የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 1 month, 3 weeks ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 7 months, 4 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 9 months, 4 weeks ago
ግጥም**
የቃላት ድርደራ የፊደላት ውበት ፤
የሆሄያት ቀለም የቀለም አንድነት ፤
በትንሽ ስንኞች ባጭር መስመራት ፤
በአንድ በሁለት አልያም በሶስት ፤
በትንሽ አንጓ በጥቂት ፊደላት ፤
ግጥም የምትለው እጅግ ብዙ አላት ።
እናም ይቺ ግጥም ልብን ነቅናቂ ፤
የልብን ሀሳብም ናት አንጸባራቂ ።
ልብን የሚያሸፍት በደስታ ማዕበል ፤
እኔም ልሄድ አሰብኩ ከጥበቦች ዐለም ።
ጥበብ ተቀበይኝ እባክሽ ብያለሁ ፤
ሀሳቤን ለማቅለል አንችን መርጫለሁ ።
(ሚካኤል ታምሬ)
@topazionnn
@topazionnn
እኔማ ባተሌ ነበርኹ
ማልጄ እኳትናለሁ
በማምሻ ቀኔ እንዳይቆጨኝ፤
(ቢሆንም)
^
ዕጣዬ ጋሬጣ ሁኖ
አንድም ቀን ለድል አያጨኝ
ማልጄ እኳትናለሁ
በማምሻ ቀኔ እንዳይቆጨኝ፤
ዳገቱን ወጣሁ ቧጥጬ
መልሼ ወረድኹ በእንጥልጥል፤
(እንግዲኽ)!
^
መሰላል መስራት ቢሳነኝ
የተስፋ ገመዴን አልጥል!
.
እኔማ ባተሌ ነበርኹ
^
ያዳምን በሚያስንቅ ልፋት
የንችርፍ ላቤ ቢወጣም፤
ደም ወዜ ክትፎ ባይገዛ
የሽልንግ ባቄላ አላጣም
(ተመስገን)
^
ዕድሜዬን መቁጠር ካቆምኹኝ
በቅጡም አይታወሰኝ፤
(ብቻ ግን)
^
ካቻምና አቡሽ ተብዬ
ዘንድሮ አባባ ልሰኝ!?
.
ለካንስ መልክ ንፋስ ነው
ተጠርጎ ያልፋል ውበትም፤
(ከመኖር ቁጥር ብጓደል)
^
ዘወትር ፈገግ እላለሁ
ግማሽ ሳቅ አልችልበትም።
#ህላዌ_ተቃርኖ (ከአባሌ ማስታወሻ)
❖❖❖❖❖❖
ላተርፍ ስል - ከከሰርኩ
እፀድቅ ብዬ - ከሰረቅኩ
እጠግብ ብዬ - ከራበኝ
የተቃርኖ መንጋ - ከከበበኝ
ዛሬ ልክ ያልኩት - ነገ ካጠረኝ
እነሆ ጌታዬ ሆይ
ደሀም
ሌባም አድርገህ
በቀጣይ ነፍሴ ፍጠረኝ?!
#በረከት_ታደሰ
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn
ማናት?
.
.
ከፍጡራን በላይ ፣
ከፀሐይ የበራች፣
ደምቃ የምትታይ፣
በቀኙ የቆመች፣
ወርቅን ተጎናጽፋ፣
ምሕረት የምትለምን፣
በኵሯን ታቅፋ፣
አለም የምታድን፣
ቃላቶች ደርድረን፣
ፅፈን የማንገልፃት፣
የጣፈጠ ስሟን፣
ጠርተን የማንጠግባት፣
እዉን ይህቺ ማናት?
..................................
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn
ሞትና ህይወት
ህይወት ማለት ፤ተጓዥ ሂደት
'ምትሰጥህ ፤ነፃ ትምህርት
ሁለት ቀለም ፤ጥቁርናነጭ
ምታሲዝህ ፤አንድ አማራጭ
ብርቱ ውጊያ ፤ባለ ትግል
ከጊዜጋ ምታነሳ ፤ወይ የምትጥል
አንዴ ጣፋጭ ፤ወይ መራራ
ስትደቁስ የማትራራ
ግማሽ ባንተ ፤ግማሽ ላንተ እየሆነች
ተለዋዋጭ ሂደት፤ 'ማትሰለች
ትልቅ ሀሰት፤ ምትክድህ በአንድ እለት
ምትሞሽርህ ለቁርጥ ቀን፤ ምትድርህ ለሞት
ሞት ማለት ፤የማይፋቅ እውነት
በሰከንዶች ውስጥ ፤ከአለም መለየት
ጣዕም አልባ ፤ባዶ ስሜት
ለዱንያ ጥፋት ፤መክፈያ ሰዓት
የምድር ሩጫን ፤የጉዞ ማብቂያ
ነብስን መከተል፤ ስጋን መልቀቂያ
አንዴ ከሄዱ ፤የማይመጡበት
ነፃ መውጫ ነው፤ ከዓለም ሰንሰለት
እንዳመጣጥህ፤ ጠርቶ የሚወስድህ
አፈር 'ሚያለብስክ፤ ለራቁት ገላህ
ደባል ማይጠራ ፤ገንዘብ ወይም ሌላ
ጊዜ የማይሰጥ ፤ከመጣ ሗላ
ይዘህ ምትሄደው፤ የኖርከው ግብርህ
ክፋና መልካም ፤ያረከው ስራህ
እንዲነው እልፈት ፤ቸኳይ እንግዳ
ከተፍ የሚለው ፤ሳትሰናዳ
ወስዶ ይከትሀል፤ ከዘመን ምርጫህ
ሲኦል ወይ ገነት፤ ልክ እንደ ስራህ።
✍️የተክልዬዋ
@topazionnn
@semetnbegtm
@semetnbegtm
share&comment እንዳይረሳ?
አለ ማፍቀር
ራቅ ብለው ፤በአይን እያዩ
ስሜት በግልፅ፤ ሳያሳዩ
ከተወዳጁ ፤እያወጉ
ቀርቦ ጠረን ፤እየማጉ
በመከተል፤ እንደ ጥላ
በመገስገስ ፤ከእሱ ሗላ
ቃል እያጡ፤ ለመናገር
በዛ ሰው ፊት ፤መደናገር
በሙሉ ቀልብ ፤እያመኑ
የቅርብ እሩቅ ፤እየሆኑ
ሳይገለፅ፤ የልብ እውነት
የሰው ደስታን፤ ላለማጥፋት
ለራስ የከጀሉት ፤ሌላ እቅፍ እያዩት
በዝምታ ፤ታጥረው
ምኞትን፤ ተነጥቀው
እንዲህም፤ አለ ማፍቀር
....
ተስፋ በሌለበት፤ ተስፋ እየቀጠሉ
ለፍቅር እየኖሩ ፤እራስን እየጣሉ
ላልተሰጠ ነገር ፤ዋጋ እየከፈሉ
ማማረርን ይዘው፤ ከአምላክ ከተጣሉ
ሙሉነትን ትቶ ፤ባዶ ሆኖ ከመጥፋት
ከምድር ከሰማዩ ፤ጠልቶ ከመለየት
ለነፃዋ ህይወት ፤ደስታን ማሰንበቻ
ማጣፈጫው ቅመም ፤አለማፍቀር ብቻ።
✍️የተክልዬዋ
@topazionnn
@semetnbegtm
@semetnbegtm
❤ቢታነፅ ቢወቀር!
(በእውቀቱ ስዩም)
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰለሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል"
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር!
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ!
ለካስ...
ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!
ፋራ ነኝ
ፋራ ነሽ ይሉኛል ቀሚስ በመልበሴ፣
እኔ ግን ልክ ነኝ ከእናቴ ነው ውርሴ።
ሀጢአትን ማንገስ ዘመናዊነት ነው አሉ ፣
ህግ አፍርሶ መኖር አራዳነት ካሉ፣
አዎ እኔ ፋራ ነኝ ያሻችሁን በሉ ።
ወንድ ከሴት ጋር መለየት አቅቶን፣
#ዘመኑ #ነው #አልን #ግራ #እየተጋባን።
ዘመን ምን አደረገ ዘመን ተኮነነች፣
ሁሉም እንደልቡ ታግሳ ባኖረች።
እራሳችንን መግዛት መታዘዝ ሲያቅተን፣
እናሳብባለን ዘመን ነው እያልን።
አሁንም እላለሁ እኔ ፋራ ነኝ፣
በሱሪ ማፍርበት ቀሚስ የሚያኮራኝ፣
ዘመናዊ መሆን ከቶ የማያሻኝ፣
እውነቱን ልንገርህ አዎ እኔ ፋራ ነኝ፣
ሜካፕ የተባለው አመድ የማይነካኝ፣
የተፈጥሮ ውበቴ ፀጋዬ የበቃኝ፣
በቀሚስ ምኮራ የኢትዮጵያ ልጅ ነኝ!!!!!!!
የማያልቅ መሻት
.
.
ከደጅ ተቀምጬ፣
በምናብ ሰምጬ፣
ሰማዩን አየሁት፣
ባርምሞ ቃኘሁት።
የማያልቅ መሻት፣
የማያርግ ጸሎት፣
የማይሰምር ስዕለት።
እኛነት ተረስቶ፣
በእኔ ተተክቶ፣
ባለማወቅ ሚዛን፣
እዉቀት ተለክተን፣
ፈጣሪን ዘነጋን።
ፍቅራችን ከሰመ፣
ምሶሶዉ ዘመመ፣
ባገራችን ሰማይ፣
ጎሪጥ ስንተያይ፣
ከወንዙ ተራጭተን፣
ባንድ እንዳላደግን፣
ህሊናችን ጠቦ፣
በክፋት ተከቦ፣
ክብራችን ረከሰ፣
ድንበሩ ተጣሰ።
በአይነ ህሊና፣
ሁሉን አሰብኩና፣
የጠዋቷ ጠሀይ፣
ደምቃ የምትታይ፣
ጨለማን ረታ፣
ያለች በፈገግታ፣
ከአንጀት የሚደርስ፣
ተስፋን የምትለግስ፣
በረቂቅ ዉበቷ፣
በዕንቁ ማንነቷ፣
ከክፋት አላቃ፣
ከራሴ አስታርቃ፣
ልቤን አበራችዉ፣
ተስፋን አደለችዉ፣
በፍቅር ሞላችዉ።
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ(@ediwub)
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn
ብሔርና ክልል -
ዘር ቀለም አልመርጥም፣
ሁሉም የሰው ልጅ ነው -
አላበላልጥም፣
በፍቅር ጎዳና
- ካገኘኋት ጓዴን
እድሌን ልሞክር
- ልጀምር መንገዴን።
✍️?????
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 1 month, 3 weeks ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 7 months, 4 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 9 months, 4 weeks ago