Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

Description
አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ_ለማስያዝ በ 0913744598 ላይ ይደውሉ።
#ጎተራ_ንፋስ_ስልክ_ማሞ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ ላይ ያገኙናል።
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

4 weeks ago
[#የCPD\_ሰልጠና\_ለምትፈልጉ\_በሙሉ](?q=%23%E1%8B%A8CPD_%E1%88%B0%E1%88%8D%E1%8C%A0%E1%8A%93_%E1%88%88%E1%88%9D%E1%89%B5%E1%8D%88%E1%88%8D%E1%8C%89_%E1%89%A0%E1%88%99%E1%88%89)፦

#የCPD_ሰልጠና_ለምትፈልጉ_በሙሉ

በተለያየ ምክንያት አርብን ጨምሮ ቅዳሜና እሁድ ላይ በምንሰጠው #የCPD ስልጠና መገኘት የማትችሉ የCPD ሰልጣኞች በየሳምንቱ ማክሰኞ፣ ዕሮብ እና ሀሙስ ላይ ስልጠናውን ማግኘት እንደምትችሉ እናሳውቃለን።

#የስልጠና_ፕሮግራማችን
በየሳምንቱ
1. አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ዋናው ሲሆን
2. ማክሰኞ፣ ዕሮብ እና ሀሙሰ ደግሞ በመጀመሪያ ዙር ለማይመቻቸው የተዘጋጀ ነው።
➩ስለዚህ በሳምንት ሁለት ጊዜ ባዘጋጀነው የስልጠና ፕሮግራም ላይ እንደየ ምርጫዎ መሰልጠን ይችላሉ።

COC ስልጠና የምትፈልጉ ሁሉ መመዝገብ ትችላላችሁ።
➩ COC LEVEL III
➩ COC LEVEL IV

ቀዳሚ ምርጫዎ እኛ እንደምንሆን አንጠራጠርም!!!
09 21 78 59 03
#Ethio_Medical_Training_PLC
CPD CENTER
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc

4 weeks, 1 day ago

#የማይታመን #ግን #ሀቅ #የሆነው #የሎሚ #ጭማቄና #ጤናችን #ትስስር

#ጠቃሚ#አስደሳችና #ዘለቂ #የጤና #መረጃዎችን #ከፈለጉ #አሁኑኑ #የጎደኝነት #ጥያቄ #ይላኩልን። እንቀበለዎታለን! ከሞላ follow ያድርጉን

ማሳሰቢያ፡ ይህን መረጃ ለሌሎች የማታጋሩ ከሆነ ማንበበዎን ያቁሙ። ምክናየቱም ሸር ለማድረግ ከርስዎ የሚፈለገው ቀናነት ብቻ ነው።

• ውድ የInfo Health Center ቤተሰቦች ሎሚን ውሀ ላይ ጨምሮ መጠጣት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት።

  1. በሽታ የመከላከል አቅምን በእጅጉ ይጨምራል።
  2. ፓታሽየም የሚባለውን ንጥረነገር በበቂ ይሰጣል።
  3. የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል።
  4. ሰውነትን በሙሉ ያፀዳል።
  5. ትንፈሳን ያድሳል።
  6. ቆዳን ጤናማ ያደርጋል።
  7. ክብደትን ይቀንሳል።
  8. አቅምን ይጨምራል።
  9. በቫይረስ የሚመጣ ኢንፌክሽንን ይዋጋል።
  10. ልክ እንደ ሻይና ቡና ያነቃቃል።

👇👇👇👇👇👇👇
በዝርዝር

• ሎሚ የጉሮሮን ኢንፌክሽን ከሚከላከሉ ፍራፍሬዎች መካከል አንዱ ሲሆን የፀረ ባክቴሪያ ሀይል ስላለው በሻይ መልክ መጠጣት ከፍተኛ ጥቅም ይሠጣል። ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳታችን(cells) እንዳይወድሙ ይጠብቃቸዋል፡፡ በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅም እንዲኖረን ያስችላል፡፡

• የሎሚ ጭማቂ የምግብ አለመፈጨትንና የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ አልካላይን ነው ስለሆነም በሰውነት ውሰጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል በተጨማሪም በሽታን ይከላከላል፡፡

• በምግብ ውስጥ ትንሽ ጠብታ ሎሚ ጨምሮ መጠቀም ደምን ያጣራል። ጥሩ የዕቃ ማፅጃ በመሆንም ያገለግላል።

• የሎሚ ጭማቂ በብርድ፣ በሳልና በትኩሳት ለሚሰቃዩ ሰዎች መድሀኒት ነላይ እንዲሁም ትኩሳት በሚኖር ወቅት ቶሎ ቶሎ እንዲያልበን በማድረግ ያስታግስልናል።

• የጥርስ ህመም በሚያጋጥምበት ጊዜ የሎሚ
ጭማቂ በህመሙ ቦታ ላይ በማድረግ እንደ ማስታገሻነት መጠቀም ይቻላል።

• በተፈጥሮ የሎሚ ጭማቂ ድድን ማሸት ከድድ መድማት ችግርና ከመጥፎ የአፍ ጠረን ይታደገናል።

• ከውሀ ጋር የተቀላቀለ የሎሚእንዳይኖር ጭማቂ መጠጣት ለኩላሊት ጠጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።

• ሎሚ ጭማቂ በተቃጠለው የሰውነታችን ቁስል ላይ በማድረግ ጠባሳ ለማድረግ ያስችላል።

• የሎሚ ጭማቂ ውስጣዊ መድማትን ይከላከላል ምክንያቱ ደግሞ ሎሚ ፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ቀዳዳ ስላለው ነው።

• የአፍንጫ መድማትን ለመከላከል በሎሚ ጭማቂ የተነከረ ጥጥ በአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ከተው ለትንሽ ደቂቃዎች ማቆየት ይመከራል።

• ሎሚ ደምን የማጣራት አቅም ስላለው እንደ ወባና አተት ያሉ በሽታዎችን ይከላከላል።

• ሎሚ የፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው እርጅናን፣ የቆዳ መሸብሸብና ቆዳ ላይ ያሉ ትንንሽ ጥቁር ነጠብጣቦችን ያስወግዳል።
• የፀሀይ ጨረርን ለመከላከል የሎሚ ጭማቂ ፊትን መቀባት ጠቃሚ ነው።

• የሎሚ ጭማቂ ከማርና ውሀ ጋር በመቀላቀል መጠጣት ጥርት ያለ የፊት ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል።

• የሎሚ ጭማቂ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል።
• ሎሚ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ስለሆነ የአስምና የመተንፈሻ አካላት ችግር ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው።

• የሎሚ ጭማቂ መጠጣት በውስጡ ፖታሲየም ስላለው በልብ ህመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ጠቃሚ ነው።
• ከፍተኛ ደም ግፊትን፣ ማዞርና ማቅለሽለሽን በመቆጣጠር አእምሮና ሰውነታችን ዘና እንዲል ያደርጋል።

• የሎሚ ጭማቂ የራስ ቆዳ አናትን መቀባት እንደ ፎረፎር፣ የፀጉር መነቃቀልና ከራስ ቅል ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከል ይጠቅማል። እንዲሁም ፀጉራችን አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርጋል።

• ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ ጭምር ከተን የምንጠጣ ከሆነ ደረጃ 2 የጉበት ፀረ- መርዝ ማስወገድ ተግባራን ያከናውናል፡፡ ጉበቶ ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባታማ ምግቦችን ሰውነቶ እንዲፈጭ ይረዳል፡፡ በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል፡፡

• በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን (kidney stone) ያሟሟል፡፡

• ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይዎች(gall stones) በሰውነታችን ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፡፡

• ሎሚ ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ስላላው የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ (Gout) እና የአጥንት አንጓ ብግነት (Arthritis) እንዳይጠቁ ይጠብቃቸዋል፡፡

• ሎሚ ከአንደንድ የካንስር በሽታዎችም ይከላከላል፡፡

እስኪ ሸር ያድርትና ሌሎችም ይመልከቱት!

የተሻለና ቶሎ ቶሎ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በሚቀጥለው ሊንክ ተወዳጁን የቴሌግራም ቻናላችንን join ያድርጉ።
https://t.me/jossiale2022

Telegram

Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ\_ለማስያዝ በ 0913744598 ላይ ይደውሉ። #ጎተራ\_ንፋስ\_ስልክ\_ማሞ\_ራሚ\_ህንፃ\_4ኛ\_ፎቅ\_ ላይ ያገኙናል።

[#የማይታመን](?q=%23%E1%8B%A8%E1%88%9B%E1%8B%AD%E1%89%B3%E1%88%98%E1%8A%95) [#ግን](?q=%23%E1%8C%8D%E1%8A%95) [#ሀቅ](?q=%23%E1%88%80%E1%89%85) [#የሆነው](?q=%23%E1%8B%A8%E1%88%86%E1%8A%90%E1%8B%8D) [#የሎሚ](?q=%23%E1%8B%A8%E1%88%8E%E1%88%9A) [#ጭማቄና](?q=%23%E1%8C%AD%E1%88%9B%E1%89%84%E1%8A%93) [#ጤናችን](?q=%23%E1%8C%A4%E1%8A%93%E1%89%BD%E1%8A%95) [#ትስስር](?q=%23%E1%89%B5%E1%88%B5%E1%88%B5%E1%88%AD)
1 month ago

#ተራ_የሚመስለን_ግን_በጣም_ወሳኝ_የሆኑ_ነገሮች_ብዙ_ናቸው

ከፓፓየ ፍሬ የሚገኝ የጤና ጥቅም
• ጤናማ የምግብ እንሽርሽሪት ይኖራል
• ካንሰርን መከላከል ይችላል
• ጤናማ ኩላሊት እንድኖር ያደርጋል
• ጤናማ ጉበት እንድኖር ያደርጋል
• ትኩሳትን ማስወገድ
• መርዛማ ነገሮችን ማርከስ
• የተስተካከለ የወር አበባና በወርአበባ ጊዜ የሚኖር ህመምን ያስወግዳል።
• ክብደትን ማስተካከል
• የአንጀት ባክቴሪያ ማጥፋት
• የአንጀት ትላትልን መግደል ይችላል።
#ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች በየቀኑ የፓፓየ ፍሬ ቢጠቀሙ የሚገርም የኩላሊትና የጉበት ጤንነት እንድኖር ያደርጋል።
#ፓፓየ ፍሬ በውስጡ ሜኒራልና ቫይታሚኖችን በብዛት ይዞል። ለምሳሌ ፖስፖረስ፡ ብረትና ካልሽየም በብዛት ይገኝበታል።
• ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች የፓፓየ ፍሬን በብዙ መንገድ መጠቀም ቢቻልም ለዛሬ አንዱን እንገራችሁ።
#አንድ ማንኪያ ተኩል የፓፓየ ፍሬ ላይ አንድ ራስ ነጭ ሽንኩርት ራ፡ ትንሽ ማር፡ የሩዝ ውሀ፡ የአትክልት ዘይትና ትንሽ ጨው ጨምረው መፍጨትና መጠቀም ነው።

ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903
#ከጎተራ_ከፍ_ብሎ_ማሞ_ባቡር_ጣቢያ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ቢሮ_ቁጥር_202 ያገኙናል።
1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093

2 months, 4 weeks ago
[#የCPD\_ስልጠና\_ቅዳሜ\_የካቲት\_16\_የሚጀምር](?q=%23%E1%8B%A8CPD_%E1%88%B5%E1%88%8D%E1%8C%A0%E1%8A%93_%E1%89%85%E1%8B%B3%E1%88%9C_%E1%8B%A8%E1%8A%AB%E1%89%B2%E1%89%B5_16_%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8C%80%E1%88%9D%E1%88%AD)

#የCPD_ስልጠና_ቅዳሜ_የካቲት_16_የሚጀምር

ኢትዮ ሜድካል ትሬኒንግ ሴንተር
➩ የሚጀምርበት ቀን #ቅዳሜ_የካቲት16
➩ ስልጠናው፦ #Syndromic_Management_of_Sexual_Transmitted_Diseases (STI)ነው።

➩ ለማንኛውም ጤና ባለሙያ ይሆናል።
#ክፍያ ለ15 CEU =900ብር ብቻ

👉 ቦታ ሳይሞላ ማስታወቂያውን እንዳዩ ደውለው ወይም ሙሉ ስም ቴክስት በመላክ ይመዝገብ።
0921785903 ላይ ይደውሉ። ወይም መልዕክት ያስቀምጡ!!!!
https://t.me/jossiale2022

2 months, 4 weeks ago

"ውልቃት (Dislocation)  ምንድን ነው?"

በሰውነታችን ውስጥ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ አጥንቶች የሚሰባሰቡበት ቦታ መገጣጠሚያ ተብሎ ይጠራል።

ውልቃት አንድ አጥንት ከመገጣጠሚያው ውስጥ ሲያንሸራተት (ሲወጣ) ይከሰታል። ለምሳሌ ፣ የክንድዎ አጥንት አናት በትከሻዎ ላይ ካለው መገጣጠሚያ ጋር ይጣመራል፡፡ ከዚያ መገጣጠሚያ ላይ ሲንሸራተት ወይም ብቅ ሲል ፣ የወለቀ ትከሻ አለዎት ማለት ነው ፡፡ ጉልበትዎን ፣ ዳሌዎን ፣ ቁርጭምጭሚትን ወይም ትከሻዎን ጨምሮ በሰውነትዎ ውስጥ ማንኛውም መገጣጠሚያ ሊወልቅ ይችላል፡፡

ውልቃት አለ ማለት አጥንትዎ አሁን ያለበት ቦታ ተክክለኛ ባለመሆኑ እንደ ድንገተኛ ሁኔታ ማከም እና በተቻለ ፍጥነት የሕክምና ዕርዳታ ማግኘት አለብዎት፡፡ ያልታሰበ ውልቃት በጅማቶችዎ ፣ በነርቮችዎ ወይም በደም ሥሮችዎ ላይ ጉዳት ያስከትላል ፡፡

ውልቃትን አንደት ይከሰታል?

መገጣጠሚያውን ከቦታው እንዲወጣ የሚያስገድደው ሀይል ወይም አደጋ ሲከሰት ውልቃት ይከሰታል፡፡ የመኪና አደጋ ፣ መውደቅ እና እንደ እግር ኳስ ያሉ ስፖርታዊ ግንኙነቶች የዚህ ጉዳት የተለመዱ ምክንያቶች ናቸው ፡፡

በመገጣጠሚያው ዙሪያ ያሉት ጡንቻዎች እና ጅማቶች ደካማ በሚሆኑበት ጊዜ በመደበኛ እንቅስቃሴዎች ጭምር ውልቃት ሊከሰት ይችላል። እነዚህ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ ደካማ ጡንቻዎች እና ሚዛናዊ ጉዳቶች ባሉባቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ብዙ ጊዜ ይከሰታሉ፡፡

ለውልቃት የተጋለጠው  ማን ነው?

ማንኛውም ሰው ከወደቀ ወይም ሌላ ዓይነት የውጭ ሀይል ካጋጠመው መገጣጠሚያው ሊወልቅ ይችላል። ሆኖም በዕድሜ የገፉ ሰዎች በተለይም የመንቀሳቀስ አቅማቸው ዝቅተኛ ከሆነ ወይም መውደቅን የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ ከሆነ ለውልቃት ከፍተኛ ተጋላጭነት ይኖራቸዋል፡፡

ልጆች ቁጥጥር ካልተደረገባቸው ወይም የልጆች ጥበቃ ባልተደረገበት አካባቢ የሚጫወቱ ከሆነ ልጆችም ለውልቃት የተጋለጡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአካላዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ደህንነቱ ያልተጠበቀ ባህሪን የሚያካሂዱ ሰዎች እንደ መገጣጠሚያ ውልቃት ላሉት አደጋዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎችም ለውልቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡

የውልቃት ምልክቶች ምንድ ናቸው?

የውልቃት ምልክቶች እንደ ጉዳቱ ክብደት እና ቦታ ይለያያሉ፡፡ የወለቀ መገጣጠሚያ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
 ህመም
 እብጠት
 የመገጣጠሚያ አለመረጋጋት
 መገጣጠሚያውን የማንቀሳቀስ ችሎታ ማጣት
 በሚታይ ሁኔታ የተጣመመ  መገጣጠሚያ

ውልቃት እንዴት ይመረመራል?

አጥንትዎ ተሰብሮ መሆኑን ወይም ውልቃት መከሰቱን ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በተቻለ ፍጥነት ወደ ድንገተኛ ክፍል መሄድ አለብዎት፡፡ ሐኪምዎ የተጎዳውን አካባቢ ይመረምራል፡፡ በአካባቢው ያለውን የደም ዝውውር ፣ የአካል ጉዳተኝነት እና ቆዳው የተቀደደ መሆኑን ይፈትሻል፡፡

ዶክተርዎ የተሰበረ አጥንት ወይም ውልቃት እንዳለብዎ የሚያምን ከሆነ ኤክስሬይ (X-ray) ያዝዛል፡፡ አልፎ አልፎ እንደ ኤምአርአይ (MRI) ያሉ ልዩ ምርመራዎችን ሊያደርግ ይችላል፡፡ እነዚህ የምስል መሳሪያዎች ዶክተርዎ በመገጣጠሚያው ውስጥ ወይም በአጥንት ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ በትክክል እንዲመለከት ያደርጉታል ፡፡

ውልቃት እንዴት ይታከማል?

ሕክምናው ውልቃቱ በየትኛው መገጣጠሚያዎ እንደተከሰተ እና የጉዳቱ ክብደት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ መገጣጠሚያው በተፈጥሮው ወደ መደበኛ ካልተመለሰ ሐኪሙ ከሚከተሉት ሕክምናዎች ውስጥ አንዱን አንደአስፈላጊነቱ  ሊጠቀም ይችላል-

 የተለያዩ ቴክኒኮችን በመጠቀም መገጣጠሚያወን መደ ቦታው መመለስ
 ድጋፍ ማድረግ
 መድሃኒት መስጠት
 የመልሶ ማቋቋም (Rehabilitation) ማድረግ
 ቀዶ ጥገናም አልፎ አልፎ ሊያስፈልግ ይችላል
ውልቃት በትክክል ወደ ቦታው በሚመለስበበት ጊዜ መገጣጠሚያው ብዙውን ጊዜ ወደ ነበረበት ሰራ ይመለሳል  እና በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደገና ይንቀሳቀሳል።

ቴሌግራም ገፃችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ: https://t.me/jossiale2022

Telegram

Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ\_ለማስያዝ በ 0932338485 ላይ ይደውሉ። #ጎተራ\_ንፋስ\_ስልክ\_ማሞ\_ራሚ\_ህንፃ\_4ኛ\_ፎቅ\_ ላይ ያገኙናል።

"ውልቃት (Dislocation) ምንድን ነው?"
3 months ago

✍️ #ማንኮራፋት
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#ማንኮራፋት የሚፈጠረው ላይኛው የመተንፈሻ አካሎቻችን ላይ በሚፈጠር መርገብገብ ነው።

#ምክንያቶቹ #ምን #ይሆኑ?

🔹 የአየር ማስተላለፊያ ትቦ መደፈን /አለርጂ፣ ሳይነስ፣ጉንፋን ፣ ቶንሲል በሽታ ፣አፍንጫ ውስጥ የሚበቅል ትርፍ ስጋ../
🔹 የመተንፈሻ ትቦ መጥበብ
🔹 አፍ ከፍቶ መተኛት
🔹 የሰውነት ክብደት ከመጠን በላይ መጨመር
🔹 የእንጥል ማበጥ
🔹ከፍተኛ ድካም
🔹 አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ እና ጫት መቃም
🔹 በጀርባ መተኛት
🔹 በቂ ውሃ አለመጠጣት
🔹 አንዳንድ መድሃኒቶች

#በቤት #ውስጥ #ምን #ማድረግ #አለብኝ?

🔹 በጎን በኩል መተኛት
🔹 ሲጋራ አለማጨስ እና አልኮል አለማዘውተር
🔹 ከፍያለ ትራስ መጠቀም (ትራስ አዘቅዝቀን በምንተኛበት ጊዜ የመተንፈሻ ትቦን ስለሚጫነው ለመተንፈስ እንድነቸገር እና እንድናኮራፋ ያደርገናል)
🔹 ውሃ በቀን ከ2.5 ሊትር በላይ መጠጣት (ጤናማ የሆነ የአተነፋፈስ ስርአት እንዲኖረን ያደርጋል)
🔹 የምንተኛበትን ክፍል ማፅዳት (ብዙውን ጊዜ የሽታ አለርጂ ካለ ማንኮራፋት እንዲመጣ ያደርጋል)
🔹 ውፍረት መቀነስ
🔹 ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች አለማዘውተር
🔹 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
https://t.me/jossiale2022

5 months, 1 week ago

የአንጎል እጢ:Brain Tumor

የአንጎል እጢ በእስትሮክ ምልክት ሊመጣ ይችላል።

እጢ ያበጠ ነገርን ጠቅልሎ የሚይዝ አገላለፅ ነው።አንዳንድ ግዜ የሰውነት ቅመም(Hormone )አምራች የሰውነት ክፍሎችን "እጢ/gland/" ብለን ልንጠራ እንችላለን።

አንድ የሰውነት ክፍል ከተፈጥሮ አሰራሩ ተለይቶ ማበጥ ሲጀምር እጢ ነው ይባላል።እጢ/Tumor/ ባህሪውን መሰረት በማድረግ በሁለት ይከፈላል።አመለኛ የሆነና ገር/አመለኛ ያልሆነ/።አመለኛ/Malignant/ በተለምዶ ካንሰር ተብሎ የሚጠቀሰው ነው።ለዚህ ያየበቃው እጢው ከአንድ ሰውነት ወደ ሌላ ሰውነት መዛመትና መሰራጨት እንዲሁም በሰፈሩ ባሉት የአካል ክፍሎች ላይ ወረራናጥፋት ሲለሚያደርስ ጭምር ነው።ገር የተባለው እድገቱ ቀስ ያለና የዘገመ፣ምንም አይነት የመዛመት እድል የሌለው አካባቢያዊ ጉዳቱም ቢሆን ቀለል ያለ በመሆኑ ' ገራ ገር' ሊባል ችሏል።

የአንጎል እጢ ሲባል አመለኛውምን ገራገሩንም ይወክላል።አብዛኛው የአንጎል እጢ ገራገር ምድብ ውስጥ ይካተታል።የአንጎልን እጢ ገራገርም ሆኖ ለየት የሚያደርግ ባህሪ ሊኖረው የቻለው መፈናፈኛ በሌለው ጭቅላት ውስጥ መገኘቱ ነው።እጢ ማቆሚያ የሌለው ስለሆነ እያደገ ሲመጣ እድገቱን የሚሸከም ቦታ በጭንቅላት ውስጥ ባለመኖሩ ገራገርም ሆኖ የከፋ ጉዳት ያስከትላል።የአንጎል ገራ ገር እጢን አሳሳቢ የሚያደርገው መፈናፈኛ በሌለበት ውስን ቦታ መከሰቱ ነው።

የአንጎል እጢ በሀገራችን በተለይም በህፃናትና ወጣቶች ላይ እየታየ መጥቷል።በውል መጠኑን መግለፅ ባችልም ብዙ ታካሚዎች እየገጠሙን ነው።በአለም አቀፍ ደረጃ የአንጎል እጢ በተለይ በህፃናት ላይ የደም ካንሰርን ተከትሎ የሚከሰት የጤና ችግር ነው ።

የአንጎል እጢ መንስኤ ይኖረው ይሆን?

እስካሁን የአንጎል እጢ ሙንስኤ/አጋላጭ/ ነው ተብሎ የተጠቀሰው አንድ ነገር ብቻ ነው።የጨረራ መጋለጥ ብቻ ነው እንደ ምክነያት የሚጠቀሰው።አንድ ሰው ለጨረራ ከኦቶሚክ ቦንብ ከጨረራ ህክምና ለጨረራ ተጋላጭ ሊሆን ይችላል።ከዚህ ዉጪ ይኸ ነው የሚባል አጋላጭ መንስኤ የለም።

ምልክቱ ምንድነው?
የአንጎል እጢ ምልክት የሚወሰነው እጢው በተነሳበት አንጎል ክፍል አማካኝነት ነው።እያንዳንዱ የአንጎል ክፍል የራሱ ስራ ስላለው...።ለማየት ከሚውለው የአንጎል ክፍል የተነሳ እጢ እይታ ላይ ችግር ይፈጥራል።ለመራመድ ከሚውል ላይ ከሆነ የመስነፍ ችጎር፣ለማሰብ ማገናዘብ ከሚጠቅም ላይ ከሆነ የአስተሳሰብናማገናዘብ እንከን ይታይባቸዋል።

ባጠቃላይ የአንጎል እጢ መኖርን በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያመላክቱ ምልክቶችና ባህሪያቶች መካከል የሚከተሉት ናቸው።
1) የራስ ምታት/ህመም/:-ቀጣይነት ያለው ራስ ህመም ቀን ተቀን እየጨመረ የሚሔድ እና በማስነጠስ አለያም በመሳል ግዜ የህመም መጠኑ የሚባባስ ከሆነ ምናልባት በአንጎል ውስጥ አካላዊ ችግር መኖርን (እጢንም ጨምሮ)አመላካች ሊሆን ስለሚችል መጠርጠር ይገባል።
2) ማንቀጥቀጥ(የሚጥል ህመም)፦ለመጀመሪያ ግዜ በወጣት ወይም አዋቂ ላይ የመጣል ህመም ሲከሰት ምስለ አንጎል ያስፈልጋል።የአንጎል እጢ ምልክት ሊሆን ስለሚችል መፍጠን ይጠይቃል።

3) የሰውነት መስነፍ:-- ሰውነት ቀስ እያለ መስነፍ ካመጣ አሁንም የእጢ ምልክት ሊሆን ይችላል።

4) የእይታ መቀነስ:-በብዥታ ጀምሮ የእይታ ልኬት እየቀነሰ ማምጣት:-
5) የባህሪ እና የአስተሳሰብ ለውጥ መኖር:
..
..ወዘተ!
ወደ መጨረሻ ደረጃ የደረሰ እጢ ሲሆን ተከታታይና ተደጋጋሚ ትውከት ምልክት ሆኖ ሊመጣ ይችላል።

"ሊሆን ይችላል" ማለትን የመረጥኩት ምንም አይነት ምልክት የአንጎል እጢ ብቸኛና መተማመኛ ምልክት ስላልሆነ ነው።ሁሉም ምልክቶች በተለያዩ ከእንጎልና ከአንጎል ዉጪም በሚመጣ ችግር ሊታዩ ስለሚችሉ ነው።
ልብ ይበሉ ከላይ የተዘረዘረት ምልክቶች ከታዩ ተገቢውን የህክምና ማጣራት ምርመራ ማድረግ አለብዎት።ማናቸውም ምልክቶች የአንጎልን እጢ መኖር አለመኖር አያረጋግጡም።ማረጋገጥ የሚቻለው የአንጎል ምስለ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው።ነገር ግን ምርመራ ለማድረግ አመላካች ምልክቶች መኖር አለባቸው።
አንባቢያን ይኸን መጣጥፍ ሲያነቡ ችግሩ ከኔ ላይ አለ ከሚል የፈጠነ ውሳኔ እንዳይወርኑ አደራ እላለሁ።
ጥርጣሬ ካለ ሀኪም ያማክሩ ።እራስን በራስ ህመምተኛ ማድረግ አደገኛ ህመም ነው ።የባለሙያ ምክረ ሐሳብ ይቀበሉ!!

ለቅድመ ማወቅ የሚደረግ ምርመራ የለም።ምስለ አንጎል ምርመራ የሚደረገው ቀይ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች / red flags sign/ ሲኖሩ ብቻ ነው።ለዚህ ደግሞ የህክምና ባለሙያ አካላዊ ና ቀለ መጠይቃዊ ምርመራ አድርጎ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው መታዘዝ ያለበት።ምርመራዎቹ መደረግ ያለባቸው አስገዳጅ ምልክቶች ሲታዪ ብቻ ነው።ልየታ የማድረግ ሀላፊነት የሀኪሙ ነው።

የአንጎል እጢ በእስትሮክ ሊገለጥ ይችላል።ያለ ምንም ምልክት ተጎጂዎች ለመጀመሪያ ግዜ በድንገትኛ የአንጎል ጥቃት ሊመጡ ይችላሉ።እስትሮክ ሆነው መጥተው ምርመራ ሲደረግ ምልክት ሳያሳይ የቆየ እጢ ሆኖ ይገኛል።ይኸን ቀድመን የምናቅበት መንገድ የለም።ለሁሉም ዋናው ማወቂያ የአንጎል ምስለ ምርመራ ነው።ግን ያለ አመላካች ምልክት የአንጎል እጢ ለማወቅ ተብሎ ምርመራ አይደረግም።

መከላከያ መንገድ፦
አላስፈላጊ ጨረራ ተጋላጭነትን በማስወገድ ከጨረራ ጋር ተያይዞ የሚከሰስን እጢ መከላከል ይቻላል። በአብዛኛው መንስኤው ስለማይታወቅ መከላከያ መንገድ የለምድ

ህክምናው :-
ህክምናው የሚወሰነው በእጢው ባህሪ እና በሚገኝበት ቦታ ነው።ለቀዶ ጥገና አመቺ በሆነ ቦታ ላይ ከሆነ ቀዶ ጥገና በተለይ ገራገር ለሆነው ተመራጭና ውጤታማ ነው።የጨረራ እና ፀረ-ካንሰር ህክምናም ተመራጭ የሚሆኑባቸው የእጢ አይነቶች አሉ።ጠቅለል ሲል ህክምናውን በተመለከ ተጓዳኝ ጉዳዮችን የሚፈልግ ስለሆነ ግለሰቡን መሰረት ያደረገ ሊሆን ስለሚችል ዝርዝር ጉዳዮች ከተጎጂዎች ጋር የሚያልቁ ጉዳዮች ናቸው።

የአንጎል እጢ አብዛኛው መታከም የሚችል ነው!!

ዶር መስፍን በኃይሉ፤የነርቭ ህክምና ሬዚደንት ሐኪም :ጥቁር አንበሳ
https://t.me/jossiale2022

Telegram

Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ\_ለማስያዝ በ 251921785903 እና 251711114443 ላይ ይደውሉ። #ጎተራ\_ንፋስ\_ስልክ\_ማሞ\_ራሚ\_ህንፃ\_4ኛ\_ፎቅ\_ ላይ ያገኙናል።

የአንጎል እጢ:Brain Tumor
5 months, 1 week ago
[#የCPD\_ስልጠና\_ማስታወቂያ](?q=%23%E1%8B%A8CPD_%E1%88%B5%E1%88%8D%E1%8C%A0%E1%8A%93_%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%82%E1%8B%AB)

#የCPD_ስልጠና_ማስታወቂያ

Ethio Medical Training Center

#ታህሳስ_6_ቅዳሜ ይጀምራል።

ስልጠናው ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች  የሚሆን ነው። 
ኮሩሱ፦ #Noncommunicable_Diseases_Management (NCDs) ነው።
• 15CEU የያዘ ሰርተፍኬት በአንድ ዙር ስልጠና ያገኛሉ።
#ሰልጣኞች
➯ ሀኪሞች
➯ ነርሶች
➯ ፋርማሲዎች
➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc
ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ።
0921785903
አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ

5 months, 1 week ago

"#ልጆች_የላም_ወተት_መች_ነዉ_መጀመር ያለባቸው?"
.
በስራ ገበታ ሳለን ቀላል የማይባሉ እናቶች አዉቀውም ሆነ ሳያውቁ "የጡቴ ወተት በቂ ስላልሆነ የላም ወተት ተጨማሪ ጀምሬለታለው" ብለው ሳያበቁ ቱከት ተቅማጥ ታመው ማየት የተለመደ ነገር ነው ።
.
ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው? ጤናማ የሆነ የልጅ አመጋገብ ምንድነው?
.
ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸዉ ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ ይህ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ  ልጆቹን ከተለያዩ በሽታዎች እንደ ተቅማጥ ፣ የሳምባ ምች ፣ የጀሮ ምርቀዛ ('ኢንፌክሽን') እና ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎች በመከላከል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
.
ጤናማ  የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉ ምንድናቸው?
.
- የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ዕድሜ
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ  በተወለዱ በ30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡
.
በተለምዶ በተለይ በገጠራማዉ አካባቢ እንዲሁም በከተማዎች አልፎ አለፎ ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ እንተወለዱ  ከእናት ጡት በፊት የሚሰጡ (prelactal feeding) እንደ አብሽ ፣ ቅቤ ፣ ሻይ ፣ ዉሃ በስኳር የመሳሰሉትን መስጠት ለኢንፌክሽን ስለሚያጋልጣቸዉ ጎጂ ባህላዊ ልማድ ነዉ፡፡
.
- ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ወራት ዕድሜ
.
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከየእናት ጡት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡
.
እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ (እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ (እንደ ገንፎ) በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡
.
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ (እንደ እንጀራ፣ ዳቦ፤ እንቁላል፣ ሥጋ፣ ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር  ይቻላል፡፡
.
- ከስድስት ወር ቀደመው ሌላ ነገር ቢጀምሩ ምን የጤና ችግር ይገጥማቸዋል?
👌ልጆች ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል::
👌ልጆች ለተቅማጥ በሽታ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል:: 
.
- ተጨማሪ ምግብ ከስድስት ወር አልፈው ቢጀምሩ እሳ?
👌 ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ሀይልና ንጥረ ምግቦች እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡
👌 ልጆች ለመቀጨጭና  ለተለያዩ የማእድን እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
.
ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?
.
- ህጻናትን ቶሎ የላም ወተት ማስጀመር ያለው የጤና ጉዳት
የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት   የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከአንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ ከአንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ (Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡
.
- የላም ወተት ለልጆች በቶሎ ማስጀመር የጤና ጉዳቶች
o ዝቅተኛ የአይረን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል
o ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለአንደኛው የስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል
o የህጻናት ሆድ ድርቀት
o የወተት አለርጂ
o ላክቶዝ ንጥረነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል፡፡
o ተቅማጥ የመሳሰሉትን የጤና እክሎች ያመጡባቸዋል
.
አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉት
መልካሙን ሁሉ ተመኘው

https://t.me/jossiale2022

Telegram

Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ\_ለማስያዝ በ 251921785903 እና 251711114443 ላይ ይደውሉ። #ጎተራ\_ንፋስ\_ስልክ\_ማሞ\_ራሚ\_ህንፃ\_4ኛ\_ፎቅ\_ ላይ ያገኙናል።

"[#ልጆች\_የላም\_ወተት\_መች\_ነዉ\_መጀመር](?q=%23%E1%88%8D%E1%8C%86%E1%89%BD_%E1%8B%A8%E1%88%8B%E1%88%9D_%E1%8B%88%E1%89%B0%E1%89%B5_%E1%88%98%E1%89%BD_%E1%8A%90%E1%8B%89_%E1%88%98%E1%8C%80%E1%88%98%E1%88%AD) ያለባቸው?"
5 months, 2 weeks ago
[#CPD\_ነገ\_ጧት\_ጀምሮ](?q=%23CPD_%E1%8A%90%E1%8C%88_%E1%8C%A7%E1%89%B5_%E1%8C%80%E1%88%9D%E1%88%AE)

#CPD_ነገ_ጧት_ጀምሮ

#Ethio_Medical_Training_and_Consultancy_Center
         CPD CENTER
#ቅዳሜ_ህዳር_29
#Pain_Management ይጀምራል።
• 15CEU የያዘ ሰርተፍኬት በአንድ ዙር ስልጠና ያገኛሉ።
#ሰልጣኞች
➯ ሀኪሞች
➯ ነርሶች
➯ ፋርማሲዎች
➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc
ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ።
0921785903
አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago