Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2
Twitter: x.com/hamster_kombat
YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official
Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/
Last updated 3 months, 2 weeks ago
Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market.
📱 App: @Blum
🆘 Help: @BlumSupport
ℹ️ Chat: @BlumCrypto_Chat
Last updated 3 months, 1 week ago
Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot
Collaboration - @taping_Guru
Last updated 1 week, 4 days ago
የኢትዮያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሃና አርዓያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር ሆነዉ ተሾሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቅርቡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው በተሰየሙት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ቦታ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ሆነዉ እንዲያገለግሉ ሹመት ሰጥተዋል።
የፍትሕ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ በነበሩት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ቦታ ተክተዉ እንዲሰሩ ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሃና አርዓያሥላሴ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል፡፡
በሌላ በኩል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሆነዉ በማገልገል ላይ የነበሩት ሰላማዊ ካሳ የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነዉ በዛሬው ዕለት መሾማቸው ታዉቋል።
#News | ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ2022 ሥራ ከጀመረ ወዲህ በሀገሪቱ የሞባይል ዳታ አገልግሎት ዋጋ እስከ 70 በመቶ መቀነሱን አስታዉቋል።
በዩናይትድ ኪንግደም የሚደገፍ የሞባይል ኔትወርክ ኦፕሬተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመላ አገሪቱ እጅግ በጣም ፈጣን የ4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት እንዲያገኙ መርዳቱ ነዉ የተሰማዉ።
በሌላ በኩል መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም ድግሞ በፈረንጆቹ 2018 ላይ ሰፊ የሆነ ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆን ከፍተኛ የታሪፍ ቅናሽ ማደረጉ አስታዉቆ ነበር።
ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የታሪፍ ቅናሽ አድርጎ የነበረው የደንበኞቹንና የማህበረሰቡን የመክፈል አቅም ያገናዘበ መሆን ይገባል” በሚል እንደሆነ በወቅቱ ገልፆ እንደነበር ይታወሳል።
Website | Facebook | X | TikTok | Instagram | Linkedin | Youtube
#News | አሐዱ ባንክ ያለመያዣ ብድር መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ
በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ወይም በማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ያለመያዣ ብድር ለመስጠት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታዉቋል።
ባንኩ እንዳለው የገንዘብ እንቅስቃሴ ወይም (Cash flow) መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ ይም "ማሕደር" የተባለ ቀላልና አመቺ የቴክኖሎጂ መተግበሪያን በመጠቀም ተበዳሪዎች የንብረት ዋስትና ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው ብድር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።
በዚህም ባንኩ "ከብዙዎች ለብዙዎች" የሚለውን መርሕ ተግባራዊ በማድረግ በጥቃቅን እና አነስተኛ የስራ ዘርፍ ለተሠማሩ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ያለመያዣ የብድር አገልገሎት ይሰጣል ተብሏል።
አሃዱ ባንክ አጠቃላይ ከሚሰጠው የብድር መጠን እስከ 25% የሚሆነውን ድርሻ ለዚህ ዘርፍ መመደብ የተገለፀ ሲሆን ይሀንን ተግባራዊ ለማድረግ ባንኩ ከኤስኤንቪ (SNV)፣ የኔዘርላንድ ልማት ድርጅት እና ከኬኤምዲ አፕሲስ (KMD Apsis) ጋር እንደሚሰራ አስታዉቋል ።
Website | Facebook | X | TikTok | Instagram | Linkedin | Youtube
#News ኢትዮጵያ ትልቁን የመድሃኒት አይነቶችን ፍተሻ እና ቁጥጥር የምታደርግበት የልዕቀት ማዕከል እየገነባች እንደምትገኝ ተገለፀ
በሀገሪቷ ክትባቶችን ፣ መድሃኒቶች እና አጠቃላይ የህክምና መሳሪያዎችን ለመፈተሽ ትልቅ አቅም ያለዉ የልዕቀት ማዕከል በቃሊቲ እየገነባች እንደምትገኝ ተገልጿል ።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እንዳስታወቀው ክትባቶችን ፣ መድኃኒቶችን ፣ የሕክምና መሳሪያዎችን ለመሞከር የሚያገለግል የልዕቀት ማዕከል በመገንባት መሆኑና የግንባታውን የመጀመሪያ ምዕራፍ 50% ደርሷል።
ይህ ፕሮጀክት የቁጥጥር ጉዳዮች የሥልጠና ማዕከልም እንዳለውና በውስጡም ይህን ሙያ ጠንቅቀው የሚያውቁ ለአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ባለሙያዎችን እንደሚያቀርብ ታምኖበታል።
#News ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የመድኃኒት እጥረት ችግር ውስጥ ትገኛለች ተብሏል
ሀገሪቷ አሁን ላይ ከፍሀኛ የሆነ የመድኃኒት እጥረት እንዳጋጠማት የተገለፀ ሲሆን ይህም ከቁጥጥር እና የዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ መሆኑ ተሰምቷል።
ሀገሪቱ ከ90% በላይ የሚሆነው የህክምና ምርቶችን የምታስገባው ከዉጪ ነዉ። ሆኖም ግን ቀጣይነት ያለው ተግዳሮቶች በመላ አገሪቱ የጤና አጠባበቅ አሰጣጥ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ተደጋጋሚ እጥረቶችን አስከትለዋል።
በኢትዮጵያ የሕንድ ኤምባሲ እንደገለጸው፣ ሀገሪቱ በፍላጎትም ሆነ በአቅርቦት ችግር ሳቢያ ጎልቶ የሚታየው የመድኃኒት እጥረት እያጋጠማት ነው። "ኢትዮጵያ የመድኃኒት ፍላጎት አላት፤ ነገር ግን አቅርቦቱ የሚጎድለው በተወሰኑ የቁጥጥር ጉዳዮች ምክንያት ነው" ሲሉ የኤምባሲው ተወካይ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር የህንድ ፋርማኮፖኢያን መቀበል እንደሚቻል አጽንኦት ሰጥተዋል። በህንድ ደረጃ የሚመረቱ መድኃኒቶች በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ ህብረት ደረጃዎች ከሚመረቱት ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚጠጋ ርካሽ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
"ሀገሮች ፍላጎታቸውን መሰረት አድርገው መወሰን አለባቸው። የአሜሪካን ፋርማኮፖኢያን ለመከተል ከመረጡ መድሀኒቶችን በከፍተኛ ዋጋ መግዛት አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል ።
#News የህንድ ኤምባሲ የህክምና ቪዛ መስጠት ያቆመው የሀሰተኛ መረጃዎች እየቀረቡለት በመሆኑ ነዉ ተባለ
በኢትዮጵያ የሚገኘዉ የህንድ ኤምባሲ ለዓመታት ሲሰጥ የነበረዉን የህክምና ቪዛ መስጠት ያቆመው አመልካቾች ሀሰተኛ ማስረጃ እያቀረቡ በመሆኑና ለህክምና ከሄዱ በኃላ በእዛው ወደ ሌላ ሀገር እየሄዱ በመሆኑ ነዉ ተብሏል።
ኤምባሲው በዚህ ጉዳይ በግልፅ መረጃ ያልሰጠ ቢሆንም የካፒታል ምንጮች ግን እንደተናገሩት ከቅርብ ሳምንታት በፊት የተቋረጠውን የቪዛ መስጠት አገልግሎት በጊዜያዊነት ለመጀመር እንደታሰበ አስረድተዋል።
እነዚሁ ምንጮች እንደገለፁት ከዚህ ቀደም ቪዛ አመልካቾች በቀጥታ ከኤምባሲው ጋር የሚያገናኛቸው ቢሆንም በቅርቡ ግን ይህንን በማስቀረት በኤምባሲው በህጋዊነት የተቋቋመው አንድ በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ የሚገኝ ኤጀንሲ ቢሮ በአመራሮች እንዲዘጋ ተደርጓል።
" ቪዛ ለመስጠት በሚል ምክንያት በህገወጥ የተቋቋመው በርካታ ኤጀንሲዎች አሉ ። ይሁን እንጂ በህጋዊነት የሚታወቀው እና በኤምባሲው እዉቅና የተሰጠው አንድ ብቻ ነዉ እሱም ቢሆንም በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኝ ሲሆን በወረዳ አመራሮች ባልታወቀ ምክንያት እንዲዘጋ ተደርጓል" ብለዋል።
የሕክምና ቪዛ ተቀባዩ ህክምና ለማግኘት ወደ ሀገር እንዲገባ የሚያደርግ የቪዛ አይነት ሲሆን ከመላው አለም የመጡ ብዙ ታማሚዎች ወደ ውጭ ሀገራት ህክምና ለመቀበል ይጓዛሉ።
የሕክምና ቪዛዎች አብዛኛውን ጊዜ የሕክምናውን ጊዜ ለመሸፈን ለአጭር ጊዜ ቆይታዎች ይፈቅዳሉ ይሁን እንጂ በርካታ ኢትዮጵያውያን ህንድ ለህክምና ሄደው ህክምና ከጀመሩ በኋላ ክፍያ የማይከፍሉ አሉና በዛው የሚቀሩ እንዳሉ ነዉ ለማወቅ የተቻለው ።
Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2
Twitter: x.com/hamster_kombat
YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official
Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/
Last updated 3 months, 2 weeks ago
Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market.
📱 App: @Blum
🆘 Help: @BlumSupport
ℹ️ Chat: @BlumCrypto_Chat
Last updated 3 months, 1 week ago
Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot
Collaboration - @taping_Guru
Last updated 1 week, 4 days ago