★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago
የተለያዩ ጸሐፊዎች የሰጡት ምሥክርነት
~~~~~~~~~~~
ምሥራቃውያን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በየዓመቱ በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ቀዳሚት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መካነ መቃብር የሚወርደውን የትንሣኤውን ብርሃን “ተአምራዊው ቅዱስ እሳት" (Holy Fire) ይሉታል፡፡ የተለያዩ ተመራማሪዎች "ይኽ ቅዱስ እሳት በየዓመቱ የሚወጣው በተአምር ነው? ወይንስ ሰው ሠራሽ ነው?" በማለት ብዙ ምርምር አድርገዋል፡፡ ይኽ የተቀደሰው እሳት (የትንሣኤው መብራት) በምዕራባውያን (በሮማውያን) ዘንድ አይታወቅም። በምሥራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ግን የእግዚአብሔር ስጦታና የትንሣኤው ኃይል ምልክት ተደርጎ ይታያል፡፡
በርእሰ ጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመግነዝ ጨርቅ ላይ ታትሞ በሚታየው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልክና ይኽ የተቀደሰው እሳት ያላቸውን አንድነትና ኅብረት አረጋግጠዋል፡፡ ቅዱስ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ በዕለተ ዓርብ የገነዙበት በፍታ በ 1350 ዎቹ ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) በፈረንሳይ ውስጥ ተገኝቷል፡፡ ይኽ በመግነዙ ጨርቅ ላይ የሚታየው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልክ ብርሃናዊ ሥዕለ ገጽ አልነበረም፡፡ በመቃብሩም ላይ የሚገኘውን ድንጋይ ለማጥናት በተደረገው ጥረትም በርካታ የምርምር መሣሪያዎች በታላቅ ንዝረት መዛባት ደርሶባቸዋል፡፡ በጥናታቸው መደምደሚያም በመግነዙ ጨርቅ ላይ የሚታየው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልክና በተቀደሰው እሳት (ትንሣኤ ብርሃን) መካከል ጥብቅ ቁርኝት መኖሩንም ተናግረዋል፡፡ በመግነዙ ላይ የሚታየው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በተቀደሰው እሳት አማካኝነት የታተመ እንደ ኾነም ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡
https://www.shroud.com › pdfsPDF
The Shroud of Turin and the Holy Fire of Jerusalem - Shroud.com
ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታላቅ ፍቅር የነበራቸው የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ አባ ጽጌ ማርያም ይኽንን በተመለከተ : "ለጽጌኪ ማርያም ከመ ይጠይቅ ትእምርቶ! በድንግልና ልደቶ ወውስተ ሰማያት ዕርገቶ እመ ኢአምነ ስሚዖ እሙታን ተንሥኦቶ! ኀበ መቃብሩ ለለዓሙ ለብርሃነ ሰማይ ርደቶ ይባእ ወይርአይ ዘይነብብ ከንቶ (ማርያም ኾይ የልጅሽን በድንግልና መወለዱን፣ ከሙታን መነሣቱንና ወደ ሰማይ ማረጉን ሰምቶ የማያምንና ተአምሩን ሳይረዳ ከንቱ የሚናገር ሰው በየዓመቱ በመቃብሩ ላይ የሚወርደውን ብርሃን ገብቶ ይመልከት፡፡" በማለት እንደ ተናገሩት የትንሣኤውን ርደተ ብርሃን ለማየት፤ ዐይተው ለማመን የሚሹ ቢኖሩ ሄደው ያረጋግጡ ዘንድ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳቸው፡፡
በድምፅ ወምስል ለማየት ማስፈንጠሪያውን የጠቀሙ ፡፡
https://www.npr.org › 2020/04/18
Holy Fire Ceremony To Mark Orthodox Easter Held In Near ...
The Amazing Story of the Miracle of the Holy Fire in Jerusalem
https://ocoy.org/author/simeon/
~•••መልካም በዓል•••~
ተጻፈ:- ሚያዝያ 07/2015 ዓ/ም
©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤” ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!
••••••••••••••••••
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ ፤ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, እና Share ያድርጉ :-
~•••••••~•••••••~•••••~
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/mikiyas.danail
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063973695479
https://www.facebook.com/mikiyas24/
የቴሌግራም ቻናል
: https://t.me/brana_Book
#ተአምራዊው_የትንሣኤ_ቅዱስ_እሳት
(Holy Fire)
ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ•••• የሚለው መዝሙር እናውቀዋለን ነገር ግን ሃይማኖታዊ ታሪካዊ ዳራውን ብዙዎቻችን በቅጡ የምናውቅ አይመስለኝም!!!
The Amazing Story of the Miracle of the Holy Fire in Jerusalem
አስደናቂው የትንሣኤው ብርሃን ከጌታችን ኢየሱስ መካነ መቃብር በድንቅ ተአምር የሚወጣ የማይዳሰስ ረቂቅ፣ የማይያዝ በተለያየ ኅብረ መልክ የሚታይ አስደናቂ እሳት ነው። ይኽ ብርሃን የሚወጣው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በሕማማት ዕለተ ቀዳሚት ነው። ይኽችን ቀዳሚት ዕለት ብርሃን የሚያሰኛትም ይኽ ተአምራዊ የትንሣኤው ብርሃን (እሳት) መውረድ ነው፡፡ ይኽ ብርሃን ጨለማ የማያሸንፈው፣ በሰው እጅ ያልተፈጠረና በልማድ ከሚታወቀው እሳት የተለየ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መገለጫ ነው፡፡
The Holy Fire (Greek Ἃγιον Φῶς, "Holy Light") is described by Orthodox Christians as a miracle that occurs every year at the Church of the Holy Sepulchre in Jerusalem on Great Saturday, or Holy Saturday, the day preceding Orthodox Easter. However, many dispute the alleged miraculous descent of the Fire.
https://en.m.wikipedia.org › wiki
Holy Fire - Wikipedia
ይኽንን የትንሣኤው መገለጫ የኾነውን ብርሃን በተመለከተ የተለያዩ ጸሐፊዎች ብዙ ጽፈዋል፡፡
~~~~~~~~~~~~
በአገራችን በዐሥራ ዐራተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንዲኹም በዐሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የተጻፉ መጻሕፍት ስለ አስደናቂው የትንሣኤ ብርሃን አመጣጥ ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር፣ ዐፄ ዘርኣ ያዕቆብ በመጽሐፈ ብርሃን፤ እንዲኹም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተአምር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል፡፡
በዐሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚኖሩ አበውም ስለ ትንሣኤው ብርሃን ምሥክርነታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ስለ ትንሣኤው ብርሃን (መብራት) መውረድ የጻፉት ምሥክርነት፤
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት በሚነበበው ድርሳኑ(መጽሐፈ ምሥጢር) የትንሣኤው ብርሃን በኢትዮጵያውያን አባቶች እጅ ብቻ ይወርድ እንደ ነበር ሲናገር
እንዲኽ ብሏል ፡-
"ኢትዮጵያውያን ...ከፍጹም ልቅሶ ጋር (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ) በተቀበረበት ሥፍራ በጎልጎታ ይማልላሉ፣ ከዚያም የነበሩት ምሥክር የኾኑ አሉ፡፡ ከትንሣኤ በፊት በፋሲካ ዋዜማ ይኽችውም የሕማማት ቀዳሚት ሰንበት ናት፤ በጎልጎታ ሥፍራ የክርስቲያን ጉባኤ ይደረጋል፡፡
በየወገናቸውም መብራት ይሰቅላሉ፡፡ በመጀመሪያ የሮም ሰዎችና መልካውያን ይዞራሉ፣ ሲዞሩም ብርሃን አይገለጥም፡፡ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ፣ የሶርያና አርመንያ፣ የማሮናም ካህናት) ይዞራሉ፡፡ ከነርሱ ጋር ኢትዮጵያዊ ከሌለ በመብራቶቻቸው ውስጥ ብርሃን አይታይም፡፡ ከነርሱ ጋር ኢትዮጵያዊ ቢኖር በኢትዮጵያዊው መብራት (በሻማው ላይ) ካልኾነ በቀር ብርሃን አይቀመጥም፡፡ በዓመቱም ከሀዲዎች ወደ ሌላ ሥፍራ ቢያዘዋውሩት እንኳን የእግዚአብሔር ፊት ይከተለዋል፡፡ በርሱም ላይ የሚያበራው መብራት ይታያል። ኢትዮጵያዊ መንገደኛ በጠፋበት ጊዜ ግብጻውያን ወደ አንድ ኢትዮጵያዊ መቃብር ሄደው አጥንቶቹን አውጥተው በልብሳቸው ቋጥረው የጌታችንን መቃብር ዞረዋል፡፡
(በዚኽን ጊዜ) የመብራቱ ብርሃን በቀንዲሉ ውስጥ ታይቷል፡፡"
ዐፄ ዘርኣ ያዕቆብ በመጽሐፈ ብርሃን ስለ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት በተናገሩበት አንቀጽ ከሮም፣ ከጽርዕና ከቍስጥንጥንያ ሰዎች ያገኙትን መረጃዎች ምሥክር በማድረግ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መካነ መቃብር ላይ ለኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ታላቅ ተአምር በተመለከተ እንዲህ ይላል:-
"••••ከኋላቸውም ከማርቆስ መንበር የኾኑት የኢትዮጵያ ሰዎች ሦስት ጊዜ ይዞራሉ፡፡ በዚኽን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ይወርዳል፤ ለኹሉም ይታያል፡፡ ከዚያም የጌታችን መቃብር በሚገኝበት የጣራ መስኮት ይገባል፡፡ በዚኽ ጊዜ መዓዛው እጅግ ያማረ ሽታ ያውጣል፡፡
ከማርቆስ መንበር በኾኑትና ሃይማኖታቸው በቀና ደጋግ የኢትዮጵያ ሰዎች ላይ ብርሃን ይወርዳል፡፡ ይኽ ለኢትዮጵያ ሰዎች የሚወርደው ብርሃን ክርስቲያኖች በሰውነታቸው ላይ በሚያደርጉት ጊዜ ለአንድ ሰዓት ያኽል አያቃጥልም፡፡ ይኽ ነገር ሐሰት አይደለም፤ እውነትና የተረጋገጠ ነው እንጂ••••" መጽሐፈ ብርሃን
የበዐለ ትንሣኤ ብርሃን (መብራት)
አወጣጥ ሥርዐት በኢትዮጵያውያን አበው መሪነት
~~~~~~~~~~~~
በኢየሩሳሌም እስከ ዐሥራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ፲፮፻፶፬ ዓ.ም) ድረስ ለኹሉም አብያተ ክርስቲያናት የትንሣኤ ብርሃን የሚወጣው በኢትዮጵያውያን አባቶች እንደ ነበር ጽፈዋል፡፡
ብርሃን በሚወጣበት ቅዳሜ ዕለት በሚሰበሰቡበት ከኹሉ አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብሮ ወደ ነበረበት የመቃብር ቦታ ነጭ ልብስ ለብሶ የሚገባው የኢትዮጵያው መምህር ነበር፡፡ በዚኽን ዕለት ጳጳሳቱና መነኰሳቱ በአንድነት ወደ መካነ መቃብሩ ሲሄዱ ከፊት ለፊት የሚሄደው ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የሚላከው ኢትዮጵያዊ አባት ነበር፡፡ ይኽ አባት ይኽንን የትንሣኤውን ብርሃን ለማውጣት ብቻ ከኢትዮጵያ የሚመጣ ነበር፡፡
የሌሎች አብያተ ክርስቲያናት መምህራን የሮም፣ የአርመን፣ የኩርጅ፣ የሶርያና የቅብጥ አብያተ ክርስቲያናት መምህራን በተቀመጠላቸው ቅደም ተከተል መሠረት ከርሱ በኋላ ወደ መካነ መቃብሩ ይገባሉ፤ ብርሃን በሚወጣበት ቅዳሜ በአንድነት ጧፍ አብርተው ከመካነ መቃብሩ ይወጣሉ፡፡
የትንሣኤውን መብራት ለማብራት ይኽ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምህር ነጭ ልብስ ለብሶ፣ ዘይት የተመላበት ያልተቃጠለ ፈትል ያለበት የብርጭቆ ቀንዲል ይዞ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መካነ መቃብር ይገባል፡፡ ወደ መካነ መቃብሩ ገብቶ መዝጊያውን ዘግቶ ይቆማል፡፡ የሌሎችአብያተ ክርስቲያናት መምህራን ደግሞ ከሕዝባቸው ጋር ጧፍ ይዘው ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ (ትንሣኤኽን ለምናምን ለእኛ፣ ብርሃን ላክልን ወደ እኛ፡፡)" በማለት እየዘመሩ በደጁ ላይ ይጠብቁታል፡፡ ይኽ በመቃብሩ ሥፍራ ያለው የኢትዮጵያ መምህር ብርሃን ከወጣለት በኋላ ሌሎቹ ገብተው መካነ መቃብሩን እንዲሳለሙ መዝጊያውን ያንኳኳል፡፡ ከዚኽ በኋላ ኹሉም መምህራን በኢትዮጵያዊው መምህር ከተያዘው የትንሣኤ መብራት በእጃቸው የያዙትን ጧፍ በፍጥነት በማብራት ወደ ራሳቸው አብያተ መቃድስ ቤተ መቅደሶች) ሄደው ብርሃነ ትንሣኤውን ያከብራሉ፡፡
ስለ ትንሣኤው ብርሃን መውረድ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማክሰኞ ዕለት ትምህርቱ ጸሐፍት ፈሪሳውያንን ዝም ስላሰኛቸው ሌሊቱን ርሱን ለመግደል ሲመክሩና ሲያሴሩ ቆይተው በዕለተ ረቡዕ ምክራቸውን በአንድ ኀሳብ ቋጭተዋል፡ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት መድኅን
ክርስቶስን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የዠመሩበት ቀን በመኾኑ "የምክር ዕለት ይባላል፡፡ ይኸውም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፮ ከቍጥር ፩ እስከ ፭ እንደ ተጻፈ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ግቢ ተሰባስበው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ለመያዝ የመከሩበት ዕለት በመኾኑ የተሰጠ ስያሜ ነው። እንዲሁም ዕለተ ኢዮብ፣ የመልካም መዓዛ ቀን በመባል ይታወቃል።
ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን!!!
እኛንም በቸርነቱ ይማረን !!!
አምላክ ከሰሙነ ሕማማት ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን!
ተጻፈ:- ሚያዝያ 03/2015 ዓ/ም
©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤” ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!
••••••••••••••••••
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ ፤ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, እና Share ያድርጉ :-
~•••••••~•••••••~•••••~
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/mikiyas.danail
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063973695479
https://www.facebook.com/mikiyas24/
የቴሌግራም ቻናል
: https://t.me/brana_Book
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago