Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ቶጳዝዮን

Description
በብዕራችን ጥበብን እናነግሳለን።
የብዙ ገጣሚያን ስራዎች የሚቀርቡበት
ምርጥ ቻናል ነዉ።
@topazionnn
@topazionnn

for any comment👇👇
@ediwub
@Tirrubel
@balageru_1
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

3 days, 3 hours ago

የማያልቅ መሻት
.
.
ከደጅ ተቀምጬ፣
በምናብ ሰምጬ፣
ሰማዩን አየሁት፣
ባርምሞ ቃኘሁት።
የማያልቅ መሻት፣
የማያርግ ጸሎት፣
የማይሰምር ስዕለት።
እኛነት ተረስቶ፣
በእኔ ተተክቶ፣
ባለማወቅ ሚዛን፣
እዉቀት ተለክተን፣
ፈጣሪን ዘነጋን።
ፍቅራችን ከሰመ፣
ምሶሶዉ ዘመመ፣
ባገራችን ሰማይ፣
ጎሪጥ ስንተያይ፣
ከወንዙ ተራጭተን፣
ባንድ እንዳላደግን፣
ህሊናችን ጠቦ፣
በክፋት ተከቦ፣
ክብራችን ረከሰ፣
ድንበሩ ተጣሰ።
በአይነ ህሊና፣
ሁሉን አሰብኩና፣
የጠዋቷ ጠሀይ፣
ደምቃ የምትታይ፣
ጨለማን ረታ፣
ያለች በፈገግታ፣
ከአንጀት የሚደርስ፣
ተስፋን የምትለግስ፣
በረቂቅ ዉበቷ፣
በዕንቁ ማንነቷ፣
ከክፋት አላቃ፣
ከራሴ አስታርቃ፣
ልቤን አበራችዉ፣
ተስፋን አደለችዉ፣
በፍቅር ሞላችዉ።

በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ(@ediwub)
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn

3 days, 13 hours ago

ብሔርና ክልል -
ዘር ቀለም አልመርጥም፣
ሁሉም የሰው ልጅ ነው -
አላበላልጥም፣
በፍቅር ጎዳና 
- ካገኘኋት ጓዴን
እድሌን ልሞክር
- ልጀምር መንገዴን።
✍️𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞

@topazionnn
@topazionnn

1 week ago

መንፈሴ ሲዝል ሰላሜ ጠፍቶ፤
ልቤ ሲታወክ ዉስጤ ተረትቶ፤
ቢጨንቀኝ ጊዜ........
አጥብቄ ለመንኩ የማርያም መንገድ፤
ካለሁበት ማጥ ያሻግረኝ ዘንድ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ኤደን ታደሰ
@topazionnn
@topazionnn

1 week, 2 days ago

*🕯️ ዛሬ ተወለደች 🕯️

ክብርሽ የሚያበራ ~ በዓለሙ ሁሉ
የምስራቋ ጸሀይ ~ ቤዛዊተ ኩሉ
የአለም መድኃኒት ~ የብርሀን እናት
የአዳም ዘር መዳኛ ~ ምክንያት ድኅነት
የፍቅር አክሊል ~ የአምላክ ስጦታ
ልዩ ነሽ ማርያም ~ የፍጥረታት ደስታ
የምንሳሳልሽ ~ የነፍሳችን ሐሴት
ሰላም ለኪ እናቴ ~ የእረፍታችን ደሴት
የድኅነታችን ቀን ~ በእርሷ ተጀመረች
ተሰፋ ትምክታችን ~ ዛሬ ተወለደች

🙏ልደትሽ ልደታችን ነው🙏    ✍️𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞✍️*

@topazionnn
@topazionnn

1 week, 2 days ago

*ተወለደች እመብርሐን!
.
.
የይሁዳ ነገድ ዉዳሴ የጨረቃ ደምግባቱ፤
የሰማይ ጫፍ ቅዳሴ የሄኖክ ነፍስ ሕይወቱ፤

የአዳም መስዋዕት የጸሎቱ ማሳረጊያ፤
የሔዋን ጭንቅ ለልቅሶዋ መደምደሚያ፤

በእግዚአብሔር ተስላ በክንፋቸዉ ያዩዋት፤
እ'ታቸዉ እንድትሆን ወደዉ የጠበቋት፤
ትንቢተ ፍፃሜ የመላእክት ናፍቆት።

የናሆም መድሀኒት የፋራን ተራራ፤
ስታበራ ታየች በሊባኖስ ስፍራ፤

ንፅሕይት እም ንፁሐን፤
ቅድስት እም ቅዱሳን፤

ወደገነት ዳግም ወስዳ ልታገባን፤
መልካሟ ርግብ ተወለደች እመብርሐን።

ኤደን ታደሰ*@ediwub@topazionnn@topazionnn

1 week, 3 days ago

ገንፎ

ሀገሬስ ገንፎ ናት
በስልጣን ማንኪያቸው የሚቆራርሷት
ቂቤ ወሬያቸውን በርበሬ ስራቸው
ጨመር አርገውባት
እሷ ያዝኩት ስትል
የስጧትን ሁሉ አጣቅሰው አላውሰው
በዛ ስልጣን ማንኪያ በህብረት አብረው
ያውም ክብ ሰርተው
እንደ ጉድ ሚበሏት የሚጎራረሷት
ሀገሬ ለእነርሱ ገንፎ ብቻ እኮ ናት
@topazionnn
@topazionnn

2 weeks, 2 days ago

ምን አይነት ትህትና ~ እንደት ያለ ፍቅር
ዝቅ ሲል ታዘዘ ~ ፈጣሪ ለፍጡር

ሐዋርያትን አጥበህ ያነጻህ ከእድፍ
የነፍሴን  ቆሻሻ አጥራልኝ ከጉድፍ
                          ተጻፈ በ✍️𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞

@topazionnn
@topazionnn

2 weeks, 3 days ago

ቅዱሱን ለመስቀል ወንበደውን ፈተው
ክፉ ተማከሩ አይሁድ በአምላክ ቀንተው

ረቡዕ ምክረ አይሁድ
✍️ በ ናሆም
@topazionnn
@topazionnn

2 weeks, 6 days ago

ትኩረት

የገጣሚያንን ሞራልና ድካማቸውን እየገደለ የሚገኝ አንድ ልጅ አለ።

የሰው ግጥምን እራሴ ነኝ የፃፍኩት ማለት እና የሌሎች ገጣሚያንን ስራ በመውሰድ ስሙን ብቻ እየቀየረ የሚያጭበረብር ልጅ ተገኝቷል።

ቻናሉን እየገባችሁ REPORT በማድረግ እናዘጋዋለን👍

https://t.me/eyobzemariyam
https://t.me/eyobzemariyam

በሰው ስራ ለመክበር መጣር ነውር ነው።

4 weeks ago

ይድረስልኝ ላንቺ ቀንሽ ለጨለመ፤
ልብሽ ለሚያነባ ዉስጥሽ ለታመመ፤

የመኖርሽ ዉሉ የህይወትሽ 'ጣሙ፤
መሪር ለሆነብሽ ሳይገባሽ ትርጉሙ፤

ይድረስልኝ ላንቺ ተስፋን ለቆረጥሽዉ፤
ከራስሽ ተጣልተሸ ሞት ለተመኘሽዉ፤

ይድረስልኝ ላንቺ.........

ምን ድቅድቅ ቢዉጥሽ ፤
ምን ፅልመት ቢከብሽ፤

ሌቱም ይገፍና ደግሞ ይነጋጋል፤
አሮጌዉ ያልፍና 'ባዲስ ቀን ይተካል።
.............................................

በዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago