ግጥም ብቻ 📘

Description
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha

@leul_mekonnen1
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

5 hours ago

ባለቅኔ ነበርኩ
ባለኝ ሰዓት ቅኔ
ያ...ኔ!

ቅኔ ይሏት እርግብ
አፍኜ ስመግብ
ስታዜም ስሰማት
መዝሙሯን ስቀማት
ቀምቼ ሳፏጨው
የሷን እየቀዳሁ፡ አድማስ ላይ ስረጨው፤
የሰማ ታማሚ፡ መስሎት የፈለቀኝ
ወደኔ እየመጣ፡ ፈውስ ሲጠይቀኝ፤
እሷ የምትለውን፡ ስሰማ ሳቀብል
ከሷ የሚፈሰውን፡ ስቀዳ ሳፀብል
የዳነው መስካሪ፡ ታምሬን ሲነዛ
ደጄን የሚናፍቅ፡ አማኝ እየበዛ
ለፀጋ ለስሜ፡ ሲመታለት ድቤ
በድንገት አምልጣኝ፡ በረረች እርግቤ።

ሄደች ከነድምጿ፡ በስም አስቀርታኝ
ሄደች ከነፈውሷ፡ ከገድሌ ጋር ትታኝ
የምበትንላት፡ ጥሬ ቀርቶኝ ከጄ
ቢረክስም በዜማ የፀደቀው ደጄ
በፈውስ ናፋቂ፡ ሰርክ ይጨናነቃል
ምስኪን! ኪን እርግቤ
እንኳንስ መሄዷን ፡መኖሯን ማን ያውቃል?

ብቻዬን አዘልኩት፡ አግኝቶ ማጣቱን
ጸጋው የተቀማ ፡ስም ሆኖ መቅረቱን
ማቃቴን አፍኜ፡ ብቻዬን ታመምኩት
በነበር ስወደስ ፡መቻልን ቃተትኩት፥

ግን አልሆነልኝም
አልጮህ ድምፅ የለኝም
ያድናቂዬ ድቤ፡ ዜማው ይበልጠኛል
አልጠፋ እንደርግቤ ማን ክንፍ ይሰጠኛል?
ታዲያ ከዚህ ስቃይ፡ ማን ያስመልጠኛል?

እውነት!

ባለቅኔ ነበርኩ፡ ያ...ኔ!
ቅኔ ይሏት እርግብ፡ እያለች ከጎኔ
ዜማዋ ሲያደምቀኝ ትንፋሿ ሲሞቀኝ
አርፎ እንደማጣጣም፡ እየቀዳሁ ስቀኝ
ያየ ሲያጨበጭብ፡ የሰማ ሲያደንቀኝ
ስጨምቃት ተጨንቃ የምታስጨንቀኝ
አንድ እርግብ ነበረች፤
አሁን ግን የለችም!
ለጠየቀኝ ሁሉ ፡እሺ ስል በርራለች።

ልክ እንደዛ ተረት፡ የልጅ መጫወቻ

ባለቅኔ ነበርኩ፡ አሁን ግን ፍራቻ
ሁሉን ነገር ላጣው፡ የቀረኝ ስም ብቻ።

By Red-8

@getem
@getem
@paappii

6 hours ago

ጥለሺኝ እየሄድሽ
.....
መንገዷን ጨርቅ አርገው፣
ህይወቷንም ቀና፤
የምል አይነት እንከፍ,
የምል አይነት ጀዝባ ፡ አይደለውምና፦

ኋላ አደናቅፎኝ
ከፎቅ ላይ ብጥልሽ
ስለምትጎጂ፤
ከተፋታን ወዲህ
መንገዱ ያሰጋል
ተጠንቅቀሽ ሂጂ።

© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii

16 hours ago

የናፈቀኝ ነገር
ያልኖርኩበት ሃገር!
ማንም ሰው ሳያውቀኝ÷ ከዜሮ መጀመር
ጠዋት የምሰማው
የማላውቃትን ወፍ፣ አዲስ አዘማመር።

የፈለግሁት ነገር
መኖሪያ መቀየር
ልብሴንም መቀየር
ለየት ቢልልኝ
የምጠጣው ውሃ÷ የምስበው አየር።

መራመድ የሚያምረኝ
በአዲስ ጎዳና ላይ ÷ በኔ እግር የነቃ
ባገኝ አዲስ ሃሳብ
አዲስ አይነት እውነት ÷ ወይም አዲስ ቋንቋ።

ማየት የምመኘው ÷ያልራቀ ወደላይ
ሰማያዊ ሳይሆን ÷አዲስ አይነት ሰማይ
በማላውቀው ቀለም ÷ አዲስ አይነት ፀሃይ።
.
.
.
የማውቀውን ሁሉ
መተካት በመሻት
ወደማይታወቅ
ህይወቴን ብሸሻት
የማልሰለቸውን ÷ አጣሁት ፈልጌው
(ስገምት ችግሩን)
አዲሱን የሚያስረጅ ÷ እኔ ነኝ አሮጌው።

በርግጥ እንኳን ማርጀት ÷ መኖር ይለመዳል?
መሰልቸትን መቻል÷ ከናፍቆት ይከብዳል?

በማውቀው አኗኗር÷ መኖር ከከበደኝ
ወደማይታወቅ ÷ ልቤ ካሰደደኝ
እኔ የሌለሁበት ÷ ማንስ በወሰደኝ?
ወላጅ ባገኘሁኝ
በሆነ አይነት ታምር÷ ዳግም በወለደኝ??

By Haileleleul Aph

@getem
@getem
@getem

6 days, 6 hours ago

እንዲገባሽ!
(የሞገሤ ልጅ)
ከመከፋት ያልፋል፣
ሃዘኔ ሃዘን ነው ይከምራል አጭዶ፣
ላላልቅ ያነደኛል፣
ከሃሳብ ወላፈን ናፍቆት እሳት ማግዶ።

ባታውቂ ነው እንጂ..
አልመጣም ማለትሽ በናፍቆት ያስምጣል፣
ከሰመመን ዘፍቆ ከቅዠት ያሰምጣል፣
ከራስ ስጋ አጣልቶ ከመንፈሥ ያርቃል፣
ሠው ማጣትም ከብዶ ሠው ማግኘት ይጨንቃል፣
ስሜት እንደ ጥይት ድንገት ይባርቃል፣
ያልበላን ሠውነት ረሃብ ያጠረቃል፣
የእስከአሁኑ እንዲህ ነው ነገንስ ማን ያውቃል?

ህ!
ህ!
እህህ!

ደሞ ያልነገርኩሽ..
ክርሥቶሥ የኛ ሺ ለሱ አንድ እለት፣
ለኔ ስትቀሪ..
አልመጣም ማለትሽ ቀኔን አርጎት ሳምንት፣
ባልነግርሽ ነው እንጂ..
ስላላወቅሽልኝ መምጣት የምትረሺው፣
ብነግርሽ ኖሮ እማ..
ባትመጪም እንኳን ከመቅረትሽ ጀርባ ጉዳቴን ባየሺው።

ደሞ የረሳሁት..
በአንድ የቀን ጉዱ አንቺነትሽ ወርሶኝ፣
እኩል እኔን ላንቺ ለማካፈል ቆርሶኝ፤
ድሮም አንድ አጥንቴ አንቺ ዘንድ ቀርቶ፣
እሱን እንደማግኘት መከፈሌ በዝቶ፤
ወይ ይዘሽ አልያዝሽው ደጅ ጥናት ጎዳው፣
ወይ ለኔ አልሆነ ራሴን ራሴ ከዳው፤
አንቺም ለመምጣትሽ አጠረኝ ማስረጃ፣
ሁለት አድርገሽኝ ሠው መሆኔን እንጃ።

እባክሽ መውደዴን ችለሽ አታኩርፊው፣
ልቤ ቆሞ ደክሟል ራርተሽ አሳርፊው፤
የኔ ብቻ ሁኚ የኔ ብቻ አለም፣
መድከሜ ላይቋጭ ላያልቅ አይርዘም፤
የኔ ብቻ ሁኚ ካምላክሽ ቀጥሎ፣
ላንቺም ግፍ ነው ማለፍ ታማሚሽን ጥሎ፤
ስለዕመቤቴ እሩሩዋ እናት፣
ቢጤሽን መጽውቺኝ ልብሽን ልመጽወት።

ያኔ እድናለሁ፣
እጠነክራለሁ አላለቃቅስም፣
አሁን ላይ ግን ከኔ፣
ማጥፋቴ ስም ሊያሰጥ አይነቃቀስም።

ተረዳሽኝ አይደል?

አዎ ተረድተሻል።
እንጂ እማ ወዳጁን፣
ካልታመመ በቀር ማስከፋት ማን ይሻል?

አዎ ተረድተሻል!

ይበልጥ እንዲገባሽ..
ምን ከቤት ቢገፋ፣
ባልለመደው ንፋስ ሊገረፍ ቢሰጥም፣
ያበደ ውሻ እንጂ፣
ያልታመመ ውሻ የጌታውን እግር ሊጎዳ አይነክስም።

አሁን ዘልቆ ገባሽ?
አዎ ተረድተሻል!
ስለዚህ እብድ ውሻሽ ለነከሰሽ ሊክስ ጤነኛ እንዲሆን ይቅርታሽን ይሻል።

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@paappii

1 week ago

"ያ ባሏ ፈታት አሉ...ወስልታበት"
"አየህ አይደል ለክፉ ክፉ ሲያዝበት?"
"ኧረ ከሷ ውጭ ሴት አያውቅም ነበር"
"ሚስትህ ነግራኝ ባይሆን አላምንህም ነበር"

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem

1 week ago

ብቻህን
(የሞገሤ ልጅ)
ያለማንም ፍቃድ ባገኘሃት ሃገር፣
ያሰኘህን ስራ፣
ያሻህን ተናገር!

እሪ በል!
ኡኡ በል!
እሪ እሚያስብል ካለ፣
ድምጽህ ከታፈነ፣
ክብርህ ከጎደለ።

በራስህ አካሄድ፣
በሃቅህ ጎዳና፣
ሰሚ የታባቱ፣
ምን ይጠቅምህ እና!

ብቻህን ተናገር፣
ብቻህን ዝም በል,
ብቻህን አግዘህ፣
ብቻህን ተገልገል!

ስላለችህ እውነት፣
ብቻህን ተሰለፍ,
ከጓዳህ አቅራቢያ፣
ከኩሽናህ ደጅ_አፍ።

ታዲያ ሞኚ እንዳትሆን!

ጥፋት እንደሚቆም፣
ፍርድ እንደሚቀየር,
በደል እንደሚያከትም፣
ጉዳት እንደማይኖር;
አስበህ ኣትጓጓ፣
የሩቁን አትጎምጅ፣
እራስህ ስለሆንክ፣
የእራስህ ወዳጅ።
ደራሽ በማሰስህ፣
ድራሽህ ሊጠፋ፣
በማጣትህ ማግጠህ፣
ጉዳትህ ሊከፋ፤
አማረህ ላታገኝ፣
ጮኸህ ልትቀማ፣
ልብህ ቢነሳሳ፣
ለሁከት ለአድማ፤
ታግለህ ላታሸንፍ፣
ጥለህ ላትሻገር፣
ኖሮ ካላገዘህ፣
ማመልከት መናገር፤
ድካምህ ቢቀንስ፣
ሠው ከምትጣራ፣
ያለአንደበትህ፣
ልብህ ለዐምላክ ያውራ!

ደግሞስ ለምን ከፋህ?

ግዜ ካልፈቀደ፣
እንዳሻህ እንድትኖር፣
እንደተባልህ መሆን፣
ማድረግ ብትቸገር፤
ፊት የነሳህ እለት፣
ፊቱን እስኪመልስ፣
መሽቶ እስኪነጋ፣
ነገን ብትታገስ፤
በላብህ ብትበላ፣
በደምህ ብትኖር፣
ለአንተ የተባለው፣
ባልቀረብህ ነበር።

By @eyadermoges1

@getem
@getem
@getem

2 months, 3 weeks ago

።  ።  ካለሽ አለሁ።። 

አንቺ ጎኔ ካለሽ ፀሀዪ ይደምቃል፣
ፍቅርሽ ገደብ የለዉ ከፍቅርም ይልቃል።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ጨረቃ ታንሳለች፣
ዉበቷ ያንስና ታቀረቅራለች።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ሳቄ ይመነጫል፣
ምንም ሆነ ምንም ጥርስን ያስከፍታል።
ገነትን ሳላየዉ ገነቴ ነሽ ብልም፣
ገነት እንደሚያምር አልጠራጠርም።
የሚያስጠላዉ ነገር
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ ፀሀይ ትጠፋለች፣
ማማሯ ያልቅና ወዲያው ትረግፋለች።
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ የለችም ጨረቃ፣
አንቺን ለመፈለግ ገብታለች መሰለኝ ባሕር ዉስጥ ጠልቃ፣
   ሄዳለች ርቃ።
ገነት እንደሚያምር ባልጠራጠርም፣
አንቺ ሲኦል ካለሽ መምጣቴ አይቀርም።
ስለዚህ ፍቅርዬ
የትም ብትገቢ እንጦሮጦስ ገደል፣
ተዘጋጅቻለሁ መከራን ልቀበል።
ምንም ብትሆኚ ሁሌ አፈቅርሻለዉ፣
ገሀነብም ግቢ እኔ ካለሽ አለሁ።

ማትስ ትምህርት እየተማርኩ xን ስፈልግ የተፃፈ ግጥም
ቀን ማክሰኞ 08:00 ቀን
ማጀቢያ ሙዚቃ : አለምአየሁ ኤርጶ ( ባይተዋር )
ምንጭ : እሷ ( xን እየፈለገች )
ገጣሚ : እኔ ( ስፈልግ አንቺን አገኘዉ )
.
By @papiel

@getem
@getem
@getem

2 months, 3 weeks ago

የመስቀል ወፍ ቢልኳትም
መናፈቅን አታወጣው
መልስ ቶሎ እየተባለች
አክርማ ነው 'ምታመጣው

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem

2 months, 3 weeks ago

, ጥላ ነው አመልሽ

ሰማይ አንቃሮ የሚያዬው
መቼም ሳይደክመው አንገቴን
ኮከብ መቁጠሬን አልተውም
እንጨት ሰብሬ ጎጆ መስራቴን

ኖረሽ ሳትጠቅሚ ለሀገር
እኛም ሳናውቀው ሞተሽ
ተናገርሽ አሉ እጅ አውጥተሽ
ከመቃብር ላይ ዎተሽ
እሳር ቅጠል ሆኖ አንቺ እንደው ዘመድሽ
የኔ አዘን የኔ እንባ የኔ ሞት አይገድሽ
አንቺ እንደው መባከን ነው ድልሽ
አንቺ እንደው ጥላ ነው አመልሽ

ጥላ የዛፍ ጥላ የቤት ጥላ የቆጥ ጥላ
ከጨረቃ
ከኩቫኩብት ከፀሀይ ብርሃን ጋር የሚጣላ
ክፉ አመልሽ ጠዋት ታይቶ ማታ ጠፊ
ሲናገሩሽ ተሎ አኩራፊ ታዳሚሽን ገራፊ
ደጋፊና መራጭሽን ሆነሽ ገፊ
ታዲያ ለዚህ ሁሉ ወዳጅሽ ሳጠቅሚው
በምን አቅምሽ ነው
ከጥበብ ጋር ግብግብ የምትገጥሚው
ከሞትሽበት ከመቃብር ገና ዎተሽ
በጥላቻ ከፈታሻት ሚስትሽ ገና ታርቀሽ
ይልቅ ክፉ ጥላ አመልሽ
ጠልፎ እንዳይጥልሽ

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem

5 months, 3 weeks ago

ከላኩት ላይመለስ ከአፍ የወጣ ቃል
መውደዴን ነግሬያት መጥላቷን ማን ያውቃል

ትጥላኝ..... እንጃ......
ትውደደኝ...... አላውቅም
ላፌ ለከት የለኝ...የማወጣውን ቃል አልጠነቀቅም
ምን ይሉታል አሁን "እወድሻለሁኝ" ብሎ መቀባጠር
ቆይቶ ለሚጠፋ ለዛን ጊዜ ስሜት ብቻ ለሚፈጠር
"እኔም" አለች ከዘገየ ስሜት ውጥን ያለቀ 'ለት
"እወድሻለሁኝ" ባልል ምን አለበት
የነበረን ስሜት ላልመልሰው ዳግም
"እኔም" ያልሽኝ ሰዓት ከምኔ ላገግም?
ይፀፅታል የችኩል ቃል
ያሰቃያል ያለፈ 'ለት
"እወድሻለሁኝ" ባልል ምን አለበት

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago