኝ አሁን ላይ የግቢ ተማሪ ነኝ ያለፈው ክረምት ወደ ቤት ለእረፍት በሄድኩበት ማህበራዊ ሚዲያ በጣም ነበር ማበዛው በተለይ #TIKTOK በአጋጣሚ አንድ አህዛብ ተዋወኩ ተመቸኝ እና ማውራት ጀመርኩ ብዙ ጊዜ ማወራው በ #Video call ነበር እያወራን 2 ወር ሆነን ሳላስበው ትኩረቴን አገልግሎቴን ሁሉ እርግፍ አርጌ ተውኩ ማለት ችላለው #Church ውስጥ በዝማሬ ነው ማገለግለው እና እሱ የሚኖረው ሸገር ነው እኔ ያለውት ሀዋሳ ነበር

ከዛን ምን ተፈጠረ ሀዋሳ ልምጣ ሲለኝ ና አልኩት ቀጥሎ ምን አለኝ ስመጣ ግን #Sex እናደርጋለን አለኝ እኔ ደሞ አይሆንም ከትዳር በፊት ምንም አይነት ንክኪ አያስፈልግም ብዬ ግግም አልኩ እና እሺ እንቢ ካልሽ "#ሰውነትሽን ሙሉ ማየት ፈልጋለው" አለኝ አኔ አሁንም እንቢ አልኩት ምን ችግር አለው አናድርግ አላልኩም እኮ ማየት ብቻ ነው ምፈልገው ማየት ምን ችግር አለው ብሎ በጣም ብዙ ቀን ጠየቀኝ ከዛ #Videocall ደወለልኝ እና ክላስሽን ቆልፊ አለኝ እኔም ቆለፍኩ ከዛ ልብስሽን አውልቂና አሳይኝ ምንም ሳትፍሪ ብሎኝ አሳየውት ከዛ አንድ ቀን #Church ሄድኩ አንድ አገልጋይ መልእክት አመጣልኝ  አካሄድሽ ጥሩ አይደለም አላማሽን የሚያስጥልሽ ነው ተይ አለኝ ከሌላም አገልጋይ መልእክቱ ተደጋገመብኝ እና ውሳኔ መወሰን እንዳለብኝ ተሰማኝ

በእግዚያብሄር ፊት ተፀፅቼ  አልቅሼ ተመለስኩ ደስ አለኝ  ለእሱም ነገርኩት መቀጠል እንደማልችል በጣም እንደተጎዳ ነገረኝ እና እኔ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር በቃ ተውኩት አሁን ላይ አስጨናቂ የሆነብኝ ነገር ምንድ ነው👉 ከሱ ጋር በ #Video call ስናወራ record አድረጎብኝ ነበር መሰለኝ እና በሱ እያስፈራራኝ ነው እና አያችው እንቢ ብሎ መተው ምን የህል ዋጋ እንዳለው በየ #Social media ቢሰራጭ የአንድ ሰው ጉዳት ብቻ አይደለም የቤተሰብ፥የጓደኛ፥የጎረቤትም ጭምር ነው አደራ ከኔ ተማሩ ዋጋ ያስከፍላል እና በጌታ ፍቅር ልለምናችው ፀሎት አድርጉልኝ🙏

ከእህታችሁ ብዙ ነገር እንደተማራችሁ ተስፋ አደርጋለው #1 የምታወሩትን የቀረባችሁትን ሰው ምረጡ #2 በጊዜው ለእግዚያብሄር ድምፅ ታዛዥ ሁኑ #3 ከማያምኑ ጋራ በማይመች አካሄድ የተጠመዳችሁ ዛሬውኑ ተመለሱ!

እኔም የሚወራ ለእህቶቼ ማስተማሪያ የሚሆን ነገር አለኝ የምትሉ ማውራት ትችላላችሁ🙏

@relationship4christ

#share #lebamsetoch

4 months, 3 weeks ago

#አስገራሚው_የፍቅር_ታሪክ

በአንድ ደሴት ላይ ስሜቶች ሁሉ ተሰብስበው ይኖሩ ነበር።ከእነዚህም ደስታ፣ሐዘን፣ዕውቀት፣ፍቅርን ጨምሮ ሌሎች ነበሩ ። አንድ ቀን ደሴቲቱ ልትሰምጥ ነው የሚል አስደንጋጭ ዜና ተሰማ። ከዚህም ጥፋት ለማምለጥ ሁሉም የየግል ጀልባዎቻቸውን ጠጋገኑና ጉዞ ጀመሩ። ፍቅር ግን እስከመጨረሻው ሊታገስ ፈለገ። ደሴቲቱ ግን እየሰመጠች ወደ መዋጥ ስትቃረብ ፍቅር እርዳታ ለመጠየቅ ወሰነ።
ይኼኔ ብልጽግና ጉደኛ በሆነው ጀልባው እያለፈ ነበረና ብልጽግና ሆይ በጀልባህ ስፍራ ልትሰጠኝ ትችላለህን? ብሎ ፍቅር ይጠይቀዋል።
የለም አልችልም እንደምታየው ጀልባዬ በብርና በወርቅ ስለታጨቀ ላንተ የሚሆን ትርፍ ቦታ የለኝም ብሎ መለሰለት።
ፍቅርም በአንድ በተዋበ ጀልባ በማለፍ ላይ የነበረውን ግብዝነት ተመለከተና እርሱን ሊጠይቅ ወሰነ። ግብዝነት ሆይ እባክህ አንተ እርዳኝ? ብሎ ለመነው።
ልረዳህ አልችልም ፍቅር እንደማይህ ሁለንተናህ በውሃ ርሷል እንዲህ ሆነህ ብትሳፈር ደግሞ ጀልባዬን ልታበላሸው ነው ብሎ መለሰለት ግብዝነት።
ይኼኔ ሀዘን እየተጠጋ ነበረና ፍቅር ገና ጥያቄውን ሳያቀርብ ኦ........ ፍቅር እኔ በጣም አዝኛለሁ ስለዚህም ብቻዬን መሆን ነው የምፈለገው! ባታስቸግረኝ መልካም ነው ብሎ አልፎት ሄደ።
ደስታም በፍቅር አጠገብ እያለፈች ነበር። ይሁን እንጂ ከደስታዋ ብዛት የተነሳ ፍቅርን ለርዳታ ሲጣራ እንኳ አልሰማችውም!
ይኼኔ ድንገት ፍቅር ሆይ ና እኔ አሳርፍሃለሁ! የሚል ድምፅ ሰማ። አንድ በእድሜ ጠና ያለ ሽማግሌ ነበር። ፍቅርም እጅግ በጣም ተደሰተ። ከደስታው ብዛት የተነሳ የሽማግሌውን ስም እንኳን ሳይጠይቅ ጀልባው ላይ ወጣ።
ወደ ደረቅ ምድርም በደረሱ ጊዜ ሽማግሌው አፍታም ሳይቆይ መንገዱን ቀጠለ።
ፍቅርም የሽማግሌውን ውለታ በመገንዘብ እዛ ቦታ ላይ ያገኝውን ሌላውን ሽማግሌ ዕውቀትን ይኼ እርዳታ ያደረገልኝ ሽማግሌ ለመሆኑ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው።
  እንዴ እሱማ ጊዜ ነዋ! ብሎ መለሰለት ዕውቀት።
ጊዜ? ሲል ጠየቀና ፍቅር በመገረም ሁሉም ጥለውኝ ሲሄዱ ጊዜ የረዳኝ ለምን ይሆን?
ዕውቀትም ጥልቅ በሆነ ጥበብ ፈገግ ብሎ እንዲህ ሲል መለሰ ምክንያቱ ምን መሰለህ ፍቅር  የፍቅርን ታላቅነት ለመረዳት ብቁ የሆነው ጊዜ ብቻ ስለሆነ ነው።

ቤተሰቦቼ ታሪኩ ይሄንን ይመስላል ይሄንን ታሪክ የወደዳችሁት ሁላችሁም like አድርጉ በሌላ ጊዜ ቆንጆ በሆኑ መንፈሳዊ ታሪኮች እንመጣለን

@relationship4christ
@relationship4christ

5 months, 2 weeks ago

I VALUE THE COVENANT FOR PURITY AND I CAN'T DEFILE MY SELF,PERIOD !!

5 months, 3 weeks ago

"ይህም በመሆኑ እግዚአብሔር ተስፋውንና ቃል ኪዳኑን ሰጥቶናል። እግዚአብሔር መዋሸት ስለማይችል በተስፋዉና በቃል ኪዳኑ የማይናወጥ እምነት ሊኖረን ይገባል።ስለዚህ የሰጠንን ተስፋ ለመጨበጥ ወደ እርሱ የቀረብን ሁሉ በዚህ ደስ ሊለንና ልንጽናና ይገባናል።ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለ ደህንነት የሰጠዉ ተስፋ ምን ጊዜም አይታጠፍም" ዕብ6:17-18። ሕያዉ ቃል አዲስ ኪዳንና የዳዊት መዝሙር

5 months, 3 weeks ago

ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፡፡

ኢየሱስ ሊመጣ በደጅ ነው፡፡
ይህ ጊዜ የመጨረሻው ዘመን መጨረሻ ነው፡፡ የተባረከው ተስፋችን የሆነው የጌታችን የኢየሱስ መምጣት እውን የሚሆንበት፥ በመምጣቱም ያመኑትንና የተከተሉትን ብሎም በተስፋ፣ በናፍቆትና በመዘጋጀት የሚጠብቁትን፥ የራሱ የሆኑትን ብቻ የሚውስድበት ጊዜ ይሆናል ፡፡ ተዘጋጅተሃል? ተዘጋጅተሻል?

“እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።”
  — ሉቃስ 12፥40

6 months, 3 weeks ago

በፍፁም ጽድቅ በሚኖረው በቅዱስ አምላክ ፊት ያለ ነውር መቆም እንዴት ያለ መታደል ነው። ክሬዲቱ ወደ መስቀል ይሄዳል; ስለ ኃጢአታችን የተሰቀለው፣ የተቀበረው እና የተነሣው ክርስቶስ ነው።

መልካም እሁድ

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago