ግጥም ብቻ 📘

Description
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha

@leul_mekonnen1
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 days, 2 hours ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 1 week ago

3 weeks, 6 days ago

...........ሳቅሽ.......

ሳቅሽ  ለመተብተብ ብቻ ሚቃጣው
የሸረሪት ድር ነው  ሸማ የማይወጣው
ሳቅሽ
የተንኮል ፈገግታ  የተንኮል ወትብትብ
የዘመን ማዘሎ  ማይቆረጥ ማተብ
ሳቅሽ
የማያልቅ ፈትል  የማይጠፋ እሳት
የሳቅሽ ሚስጥር ነው እሳትን ማስነሳት

By kerim

@getem
@getem
@getem

3 weeks, 6 days ago

▪️የዛን ቀን▪️

እግሬ አስጠልቶኛል

አንቺ ካለሽበት የዛን ቀን ወስዶኛል።

አይኔን ማይበትን ጠልቻለው ከቶ

የዛን ቀን ከሰዎች ስላየሽ ለይቶ።

ጆሮዬንም ቢሆን አልወደው እኔማ

የዛን ቀን ያንችን ድምፅ መርጦ ስለሰማ።

እውነታው ግን

እግሬና አይኖቼን አልያም ጆሮዬን
         ለመጥላት አስቤ

ካለሽበት ሄዱ አዩሽ ሰሙሽ በሚል
         ምክኒያት አሳብቤ

አጥፍተዋል ብልም እውነታውን ሳስብ  
         ሀሳቤን ሰብስቤ

ለካስ ጉድ የሰራኝ አንቺን መውደዱ ነው
         የዛን ለታ ልቤ።

እናማ

የኔ ላላረግሽ ካጠገቤ ላጣሽ

ልቤ በወደደሽ ሆንኩኝ ሌላን ወቃሽ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem

3 weeks, 6 days ago

/ ለምን ጠላሻለሁ/
መቼ ተለወጥኩኝ እንደዛው ነኝ እኔ
ተለዉጧል እርሱ አይደለም እንደ ያኔ፤
እያልሽ የሌለኝን ማንነት አትስጪኝ
ከመሬት አንስተሽ ከሰው አፍ አታውጪኝ፤
ደሞስ መች ሊጨክን ልቤስ ሊደነድን
በሕይወት ሳለሁኝ ከቶ ሳልሆን በድን፤
የኔ የዋነቴን የልቤንም አይተሽ
ዛሬ ምን ሲል ታየሽ ያኔ የሄድሽው ትተሽ፤
እርግጥ ሰው ባጠፋው ፀፀቱ ባይቀርም
ወደሽኝ ቢሆን ኖሮ በኔና አንቺ አይከርም፤
ታዲያ መች እንደዛ ሆኖ ያንቺ ቀረቤታ
ፌዝ አዘል ነበረ የጥርስሽ ፈገግታ፤
ያኔ ማፍቀርን ጠግቤው መፈቀር ቢርበኝ
ያንቺ ልብ በፍቅር መች አምኖ ቀረበኝ፤
አሁን ላይ ጥያቄሽ ለይቅር ከሆነ
ጥፋት እንዳጠፋሽ ልብሽ ይህን ካመነ፤
በሰው ቂም አሊዝም ይቅር ብዬሻለሁ
ዳግም ባልወድሽም ለምን ጠላሻለሁ;
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem

2 months, 3 weeks ago

እውነት እውነት ልጁ ያምራል
ያለእንከን ይወደዳል
ሰላም ያለው እርግት ያለ
መልክ ቁመት የታደለ
በፈገግታው ገዳይ ሁሉን
ግርማሞገስ ገላጭ ቃሉን
ደሞ ጎበዝ ደሞ አስተዋይ
ቢገለውስ ይፈረዳል በ ቃየል ላይ?

ተፃፈ በ Le ለ Abel

@getem
@getem
@paappii

2 months, 3 weeks ago

ለምሠራው መልአክ
።።።።።።።።።።።።።።
ካንቺ ላይ ቆንጥሬ
የሆነች በጎነት
ከልቤ ገነት ውስጥ ባዲስ በመፍጠሬ
ቀዬው በተደሞ
ሲነጋገር ቀድሞ
ዝም እግዜርሽ ደግሞ!

ካንቺ ላይ ቀንሼ
የሆነች ፈገግታ
እርቃኗን እንዳለች ፊቴ ላይ ነስንሼ
(በሳቅ በመቆሜ)
ቀዬው በፈገግታ ሲነጋገር ቀድሞ
ፀጥ እግዜሬ ደግሞ!

ካንቺ ላይ ወስጄ
የሆነች ጨዋነት
ስድ ገላዬ ላይ እንደ ልብስ ገድግጄ
(ክብሬን በማወጄ)
ምድር በትህትና
ሲያወራ እንደገና
ዝም፣ የግዜር ፅሞና!

እንዲ እየሸረፍኩሽ
እኔና ትናንቴ ባዲስ ክብር ገነናል።
እግዜር ከፅሞናው
አንቺን ልጁን ሲያጣሽ ይናገር ይሆናል
በሚል ጅምር ተስፋ
ካንቺ እየቀነስኩኝ ወደኔ ሳከማች
አንዲት ቃል ተሰማች
"ሁሉን መውሰድ ለካ ይቀለዋል ለሟች።"

አጥቻለሁና
ባንቺ እየቀባባሁ የነተበ መልኬን
ከሞቴ ተኝተሽ ውለጂው መልአኬን።

@getem
@getem
@paappii

#Yadel Tizazu

2 months, 3 weeks ago

ዝምታ ሲደመጥ

አቤት! ጩኸቱ ዝምታ
ጆሮ ጠልዞ ናላ ሲመታ
ከወዲያ ወዲህ ሲያላጋ
በሞገዱ ቋጥኝ ሲያናጋ
ነጎድጓድ ነው ነው ዝምታ
የገዛ ራስ ጉርምርምታ
የደምን ፋፋቴ ጉዘት
የልብን ህይወታዊ ዑደት
እንደጢስ አባይ ፏፏቴ ቅኝት
ሰማይ ሰቅሎ ዶሎ አዘቅት
ያኖጋዋል ሲያዳምጡት
በሁካታ ዉስጥን ሞልቶ
በፀጥታ ነፍስ ዘርቶ
ከአፅናፍ አፅናፍ አስተጋብቶ
እንኳንማ ጆሮ ቀርቶ
ይደመጣል ባይን ገብቶ
ነጎድጓድ ነው ዝምታ
የገዛ ራስ ጉርምርምታ
እንዳፍላ ጎርፍ ይነደፋል
ሳይቀዝፍ ያጓጉዛል
ታገር አገር ያዘልላል
ማሚቶ አለዉ ይመልሳል
ነጎድጓዱ ዝምታ
የገዛ ራስ ጉርምርምታ።

@topazionnn
@getem
@getem

3 months ago

( የፍቅር ሆዳም ነኝ )

የፍቅር ሆዳም ነኝ ስሜ የማልጠግብሽ
አንቺን በምናቤ ሁልጊዜም ባስብሽ
ውብ አይኖችሽን ባይ ሆኘ ካጠገብሽ
       እኔ ግን
የፍቅር ሆዳም ነኝ አይቼ የማልጠግብሽ
የፍቅር ሆዳም ነኝ ስሜ የማልጠግብሽ

አዎ እኔማ የፍቅር ሆዳም ነኝ
አንቺን በማፍቀሬ እግዚሄር ቢኮንነኝ
አልፈራም ሲኦልን እኔ ያንቺ ደፋር ነኝ
       ለስጋዬ አድልቼ
በነብሴ የጨከኩ የፍቅር ሆዳም ነኝ

አውቃለሁ ይህ ሆዳምነት እኔን ጎድቶኛል
ውዴ ባፈቀርኩት ሁሉ ዛሬም ያስክደኛል
አዎ ይህ ሆዳምነቴ እኔን ጎድቶኛል
ባመኩት አስክዶ ከእግዚሄር አጣልቶኛል

ካለፈው የማልማር ሆኘ የሰው በድን
አዎእኔ የፍቅር ሆዳም ነኝ ተመክሬም ማልድን

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem

3 months ago

?ማነው......
    የሚታዬን እሳት
      ከሩቅ ማዶ ያስወደደን ?
           ክብሪት ስንጥር ጭሮ ፥
                ተስፍ አምስሎ የሸወደን ?
                               ማነው ?

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii

3 months ago

ጀንበር ከምድር መራቁ
ወርቅ ካፈር መደበቁ
እውነት ከልብ መወሸቁ
ሁሉ አጥፊውን በማወቁ።

ፈራኹ
አብረቀረቅን...
የእንባ ዓለም ዳር ተሳሳቅን
ከፈነዳ ኮከብ ባስን
የብርሃን ዲን ለበስን...
ተነከርን ከሳቅ ግዮን
የስንቱን ዐይን ጠርተን ይሆን?

ውርጫም ዘመን ልቤ ልኩስ
ቀዝቃዛ ዐለም ገላሽ ትኩስ
እቶን ስስቅ ፍም ስትስቂ
ቢያጠፋንስ ከብቦ ሟቂ ?

ፈራኹ...
አብረቀረቅን
ገሞራ ሳቅ ከልባችን
የሳት እራት ታዛቢያችን
ቢግተለተል በዙሪያችን
ፈራኹለት...ለፍቅራችን

ይፈጥን ይሆን መክሰሚያችን?

@getem
@getem
@paappii

By Rediet aseffa

3 months, 1 week ago

ያቺ ሴት አዳሪ
.
.
.
.
ንግግር ስትጀምር፥ ፈገግታን አክላ፥ ጥርሷን ታሳያለች፤
ስዉሩ ህመሟን፥ ከሰው ለመደበቅ፥ ሠርክ ትስቃለች፤
ህይወቷን ለማኖር፥ አማራጭን አጥታ፥ ኑሮዋ ሲከፋ፤
በኩል ተደልዞ፥ የልጅነት መልኳ፥ ወዝነቱ ጠፋ፤

ያቺ ሴት አዳሪ
.
.
.
አይዞሽ ባይን ያጣች፥ ሁሉም የሚሸሻት፥ ዘማዊት ነች ብሎ፤
ስሜቱ የነዳዉ፥ እንደ ሸቀጥ እቃ፥የሚገዛት ከፍሎ፤
ቁስሏን ልታስታግስ፥በቢራዋ ጠርሙስ፥ ራሷን ደብቃ፤
ሲጋራ ለኩሳ፥ ካፏ ስታላትም፥በእጆቿ አንቃ፤
የሚጮኸው ልቧን፥ በሙዚቃው ንዝረት፥ ዝም ልታሰኘዉ፤
የናወዘ አካሏን፥ በአስረሽ ምቺው ሰበብ፥ ልታደነዝዘዉ፤
በመጠጡ ግለት፥ ጭንቀቷን ለመርሳት፥ ሰክራ ልታጠፋዉ፤

ከሰው ስትገናኝ፥ ፈገግታን አክላ፥ ጥርሷን ታሳያለች፤
ስዉሩ ህመሟን፥ ከሰው ለመደበቅ፤ሠርክ ትስቃለች፤

ይህቺ ሴት
.
.
ከምድራዊዉ ሲኦል፥ ሀዘን ከከበበዉ፥ ከፈቃድ ባርነት፤
መዉጣትን ትሻለች፥ ከቡና ቤት አለም ፥ካለችበት ጽልመት፤
እሷም ተለዉጣ፥ ነገን ታስባለች፥ ኑሮን ለመጀመር፤
ሰርታ ልታስመልስ፥ የጠፋውን ስሟን፥ ያጣችውን ክብር፤
ጨለማውን ገፋ፥ ብርሃን መልበሷን፥ ወጥታ ለመመስከር።
@topazionnn
@getem
@getem

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 days, 2 hours ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 1 week ago