✨Premium emoji №1✨
Feedback - @ukngs
Last updated 1 year, 3 months ago
Wallpaper 4K 3D + Pc ✣ Themes Telegram
.
⭕ › ᴛʜᴇ ʙᴇꜱᴛ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴛʜᴇᴍᴇꜱ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ
⭕ › ᴛʜᴇ ʙᴇꜱᴛ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴡᴀʟʟᴘᴀᴘᴇʀ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ
.
?️ • @lEO_adminTel | admin • ⛑️
Last updated 3 months, 1 week ago
«احسان حیدری»
??
.
inst?️: ehsanheydar1 (+169k)
Last updated 1 week, 5 days ago
በዚ ጊዜ ስራ በ Telegram ሆኗል⭐️
ይህንን በማስመልከት ለመግዛት አስቸጋሪ የሆነዉን Telegram account✅
-በርካሽ ወጋ❤
-በፍጥነት⭐️
-በታማኝነት✅️
አቅርበንሎታል⭐️
ለማንኛውም ስራ መጠቀም ትችላላችሁ ?
-Member add ለማረግ
-ለ Promotion
Account spam ከተባለበቹ(limit)
-እንደ 2nd account ለመጠቀም
እና ብዙ ብዙ ስራዎችን ለመስራት
accountኦቹ Fresh እና ምንም ያልተሰራባቸዉ ናቸዉ?
100% safe?
So እጃችን ላይ ያሉት አካዉንቶች
?ሳያልቁ ? ያናግሩን
@menetser21 ⭐️@miker_mike ⭐️⭐️
┉┉✽»?✿? ✽┉✽»?✿?»✽┉┉┉
?♂️?♀️✏️.....ሞክሼዎቹ ✏️...?♂️?♀️
┉┉✽»?✿? ✽┉✽»?✿?»✽┉┉┉
ተከታታይ ልብ ወለድ ፡፡
ዛሬ ምሽት 12:00 ላይ ክፍል 1 እንዲውም #ክፍል2 2:00 ይዘን እንመጣለን!!!
✍️@menetser21 ✍️
ለፈገግታ! ?***
ስትወድቅ እኔ አለው!
ማን?
መሬት።
ደህና ዋሉ!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! ?***
?ᵀᴴᴬᴺᴷ ᵞᴼᵁ ᶠᴼᴿᴰ ᴶᴼᴵᴺᴵᴺᴳ ᵁˢ ²‑²⁰¹⁶ ***አባባሎች
➩ እርጅና በአንድ ቀን አልመጣም
➤ አፍሪካውያን
➩ ተጠማሁ ከምትል የውሃ ጉድጓድ ቆፍር ። ➤ ላቲኖች
➩ ፍየሉን ትከሻው ላይ እንዲሆን የፈቀደ
ብዙም ሳይቆይ ላሚቷን ለመሸከም ይገደዳል። ➤ ጣልያኖች
➩ እግዚአብሔር በማለዳ ለሚነሱት ይሰጣቸዋል። ➤ ሩስያውያን
➩ ለታታላቆች ክብር የሚሰጥ ሰው ለራሱ ታላቅነት መንገድ ይጠርጋል።
➤ ቻይናውያን
? ፍቅር ....
? ተራሮችን ልገፋልሽ ባልችልም አብረን መውጣት አያቅተንም።
?♂... አንተ እሷን ታልማለህ ግን ስምህን እንኳን ረስታዋለች ። ?
?... በነገራችን ላይ አንቺ የሰጠሽኝን ፈገግታ እስካሁን ለብሼዋለሁ።
መረጃዎች
?...የኖቤል ተሸላሚዎች ውድ የሆነ ሽልማት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ $1 ሚሊየን ዶላር ይበረከትላቸዋል።
?.. አይብ አደንዛዥ ዕዝ የሚያጠቃውን የአምሮ ክፍል በተመሳሳይ ያጠቃል።
???.. ከ90% በላይ ምርጥ ጓደኛ(best friends) እንሆናለን ያሉ ሰዎች ጓደኛ እንኳን መሆን አይችሉም።
?? ከራሳቸው ጋር የሚያወሩ ሰዎች ከፍ ያለ IQ እንዳላቸው ይታመናል።
ይህን ሰምተሽ ደግሞ በየመንገዱ እየለፈለፍሽ ሂጂ አሉሽ ?
ለፈገግታ ...
? ሚስቴ አስቀይማኝ ከሄደች በኋላ
ተመልሳ ይቅርታ ስትጠይቀኝ .. ስሟን SAT ብዬ ቀየርኩላት ??
?#ሙዲ:- አሌ ሚስትህን አበድረኝ??#አሌ:- መቼ ትመልስልኛለህ#ሙዲ:- ለክረምት ብቻ ከዛ እመልስልሀለው#አሌ:- እሺ ውሰዳት?? ኢትዮጺያዊነት መልካምነት JTV ኢትዮጺያ???
በመጨረሻም ....#የመኪና_በር? ከፍቶ የሚያስገባኝ ባል ነው የምፈልገው ያለችው ልጅ
ከወያላ ወለደች አሉ ??***
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲ ? ?
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ
✦ @DBC_TUBE
የቀጠለ .....
አዘናግቼ፣ ቀን ጠብቄ ነበር እኮ ያባረርኳት! ሳትፈልግ፣ በእልህ ነው የገባችበት እንዳልል፣ እኔ እንዳውቅና እንድቀና ብላ እንኳን በበሬ ይዛው አልፋ አታውቅም፡፡ንቃኝ ነው እንዳልል፣ ንዝንዟ የቅናት ውጤት ነበር፡፡ ወይ እሱ አፍሮ፤
የድብቅ ይሁን ብሎ አስማምቷት ይሆናል፡፡ ታዲያ ስልኳን ለምን አነሳው? ስብሰከሰክ ቆየሁ፡፡ አውጥቼ ብጥላትም፤ እንዲህ በአንዴ አንስቶ
ከጉያው የሚሽጣት ይኖራል ብዬ አልጠበቅሁም ነበር፡፡ ሰው እንዴት
ሰው የጣለውን እያየ፤ ‹ለምን ጣላት?› የሚለውን እራሱን ሳይጠይቅ ያነሳል? ከበሮ በሰው እጅ ሲያዩት ያምር፤ ሲይዙት ያደናግር ሲባል ያልሰማ መሆን አለበት፡፡ ነገ ንዝንዟ አውጥቶ
እንዲወረውራት ሲያደርገው፤ የኔ ችግር ምን እንደነበር ይገባዋል፡፡
ንዝንዟ ሲያነስረው፣ ያን የምወደውን ሰውነቷንና ‹ሰውነቷ› እያለ የሚያላዝነውን ሬዲዮን አውጥቼ ለምን እንደሠበርኩ ይገባዋል፡፡ አመሻሽ ላይ ደወለችልኝ፡፡ ቁጥሯ እንጂ ደዋይዋ እሷ ባትሆን ብዬ
ማንሳቱን ፈርቼ ቆየሁ፡፡ ደግሞ ቁጥሯን ‹ላቭ› ብዬ ‹ሴቭ› እንዳደረግሁት ነው፡፡ እንዴት እስካሁን አላጠፋሁትም? እረስቻት ነው ወይስ እረፍት ላይ ስለነበርኩ? ወደ መዘጋቱ ሲደርስ እንደ ምንም ጉልበት አሰባስቤ ስልኩን አነሳሁት፡፡ ለምን አርፌ እንደማልቀመጥና
እንደምጨቀጭቃት ጠየቀችኝ። ከዛ ፍቅር እንዳለብኝና ልረሳት እንዳልቻልኩ፣ በኔ ቦታ ሆና መለሰች፡፡ ካሁን በኋላ ብረሳት እንደሚሻላትና የራሴን ህይወት ብጀምር እንደሚበጀኝ መከረችኝ።
በመጨረሻም ይሄን ቁጥር ለታናሽ ወንድሟ እንደሰጠችውና አዲስ
ቁጥር እንደያዘች፤ ወንድሟን ከአሁን በኋላ እየደወልኩ እንዳላስቸግረው አስጠነቀቀችኝ፡፡ ቅድም ስደውል ያነሳው ታናሽ ወንድሟ እንደሆነ ድምጹ መጣልኝ፡፡ በንዝንዘ ምክንያት የፈታኋት ሚስቴ፤ ተንቀልቅዬ በመደወሌ
ትነዘንዘኝ ጀመር። ለደቂቃዎች በጥሞና ስሰማት ከቆየሁ በኋላ፣ ቀን አስቤዛዎቹ ላይ እንዳደረግሁት፤ የምትለውን መስማት ትቼ ስልክ በያዘው ጆሮዬ አፍጥጬባት፣ ጉድለቴ እሷ እንደሆነች መመዘን ጀምርኩ፡፡ ለደቂቃዎች በጆሮዬ ባፈጥባትም ምንም የሞላ ነገር ሳጣ፤ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘግቼ ተቀመጥኩ፡፡
ስልኩን ጆሮዋ ላይ ከዘጋሁ በኋላ በአስር ደቂቃ ውስጥ አስር ጊዜ ደጋግማ ደወለች፡፡ እንዳላየ ዝም አልኳት። የጽሑፍ መልዕክት ላከች፡፡ ሳላነብ አጠፋሁት። ሌላ የጽሑፍ መልዕክት ለመጻፍ በሹል
ጥፍሯ የስልኳን ‹ስክሪን›፣ በእልህ ስትጠቀጥቀው ይሰማኛል፡፡ ጥፍሮቿ የሚነጥሩበት የእስክሪኑ ሜዳ የሚያወጣቸው የተለያዩ ድምጾች፣ እየጻፈች ያለችው ስድብና እርግማን እንደሆነ ነገረኝ፡፡ ስልኬን አጥፍቼ ትውት!
ይህቺን አለብላቢት ከሰውነቷ በተጨማሪ ምኗን ነበር የወደድኩት? ድጋሚ ሰውነቷን? ከእሱ በተጨማሪ አጠገቤ በመሆኗ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ከእሷ ጋር ማውራቱና መሣሣቁም ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ከእነ ባለቤትዎ ብለው በሚጠይቁ ግብዣዎች ላይ አብራኝ ስትገኝም ደስ
ይለኝ ነበር፡፡ ሲከፋኝና ስደሰት፣ ስሜቴን የምትጋራልኝ የኔ ሰው መሆኗን ሳስብም ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ምናልባት በእሷ ደስተኛ የነበርኩ ባይሆንም፣ በነበረው የፍቅር ግንኙነት ደስተኛ ነበርኩ ማለት ነው። ያ
ነው እንዴ የጎደለኝ? ይሄን ጥያቄ ስጠይቅ አንጀቴ መልሱን እንደደረስኩበት በመርገብገብ አሳወቀኝ፡፡ በዚያች ቅጽበት ትንሽ ቀለል ሲለኝ ተሰማኝ፡፡ አዎ እሷ ሳትሆን “የኔ የምለው ሰው” ነው የጎደለኝ - ዩሬካ!
ድንገት የቤቴ መዝጊያ በኃይል ተንኳኳ፡፡ መዝጊያዬ ያወጣው ድምጽ ቅድም የፈታኋት ሚስቴ፣ ጥፍሮቿ የሞባይሏን ስክሪን ሲቀጠቅጡ፣ ስክሪኑ ካወጣቸው ድምጾች ጋር ተመሳሳይነት ነበረው። ቀጭንና ወፍራም ቢሆኑም ቅሉ፡፡ እንደገና በኃይል በሬን አንገጫገጨችው።
ሲያሾፍብኝ የነበረው በር እንዲህ በመደብደቡ ደስ ቢለኝም፣ ከዛሬ
ምሽት ጀምሮ ለሳምንት ያህል የሰፈሩ የቡና ወሬ ማዳመቅያ እንደምሆን አልጠፋኝም፡፡
?........ተፈፀመ.......?****
?የᴅʙᴄ ᴛᴜʙᴇ ᴇᴛʜɪᴏᴘɪᴀየዘውትር ዝግጅቶች*?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*
`?ቀን ? 2:00?*** ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ !
?አንጀት አርስ አባባሎች ገራሚ ቀልድች ?`*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*ቀን *? *6:30 ➠ ? የተመረጠ ምርጥ ግጥም?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*?*ምሽት *?*12:00 ?ልብወለድ ?*
?*ምሽት *?*2:00?ልብወለድ ቀጣዩ ክፍል ?*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*? በተጨማሪም ቻናላችን ይቀላቀሉ?*?*?**
?ᵀᴴᴬᴺᴷ ᵞᴼᵁ ᶠᴼᴿᴰ ᴶᴼᴵᴺᴵᴺᴳ ᵁˢ ²‑²⁰¹⁶
<<የኔ የምለው ሰው>>
ከቃል ኪዳን ..... ✍**
?... የመጨረሻ ክፍል ...?
መስኮቴ ይሄኔ በሣቅ ይንክተከታል፡፡ ቆይ መልሱ ሣቅ ነው እንዴ? በሩና መስኮቱ
እስኪሰነጠቁ ወይ ስንጥቃቸው እስኪሰፋ አብረው ይስቃሉ፡፡ ሁለቱንም በተራ በተራ እመለከታቸዋለሁ፡፡ የበሩ ሣቅ ያስጠላኛል። መስኮቱ ድምጹ ብቻ ስለሚሰማ ያን ያህል የሚያናድድ አልነበረም። አንድ ቀን እንደ ብርድ ልብስ የወፈረ መጋረጃ ገዝቼ በሩንም፤ እግረ
መንገዴን የተፈረፈረው ግድግዳንም ሸፈንኩት፡፡ በሩ አኮረፈ፡፡ ወደ ጆሮው ጠጋ ብዬ፤ ‹‹ይኸውልህ አደብ ካልገዛህ ገና ነቅዬ አውጥቼ እወረውርሃለሁ፡፡
በየመንገዱ የሚሸጡት ንቃይ በርና መስኮቶች ከየት የመጡ መሰለህ? እንዳንተ የሚያስቸግሩት ናቸው፡፡››
መስኮቱ ይሄን ሲሰማ ከመሸማቀቁ የተነሳ፤ የሆነ አካሉ ቋ ብሎ ሲሰበር ተሰማኝ፡፡ እሱም ላይ በዛቻ ጣቴን አወዛውዤበት ተቀመጥኩኝ፡፡
ጉድለቴ ምን እንደሆነ ማወቅ ብፈልግም፤ ‹ምንድን ነው ጉድለቴ?› ብዬ ከመጨነቄ ውጪ እራሴን ‹ምንድነው ግን ጉድለትህ?› ብዬ መጠየቅ እፈራለሁ። ምናልባት ውስጤ ከራሴ እንኳን ሸሽጌ
የደበቅሁት ነገር ሳይኖር አይቀርም፡፡ ወይ ደግሞ ድንገት በሽታዬ መድኃኒት የሌለው እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡ መድኃኒት ከሌለው፣ በሽታውን ማወቁ በምን እንደሚሞቱ ከማወቅ በዘለለ ምንድን ነው ጥቅሙ? ችግሩ ለመሙላትም ሆነ እየጎደሉ ለማለቅ አንድ ሰው ጉድለቱን ማወቅ አለበት፡፡
ቆይ፣ ቆይ ሚስቴ መሄዷ ይሆን እንዴ ያጎደለኝ? እሱ ያጎድላል እንዴ?
እሷ በመሄዷ ምንድን ነው የቀረብኝ? እንደውም ከንዝንዟ ተገላገልኩ እንጂ! ግን ይሄን እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?
የማጀቴ ጉድለት ካጎደለኝ ብዬ ለማረጋገጥ አስቤዛዬን ከገዛሁ፤ እሷ
እንዳጎደለች ለማወቅ እሷን ማናገር አለብኝ ማለት ነው፡፡ ወደ እሷ ጋር የምደውልበት ምክንያት ሳፈላልግ ጸሐይ አዘቀዘቀች፡፡ ዝም ብዬ ብደውልላት ናፍቅያት ሊመስላት ይችላል፡፡ ነይና ሻሽሽን ውሰጂ ልበላት እንዴ? ሻሿን እስካሁን ከእጄ ላይ እንደጠመጠምኩት ነው። ያለችውን ትበል ብዬ ደወልኩ፡፡ ወንድ ልጅ አነሳው። እየተንተባተብኩ እንዳለች ጠየቅሁት። ሳይንተባተብ
እንደሌለችና ስትመጣ መልዕክት ሊነግርልኝ እንደሚችል ነገረኝ፡፡
እኔ ቅሌታሙና ወራዳው፣ መልሼ እንደምደውል ነግሬው፣ ስልኩን
ዘጋሁት፡፡ ከተለያየን ስንት ጊዜ ሆኖ ነው፣ ስልኳን የምትሰጠው ፍቅረኛ ያበጀችው? እሷ እያለች ገዝቼው የነበረው አምስት ሊትር ዘይት እንኳን ገና አላለቀም። ደግሞ ድምጹን የማውቀዉ መሰለኝ።
የሰፈራችንን ልጅ ፍቅረኛ አድርጋ፤ ተርመጥምጣ እንዳይሆን ብቻ።
ለነገሩ እራሴ እስካባረርኳት ድረስ የፈለገችውን አማርጣ ጓደኛ ማድረግ ትችላለች። ሳበራት እስከሌላ ሠፈር ድረስ ማብረርና ከዛው ፍቅረኛ እንድትይዝ ማድረግ ነበረብኝ፡፡ ቆይ ከማን ጋር ሆና ነው? ውጪ እየበሉ ደጅ እያመሹ መምጣት ከመረጃ እንድርቅ አድርጎኛል፡፡ ጎዶሎው ጓደኛዬም አፍላ ፍቅር ላይ ሆኖ ለኔ የሚነግረው ቀርቶ እሱም የሚሰማው አጥቷል፡፡ ቆይ ማነው በእኔ እግር ለመተካት ሲያደባ የነበረው? ማነው እንደወረወርኳት የቀለባት? በርግጥ በዛ ሰውነቷ ይሰያት የነበረው ጎረምሳ ብዙ ነበር። ለነገሩ ማንም የራሱ ያድርጋት!፡፡ የሚገርመው የእሷ ባለመጠባበቂያ መሆን ነው**።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲ ? ?
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ
✦ @DBC_TUBE
?ᵀᴴᴬᴺᴷ ᵞᴼᵁ ᶠᴼᴿᴰ ᴶᴼᴵᴺᴵᴺᴳ ᵁˢ ²‑²⁰¹⁶
...........አብዛኞቻችን ሥለ ነገ ማሠብ ምን እንበላለን፣እንጠጣለን፣እ
ንለብሣለን.....ብለን እንጨነቃለን ጭንቀት ካለ ደግሞ የምናገኘውን
ደሥታ ይቃረናል፡፡ አንዳንዴ ሣሥበው በህይወታችን ውሥጥ
# ለነገ_ባንጨነቅ_ኖሮ ህይወታችን ሙሉ ለሙሉ ደሥተኛ ይሆን ነበር
ብዬ አሥባለሁ፡፡ ይህንን ሳስብ አንድ የመፅሐፍ ቅዱሥ ጥቅሥ ትዝ
ይለኛል " ለነገ_አትጨነቁ " ማ.ቴ 6፡34 ልክ ነው፡፡ ምክንያቱም ምንም
የሌለው ሰው ዛሬን ጠግቦ ሳለ ለነገ እያሠበ ዛሬን ያገኛትን ደሥታ
ወይም ጥጋብ ያጣል በሌላ በኩልም አለ የተባለ ሀብታም ሦሥትና
አራት ፎቅ ኖሮት ነገን እያሠበ በጭንቀት ታሞ ሥንት ለፍቶ
ያጠራቀመውን በህክምና መልሶ ያጣዋል፡፡
ዛሬን ጥሩና ደሥተኛ መሆን ሥለነገ ማሠብ ማቆም ዛሬን መኖር ነገ
ስለራሷ ታስባለች እኛ የዛሬ ሰው ነን የተሰጠንን ጊዜ በመተሳሰብ ፣
በመፈቃቀር ፣ በመዋደድ ፣ በመረዳዳት ካሳለፍን......ነገ ጥሩ ሆኖ
ይጠብቀናል፡፡ ነገን አስበን ያለንን ትርፍ ነገሮች ደብቀን ብዙ ሺህ
ብሮችን በተለያዩ ባንኮች አስቀምጠን......እዛጋ ደግሞ አንዱ ወገናችን
ሚበላው ፣ ሚጣው ፣ ሚለብሰው ፣ ሚታከምበት ፣ ሚጫማው....አጥቶ
እኛ ለነገ እናስባለን ሲገርም!!! ሥለዚህ ባንድ መልኩ ለነገ ማሰብ #
የሌላን_ሰው_ዛሬን_መቀማት ይመስለኛል፡፡ ታዲያ እኛ ተርፎን ለነገ
ከምናስብ ለምን...የወገናችንን ዛሬ ለምን አንሰጠዉም?? ግን ለምን??
ግን ሳስበው እንዲህ ብናረግ ሣይሻል አይቀርም .....ለነገ በምንለው
ማንኛውም ነገር ለተቸገረው በመለገስ.......የእኛንም የሌሎቹንም ዛሬ
ለማሳመር መጣር ፣ መሞከር ሳይሻል አይቀርም ባይ ነኘ፡፡ ሁሌም መካሪ
ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲ ? ?
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ
✦ @DBC_TUBE
?ᵀᴴᴬᴺᴷ ᵞᴼᵁ ᶠᴼᴿᴰ ᴶᴼᴵᴺᴵᴺᴳ ᵁˢ ²‑²⁰¹⁶ ?አዲሱ ቻናላችን ይቀላቀላሉ የቀልድ እልፍኝ ♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲ ? ? ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ ➡️ @DBC_TUBE ➡️ @DBCTUBE_1 ➡️ @DBCTUBE_2 ➡️ @DBCTUBE_3
Telegram
attach 📎
?ᵀᴴᴬᴺᴷ ᵞᴼᵁ ᶠᴼᴿᴰ ᴶᴼᴵᴺᴵᴺᴳ ᵁˢ ²‑²⁰¹⁶
**<<የኔ የምለው ሰው>>
ከቃል ኪዳን ..... ✍
ክፍል ..... 2⃣
ሚስቴን ጠልቼ ብፈታትም፤ አፍቅሬ ነበር ያገባዋት፡፡ ‹ሰውነቷ› የሚለው የሙሉቀን መለሰ ዘፈን ለእሷ የተዘፈነ ነበር የሚመስለኝ፡፡ አንዳንዴ ሙሉቀን በአካል የሚያውቃት ስለሚመስለኝና ስለምቀና
ሙዚቃው ሲመጣ እዘጋዋለሁ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ሚስቴ ሰውነቷ ሳያንሳት፤ ሳታገባ ሠላሳ እንዳለፋት ሴት ንዝንዟ ባሰ፡፡ ሚስቴ መነዛነዝ ከመጀመርዋ ከወራት በፊት፤ አንድ ጠዋት አባቴ መጥቶ፤ ‹‹ልጆቼ፤ ሁለት ዓመት ታለፋችሁ፣ ፍቅራችሁ እያለቀና እየተሰለቻቻችሁ ስለምትመጡ ውለዱ፡፡›› ሲል መከረን፡፡ እኛ ግን ሀብት ንብረት ካላፈራን ብለን እንቆይ አለን፡፡ ሁለት ዓመት ሲያልፍ ሚስቴ ንዝንዝ ጀመረች፡፡ የሙሉቀን ‹ሰውነቷ› እንኳን በሆነ አስማት ተገልብጦ፤ ‹ንዝንዟ› እያለ ይሰማኝ ጀመር። አንድ ቀን ዘፈኑ ሲመጣ
ሬዲዮኑን ሰብሬ እሷንም፤ ‹‹በቃኝ ሂጂልኝ!›› አልኳት፡፡ ‹‹ከሠፈሬ የት ልሂድልህ? ደግሞ ይሄን ቤት፣ ቤቴ ነው ብለህ ውጪ ልትል ነው እንዴ? አባትህ የሰው መተላለፍያ የነበረውን መንገድ
አጥረው፣ ቤቱን እንደሠሩት የማላውቅ መሰለህ? እኛ ህጻን እያለን ወደ ትምህርት ቤት የምንሄድበትን መተላለፍያ እኮ ነው አጥረው ቤት ያደረጉት፡፡›› አለችኝ፡፡ ከዓመታት በፊት ጎዶሎው ጓደኛዬ፣ ነዝናዛዋን ሚስቴን ላገባት መወሰኔን ስነግረው፣ ሰፈር ውስጥ መርመጥመጥ እንደማይበጀኝና
ገመናዬን ከምታውቅ ሴት ጋር ትዳር መመስረት እንደሌለብኝ ተቆጥቶ ነግሮኝ ነበር፡፡ ይኸው ያለው ደረሰ፡፡ ሚስቴ በተጣላን በሠልስቱ ነጠላዋን አንጋዳ ለብሳ ቀበሌ ስትሄድ አየኋት።
እንዳትከሰኝ አልደበደብኳት፤ ፍቺ እንዳትል በህግ አላገባዋት ብዬ
ችላ አልኳት፡፡ እሷ ግን የቀበሌ ደንብ ማስከበር ይዛ መጥታ፣ “አባቱ
መንገዱን አጥረው እኛ በየት በኩል እንለፍ!” ብላ ቀኑን ሙሉ ስትረብሽ ዋለች፡፡ ሚስቴ እንዲህ ባደረገች በነጋታው፣ ጎዶሎው ጓደኛዬ፣ የጎደለ
የላስቲክ ውሃ ይዞ ቤቴ መጣ፡፡ ያለው በመድረሱ ትንንሽ ዓይኖቹን፣ በትልልቅ ዓይኖቼ ማየት ፈራሁ፡፡ ፈራ ተባ እያልኩኝ፤ ‹‹ትዝ ይልሃል ሚስት ፍለጋ ሰፈር ውስጥ አትርመጥመጥ ያለከኝ?››
አልኩት፡፡ ዝም አለኝ፡፡
‹‹የዛኔ ‹እንዴት ከሠፈርህ ልጅ ጋር ትርመጠመጣለህ?› ስትለኝ
ውጤቱ ባይታየኝ፤ በልቤ ‹ይሄ ጫኝና አውራጅ! ሰፈር ውስጥ አዲስ
ተከራይ በመጣ ቁጥር፣ ከጓደኞቹ ጋር ከሰፈራችን የመጣን ጭነት፣ ከእኛ ውጪ ማንም አያወርድም እያለ እየተጣላ፣ እኔ የሰፈሬን ቆንጆ ለሌላ አሳልፌ እንድሰጥ ነው እንዴ የሚፈልገው?› ብዬ ረግሜህ
ነበር፡፡›› ጓደኛዬ በቁጣ ተመለከተኝ፡፡
‹‹አንተ ግን የሆዴን እርግማን ሳታይ ‹ከአብሮ አደግህ አትሰደድ ሲባል አልሰማህም? ትዳር ከላጤነት ስደት ነው፡፡ ትዳራዊ ስደትህን ከአብሮ አደግህ ጋር ካደረግህ ነገ ቀን ሲጎድል፤ በቀይ ሽብር እንደተከሰሱት ገመናህን አጋልጣ ትሰጥሀለች አልከኝ፡፡› እኔ ግን ተገብዤ እንደገና በሆዴ ‹ቆይ ይሄ ጎዶሎ ምን አባቱ ነው የሚለኝ?› ብዬ ሰደብኩህ።›› ጎዶሎው ጓደኛዬ ፊቱ፣ ለግዙፍ ሰው የሚበቃን መቅላት፣ በንዴት ቀላ። ደግነቱ የፈለገ ቢናደድብኝ፣ ቤቱ ገብቶ የዕለት ውሎ መመዝገቢያው ላይ ንዴቱን ከማስፈር በዘለለ ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ ‹‹ምኗን አይተህ ነው? የድሮውን እንዴት እረሳኸው?” አልከኝ፡፡
‹‹ሰውነቷ!›› አልኩ፡፡ “ይሁና” ብለህ እዝን ብለህ ወጣህ፡፡ ዛሬ ሲደርስብኝ ግን ይኸው እውነቱን ፊቴ ቆሞ አየሁት፡፡
‹‹አዎ እኔም ዛሬ እውነቱ ተገለጠልኝ፡፡ እኔም አመጣጤ ለሱው
ነበር፡፡›› አለኝ ጎዶሎው፡፡ ‹‹ማለት?›› ምን ሊለኝ ነው በሚል መገረም ውስጥ ሰጥሜ ጠየቅሁት፡፡
ከብዙ ፈራ ተባ ማለት በኋላ፣ የሠፈራችንን አንዲት ጎዶሎ ሊያገባ፣
በርበሬ ማስቀንጠስ መጀመሩን ነገረኝ፡፡
‹‹የጫኝና አውራጅ አመልህ አለቅ ብሎህ ነው ወይስ ምን ተገኘ?›› አልኩት በንዴት፡፡ ‹‹ሰውነቷ!›› አለኝ፡፡ አሽሙር መሆኑ ነው፡፡ ‹‹እሺ አንተም ጎዶሎ፣ እሷም ጎዶሎ - ጎዶሎ ልትወልዱ?››
አሽሙሩን፣ በአሽሙር ለመመለስ እየሞከርኩ፡፡ ‹‹ሳንወልድ ብንፋታስ?›› አለኝ፡፡ ሌላ አሽሙር! አጭር ሰው ተንኮለኛ ከተባለ፣ ጎዶሎ ምን ሊባል ይሆን? የራሱ ጉዳይ! እንደኔ ቀምሶ ይየው ብዬ ተውኩት፡፡ ሚስቴን ያበረርኳት ጊዜ ዕቃዋን እየሸከፈች፣ ለወራት የሚበቃ ንዝንዝ አሻረችኝ፡፡ ወጉ አይቅርብኝ ብላ እንጂ ሶስት አራት ቤት አልፋ እናቷ ቤት ለመግባት ዕቃ መሸከፍ አያስፈልጋትም ነበር፡፡ ዕቃዎቿን ሸክፋ
ስትጨርስ፣ ዓይኖቿ ሟሙተው የሚፈሱ እስኪመስሉኝ አለቀሰች፡፡ አልቅሳ ስታበቃ አልጋችንን ከሸፈነው መጋረጃችን ውጪ ያለው የቤቱ ክፍል እንኳን የማያቃቸውን ገበናዎቼን እያነሳች ሞለጨቺኝና
ወጥታ ሄደች፡፡ በመሄዷ ቀለለኝ፡፡ እቤት አለመኖሯን ሳስብ፣ ዓመቱን ሙሉ
ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሲዘጋጅ ከርሞ ፈተናውን እንደጨረሰ ተማሪ ተደሰትኩ። ደስታዬ ግን እንደጠበቅሁት ፍጹም አልነበረም፡፡ ፈተናውን መጨረሱ በራሱ እረፍት አይደለም ለካ? ከሌላኛው ቀን በኋላ ውጤቱ ያሳስባል፡፡ እንደውም ፈተናውን ከመጨረሱ፤ ውጤቱን ማወቁ ዘለግ ያለ ደስታ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ሚስቴን ከአጠገቧ ተኝቼ፣ ስነቃ፣ ከእነ ንዝንዟ ተሰውራ እንዳገኛት የሚማለድ አዲስ ጸሎት በምሽቱ የሠርክ ጸሎቴ ላይ ጨምሬ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ የተዘጋ በሬን ከፍቼ ስገባ፣ በሩን እሷ ልትገባ ስትመጣ
እንዲሰወራት፤ አስተዛዝኜ ነግሬው ነበር፡፡ ‹ቆይ የነዘነዘችህ ሌላ ሴት በር የለችም?› እያልኩ ቁስሉን ለመንካት እሞክራለሁ። ቁስል እንደሌለው ደረቱን ነፍቶ ዝም ይላል፡፡ ‹ታዲያ ቀለም ቀቢው
‹በስትኮ› ሊደፍነው ያልቻለው ቋርህ ከየት መጣ?› በሩ በዝምታው ይጸናል፡፡ ተናድጄ ወርውሬ እዘጋዋለሁ። ከበሩ በላይ ያለው ግድግዳ እየተፈረፈረ ወለሉ ላይ ይወርዳል፡፡ በሩ የዛኔ ‹አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ
ያወጣል› ይልና በበርኛ ይሥቃል። አፈሩን ጠርጌ አውጥቼ ፊት ለፊቱ ቆሜ በንዴት አፈጥበታለሁ። ንዴቴን ሲያይ ይበልጥ
ይንከተከታል። ወዲያው በሚያውቀው አንድ ቀልድ፤ እንደ ቅዱሳን ሥዕል፣ በነጭ መጋረጃ ወደተሸፈነው መስኮቱ ዞሮ፤ ‹‹ኖክ! ኖክ! ኖክ!›› ይላል
‹‹ሁ ሂዝ ዜር?›› መስኮቱ ድምጹ ብቻ ነው የሚሰማው።
‹‹በሩን እጎዳለሁ ብዬ፤ ወርውሬ ዘግቼ፣ የግድግዳ ፍራሽ የተረፈኝ….›› በሩ በሣቅ እንደታጀበ ይጠይቃል።#ይቀጥላል ....**.
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲ ? ?
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ
✦ @DBC_TUBE
✨Premium emoji №1✨
Feedback - @ukngs
Last updated 1 year, 3 months ago
Wallpaper 4K 3D + Pc ✣ Themes Telegram
.
⭕ › ᴛʜᴇ ʙᴇꜱᴛ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴛʜᴇᴍᴇꜱ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ
⭕ › ᴛʜᴇ ʙᴇꜱᴛ ᴛᴇʟᴇɢʀᴀᴍ ᴡᴀʟʟᴘᴀᴘᴇʀ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ
.
?️ • @lEO_adminTel | admin • ⛑️
Last updated 3 months, 1 week ago
«احسان حیدری»
??
.
inst?️: ehsanheydar1 (+169k)
Last updated 1 week, 5 days ago