የአቡ ኢልሃም ሙሀመድ ኑር ያለቁ ደርሶች የሚለቀቅበት ቻናል

Description
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc

2 months, 2 weeks ago

ከደርስ የተወሰደ

መቼም በጀናዛም ቢደዓ የሚሰራ አለ ትሉኝ ይሆናል በርካታ ቢደዓዎች አሉ አዳምጡት❗️

https://t.me/sunah123
https://t.me/sunah123

2 months, 2 weeks ago

የሱፍዬችን ጉድ አዳምጡ እና እናንተ ፍርድ ስጡ ድንን ያወድማሉ ስንል በመረጃ እንጂ
ያለመረጃ አይደለም

ነብዩ ሲወለዱ ድምፃቸውን ሰምቻለሁ እያለ ነው፣ ኢስራዕና ሚዕራጅ ነብዩ ሲወጡ አብሬ ነበርኩ እያለ ነው፣ ለነብዩ የተወረደውን ቁርዓን እየተሻረ(እየተነሰኸ ) አስቸግሮናል እያለ ነው

አሏህ ከሱፍያ ኮተት ይጠብቀን

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ ተቀርተው ያለቁ እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል።

?????

https://t.me/sunah123

2 months, 2 weeks ago

?ወቅታዊ ከዚህ በፊት የተደረገ የጁምዓ ኹጥባ

? ዘመን መለወጫ በሙስሊሞች ላይ ያለው አደጋ

ልጆችን ለዘመን መለወጫ ብሎ

?ፀጉር ማስቆረጥ
?ልብሶችን መግዛት የተለያዩ ነገሮችን መግዛት ያለው አደጋ

?በኡስታዝ ሙሀመድ ኑር (ሀፊዞሁሏሁ ተዓላ )

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር)

?????

https://t.me/sunah123

5 months, 1 week ago

8 - ሰባተኛውን ዙር ጠዋፍ ሲያበቃ ትከሻውን በፎጣው ይሸፍንና ክፍት ማድረጉን ይተዋል፡፡ እድጥባዕ በዑምራ ጠዋፍ ወይም በጠዋፉል ቁዱም ብቻ እንጂ ከዚህ ውጭ ሱንና አይደለምና፡፡

በመቀጠል ወደ ኢብራሂም መቆሚያ (መቃሙ ኢብራሂም) ያመራና ከተቻለ ከመቆሚያው ኋላ ሁለት ረክዓ ሶላት በመጀመሪያው ከፋቲሓ በኋላ ሱረቱል ካፊሩን በሁለተኛው ሱረቱል እኽላስን በመቅራት ይሰግዳል፡፡ ከመቃሙ ጀርባ መስገድ ካልተቻለው በፈለገበት ቦታ ላይ ይሰግዳል፡

መመሪያዎች

1 - አንድ ሙስሊም ሐጀሩል አስወድን ለመሳለም ወይም ለመሳም ብሎ ጠዋፍ የሚያደርጉ ሰዎችን መጋፋትና ማስቸገር የለበትም፡፡ በሌሎች ላይ ችግር የሚፈጥር ከሆነ በጠዋፍ ላይ ፈጣን አካሄድን (ረመል) መተው ይኖርበታል፡፡

2 - በጠዋፉ ወቅት የተመቸውን ዓይነት ዱዓእ ያደርጋል፡፡ ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ ጠዋፍ የተለየ ዝክር የለውም፡፡ በጠዋፉ ጊዜ ቁርኣን ቢቀራ ችግር የለውም፡፡

3 - እድጥባዕ በዑምራ ወይም በቁዱም (የመድረሻ) ጠዋፍ ሁሉም ዙሮች ውስጥ ሱንና ነው፡፡

4 - ሴት በጠዋፍ ጊዜ ጌጦቿን ከማሳየትና የሽቶ ጠረን ለሌሎች እንዳይደርስ፣ ድምጽዋን በዝክርና በዱዓእ ከፍ ከማድረግ መጠንቀቅ ይኖርባታል፡፡

9 - ከዚያ ወደ መርዋ ያመራና አጠገቡ ሲደርስ ከቁርኣን የሚከተለውን የአላህ ቃል ይቀራል፡- ‹‹ሶፋና መርዋ ከአላህ (ትእዛዝ መፈጸሚያ) ምልክቶች ናቸው፤ቤቱን (ከዕባን) በሐጅ ወይም በዑምራ ሥራ የጎበኘ ሰው፣ በሁለቱ (መካከል) በመመላለሱ በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፤መልካምን ሥራ በፈቃደኛነት የሠራ ሰው (አላህ ይመነዳዋል)፤አላህ አመስጋኝ ዐዋቂ ነውና፡፡›› [አል-በቀራህ:158]

10 - ወደ ሶፋ ይወጣና ፊቱን ወደ ቅብላ አዙሮ አጆቹን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ‹‹ላ እላሀ እል’ላል’ሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ፣ ወሁወ ዐላ ኩል’ሊ ሸይእን ቀዲር፡ ኣይቡነ ታእቡነ፣ ዓብዱነ፣ ሳጅዱነ፣ ልረብ’ብና ሓሚዱነ፤ሰደቀል’ሏሁ ወዕደሁ፣ ወነሰረ ዐብደሁ፣ ወአህዘመል አሕዛበ ወሕደህ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ]

በማለት የአላህን ያወድሳል፣ ያመሰግናል፡፡ ከዚያም ዱዓእ ያደርግና ዝክሩን እንደገና ይደግመዋል፡፡ አሁንም ዱዓእ ያደርግና ዝክሩን ለሦስተኛ ጊዜ ይደግማል፡፡

11 - ከሶፋ ጉብታ ወርዶ ወደ መርዋ ያመራል፡፡ በሁለቱ አረንጓዴ ምልክቶች [አረንጓዴ ምልክቶቹ በሶፋና መርዋ መካከል ሲመላለሱ እሜት ሃጀር በፍጥነት የተጓዙበትን ቦታ የሚያለክቱ ናቸው፡፡] መካከል በፍጥነት ተጉዞ ወደ መርዋ በመድረስ ሶፋ ላይ የፈጸመውን ሁሉ እዚህም ይፈጽማል፡፡

12 - በሶፋና መርዋ መካከል ሰባት ዙር በፍጥነት ይመላለሳል፡፡ (ሰዕይ መሄጃው አንድ ዙር፣ መመለሻውም አንድ ዙር ነው)፡፡ ለሰዕይ የጦሃራ መኖርና ሰዕይና ጠዋፍን ማከታተል ሱና ሲሆን፣ ያለ ጦሃራ ቢደረግም ሰዕዩ ትክክለኛ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

በሶፋና መርዋ መካከል በፈጣን እርምጃ መጓዝ

13 - ሰዕይ ካደረገ በኋላ ግልጽ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ ጸጉሩን ያሳጥራል፤ሴት ከጸጉሯ ከሁሉም አቅጣጫ የጣት አንጓ ያህል ታሳጥራለች፡፡ ለወንድ በላጩ መላጨት ነው፡፡

ከአቡ ሁረይራ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ‹‹አላህ ሆይ! ለተላጪዎች ምሕረት አድርግላቸው›› ሲሉ (ሶሓባ) ለአሳጣረዎችም? አሏቸውና ‹‹አላህ ሆይ! ለተላጪዎች ምሕረት አድርግላቸው›› አሉ፡ ለአሳጣሪዎችም? ሲሏቸው (በሦስተኛው ላይ) ‹‹ለአሳጣሪዎችም›› አሉ ብለዋል፡፡ [በቡኻሪ የተዘገበ] 

በተመቱዕ ተጠቅሞ ከሆነ ጸጉር ሊያድግበት የሚችል በቂ ጊዜ ስለማይኖር መላጨቱን ለሐጅ አቆይቶ ማሳጠሩ በላጭ ይሆናል፡፡

14 - ከዚያም ከዑምራ እሕራም ተሐል’ሉል አድርጎ ነጻ ይሆናል፡፡ በዚህም ዑምራው ይጠናቀቃል፡፡

ሴት በጠዋፍና በሰዕይ በጠዋፉ በፍጥነት የማትጓዝና በሰዕይም በሁለቱ አረንጓዴ አምዶች መካከል በፈጣን እርምጃ የማትመላለስ ከመሆኗ በስተቀር በሌላው ክንውን ልክ እንደ ወንዱ ነች፡፡ ጸጉሯንም የጣት አንጓ ያህል ከሁሉም አቅጣጫ ታሳጥራለች እንጂ አትላጭም፡፡

https://t.me/sunah123

https://t.me/sunah123

Telegram

አቡ ኢልሐም አስ_ሰለፊ (የኡስታዝ ሙሀመድ ኑር)ያለቁ ና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ በሀምዛ መስጂድ ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል። ***👇******👇******👇******👇******👇*** https://t.me/sunah123

8 - ሰባተኛውን ዙር ጠዋፍ ሲያበቃ ትከሻውን በፎጣው ይሸፍንና ክፍት ማድረጉን ይተዋል፡፡ እድጥባዕ በዑምራ ጠዋፍ ወይም በጠዋፉል ቁዱም ብቻ እንጂ …
5 months, 1 week ago

አይ’ያም አት’ተሸሪቅ

አይ’ያም አት’ተሸሪቅ ከዒድ ቀጥለው ያሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲሆኑ እነሱም ፡- የዙልሕጃ ወር አስራ አንደኛው፣ አስራ ሁለተኛውና አስራ ሦስተኛው ቀናት ናቸው፡፡ በዚህ የተሰየሙት የኡድሕይያ ሥጋ ተቆራርጦና ተዘልዝሎ በጸሐይ ይደርቅባቸው ስለነበረ ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ስለነዚህ ሦስቱ ቀናት ሲናገሩ ‹‹ንቁ! እነኚህ ቀናት የመብላት የመጠጣትና የአላህ ዝክር ቀናት ናቸው፡፡›› ብለዋል፡ [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ]

አስራ አንደኛው ቀንና ሌሊቱ

በአስራ አንደኛው ቀን ዋዜማ ሌሊት ሚና ማደር ግዴታ ነው፡፡ በአስራ አንደኛው ቀን ፀሐይ ከእኩለ ቀን ካለፈች በኋላ በሦስቱ ጀምራዎች በያንዳንዳቸው ሰባት ሰባት ጠጠሮች [ጀምራዎች በሚና ጫፍ ላይ የሚገኙ በያንዳንዱ መሀል የቆመ ግዙፍ ምሰሶ ያላቸው ሦስት ገንዳዎች (ገበቴዎች) ሲሆኑ፣ የመጀመሪያው ትንሹ ጀምራ፣ ሁለተኛው መካከለኛው ጀምራ፣ ሦስተኛው በሚና ጠረፍ በመካ አቅጣጫ የሚገኘው ትልቁ (አልዐቀባ) ጀምራ ናቸው፡፡] ይወረወራሉ፡፡

የጠጠር አወራወር

በመጀመሪያው ጀምራ ይጀምርና ሰባት ጠጠሮችን አንዱን ከሌላው በማስከተል ይወረውራል፡ ከያንዳንዱ ጠጠር ውርወራ ጋር ተክቢራ ይላል፡፡ የሚወረወሩ ጠጠሮች የግድ ገንዳው ላይ መውደቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚያ ትንሽ ራመድ ብሎ ይቆምና እጆቹን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ዱዓእ ያደርጋል፡፡

በመቀጠልም በመካከለኛው ጀምራ እንደ መጀመሪያው ሰባት ጠጠሮችን ይወረውርና እጆቹን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ዱዓእ ያደርጋል፡፡

ከዚያም በአልዐቀባ ጀምራ ሰባት ጠጠሮችን በተመሳሳይ ሁኔታ ይወረውራል፡፡ ከዚህ በኋላ ለዱዓእ አይቆምም፡፡

የመጀመሪያው ጀምራ

የአልዐቀባ ጀምራ

መካከለኛው ጀምራ

አስራ ሁለተኛው ቀንና ሌሊቱ

በአስራ ሁለተኛው ቀንም ሚና ማደር ግዴታ ነው፡፡ በዕለቱ ፀሐይ ዘንበል ካለች በኋላ ሦስቱንም ጀምራዎች በአስራ አንደኛው ቀን በወረወረበት ሁኔታ ይወረውራል፡፡

በዚህ ቀን መቸኮል ከፈለገ ጠጠሮቹን ወርውሮ ከፀሐይ መጥለቅ በፊት ሚናን ለቆ ይሄዳል፡፡ ሚና ውስጥ እያለ ፀሐይ ከጠለቀች ግን ሚና ውስጥ አድሮ አስራ ሦስተኛውን ቀን የጠጠር ውርወራውን ማከናወን ይኖርበታል፡፡

ይህም ተጨማሪ ሰናይ ተግባር ይሆነዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏልና ፡- ‹‹የተቻኮለ ሰው በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፤የቆየም ሰው በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፤(ይህም) አላህን ለፈራ ሰው ነው፤›› [አል-በቀራህ:203]

ማለት የተፈለገው የቸኮለ ሰው ከአያም አትተሸሪቅ አሰራ አንደኛውንና አስራ ሁለተኛውን፣ የቆየው ደግሞ አስራ ሦስተኛውንም ያሟላል ማለት ነው፡፡

አስራ ሶስተኛው ቀንና ሌሊቱ

በአስራ ሦስተኛው ቀን ከቀትር በኋላ ቀደም ሲል በአስራ አንደኛው ቀን ባደረገው ሁኔታ ሦስቱን ጀምራዎች ይወረውራል:፡ የውርወራ ወቅቱም ከዚህ ቀን ፀሐይ መጥለቅ ጋር ያበቃል፡፡

ውርውራን ማዘግየት

ሐጅ አድራጊው የጠጠር ውርወራውን ወደሚቀጥለው የውርወራ ቀንና እስከ መጨረሻው የውርወራ ቀን ድረስም ማዘግየት ይፈቀድለታል፡፡ ሦስቱም የተሸሪቅ ቀናት የውርወራ ቀናት ናቸውና፡፡

ላዘገየ ሰው የአወራወር ሁኔታ

የመጀመሪያውን ቀን ውርወራ በሦስቱም ጀምራዎች በመወርወር መጀመር፤ከትንሹ ጀምራ ሲመለስ የሚቀጥለውን ቀን ውርወራ እየወረወረ ሁሉንም ይወረውራል፡፡ ወርውራው ከቀትር በኋላ ብቻ መከናወን ይኖርበታል፡፡

ጠዋፍ አልወዳዕ (የመሰናበቻ ጠዋፍ)

ሐጅ አድራጊው ከመካ መውጣት ከፈለገ የመሰናበቻ ጠዋፍ በከዕባ ዙሪያ ያደርጋል፡፡ ጠዋፉል ወዳዕ ከሐጅ ዋጅቦች አንዱ ሲሆን ከጠዋፉ በኋላ ሰዕይ አይኖርም፡፡ የወር አበባና የወሊድ ደም ካለባቸው ሴቶች ላይ ግዴታነቱ ይነሳል፡፡

ጠዋፍ አልእፋዷን እስከ ጠዋፍ አልወዳዕ ማዘግየት

ጠዋፍ አልእፋዷን እስከ ጠዋፍ አልወዳዕ ማዘግየት የተፈቀደ ነው፡፡ በላጩ ግን አለማዘግየቱ ነው፡፡ ኒይያው ለጠዋፍ አልእፋዷ ከመሆን ሸርጥ ጋር ከጠዋፉ በኋላ ሰዕይ ቢያደርግ እንኳ ከጠዋፉል ውዳዕ በጠዋፉል እፋዷ ብቻ መብቃቃት ይቻላል፡፡

- ከጠዋፍ ጀርባ ያለው ጥበብ :

ከጠዋፍ፣ ከሰዕይ እና ከጠጠር ውርወራ ጀርባ ያለው ጥበብ (ሕክማ) የየየአላህን ዝክርና ውዳሴውን ሕያው ማድረግ ነው፡፡ ከዓእሻ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ፡- ‹‹በቤቱ (በከዕባ) ዙሪያና በሶፋና መርዋ መካከል ጦዋፍ የተደረገው፣ የጠጠሮች ውርወራም የአላህን ዝክር ቋሚ ለማድረግ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ]

የዑምራ አፈጻጸም

1 - ዑምራ አድራጊው ወደ ሚቃት ሲደርስ ገላውን ታጥቦ ሽቶ ተቀባብቶና የእሕራም ልብስ ለብሶ ‹‹ለብበይከ ዑምረተን›› በማለት ኒይያ ያደርጋል፡፡

2 - ‹‹ለብ’በይከ አል’ሏሁም’መ ለብ’በይከ፣ ለብ’በይከ ላ ሸሪከ ለከ ለብ’በይከ፣ እን’ነል ሐምደ ወን’ንዕመተ ለከ ወልሙልከ፣ ላሸሪከ ለከ›› በማለት ተልቢያ ማስተጋባት ይጀምራል፡፡  [በቡኻሪ የተዘገበ] ቤቱን (ከዕባን) በዓይኑ እስኪያይና ሐጀረል አስወድን እስኪሳለም ድረስ ተልቢያ ማስተጋባቱን ይቀጥልበታል፡፡

3 - ወደ ተከበረው መስጊድ (መስጅድ አልሐራም) ሄዶ የቀኝ እግሩን በማስቀደም የመስጊድ መግቢያ ዱዓእ አድርጎ ይገባል፡፡

4 - ተልቢያውን ያቋርጥና በከዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ በመጀመር ጥቁሩን ድንጋይ በመሳለም ከተቻለ በመሳም ካልተቻለ በእጁ እያመላከተ ፡- ‹‹ብስምል’ላህ ወል’ሏሁ አክበር፣ አሏሁም’መ ኢማነን ብከ፣ ወተስዲቀን ብክታብከ፣ ወወፋአን ብዐህድከ፣ ወእት’ትባዐን ልሱን’ነት ነቢይከ መሐመድን ﷺ›› ይላል፡፡ [በቡኻሪ የተዘገበ] 

ትርጉሙ፡- ‹‹በአላህ ስም (እጀምራለሁ)፣ አላህ ከሁሉም በላይ ኃያል ነው፣ አላህ ሆይ! በአንተ በማመን፣ የመጽሐፍህንም (የቁርኣንን) እውነተኛነት በማረጋገጥ፣ ቃል ክዳንህንም ለመሙላትና የነቢይህን የሙሐመድን ﷺ ሱና በመከተል ነው (ይህን ዕባዳ የምፈጽመው)፡፡›› ማለት ነው፡፡

5 - ቤቱን በስተግራው በማድረግ ከሐጀሩል አስወድ ተጀምሮ በሐጀሩል አስወድ የሚያበቃ ሰባት ዙር በከዕባ ዙሪያ ይዞራል (ጠዋፍ ያደርጋል)፡፡

6 - በመጀመሪያዎቹ ሦስት ዙሮች በፈጣን አካሄድ (በረመል) መዞር ሱና ሲሆን፣ በሁሉም ዙሮች የቀኝ ትከሻውን ገልጦ ፎጣውን ከብብቱ ሥር በማሳለፍ ጫፎቹን በግራ ትከሻው ላይ ማድረግም (እድጥባዕ) ሱና ነው፡፡

ገላን መታጠብ

ሽቶ መቀባት

እሕራም

ለጠዋፍ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

ለጠዋፍ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ፡- ኒይያ፣ ጦሃራ፣ ሀፍረተ ገላን (ዐውረት) መሸፈን፣ ሰባት ዙር መዞር፣ ዙሩን ከጥቁሩ ድንጋይ መጀመር፣ ቤቱን ከበስተግራ ማድረግ፣ ለሶላት እቃማ ካልተደረገ ወይ ሶላቱል ጀናዛ ኖሮ አቋርጦ ካቆመበት የሚቀጠል ካልሆነ ሰባቱንም ዙሮች ማከታተል እና በጠዋፉ ቤቱን ሙሉ ለሙሉ የሚዞር መሆን ናቸው፡፡ ከሕጅር በኩል ገብቶ ቢዞር ሕጅር የከዕባ አካል በመሆኑ ጠዋፉ ትክክለኛ ሊሆን አይችልም፡፡

7 - በጠዋፍ ጊዜ የፈለገውን ዱዓእ ያደርጋል፡ በሩክን አልየማኒ ትይዩ ሲደርስ ይሳለመውና ተክቢራ ይላል፡፡ መሳለም ካልቻለ ግን በእጁ አያመለክትም፣ ተክቢራም አይልም፡፡

በሩክን አልየማኒና በሐጀሩል አስወድ መካከል የሚከተለውን ይላል፡- ‹‹ረብ’በና ኣትና ፊድ’ዱንያ ሐሰነተን ወፊል ኣኽረት ሐሰነተን ወቅና ዐዛበን’ናር፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] 

ትርጉሙ:- ‹‹ጌታችን ሆይ! በቅርቢቱ ዓለም ሕይወት መልካሙን ነገር ስጠን፣ በወዲያኛው የመጨረሻ ሕይወትም መልካሙን ስጠን፡፡›› ማለት ነው፡፡

5 months, 1 week ago

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
وَاللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، وَللهِ الْحَمْدُ
https://t.me/sunah123
https://t.me/sunah123

Telegram

አቡ ኢልሐም አስ_ሰለፊ (የኡስታዝ ሙሀመድ ኑር)ያለቁ ና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ በሀምዛ መስጂድ ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል። ***👇******👇******👇******👇******👇*** https://t.me/sunah123

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَكْبَرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ..
6 months, 4 weeks ago

ኢማሙ_አሕመድ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ሀቅን የተናገረ፣ የሰለፎችን ፈለግ የተከተለ፣ ሱናን አጥብቆ የያዘ፣ ደጋጎቹን የተከተለ፣ የቢድዓ ባለቤቶችን የራቀ፣ ከነሱ ጋር መቀማመጥን የተወና ይህን ሁሉ ሲያደርግ የአሏህን ምንዳና ወደሱ መቃረብን ፈልጎበት ያደረገን ባሪያ አሏህ ይዘንለት።»

? ۞ طبقـات الحنابلـة【1/36】۞

https://t.me/sunah123

Telegram

አቡ ኢልሐም አስ_ሰለፊ (የኡስታዝ ሙሀመድ ኑር)ያለቁ ና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ በሀምዛ መስጂድ ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል። ***👇******👇******👇******👇******👇*** https://t.me/sunah123

ኢማሙ\_አሕመድ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
6 months, 4 weeks ago

ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«አሏህና መልዕክተኛው ባሉበት ጎን ሁን፣ ሰዎች በሙሉ በሌላኛው በኩል ቢሆኑም።»

? ۞ الفـــوائــد【167】۞
https://t.me/sunah123

Telegram

አቡ ኢልሐም አስ_ሰለፊ (የኡስታዝ ሙሀመድ ኑር)ያለቁ ና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ በሀምዛ መስጂድ ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል። ***👇******👇******👇******👇******👇*** https://t.me/sunah123

ኢብኑል\_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
7 months ago

*✏️السلام  عليكم  ورحمة الله  وبركاته*

*?ታላቅ ብስራት?***

➥  በፉሪ በሀምዛ መስጂድ  ከመግሪብ  እስከ ዒሻ እና ከሱብሂ በኋላ ሲሰጥ የነበረዉ ደርስ በረመዷን ምክንያት መቋረጡ ይታወቃል።
በመሆኑም ተቋርጦ የነበረዉ ደርስ  በአሏህ ፈቃድ በዉዱ ኡስታዛችን በኡስታዝ ሙሃመድ ኑር ሰኞ ( ሚያዚያ 14) የሚጀመር መሆኑን እናሳዉቃለን።

ስለሆነም Telegram ለማይጠቀሙ ና ላልሰሙ ወንድሞቻችን በስልክ በመደወል  ደርስ ሰኞ የሚጀመር መሆኑን አሳዉቋቸዉ !! ለኸይር ስራ እንሽቀዳደም
https://t.me/sunah123

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc