ግጥም በሜሮን ዮሐንስ (ሜራ)

Description
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc

2 days, 8 hours ago

@semetnbegtm
         ኦ ሚካኤል...
ፍፁም ትሁት ቢሆን ተሠጠው ልዕልና
ተርበው ለጠሩት የሚመግብ መና
ሞግዚት ነው በዓለም ለሌላቸው ወላጅ፣
ለታመኑት አባት ጠላትን አሳዳጅ
..
ነገድ ብሔር አይለይ ሲቀበል አደራ
ልጆች አሳዳጊ ከፊት እየመራ
ቦታ አይወስነው ጊዜ አይወስነው
                ልጆቹን ሲጠብቅ፣
ስሙ ግርማ ያለው ጠላት የሚያስጨንቅ
የማይሰለች አባት ፍቅሩ የሚጨምር
የሞትን ደብዳቤ በህይወት የሚቀይር
..
ልዑል እምልዑላን ስልጣኑ ከፍ ያለ
ሠልፉን እየመራ ዘንዶውን የጣለ
እሱ ያልረዳው ሠው አይገኝ በዓለሙ
ለአህዛብ አደለም ክርስቲያኖች ስሙ
..
ዓለም ጥበበኛ ያውቅበታል ሴራ
ቆላ ደጋ ብሎ ቢደግስ መከራ
ስጋችሁ አይራድ ፍፁም አትደንግጡ
ሠልፋችሁን ይምራ ልክ እንደ አፎምያ
                   ለሚካኤል ስጡ፣
የዓለምን ሴራ የገንዘብን ድግስ 
                  በእምነት ብለጡ፣
የሚካኤል ልጆች አትፍሩ ቀኑ
                      ቢጨልምም
እንኳን የአዳም ዘር ዘንዶው አልቻለውም!!

ገጣሚ_ ኤርሚ ግርማ

@semetnbegtm
@semetnbegtm

1 week, 6 days ago

(ቅዱስ እብዶች)

እድሜ ለነአዳም ለአናስሮቹ
እድሜ ለእባብም ለግብረአበሮቹ
ክፉ አድርገውን
አሳበዱን እንጂ ሰው አረጉንና
ቅዱስ እብዶች ነበርን
እርቃን የምንዞር በገነት ጎዳና።

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

2 weeks, 1 day ago

ማለዳን ምንተነፍስሽ የንጋት ተፈጥሮ ቋንቋ
የሰው መሆን ሌላ መልኩ ሴት የመሆን ውብ ሀቂቃ
ያንቺ አምላክ ፀሎት ሲሰማ አሜኑን በፍቅር ሲያሽረን
ዛሬ ላይ ተወለድሽና በአንቺ ውስጥ እኛን ፈጠረን
ልዩ ነው የኔ ዓለም ዕጣሽ
እሰየው እንኳንም መጣሽ
     ይኸዋ
ፈገገ የሰማይ ጥርሱ
ተረሳ የፅልመት ክሱ
ተካሰች ምድር በአበባ
ተሻረም የእልፉ እንባ
        ብቻ
ቅኔ ነውና ዕድሜ እሰየው ዛሬም ኖርሽልን
ዕለት ዕለት ልትናፈቂ እንኳንም ተወለድሽልን

🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂

LIJ DAN

ዳኒዬ በጣምምም ነው ማመሰግነው ብዕርህ አይንጠፍ😍🙏

3 months ago

​​​​#ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡

የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡

አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

…………………………………………
የተገኘው፣ ከዝማሬ ዳዊት ገፅ ነው
ሰናይ በዓል፣፣

5 months, 3 weeks ago
Share share ...***?******?******?***

Share share ...???
☝️☝️

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc