★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 3 weeks ago
እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።
መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77
#ፋኖነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ፋኖነት /አማራነት /ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏
Last updated 6 days, 14 hours ago
ወሳኝ እና አጠር ያለ ከዐረብኛ ወደ አማርኛ የተመለሰ ጽሁፍ ነው አንብቡት!
አዲስ መፅሐፍ
"الدعوة إلى وحدة الأديان كفر بواح"
"ወደሐይማኖቶች አንድነት የሚደረገው ጥሪ ግልፅ ክህደት ነው"
በሸይኽ ሑሴን ሙሐመድ አስ`ስልጢ -ሃፊዞሁሏህ-
#ከዓረበኛ ወደአማረኛ የተመለሰ
በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
كن على بصيرة
አልሐምዱሊላህ ሸይኻችን ሸይኽ ሐሰን ገላው ሃፊዞሁሏህ ከእስር ተለቀዋል
العلماء والقادة السلفيين الذين جاهدوا على إظهار الحق ودحض شبه المناهج الجديدة ونشر التوحيد والسنة في العالم وإطفاء ما يضادهما:
الشيخ ابن باز، والشيخ ابن عثيمين، والشيخ الفوزان، والشيخ ربيع المدخلي، والشيخ محمد أمان الإثيوبي ثم الهرري ثم الجامي، والشيخ الألباني ، والشيخ مقبل بن هادي اليمني الوادعي ، والشيخ صالح اللحيدان، والشيخ يحيى النجمي والشيخ حمدي بن عبد المجيد السلفي وغيرهم....
ሀቅን ግልፅ በማድረግ የአዳድስ ቡድኖችን ሹብሃ(ማጭበርበርያ) በማስወገድ ፣ተውሂድ እና ሱናን በዐለም በማሰራጨት፣የነዚህ ተቃራኒ የሆኑ ተግባሮችን በማጥፋት የታገሉ የሱኒዮች(የሰለፊዮች) መሪዎችና ዑሞች: -
ሸይክ ኢብኑ ባዝ፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን፣ሸይክ ፈውዛን ፣ሸይክ ረቢዕ አልመድኸሊይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልኢትዮጲ አልሀረሪ አልጃሚ, ሸይክ አልአልባኒ፣ሸይክ ሙቅቢል አልየመኒ አልዋዲዒ ፣ ሸይኽ ሷሊህ አልሉሃይዳን፣ ሸይኽ የህያ አንነጅሚ ሸይኽ ሀምዲ ኢብኑ ዐብድል መጂድ እና ሌሎችም ...
تمسك بهؤلاء وأمثالهم حتى تثبت على عقيدتك وتسلم من شبهات الجديدة التي تبث صباحا ومساء بلباس الحق، وانظرها كنظرة الماء في الزجاجة كما نصح الإمام المجتهد المجدد ابن تيمية لتلميذه ابن القيم (رحمهما الله) بذلك تجاه الشبه.
በዐቂዳህ እንዲትፀና ጧት እና ማታ በሀቅ ስም ከሚሰራጩ ማዎዛገብያዎች ሰላም ትሆን ዘንዳ እነዚህን ዑለሞች እና አምሳያዎቻቸውን አጥብቀህ ያዝ! ልክ በብርጭቆ ያለውን ወሃ የሚትመለከተውን አይነት እይታ እዪ(ማለትም ለሚከሰቱ ማደናገሪያዎቹ ሁሉ እጅ እንዳትሰጥ) ታለቁ ታጋይ እምብዛው ልጠፋ የቀረበውን የሰለፎችን ጉዳና(ሱናን) አዳሽ የሆነው ኢብኑ ተይሚያ(ረህመሁሏህ) የተለያዩ ማደናገሪያዎችን አስመልክቶ ተማሪውን ኢብኑልቀይሚን(ረህመሁሏህ) በዚህ ምክር እንደመከረው አንተም በማደናገሪያዎች ሁሉ አትታለል። ቀደምት ሰለፎች ብሎም የቀደምት ሰለፎችን መንገድ ለዚህ ትውልድ ያስተላለፉት እነዚህ ታላላቅ ጀበሎች ምን ነበር አቋማቸው የምለውን እወቅ።
“ሀጂ ኢብራሂም - ከሙፍቲን ዑመር ይሻላል....(እንትና ከእንትና ይሻላል) " እያልክ አትዘናጋ። በጠላቶችህ ክፋት ልክ አንተም በጥንቃቄ ላይ ካልሆንክ የጉዳትህ መጠን የከፋ ነዉ የሚሆነዉ።
“የዝንጀሮ ቆንጆ የለዉም"፣ የጠላቶች ወንበር መቀያየር እንዳያደነዝዝህ! ሀጂ ኢብራሂምና ግብራበሮቹ ከዑመር ገነቴና ደጋፊዎቹ ይሻላሉ ብሎ የሚያስብ ካለ ራሱን ያታለለ ሰዉ መሆን አለበት።
ምክንያቶች:-
1ኛ ) ሀጂ የኢኽዋን አስተሳሰብ አራማጅ ነዉ። ኢኽዋን ደግሞ ከሌሎች ፍርቃዎች በብዙህ ጉዳዮች እንደሚከፋ ለማንም ግልፅ ነዉ።
2ኛ) ከኢኽዋንም የዋናዎቹን (የነሀሰን አልበና) እስተሳሰብ አለዉ። ለምሳሌ ሀጂ አደገኛ በሆነዉ “ወህደተል አድያን” (የሀይማኖቶች አንድነት) የሚያምን ሰዉ ነዉ። ይሄንንም በምስራቅ ሀረርጜ/ጭሮ ከተማ በተደረገዉ በአንድ ስብሰባ እንዲህ በማለት ግልፅ አድርጎታል። ⤵️
«የትኛዉንም ሀይማኖት ብትወስዱ መመለሻዉ ወደ ነቢ ኢብራሂም ነዉ። የትኛዉም ሀይማኖት! በጣም የሚደንቃችሁ በአለም ደረጃ ከተለያዩ ሀይማኖቶች የተወጣጡ ምሁራን የኢብራሂምያ ሀይማኖቶች (አይሁድ፣ ክርስቲያንና ኢስላም) ተብሎ አንድነት ለመፍጠር ተስማምተዋል።» ይላል‼️
ይሄ አስተሳሰብ ምን ያህል አደገኛና የኩፍር ንግግር እንደሆነ ካላወክ ምንም ሊረዳህ አልችልም!!!
[ልብ በሉ:- ሀጂ ይሄንን ሲናገር የምላስ መንሸራተት ወይም ድንግት የሰማዉን ወሬ አይደለም የተናገረዉ። “ከአለም ክፍል የተወጣጡ የሀይሞኖት ምሁራን የኢብራሂምያ ሀይማኖቶችን አንድነት ለማምጣት እየሰሩ ናቸዉ” ማለቱ ምን ያክል በጉዳዩ ተሳትፎ እንዳለዉ ነዉ የሚያሳየዉ። ይሄንኑ እዉነታ ሼይኽ ጣሃ ኸድር “የኢትዮጽያ ኢኽዋኖች እና ዋና ዋና መገለጫዎቻቸዉ” በሚል ርዕስ (በአፋን ኦሮሞ) በደረጉት ሙሓደራቸዉ ተናግረዋል።
3ኛ ) ሰለፊዮችን በቀጥታ ከማጥቃት ረገድ ሀጂ ከገነቴዉ ይከፋል። እስካሁንም በተጨባጭ ያየነዉም ይሄንኑ ነዉ። በዛዉ በጭሮ ስብሰባ ላይ እንዲህ በማለት በሰለፊዮችም ጭምር ዛቻ ሰንዝሯል:-
«ኦሮሚያ ዉስጥ ከኔ ፍቃድ ዉጭ ምንም አይነት የዳዓዋ እንቅስቃሴ ማድረክ አይቻልም፣ በኤን-ጂ-ኦ (NGO) ስምም ብሆን... » እያለ የሰለፊዮችንም እንቅስቃሴ ለመግታት ዝቷል።
ይሄንን ሊል የቻለዉ የመርከዝ “ጃሚዐቱ ሰለፊ” ሼይኽ አብዱልሀሚድ አወል በጭሮ አቅራብያ የሚገኝና በነሀጂ ኢብራሂም መሪነት ሲዘምቱበትና ሲያሳስሩ ሼይኹ በ“ኢትዮጵያ አህሉ ሱና ማህበር” ህጋዉነቱን ስያረጋግጡ ይሄንንም በማስፈራራት ሊያስቆሙ ማስፈራርያ ማድረጋቸዉ ነበር)። ሀጂ ኢብራሂም በኦሮሚያ በተለያዩ ቦታዎች ሰለፍዮች ለመታሰራቸዉ ከጄይላኒ ጋር ሆኖ ቀጥታ ትዕዛዝ የሚሰጠ እሱ ነዉ። ለዚህም በቂ ማስረጃ አለን!!!
ስለዚህ ሀጂ ኢብራሂም በአቂዳም ብሆን ከነዑመር ገነቴዉ የማይሻል፣ ሰለፊዮች ላይ ጥቃት ከምድረስ ደግሞ ከሱም የባሰ ሰዉ ነዉ። ዝም ብለህ “መጅሊስ ተስተካከለልን” ወዘተ እያልክ እትጃጃል!!! እነዚህ ምንም የማይፈይዱህ፣ (በሀቂቃዉም) የማይጎዱህ የዝንብ ስብስብ ናቸዉ። አንተ ትክክለኛ ጎዳና ላይ ከሆንክ የሚረዳህ አላህ ነዉ፣ ከዛህን በኃላ አብሮህ ያሉ የቀጥተኛ መንገድ ባለቤት ሙስልሞች ናቸዉ!!!
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
#ኸድር አቦምሳ
ሀጂ ኢብራሂም ማስፈራርያ ለሰለፊዮች:-
"አንዳንዴም NGO ሊሆን ይችላል (ኦሮሚያ ዉስጥ ዪዞ ለዳዓዋ የሚንቀሳቀሱት)። የፈለገ NGOም ብሆን በክልሌ ዉስጥ እኔ ስለሆንኩ የማስተዳድረዉ፣ የፈለገ ከፌዴራልም የሚመጣ NGO ብሆን ከኦሮሚያ የኢስላም ጉዳዮች ም/ቤት እውቅና እስካልተሰጠው ድረስ ቦታ የሌለው መሆኑን እንገልፃለን። በዚህ አጋጣሚ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሰላምና ፀጥታ አካላት ከጎኔ ይገኛሉ፣ ጉዳዩም ደርሰዋቸዋል ብዬ አስባለሁ "
#ኸድር አቦምሳ
#ሸይኽ ሀሰን ገላው ዛሬ ላይ ብዙዎች የዲን መዕረግ ተሸክመው በዲን ስም ጥቅማቸውን በሚያሯሩጡበት፣ከአጥፊው አህባሽ ቡድን ጋር የውሸት አንድነት በሚሰብኩበት ወቅት በሀቅ ላይ ፀንተው ደዕዋቸውን በአማራ ክልል በትጋት እያስፋፉ ያሉ፣የደዕዋቸው ፍሬ ከክልላቸው አልፎ ወደ ተለያዩ ክልሎች የደረሰ፣በአካልም ሆነ በሩቅ ደዕዋዎቻቸውን ያዳመጠ ስለ ስብእናቸው የሚመሰክር ዛሂድ የሆኑ ውድና ብርቅዬ ሸይኽ እንጂ ለእስር የሚያበቃቸው አንድም ይህ ነው የሚባል ነገር የሌለባቸው ሰው ናቸው።
ይህንን ደግሞ አይደለም ወዳጅ ጠላት ይመሰክራል!
በእስር ላይ ያሉት #ሸይኽ ሀሰን ገላው እና ሌሎች ወንድሞች እስካሁን አለመፈታታቸው ይታወቃል። አሁንም ምክንያቱ ያልታወቀው የግፍ እስሩ ቀጥሎ በደሴ ወንድሞች እና ኡስታዞች እየታሰሩ ነው። ይህ እስር አዝማሚያው እንደሚያሳየው ሁሉም ቦታ የምቀጥል ይመስላል።
የትኛውም ግፉን ቀማሽ ይህ እስር እና እንግልት ከድሮም ያለ ነብያቶች እንኳ ያልተረፉት ሱና መሆኑን ልያውቅ ይገባል። ቅሉ ግን የመታሰርህ ሰበብ ሰርቀህ፣በድለህ፣አጭበርበርህ፣በፖለትካ ተጨማልቀህ አይሁን እንጂ ሀቅን ለማንገስ፣የነብያቶችን እና የቀደምት ሰለፎችን መንገድ ለማህበረሰቡ ለማድረስ ምንም ሳይበግርህ ሌት ቀን በመልፋትህ፣ጥመትን እና ተባባሪዎቹን አልቀበልም ብሎም አልታገሳቸውም በማለትህ የሚደርስህ ገፋት የእውነተኝነትህ ማረጋገጫ፣የነ ኢማም አህመድ ፣ኢብኑ ተይሚያ እና የሌሎች ፈርጥ ሙጃህዶች ቅሪት መሆኑን በመገንዘብ ታስረህም ተገርፈህም ልትፀና ነው የሚገበው።
ያ ሙጃህዱ የሀቅ ሰዎች ተምሳሌት ኢብኑ ተይሚያ (ረህመሁሏህ) እንዲህ ይል ነበር: -
ما يصنع أعدائي بي، أنا جنتي في قلبي، وبستاني في صدري، أين رحت فهي معي لا تفارقني، أنا حبسي خلوة، وقتلي شهادة، وإخراجي من بلدي سياحة.
" ጠላቶች በኔ ላይ ምንድነው ልሰሩ የሚችሉት?! ጀነቴ በልቤ ውስጥ ነች፣ ማሳ(አታክልት) በደረቴ ውስጥ ነው፣ የትም ቢሄድ እሷ ከኔ ጋር ነች አትለየኝም፣እኔ መታሰሬ ለኔ ኸልዋ(መገለያዬ) ነው ፣ እኔን መግደል ለኔ ሸሃዳ ነው፣ እኔን ከሀገር ማስወጣት ደግሞ ለኔ ጉብኝት ነው"
ኢብኑ ተይሚያ ጠላት ከነዚህ ከሦስቱ ውጭ ሌላ ማድረግ የሚችለው እንደሌለ፣እነዚህ ተፈፃሚ ቢሆኑ ራሱ ለአማኝ በሀቅ ላይ ለቆመ ሰው መልካም እንጂ ቅጣቱ እንዳልሆነ እየነገረን ነው።በሀቅ ላይ ሆናችሁ በተለያዩ ቦታ ብዙ በደል እና እንግልት የሚደርስባችሁ መሻይኮች፣ዱዐቶች፣ወንድም እህቶች በዚህ በኢብኑ ተይሚያ ንግግር ተጽናኑ ተበራቱ።
"والعاقبة للمتقين"
كان الشيخ المربي محمد أمان الجامي -رحمه الله- مشتغلا بالعلم والتعليم حتى تظن أنه لا يحسن إلا العلم.
ويوصي الطلاب بالانشغال بالعلم والعقيدة خاصة وترك ما يقطع عليهم الطريق من منغصات الفتن.
فإذا رأى انحرافا وفتنا انبرى كالأسد ورمى الباطل بالعلم والحق حتى يخمد نارها ثم يعود للعلم.
فضيلة الشيخ هاشم الحسيني
"በትክክለኛ ዲን ላይ ኮትኳች ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልኢትዮጲ አልሀረሪ አልጃሚ(ረህመሁላህ) እውቀትን እንጂ ሌላ ነገር አይችልም ብለህ እስክትጠረጥር ድረስ በእውቀት እና በማስተማር ቢዚ ነበሩ። ተማሪዎችን በእውቀት እና በዐቂዳ ላይ ላይ ይመክሩ ነበር። በተለይም ከዒልም ከሚያሪቀው መንገድ ከአስቸጋሪ ፈተናዎች በመራቅ ላይ ይመክሩ ነበር።
ጥመትን እና ፈተናዎችን በተመለከተ ጊዜ እንደ አንበሳ( ለሀቅ በወኔ የሚወጣ ድምፅን ለማመላከት ነው)ባጥልን በእውቀት እና በሀቅ እሳቱ የሚጠፋ ያህል ይወረውራል። ከዚያም ወደ እውቀቱ ይመለሳል።"
#የሀበሻው ተራራ -#የመዲናው ፈርጥ ፣የጃሚዐቱልኢስላሚያ የሀዲስ ክፈል ዲን(ኃላፊ)፣የመስጂደነበዊ ድምቀት፣በአውሮፓ ፣ በኤዢያ፣በአሜሪካ፣በአውስተራልያ፣በአፍሪካ ተዋቂ እትብቱ በተቀበረበት በትውልዱ ሀገር ኢትዮጵያ በሱና ሰዎች ዘንድ እንጂ እምብዛም የማይታወቅ የታላላቅ የዐለም ከዋክብት የሆኑት የነ ሸይኽ አብኑ ባዝ፣ሙፍቲ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂም፣ ሙፈስሩ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን አፍሪቂ ሞሪታኒ አሽሺንቂጥ፣ ሸይኽ ሃማድ አልአንሷሪ፣የተዋቂው ዋሲጥያ ሸርህ ባለቤት ኸሊል አልሃራስ የነዚህ ተማሪ የነበረ ለእውቀት ከሀበሻ ወደ ሶማሊያ፣ከሶማሊያ ወደ የመን የተሰደደ የመጨረሻውን የእውቀት ስደት እና መኖርያ ሰውዲ # መዲና ያደረገ ዐሊም ነበር።
ብሎም እነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ፣ሸይኽ ፈውዛን፣ሸይኽ ሷሊህ አስሱሃይሚ፣ሸይኽ አብዱሏህ አልቡኻሪ፣ሸይኽ ሱለይማን አርሩሃይሊ ...ወዘተ ቁጥራቸውን ለመዘርዘር የሚከብዱ ብዙ ዐሊሞች ታላቅ ዐሊም፣ታጋይ፣በሀቅ ላይ የማይደራደር መሆኑን የገለፁለት ኮከብ ነው።
# ይህ ሁሉ ማእረግ ያለውን ሰው እንዴት የሀገሩ ሰዎች አያውቁትም የምለው ጥያቄ ማንም አስተዋይ የሆነ ሰው ልያነሳው ይችላል። አዎ! ልነሳም ይገባል። ምክንያቱ ከወዲህ ነው: - ይህ ታላቅ ሰው ዛሬ ላይ ብዙ እውቀት አላቸው የሚባሉ ሰዎች ሰውን፣መንግስትን በማይነካ ለፖለትካው፣ለካፊሩም በምመች መልኩ መርጠው ደዕዋ እንደሚያደርጉት አይነት ሳይሆን ነብዩ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የቁረይሾች ሴራ፣ተንኮል፣ውሸት፣አደጋ እና ማሳደድ ሳይበግራቸው ለዛ ማህበረሰብ የሚያስፈልገውን እና የማህበረሰቡ ችግር በነበሩ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው ደዕዋቸውን ያደርጉት እንደነበር ይህ ዐሊም ዛሬ ላይ በወቅቱ የተንሰራፈውን ከሽርክ፣ከቢድዐ የሚያስጠነቅቅ በተለይም በኢስላም ስም አድስ የተጠነሰሱ ኢኽዋን፣ተብሊግ ፣ሱፊያ የመሳሰሉ ቡድኖችን ከነ መስራቾቻቸው እና መሪዎቻቸው እርቃን አስቀርቶ ማሕበረሰቡ እንድያውቂ ትግል ስላደረገ ሰው እንዳያውቃቸው በሀበሻ ምድር ስማቸው በመጥፎ ተስሎ ለማህበረሰቡ ይቀርብ ስለነበረ ነው።ለምሳሌ ዶ/ር ጀይላን እንዲህ ይል ነበር : -"ዑለሞችን በመሳደቡ ሰበብ አላህ በሰረጣን(ካንሰር) ፈትኖ እንድሞት አረገው"
በመሰረቱ ይህ ውሸት ነው። ይህ ዐሊም የሞቱት በጉበት ሕመም ምክንያት ነው፣ ደግሞስ ከመቼ ጀምሮ ነው የአንድ ሰው አሟሟት ለመጥፎነቱ መረጃ የሚሆነው?! "ዑለሞችን በመሳደቡ" ያለው ደግሞ መጥፎ ዐቂዳን ለሙስልሙ የሚያስተምሩ ሰዎችን ማጋለጥ በሸሪዐ ስድብ አይደለም፣የባጢል ሰዎች ዘንድ ስድብ ነው። ልክ የነብዩ ኢብራሂም(ዐለይሂስሰላም) ሕዝቦች ኢብራሂም" ጣኦትን አታምልኩ አይበሉም አይጠጡም አይደርሱላቹም" በሚሏቸው ጊዜ "አማልክቶቻችንን ይሳደባል" ይሉ እንደ ነበር፣ ቁረይሾችም ነብዩ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብላችሁ መስክሩ" ባሏቸው ጊዜ " ዝምድናን ቆራረጠ፣ገጣሚ፣ጠንቋይ፣ቁርኣንን ከሌሎች የኮረጀ፣ አላህ ልጆቹን በጊዜ እየወሰደ(በሞት) ዘሩን አጥፍቶ ዘሩ የተቆረጠ ...." ይሉ እንደነበር።
#ስጠቃለል በኢትዮ ልታዎቁ ያልቻሉት በስማቸው ላይ ጥላሸት ተቀብቶ ማህበረሰቡ እንዳያቃቸው ስለተሰራበት ነው።ለዚያም ነው በተለያዩ ጊዜ " ክብር ለዑለማዎቻችን" እያሉ በመውሊድ የሚታወቁትን ሁላ በቲቪዎቻቸው ስያስተዋውቁን የነ #ሙሐመድ አማን አይነቱ የሀገራቸው ዐሊም ትዝም የማይላቸው።
والله نحبك في الله رغم أنف كل المخالفين!
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 3 weeks ago
እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።
መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77
#ፋኖነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ፋኖነት /አማራነት /ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏
Last updated 6 days, 14 hours ago