★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡
በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡
እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
“አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡ ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"
✨ቅዱስ_ኤፍሬም✨
እንኳን አደረሳችኹ
????????????
✝ እንኳን አደረሳችሁ ለፆመ ነቢያት ✝
ፆሙን ለማበርከት ያብቃን
© ማኀበረ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ዘኢቲሳ
✨✨✨??????✨✨✨
"ትህትናሰ ትሬስዮ ለሰብእ መልአከ ዘበምድር"
ትርጉም
"ትህትናስ ሰውን በምድር ያለ መልአክ ታደርገዋለች"
ማር ይስሐቅ
ወደ ኢየሩሳሌም ሲመላለሱ በታላቅ ድንጋይ ላይ ተጭነው ድንጋዩም በደመና አምሳል ይታዘዛቸው የነበሩት የቦረናው አቡነ ገብረ እንድርያስ ጠበላቸው ውስጥ እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡ (የፎቶው ላይ የሚታየውም ይኸው ዕንጨቱ ከጠበላቸው ውስጥ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ የወጣው መቁጠሪያ ነው፡፡ እርሱም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው፡፡)
የትውልድ ሀገራቸው ወሎ ቦረና ጋስጫ ነው፡፡ አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ እናታቸው አርሴማ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጧቸው፡፡ መምህሩም ጸጋ እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ዐውቀው ‹‹ብዙዎችን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ የመጻሕፍትንም ትርጓሜ በሚገባ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሌም ይባል የነበረውን ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው፡፡
ጻድቁ በአቡነ ዮሐንስ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፡፡ አባታችን ሙታንን በማስነሣትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡ ብዙ አባቶች ሱባኤ ይይዙበት በነበረው በሰኮሩ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ዑራኤል በወርቅ ጽዋ ሰማያዊ ወይንና ኅብስት መግቧቸዋል፡፡ እመቤታችንም ሦስት ጽዋ ማየ ሕይወት ሰጥታቸው ሕሙማንን ፈውሰውበታል፡፡
በስማቸው የፈለቀው ጠበል እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ጠበሉ ውስጥ እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡ ይኽም እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል፡፡ ጠበሉ ውስጥ ማታ የነከሩትን እንጨት ጠዋት ላይ መቁጠሪያ ሆኖ ያገኙታል፡፡ እጅግ አስገራሚ ነው በእውነት! መቁጠሪያውም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው፡፡ ነገር ግን ጠበሉ ያለበት አካባቢው በመርዛማና አደገኛ እባቦች የተሞላ ነው፡፡ ሆኖም ግን እባቦቹ የጻድቁ ግዝት ስላለባቸው በገዳሙ ክልል ማንንም አይነኩም፡፡ ጠበሉ የሚገኘው ከገዳሙ የአንድ ሰዓት ተኩል መንገድ ርቀት ላይ ነው፡፡
የማንዳባው አቡነ ያሳይ የተባሉት ጻድቅ የመድኃኔዓለምን ታቦት ይዘው ወደ ደሴቲቱ የገቡት ትልቁን ድንጋይ እንደ ጀልባ ተጠቅመው በድንጋዩ ላይ ተቀምጠው የጣናን ሐይቅ እየቀዘፉ ነበር፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስም ዐርብ ዐርብ ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በትልቅ ድንጋይ ላይ እንደ ደመና ተጭነው ነበር፡፡ ያ እንደ ደመና ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡
ኅዳር 7 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላታቸው ታስበው የሚውሉት ሲሆን በየወሩም በ7 ይታባሉ። ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
(ምንጭ፡- ከገዳሙ የተገኘ ማስታወሻና ቅኝት፣ የቅዱሳን ታሪክ-122)
አለው፡፡ የሰይጣን መጨረሻው ይህ ነው፣ የሰው ልጅ በሕይወት ሳለ ሲያስክድ፣ ሲያስት፣ ክፉ ሥራን ሲያሠራ ይኖርና በመጨረሻ መክዳትና በሲኦል ማጋዝ ባሕርይው ነው፡፡ በዚያም ለዘለዓለም የሲኦል ባሪያ አድርጎ በታላቅ ሥቃይ ሲያሠቃይ ይኖራል፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን ቃል ከሰይጣን ከሰማ በኋላ ደንግጦ በክፉ አሟሟት ሞቶ ዘላለማዊ ፍርዱን አግኝቶ ወደ ሲኦል ወረደ፡፡
የልዳው ፀሐይ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የሌሎቹም ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡ የንጉሡም ጭፍሮች የመጥምቁን ራስ በወጪት አድርገው ለንጉሣቸው ሄሮድስ ሰጡት፡፡ ሄሮድስም ለሄሮድያዳ ልጅ ሰጣት፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ግን በወጪት ላይ ሆና ሕዝቦቹና የመንግሥቱ ታላላቅ ሰዎች እየሰሟት በየመኳንንቱ ፊት ንጉሥ ሄሮድስን ‹‹የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት አይገባህም›› እያለች መጀመሪያ ትዘልፈው እንደነበረው ሁሉ አሁንም ዘለፈችው፡፡ መዓዛዋም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር፣ ዐይኖቹም እንደፀሐይ ያበሩ ነበር፡፡
የሄሮድያዳም ልጅ የመጥምቁን ራስ ወስዳ ለእናቷ ልትሰጣት ስትል ዐይኖቹ እንደፀሐይ ሲያበሩ ብታየው ‹‹ንጉሡን አትፈራውምን?›› በማለት ተቆጣች፡፡ በመቀጠልም ‹‹እነዚህን ዐይኖቹን በወስፌ እያወጣሁ እጥላቸዋለሁ፣ ምላሱንም ደግመኛ እንዳይገሥጽ ቆርጨ እጥላቸዋለሁ›› በማለት ፊቱን በጥፊ ለመምታት እጇን ስታነሣ ያንጊዜ የዮሐንስ ራስ ክንፍ አውጥታ በረረች፡፡ በአየር ላይ ሳለችም ዳግመኛ ‹‹የተረገምሽ ሄሮድያዳ የባልሽን ወንድም ሄሮድስን ማግባት አይገባሽም፣ ቀድሞ የምዘልፍሽ አሁንም የምዘልፍሽ እኔ ነኝ›› እያለች የዮሐንስ ራስ የቤቱን ጣሪያ ሰንጥቃ እንደንሥር በአየር በራ ሄደች፡፡
ከዚህም በኋላ ለጥፊ የዘረጋቻቸው የሄሮድያዳ እጆቿ ከትከሻዋ እየተቆረጡ መሬት ላይ ወደቁ፤ እውነቷንም መሬት አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ዘፋኟ ልጇም አብዳ የቤተ መንግሥቱን ዕቃ ሁሉ መሰባበር ጀመረች፡፡ የንጉሡ አንዱ ጭፍራም የሄሮድያዳን በእሳት እንደተለበለበ የግንድ እሳት የመሰለና የተቆረጠ እጇን አምጥቶ ለሄድሮስ ሰጠውና የሆነውን ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገሩ እውነት መሆኑን ሄዶ ባየ ጊዜ በሀፍረት እጅግ ተሸማቀቀ፡፡ ዘፍና በማስደሰት የዮሐንስን ራስ እንዲያስቆርጠው ያደረገችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅም አብዳ በቤተ መንግሥቱ ስትለፈልፍ አገኛት፡፡ ሄሮድስም መኳንንቶቹን ‹‹በቤተ መንግሥቴ የተደረገውን ይህን ነገር ለማንም አትንገሩ›› ብሎ አማላቸው ነገር ግን ያበደችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅ ራሷ ሄዳ ሄሮድስን ‹‹የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት ፈጽሞ አይገባህም›› እያለች በመኳንንቶቹ ፊት ገሠጸችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ቃል ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተናደደና ‹‹ቀደሞ ያልሆነ ሥራ ታሠራ በኋላ ደግሞ ምሥጢር ታወጣ ንሣ በሰይፍ ቁረጣት›› ብሎ አንገቷን በሰይፍ አስቆረጣት፡፡ ሥጋዋንም ዓሣ አንበሪ ተቀብሎ ዋጣት፡፡ ሄሮድም የወንደሙን ሚስት ሲያገባ አስቀድሞ አግብቷት የነበረችውን ሚስቱን በግፍ አባሯት ነበር፡፡ እርሷም ይህንን ሄሮድስ ያደረሰባትን ግፍ ለአባቷ አርጣ ብትነግረው አባቷ ብዙ ጦር ሰብስቦ መጥቶ ምድረ ገሊላን በኃይል አፈራረሳት፡፡ የበላዩ ንጉሥ ቄሳርም የገሊላን መፍረስና መውድም ሲሰማ ምክንያቱን ቢጠይቅ ሄሮደስ ባደረገው ግፍ ምክንያት መሆኑን ነገሩት፡፡ ቄሳርም ሄሮድስን ከሥልጣኑ ሽሮ አጋዘውና በወህኒ ጣለው፡፡ ሄሮድስም በወህኒ ቤት ሳለ አብዶ ራሱን ስቶ የገዛ አካሉን እየነጨ እየበላ ቷ ብሎ ፈንድቶ ተልቶ ሸቶ እጅግ ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡
ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ መለስ ብሎ እንዲህ በማለት ሥልጣን ሰጣት፡- ‹‹እነሆ መንፈስሽን በራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ በሰማይም የምትበሪበት እንደ ንሥር ክንፍ ሰጥቼሻለሁና እንደንስር በሰማይ እየበረርሽ በዓለም ሁሉ እየዞርሽ የሄሮድስንና የሄሮድያዳን ኃጢአት ግለጭባቸው፤ እስከ 15 ዓመት ድረስ ገቢረ ተአምራት የምታደርጊበት ኃይሌን መንፈሴን በእራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ›› አላት፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ዮሐንስን ‹‹እኔም ከ3 ዓመት በኋላ ለአዳም የሰጠሁትን ተስፋ ፈጽሜ በሞቴ ወደ ሲኦል ወርጄ ነፍሳትን ከዲያብሎስ እጅ ማርኬ በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ተነሥቼ ወደ ባሕርይ ክብሬ ተመልሼ ወደ ሰማይ አርጌ ባባቴ ቀኝ በተቀመጥኩኝ ጊዜ ከ15 ዓመት በኋላ ርጉም ሄሮድስ ካስፈጃቸው ከትንንሾቹ ሕፃናት ጋራ ትሆን ዘንድ በአባቴ ፈቃድ እራስህን ተሸክመው ወደ አባትህ ወደ ዘካርያስ ያመጧት ዘንድ እኔ መላእክትን አዛቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ግን ነፍስህን በእኔ ቀኝ ባባትህ በዘካርያስ አጠገብ አኑሬያታለሁ መንፈስህንም እስከ 15 ዓመት በእራስህ ውስጥ እንድትኖር አዝዣታለሁ፣ ሥጋህም ከነቢዩ ከኤልሳዕ ጋር እንዲቀመጥ አድርጌያለሁ›› አለው፡፡
ከዚህም በኋላ ጌታችን እንዳዘዛት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እራስ እንደንስር በአየር ላይ እየበረረች የምታስተምር ሆነች፡፡ በምሥራቅ በኩል ሄዳ በዐረብ አገር ውስጥ በሰማይ ላይ ስታስተምር በዚህች ዕለት ጥቅምት 30 ቀን በግልጽ ታየች፡፡ ነጋዴዎች ድምጹዋን ሰምተውና አይተዋት እጅግ ተደስተው ገንዘባቸው ሁሉ ጥለው የቅዱስ ዮሐንስን እራስ ለመያዝ ሰውነታቸውን ብዙ አደከሙ፡፡ ነገር ግን ለመያዝ አልተቻላቸውም፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰማይ ‹‹የምትያዝበት ጊዜ ስላልደረሰ ሰውነታችሁን አታድክሙ›› የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣላቸው፡፡ መፈለጋቸውንም ተው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስም እራስ 15 ዓመት ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዐረብ ሀገር ዐረፈች፡፡ የታዘዙ ቅዱሳን መላእክትም መጥተው ከቅዱስ ዮሐንስ እራስ ከተባረኩ በኋላ በታላቅ ዝማሬ እያመሰገኑ የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ወስደው በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ አብረው ቀበሯት፡፡ ቅድስትን ነፍሱንም እያመሰገኑ ወደ ሰማይ አሳረጓት፡፡ በዚያም በሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ወድቃ ከሰገደች በኋላ አባቷ ዘካርያስንና እናቷ ኤልሳቤጥን እጅ ነሳቻቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በ3ኛው ሰማይ ውስጥ ተቀመጠች፡፡ ጌታችን ሦስቱን ሰማየ ሰማያት ርስት ጉልት አድርጎ ሰጥቶታልና፡፡
የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
(ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ-ሚጣቅ አማኑኤል እትም፣ ገድለ ሐዋርያት፣ የጥቅምት ወር ስንክሳር)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 30-በግብፅ ምድር ያሉ ጣዖታትን ፈጽሞ ያጠፋ እስከ ኢትዮጵያም ድረስ መጥቶ ወንጌልን ያስተማረ በመጨረሻም አረማዊያን አካሉን በበሬ አስጎትተው ሥጋው ተበጣጥሶና ተቆራርጦ እስኪያልቅ ድረስ ያሠቃዩት፣ የቀረውንም አካሉን ሰብስበው በእሳት ያቃጠሉት፣ የከበረች ወንጌልን የጻፈ፣ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ልደቱ ነው፡፡
+ የመጥምቁ ዮሐንስ አንገት በግፍ በሰማዕትነት ከተቆረጠች በኋላ በግልጽ የታየችበት ዕለት ነው፡፡ ይኸውም የመጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በአየር ውስጥ እየበረረች 15 ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ በዚህች ዕለት በዐረቢያ ምድር በግልጽ ታይታለች፡፡
+ መኑፍ ከሚባል ሀገር የተገኙት ጻድቁ አባ አብርሃም ዕረፍታቸው ነው፡፡
አባ አብርሃም፡- ይኸውም ቅዱስ በሚባል ሀገር እግዚአብሔርን ከሚፈሩና እጅግ ባለጸጎች ከሆኑ ደጋግ ወላጆቹ ተወለደ፡፡ ባደገ ጊዜም የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ወዶ ወደ ላዕላይ ግብፅ ተሳፍሮ ሄዶ በታላቁ አባት በአባ ጳኩሚስ እጅ መነኮሰ፡፡ እሳቸውንም እያገለገለ በገድል ተጠምዶ እየኖረ 23 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጳኩሚስን አስፈቅዶ ብቻውን በዋሻ ውስጥ መኖር ጀመረ፡፡ ለዕለት ጉርሱ ጥሬ መግዣ ይሆነው ዘንድ ዓሣ ማጥመጃ መረብም ይሰፋ ነበር፡፡ ጌታችንም መረቦቹን የሚሸጥለት ሰው ላከለት፡፡ እርሱም መረቦቹን ሸጦ ምግቡን አተር ይገዛለታል፡፡ ከእርሷም አንድ እፍኝ ብቻ አስቀርቶ በውኃ አርሶ ይመገብና የቀረውን ለሌሎች ይሰጣል፡፡
አባ አብርሃም በእንዲህ ዓይነት ጽኑ ተጋድሎ 17 ዓመት ኖረ፡፡ በየሁለት ዓመቱ ወደ መነኮሳቱ እየተመለሰ ሥጋውን ደሙን እየተቀበለ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር፡፡ ዕረፍቱም በደረሰ ጊዜ የአባ ጳኩሚስን ረድእ አስጠርቶት አብረው ጸሎት ካደረጉ በኋላ አባ አብርሃም በዚያው ጥቅምት 30 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ መነኮሳቱም መጥተው ከሥጋው በረከትን ተቀብለው አስክሬኑን ወስደው ከቅዱሳን ጋር አኖሩት፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ልደቱ ነው፡፡ (የዕረፍቱን ዕለት ሚያዝያ ሠላሳን ይመልከቷል፡፡)
ማርቆስ ማለት ‹‹አንበሳ፣ ንብ›› ማለትነው፡፡ የቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው፡፡ እናቱ ማርያም ቅዱሳን ሐዋርያትን ታገለግል ስለነበር ቤቷንም ለጸሎት እንዲሆን አደረገች፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በትውልዱ ዕብራዊ ሲሆን ቤተሰቦቹ ግን ይኖሩ የነበሩት በሰሜን አፍሪካ ቀሬና በተባለችውና በዛሬዋ ምዕራባዊ ሊቢያ ጠረፍ አካባቢ ነበር፡፡ ነገር ግን የሰሜን አፍሪካ ዘላን ጎሳዎች የሆኑት በርበሮች በየጊዜው ከተማቸውን እየዘረፉና ጥቃት እየሰነዘሩ ሲያስቸግሯቸው እናቱ ማርያምና አባቱ አርስጦቡሎስ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢየሩሳሌም በመመለስ በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ማርቆስም በዚያው ስላደገ በዘመኑ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት ተምሯል፡፡ የላቲን፣ የግሪክና የዕብራይጥ ቋንቋዎችን በደንብ ያውቅ ነበር፡፡
ወንጌልን መጀመሪያ ከጌታችን በኋላም ከቅዱሳን ሐዋርያት እየዞረ ስለተማረ ንብ ተብሏል፣ አንበሳ የተባለበትም ምክንያት አንበሳ ላምን እንደሚሰብር ማርቆስም እንዲሁ በላም አምሳል ተሠርተው ሲመለኩ የነበሩ የግብፅ ጣዖታትን ሰባብሮ አጥፍቷልንና ነው፡፡
ጌታችን በይሁዳ አውራጃዎች እየተዘዋወረ ሲያስተምር ቅዱስ ማርቆስ ያንጊዜ ገና ሕፃን ነበር፡፡ ለዚህም ነው ጌታችን መከራ መስቀሉን እየተቀበለ ወደ ቀራንዮ ሲሄድ ማርቆስ ዕርቃኑን በነጠላው ሸፍኖ ሲከተለው አይሁድ ሊይዙት ባሰቡ ጊዜ ጨርቁን ጥሎ ራቁቱን የሸሸው፡፡ ሐዋርያት ዓለምን ዕጣ በዕጣ ተከፋፍለው ሲወጡ ቅዱስ ማርቆስ በበርናባስ አቅራቢነት ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በመጀመሪያ ጉዞው በ46 ዓ.ም ለስብከተ ወንጌል ወጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ጵንፍልያ በምትባል ከተማ ላይ ‹‹እናቴ ናፈቀችኝ›› ስላለ በርናባስ ይዞት ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል፡፡ ሐዋ 13፡13፡፡ ነገር ግን ሐዋርያት ከሄዱበት ተመልሰው ስላደረጓቸው ተአምራት ሲናገሩ ሲሰማ ተጸጸተ፡፡ ድጋሚም ከበርናባስ ጋር ሄደ፡፡ በርናባስም ካረፈ በኋለ ወደ ሮሜ ሄዶ ቅዱስ ጴጥሮስን ተቀላቅሎ ደቀ መዝሙሩ ሆነ፡፡ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጎመለትን ወንጌል ጻፈ፡፡ በሮሜ ሀገርም አስተማረበት፡፡
ከዚህም በኋላ በጌታችንም ትእዛዝ በ60 ዓ.ም ወደ ሰሜን አፍሪካ መጥቶ እስክንድርያ ደረሰ፡፡ በሀገሪቱም አምልኮተ ጣኦት በስፋት ተንሰራፍቶ ስለነበር ወንጌልን እንዴት አድርጎ መስበክ እንዳለበት እያሰበ በከተማ ሲዘዋወር የእግሩ የጠፈር ጫማው ተበጠሰና ለአንድ ሰፊ ሰጠው፡፡ ጫማ ሰፊውም ሲሰፋ እጁን ስለወጋው ‹‹ኤስታኦስ›› ብሎ በዮናናውያን ቋንቋ ጮኸ፡፡ ትርጉሙም አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ያን ጊዜም ቅዱስ ማርቆስ ጫማ ሰፊውን ‹‹ለመሆኑ አሁን የጠራሃውን አምላክ ታውቀዋለህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ጫማ ሰፊውም ‹‹ሲሉ እሰማለሁ እንጂ አላውቀውም›› አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም የቆሰለች እጁን በተአምራት ፈወሰውና ወንጌልን ሰበከለት፡፡ እርሱም ወደ ቤቱ ወሰደውና ለቤተሰቡም ጭምር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ጋበዘው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ጫማ ሰፊው (ስሙ አንያኖስ ይባላል) ሄዶ ወንጌልን ሰበከ፡፡ በግብፅም የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአንያኖስ ቤት ተመሠረተች፡፡
ቅዱስ ማርቆስም በእስክንድርያ ወንጌልን ሰብኮ አገልጋዮችን ሾሞ ወደ ሰሜን አፍሪካና ሌሎች አምስት ሀገሮች ሄዶ ወንጌልን ሰበከ፡፡ ወደ ትውልድ ሀገሩ ቀሬናም ሄዶ ሰብኳል፡፡ ከ2 ዓመትም በኋላ ወደ እስክንድርያ ቢመለስ ክርስቲያኖችን ጸንተው ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው፡፡ ከሀዲዎችም ሊገድሉት ሲሞክሩ እየተሰወረባቸው እየወጣ ወደ አምስቱ ሀገራት እየደረሰ ይመለስ ነበር፡፡ ነገር ግን የትንሳኤን በዓል ለማክበር ወደ እስክንድርያ መጥቶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ እየቀደሰ እያለ ጣዖት አምላኪዎች ሰብረው ገብተው ይዘውት አንገቱን አሥረው ቀኑን ሙሉ ከተማውን እየጎተቱት ሲያዞሩት ዋሉ፡፡ በቀጣዩም ቀን እንዲሁ አስረው መሬት ለመሬት ሲጎትቱት ስለዋሉ በዚያው ዐረፈ፡፡ እሳት አንድደው ሥጋውን ሊያቃጥሉት ሲሉ ኃይለኛ ዶፍ ዝናብ ስለወረደ ጨረቃና ፀሐይም ስለጨለሙ አረማውያኑ ፈርተው ሸሹ፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ሰማዕትነቱን የፈጸመው በ68 ዓ.ም ሚያዝያ 30 ቀን ነው፡፡
የቅዱስ ማርቆስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+++
የመጥምቁ ዮሐንስ አንገት ከተቆረጠች በኋላ 15 ዓመት በአየር እየበረረች ስታስምር እንደኖረች፡- የመጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በአየር ውስጥ እየበረረች 15 ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ ጥቅምት 30 ቀን በዐረቢያ ምድር በግልጽ ታይታለች፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሄሮድያዳ ልጅ ርጉም የሆነ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገና እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡ እርሱም አስቀድሞ ‹‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?›› እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ እርሱም ስለማሐላው የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡ በመጀመሪያም የሄሮድስ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሲሄዱ ቅዱስ ዮሐንስም
አቡነ ሳሙኤል ወደ ምድረ ርስቱ ደብረ ወገግ እየሄደ በዚያ ያሉ ልጆቹን እያጽናና ወደ እንደግብጦን አውራጃም እየተመለሰ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ወንጌልን እያስተማረ፣ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስትና እየቀየረ፣ አጋንንትንና መመለኪያ ቦታዎቻቸውን እያጠፋ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ በቅዱስ ገድሉ ውስጥ በጣም አስገራሚ በሆነ መልኩ እጅግ ብዙ ታሪኮች ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ታሪኮች ውስጥ አቡነ ሳሙኤል በሀገራችን በጣም ብዙ ጣዖታትንና መመለኪያ ቤቶቻቸውን እያጠፉ፣ በሰዎች (በጠንቋዮች) ላይ፣ በዛፍና በባሕር ውስጥ አድሮ ይመለኩ የነበሩ ሰይጣናት አጋንንትን በሚያመልኳቸው ሰዎች ፊት እያጋለጡና እያዋረዱ ሰዎቹን አስተምረው አጥምቀው ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሷቸው ቤተክርስቲያንም በመሥራት ሐዋርያትን መሰሉ፡፡
ሰይጣን አድሮባቸው የነበሩ ጠንቋዮች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ዕቃዎችን ጻድቁ እየባረኩና እየቀደሱ ለቤተክርስቲያን መሥሪያና መጠቀሚያነት ያውሉት ነበር፡፡ ይህም ገና ሳይወለዱ በአቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮላቸው ነበር፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት ‹‹ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ይሆናል›› ብሎው ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡
ጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፣ ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፣ በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፣ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፣ በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፣ በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ እንደዚሁም ሌሎች ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡
በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ውስጥ የተሰወሩ እጅግ በርካታ ቅዱሳን ስለመኖራቸው በገድለ አቡነ ሳሙኤል መቅድም ውስጥ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ አሁንም ሆነ ወደፊት በቦታው ላይ የተሰወሩት ቅዱሳን ለገዳማውያንኑም ሆነ በዓለም ለሚኖሩ ምግባርን ከሃይማኖት አስተባብረው ለያዙ ሰዎች እየተገለጡላቸው ይታዩዋቸዋል፣ መልእክትም ይነግሯቸዋል፡፡ እንዲሁም ስውራኑ ባሉበት ቦታ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ዕጣን ይሸታል፣ ቀንና ሌሊት አራዊት ሲሰግዱበትና ሲጠብቁት ይታያል፡፡
የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አቡነ ዕንቈ ብርሃን፦ ጻድቁ የንጉሥ ልጅ ናቸው። የአባታቸውን ንግሥና ንቀው ዓለምን ከነግሳንግሷ እንደትቢያ ቆጥረው በመተው በረኀብ በጥም በጾም በጸሎት በታላቅ ተጋድሎ መኖርን ስለመረጡ እንደሙሽራው ገብረ ክርስቶስ መናኔ መንግሥት ወብእሲት ናቸው።
አቡነ ዕንቈ ብርሃን በምንኩስና እግዚአብሔርን ለማገልገል ከአባታቸው ቤተ መንሥት ወጥተው ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሔደው ገዳም ገብተው ትምህርተ ሃይማኖትን ተማሩ። በገዳም ውስጥ አባቶችን በጉልበት ሥራ እያገለገሉ በትምህርታቸውም ብሉይንና ሐዲስን እንዲሁም የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ሁሉ አጠናቀው ተማሩ። ከዚኸም በኋላ የገዳሙ አበ ምኔት አባታችንን ‹‹ስምህ ማን ይባላል? ሲሏቸው አባታችንም ስማቸው ዕንቈ ብርሃን እንደሚባል ነገሯቸው። አበ ምኔቱም ‹በእኛ ዘንድ እንደ ደማቅ ብርሃን ደምቀህ አብርተሃልና ከዚኽም በኋላ እንደ ድሮው ስምህ ዕንቈ ብርሃን ይባል፣ አማን በአማን ዕንቈ ብርሃን ነህ›› አሏቸው። አቡነ ዕንቈ ብርሃን ከመነኰሱ በኋላ በገድል ላይ ገድል በመጨመር በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ። እርሳቸውም በነበሩበት አካባቢ በጣዖት አምልኮ ውስጥ የነበሩትን ብዙ ሰዎች የከበረች ወንጌልን አስተምረው ክርስቶስን ወደማመን መለሷቸው።
ከዚኽም በኋላ አቡነ ዕንቈ ብርሃን በ16ኛው መክዘ ወደ ኤርትራ በመምጣት ልዩ ስሙ ደብረ ኣንገብ ደቂ ሻሓይ›› በሚባል ቦታ ተቀመጡ፣ ይኸም ቦታ ከአስመራ 30 ኪሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ዞን ጋሽ ባርካ በንዑስ ዞን ሎጎ ዓንሰባ ላይ ይገኛል። አቡነ ዕንቈ ብርሃን በዚ'ኸ ቦታ ላይ ብዙዎች ቅዱሳንን አስተምረው ከብቃት ደረጃ ያደረሱና በምንኩስና በርካታ ቅዱሳን የወለዱ አንጋፋ አባት ናቸው። ከልጆቻቸውም ውስጥ የፀዓዳ ዓምባው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል አንዱ ናቸው።
ጻድቁ በገዳማቸው በደብረ ኣንገብ ውስጥ በርካታ ተኣምራትን በማድረግ የሚታወቁ ሲሆን ምድርን ባርከው ያፈለቁት ፈዋሽ ጠበል በርካታ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል። ዳግመኛም ለሰውም ለእንስሳትም የሚሆን ውኃን አፈለቁ።
የአቡነ ዕንቈ ብርሃን የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክቱ ጋር ተገለጠላቸውና ‹ስምህን የጠሩትን፣ ዝክርህን የዘከሩትን ደብርህን ያነጹትን፣ ገድልህን የጻፉትንና ያነበቡትን የሰሙትን ሁሉንም እምርልሃለሁ የሚል ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባላቸው። ከዚኽም በኋላ የጸሎት በኣታቸው ተከፈተችና አባታችንም እዚያው ሲያርፉ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው፤ ወዲያውም በኣታቸው እንደቀድሞው ተዘጋች
ከአቡነ ዕንቈ ብርሃን ዕረፍት በኋላም ገዳማቸው ለብዙ ባሕታውያን መኖሪያ ሆነ። እንዲሁም በግራኝ አህመድ የ15 ዓመት የመከራ ዘመን ወቅትም ለ79 ታቦታትና ለበርካታ ቅዱሳት መጻሕፍት መሠወሪያ (መሽሽጊያ) ቦታ ሆኖ አገልግሏል። የመከራውም ዘመን ካለፈ በኋላ ታቦታቱ ወጥተው ለተለያዩ ገዳማትና አድባራት ተሰጡ። አሁን ላይ ግን በዚህ ታሪካዊ ገዳም ውስጥ የሚኖሩት መነኰሳት ጥቂት ከመሆናቸውም በላይ ገዳሙ እየተዳከመ ስለሆነ መነኰሳቱ የገዳሙን ክብር ለመጠበቅ ብዙ እየደከሙ ይገኛሉ። የአቡነ ዕንቴ ብርሃን የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ጥቅምት 29 ቀን በገዳማቸው ደብረ ኣንገብ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።
? እስመ በዛቲ ዕለት አዕረፈ እግዚአብሔር አምላክ እምኩሉ ግብሩ ዘአኀዘ ይግበር ?
ትርጉሙም
? በዚች ዕለት አምላካችን እግዚአብሔርን ሊሠራው ከጀመረው ሥራ ሁሉ ዐረፎባታልና ?
ድርሳነ መስቀል
? እንኳን ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ?
? እንኳን ለዘመነ ዮሐንስ በስላም አደረሳችሁ ?
? በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ?
? እንኳን ለቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም አው ለቅዱስ ጦቢት ወአባ አጋቶን ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ ?
? መስከረም ፲፮(16) ቅዳሴ ቤተክርስቲያን ዘመቃብር እግዚእነ ወዕረፍቱ ለጦቢት ገማልያል ወአባ አጋቶን ዘተፍፅመ እብነ ?
? ዘነግህ ምስባክ ?
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እምኩሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ
ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር
? ትርጉም ?
ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ
እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል
የእግዚአብሔር አገር ሆይ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል
መዝ ፹፮-፩
86 1
? ወንጌል ?
ማቴ ም ፭ ቁ ፲፫-፲፯
5 13 17
? የቅዳሴ ምንባባት ?
፩ ቆሮ ም ፫ ቁ ፲-፲፰
ያዕቆብ ም ፩ ቁ ፲፱-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፲፭ ቁ ፲፫-፳፩
? ምስባክ ?
እቤ አዐቅብ አፉየ ከመ ኢይስሐት በልሳንየ
ወእንበርኩ ዐቃቤ ለአፉየ
ሶበ ይትቃወሙኒ ኃጥኣን በቅድሜየ
? ትርጉም ?
በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ
ኀጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ
በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ
መዝ ፴፰-፩
38 1
? ወንጌል ?
ዮሐ ም ፱ ቁ ፩-፲፪
9 1 12
? ዓዲ ?
? ምስባክ ?
አሠንያ እግዚኦ በሥምረትከ ለጽዮን
ወይትሐነጻ አረፋቲሃ ለኢየሩሳሌም
አመ ትሠምር መሥዋዕተ ጽድቅ
? ትርጉም ?
አቤቱ በውዴታህ ጽዮን አሰማምራት
የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ይታነፁ
የጽድቁንም መሥዋዕት
መዝ ፶-፲፰
50 18
? ወንጌል ?
ዮሐ ም ፲ ቁ ፳፪-ፍ.ም
10 22 ፍፃሜው
? ቅዳሴ ?
ዘእግዚእነ (ነአኩተከ)
" በሰማያት ሆነህ ኢየሩሳሌምን ጎብኛት የመላዕክት አለቆች የሚሆኑ የሥልጣናት ጌታቸው የአጋዕዝትም ኃይል ብርሃንን የተጎናጽፋ የመናብርትም ክብራቸው የደስታ የነገሥታት ንጉሥ ሁሉን በእጅ ይዞ የሚገባ አብ "
ቅዳሴ እግዚእነ
ም ፩ ቁ ፳፮
1 26
? በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ በረከት ያድርግልን ቸሩ አምላክ ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ከቤተክርስቲያን ቅድስት በረከት ይክፈልን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ከንግሥት ዕሌኒ በረከቷ ይደርብን በዓል ተከተሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱሳን ይሰውረን ድርሳነ መስቀል መልክአ መስቀል ውዳሴ መስቀል የተቀበለ የኛም ፆም ፀሎት ምጽዋት ምስጋና በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያም ለቅዱስ ያሬድ ማኀሌት ዓይን ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ለቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት ለአባ ኪሮስ ለአባ መባአፅዮን ለአፄ ዘርእያዕቆብ ለአፄ ናዖድ ለአፄ ዳዊት ለአፄ ልብነድንግል ለአፄ አብርሃ ወአፅብሃ የተለመነች ኪዳነ ቃሏ ማርያም ድንግል ለኛም በቸርነት በምህረት ትለመነን ዘመኑ ዘመነ ድኀነት ዘመነ ንስሐ ያድርግልን ነፍሳት ሙታን ይማርልን ሕያዋን ይጠብቅልን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ለቅዱስ ስጋው ለክቡር ደሙ ያብቃን መልካም የደመራ እና የመስቀል ይሁንላችሁ ?
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago