📚የአንብብ ትውልድ📚

Description
☞ይህ ቻናል የተከፈተው የሰዎችን የማንበብ ልምድ ለማሳደግና አንባቢ የሆኑ ትውልዶችን ለመፍጠር ነው!!

✔አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች
✔ግጥሞች
✔ምክር አዘል ቁም ነገሮች
✔እንዲሁም የተለያዩ መፅሀፎች በ pdf ይቀርብበታል

አንባቢ ከሆኑ ይቀላቀሉን💝አንባቢ መሆን ብልህነት ነው💝



for any comment☞ @Anbabyan2bot
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago

1 year ago

✍️«አላህን ስናመሰግን ሁሌም ሁሉ'ም ነገር ይጨመርልናል፤ ከስጦታዎች ሁሉ ለሰው ልጅ በዱንያ ላይ ያለ የአላህ ስጦታ አላህ እርሱ ራሱ በሚወደው ነገር ላይ ደስተኝነትን መስጠቱ ነው።»

አላህ ሆይ!ይቺን የትንኝ ክንፍ የማትመዝን የሆነችውን አለም እስካለን ደስታችንን ከፊታችን ላይ አትንፈገን፤ ለሷም ተሸናፊዎች አታድርገን
‼️
?*????

1 year ago

╔═══════════╗
    የአሊሟ ሴት ገጠመኝ
╚═══════════╝

የሸይኽ ሰኢድ ኢብኑ ሙሰዪብን የዕውቀት ገበታን ያዘወትራል። በረሀውን አቆራርጦ በብርድ በቁሩ፣ በሙቀት በግለቱ አንገቱን ሰበር አድርጎ ጆሮውን ቀስሮ ከማዕዱ ይቋደሳል። አቡ ወዳአ ሲሉም ይጠሩታል።
    የጀነቱ ጨፌ ከሚቀጠፍበት ሥፍራ ለሁለት ወራት ከራቀ በኋላ ወደ ዒልም ገበታው ዳግም ተመለሰ።
    ሰላምታን ከኡስታዙ ጋር ተለዋወጠና የናፈቀውን ትምህርት መከታተል ጀመረ። ደርሱ እንዳበቃ በምን ምክንያት እንደቀረ ለምንስ ሳይናገር እንደጠፋሁ ሸይኹ ጠየቁ። ባለቤቱ ሞታበት ሀዘን ላይ መቆየቱን አብራርቶ አስረዳቸው።
  ሰው ከበዛበት ቦታ ገለል አድርገው ወሰዱትና እንዲህ በማለት ጠየቁት፦
  "አዲስ ሚስት ለማግባት አላሰብክምን?!"
"ለኔ አይነቱ የቲም ሆኖ ላደገ፣ ድሃ ሆኖ ለኖረ ልጁን የሚድር ማን አለ?! ወላሒ አሁን ከሁለት ዲርሃም ሀብትም ሆነ ንብረት የለኝም" በማለት መለሰላቸው።
"ልጄን እድርልሀለው" አሉት።
    ታላለቅ ባለስልጣናት ልጃቸውን ጠይቀው አልድርም ማለታቸውን ያውቃልና ይህን ቃል ሲሰማ ምላሱ ተኮላተፈ። ተንተባተበ።
"የችግር ህይወቴን አውቀው ልጅዎን ሊድሩኝ?" በማለት በተደናገጠና በተቆራረጠ ድምፅ ጠየቀ።
  "አዎ! ልጄን እድርልሃለው ኃይማኖቱና ሥነምግባሩ ያማረ ሰው ካገኘን ልጃችንን እንድንድር እስልምና ያዘናልና አንተ ደግሞ በሥነ ምግባርህ ትሁትን አደብ ያለህ መልካም ሰው ነህ" በማለት መለሱለት።
    ለምስክርነት የሚሆኑ ሁለት ሰዎችን ጠሩና ያለችውን ሁለት ዲርሀም መህር አድርገው ኒካሁ ታሰረ።
    ከድንጋጤና ከደስታው ብዛት የተነሳ የሚናገረውን ማወቅ ተሳነው። ከተቀመጠበት ብድግ አለ። ቀኑን ፆመኛ ስለነበር መስጂድ ገብቶ የመግሪብ ሰላት ሰገደና ወደ ቤቱ አቀና። ልጅቱን ሳያውቃትና ሳያያት መቀበሉ ገርሞት አንገቱን ነቀነቀ።
ትርክቱን ለባለታሪኩ እንተውለት
   "ቤት እንደገባሁ ፋኖሴን አብርቼ የማፈጥርበትን ዘይትና ዳቦ አቀረብኩ። አንድ ሁለት እንደጎረስኩ የቤቴ በር ተንኳኳ። "ማነው?" በማለት ከበሩ ኋላ የቆመውን ሰው ማንነት ለማጣራት ጠየቅኩ። "ሰዒድ" የሚል ምላሽ ሰማሁ። በአላህ እምላለሁ!ሰዒድ በሚል መጠሪያ የማውቃቸውን ሰዎች ሁሉ ሳስብ ኡስታዜ ሰዒድ ኢብኑ ሙሰዪብ ይሆናል ብዬ ፈፅሞ አላሰብኩም። አርባ ዓመታትን ሙሉ ቤቱ ወይም መስጂድ እንጂ ሌላ ቦታ ታይቶ አይታወቅም። አወል ሰፍ እንጂ የሰውን ጀርባ እያየ ሰግዶ አያውቅም። በሩን ከፈትኩ ከፊት ለፊቴ ኡስታዜ ቆሟል። ደነገጥኩ። "ልጁን ለኔ አይነቱ መናጢ ድሃ በመዳሩ ተፀፅቶ ሀሳቡን ሊቀይር ነው የመጣው ብዬ አሰብኩ "ያ አባ ሙሐመድ! እዚህ ድረስ በመምጣት ለምን ደከምክ ሰው ልከህ ብታስጠራኝ እመጣ ነበር" አልኩትና ወደ ቤት እንዲገባ ጋበዝኩት።
      "ዛሬ መምጣት ያለብኝ እኔ ነኝ። የመጣሁትም  ልጄ ሚስትህ ሆናለችና እሷ አባቷ ቤት ብቻዋን አንተም በቤትህ ያለ አጫዋች ስለሷ እያሰብክ ብቻህን መሆንህን ጠልቼ ይዣት መጥቻለሁ" አለና ከጎኑ ወደቆመችው መልከ መልካም እንስት ዞሮ "ልጄ ሆይ!  በአላህ ስምና ረድኤት ወደ ባልሽ ቤት ግቢ" በማለት የአባትነት ትዕዛዙን አስተላለፈ። ከሀያዕዋ የተነሳ ወደኔ ስትራመድ ቀሚሷ አደናቅፏት ልትወድቅ ተቃረበች።
    አባቷን አንኳ በስርዐት ሳልሰናበት እየተጣደፍኩ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ። ድህነቴ ስላሳፈረኝ የፋኖሱን ብርሃን አደብዝዤ ዳቦና ዘይቱን አልጋ ስር ደበቅኩት።
    የቤቴ ጣራ ላይ ወጥቼ "ሰዒድ ኢብኑል ሙሰዪብ ልጁን ዳረኝ ቤቴ ድረስም ይዞልኝ መጣ" ብዬ ከፍ ባለ ድምፅ አዋጅ አልኩ። ከጎረቤቶቼ መካከል አንዲት አሮጊት በመስኮት በኩል አንገቷን ብቅ አርጋ እንዲህ አለችን፦
"አንተ ሰው! ለመሆኑ የምትናገረውን ታውቃለህ? ሰዒድ ልጁን ድሮህ ከቶውንም ቤትህ ድረስ ይዞልህ ሊመጣ? እሷ እንኳን ላንተ ለድሃው ለታላቁ መሪ ልጅ ወሊድ ቢን አብዱልመሊክ እምቢ ተብላለች ውበቷስ ቢሆን ላንተ ለደሃውማ አትገባም"
"ግቡ ቤቴ ናት ያለችው ተመልከቷት እውነተኛነቴን ታረጋግጣላችሁ" አልኳት።
    ከአዲሷ ሚስቴ ጋር የጫጉላ ቆይታዬን ጨርሼ ወደ ቀድሞው የዕውቀት ገበታ ዒልምን ለመቋደስ ስነሳ...
"አንተ የዓይኔ ማረፊያ የቤቴ ሙሶሶ ባሌ ሆይ! አባቴ ጋር ያለው እውቀት ሁሉ እኔም ጋር አለና ቁጭ ብለህ ቅራ" በማለት በጆሮዬ ሹክ አለችኝ።
    ቁርአንን በቃልዋ የሸመደደች። የረሱልን ﷺ‎ ሐዲስ የሐፈዘች የጌታዋን ቃል አክባሪ፣ የተማረችውን ዕውቀት ተግባሪ፣ አላህን ፈሪ የባሏን ሀቅ ጠባቂ መልከ መልካምና እጅግ ቆንጆ እንስት ሆና አገኘኋት።

አጂብ ነው የአላህ ስራ!!

@@Anbabiwoch ??

1 year ago

ውድ አንባቢያን ቻናሉን የምትወዱት ከሆነ ለሌሎች በመጋበዝ ተባበሩን ባረከላሁፊኩም

ጓደኞቻችሁን አድ አርጉ?
https://t.me/Readers_group

1 year ago

ያኔ ነበር!
(ሪዛል ሁዳ)
.
.
ዝንጉነቱ አስረስቶት
በብክነት ውስጥ ሲኳትን፤
ልቡ በኩራት ተሞልታ
የበታቾቹን ሲጨቁን፤
< ከኔ በላይ ማን አለና!>
ብሎ በራሱ ስኩራራ፤
በችሎታው 'የተመካ
ለልቡ በሽታን ሲያግራራ፤
ያኔ ነበር!... መለከፉ
ነፍሱን ወደ'ሳት ሲጣራ!
:
የአደምን ልጅ በሙሉ
ሊያሳስት ቃል የተጋባ፤
ካመስጋኞች አስሰርዞ
በጥፋት እሳት ሊያስገባ፤
ከ'ሳት ሁኖ ለአፈሩ
ማጎንበሱ ውርደት መስሎት፤
መጎረሩ ያከሰረው
ያባረረው ካ'ላህ ራህመት።
የሱን ጥፋት ጠላትነት
የዘነጋው የሰው ዘሩ...
ከወዳጁ ተራ መሃል
የሸይጧኑን ስም ማስፈሩ፤
ያኔ ነበር!... ስህተቱ
ከጠላቱ 'ኩል ማበሩ፤
:
ያታክልቱን ሰዎች ታሪክ
በቁርአን የተወሳውን፤
ባንድ ለሊት ስትወድም
ጁምኣን ጠብቆ የቀራውን፤
መኩራራቱ እንዳጠፋው
እያወሳለት ሲረሳው፤
ያኔ ነበር!....ረሺነቱ
ወንጀሉ ላይ ያቆየው።
:
:
የዚችን አለም ጠፊነት
በአንድ ንፊ መውደሟ!
የበታቹ ካረጋቸው
እኩል ጀሰዱ ሲሟሟ፤
ቅዠት ከመሰለ እውነታ
ከፊት ለፊት መጋፈጡ፤
ለጥፋት እንደዳረገው
የተመካበትም ሀብቱ፤
ሚዛኑ ላይ ሳይመዘን
ሲቀር ዱንያ ለወራሹ፤
የነፍሱ ክፋይ እናትም
ሁሉም ጥለውት ሲሸሹ፤
የበታቹ ያደረገው
ሲሆን የጀነት ወራሹ፤
ልብ ብሎት በነበረ
ነፍሱን ሳይወስዳት ዙልአርሹ!
ያኔ ነበር!...
ነፍሱን ከመካብ 'ሚያግዳት
ቀኖቹ ገና ሳይመሹ።

@Anbabiwoch

1 year ago

? ኡመቱል ኢቅራዕ ተብለን
ኡመቱል internet መሆናችን
በጣም ያሳዝናል ።

1 year ago

#የመፅሀፍ_ግብዣ

ርዕስ- ሪያዱ ሷሊሒን
ፀሀፊ - ኢማም ነወዊ
ተርጓሚ - ነጃሺ አሣታሚ ድርጅት

የሶሒሕ ሀዲሶች (ትክክለኛነታቸው እርግጥ የሆኑ የነብዩ ሙሀመድ ወይም የባልደረቦቻቸው ንግግሮች) ስብስብ የሆነው የኢማም ነወዊ መፅሀፍ ሪያዱ ሷሊሒን ከቁጥር 1 - 84 ሐዲስ

? @Anbabiwoch

1 year ago
1 year ago
1 year ago

**የብልህ አባት እና ልጅ ወግ!!
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
ልጅ፦  አባዬ ከእንግዲህ በቃኝ መስጂድ ሁለተኛ አልመጣም።

አባት፦  ምን ነው ልጄ? ምን ተፈጠረ ?

ልጅ፦ መስጅድ የሚመጡ ምዕመናን ግማሹ
ስልካቸውን ይነካካሉ ግማሾቹ በሃሜት የሰውን ስም እያነሱ ያወራሉ እዚህ መምጣቱ ጥቅሙ አልታየኝም።

አባት፦ መልካም ልጄ! ከውሳኔህ በፊት አንድ ነገር ብቻ ላስቸግርህ ?

ልጅ፦ እሺ አባዬ ምንድን ነው ?



አባት፦ በብርጭቆ ውሃ ሞልተው እያቀበሉት ይሄን ውሃ ምንጣፍ ላይ ሳይንጠባጠብ አንድ ጊዜ መስጂዱን ዞረህ ተመለስ።

ልጅ፦ እሺ በማለት የብርጭቆውን ውሃ በእጁ በጥንቃቄ
በመያዝ በእርጋታ መራመድ ጀመረ።
ዙሩንም አጠናቆ ወደ አባቱ ዘንድ በመመለስ ብርጭውቆን አስረከበ ..



አባት፦ ልጄ ሆይ! ስልክ የሚነካኩ ሰዎችን ተመለከትክን ?

ልጅ፦ አልተመለከትኩም አባዬ።

አባት፦ ሰዎች የሌሎችን ስም አንስተው ሲያሙ ሰማክ ?

ልጅ፦ አልሰማሁም።

አባት፦ ለምን ?

ልጅ፦ የያዝኩት የብርጭቆ ውሃ እንዳይንጠባጠብ ብርጭቆውም ወድቆ እንይዳሰበር ሙሉ ትኩረቴን በጠቅላላ እሱ ላይ አድርጌ ስለነበር ሌሎችን አልታዘብኩም።

አባት፦ አየህ ልጄ መስጂድ ውስጥ ሙሉ ትኩረትህን ወደ ፈጣሪያችን ወደ አሏህ ካደረግክ ሰዎችን ለመታዘብ ጊዜ አይኖርህም።

[ሱበሃን አሏህ] ምንኛ ያማረ ምክር ነው..**

1 year, 1 month ago
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago