ကြော်ငြာများထည့်သွင်းလိုပါက ဒီအကောင့်ကိုဆက်သွယ်ပေးပါ👇👇
@sithuaung2006
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ကြော်ငြာထည့်သွင်းလိုပါက
@sithuaung2006 တခြားအကောင့်လုံးဝမသုံးပါ
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ကြော်ငြာများထည့်သွင်းလိုပါက ဒီအကောင့်ကိုဆက်သွယ်ပေးပါ👇👇
@sithuaung2006
Last updated 6 days ago
*❤️?*?✝
"እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ
የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"ሉቃ.2፥10-11
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ መልካም በዓል ይሁንላችሁ
ʟɪᴛᴛʟᴇ ᴛʜᴏᴜɢʜᴛs? (ᴇᴜᴘʜᴏʀɪᴀ?)**
ለSecret Friend Gift እንሰጣጥ የነበረው Mood'ስ?*❤️ ❄️*?**
ʙᴇᴛᴏᴄʜ?
ፍቅር ይዟቹ ያውቃል?
የኛ waveroch በቀጣይ be like:-
የአህያን ስጋ ከበሬ የሚለዩበት Appሊንክ ለማግኘት ከስር ያለውን ይጫኑ?????
❤️ፍቅር ሲፈርድ ?
?ክፍል አንድ
በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ ትረካ
ሳራ ትባላለች የሀረር ልጅ ናት እዚህ ከተማችን አዲስ አበባ መኖር የጀመረችው አባቷ በስራ ምክንያት ሀረርን ለቆ ሸገር ሲገባ ነው ... ታድያ ሳራ እድሜዋ 13ን ሲያልፍና ከህፃንነት ወደ ታዳጊ ወጣት ስትሸጋገር ውበቷ እንደልጅነቷ እዩኝ እዩኝ አይልም ነበር ሳራ በአንፃሩ ... አፍንጫዋ ጎራዳ ፀጉሯ ገባ ገባ ያለ ከመሆንም አልፎ ከርዳዳና ከለሯ የቀይ ዳማ የማይሉት ወደ ነጭነት ያደላ ነበር በዚህም ሁሌም ቢሆን ከቆንጆዋ የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ቤቲ ጋር ስትሆን ብዙ ተማሪዎች ሙድ ይይዙባት ነበር ...
ሳራ በራሷ የማትተማመን ሴት ናት 7ኛ ክፍልን ተፈትነው ክረምት ሲገባ ሳራ ደስታዋ ወደር አልነበረውም ከቤት ለመውጣት ምክንያቷ ትምህርት ስለነበር ትምህርት አለመኖሩ ለሷ ትልቅ ደስታ ነው አባቷ ይህን ቢያውቅም ምንም ማድረግ አልቻለም እናቷን አታውቃትም ይሄ ተፅኖ አሳድሮባት ይሆናል ሲል አባቷ በስተርጅና ሚስት ለማግባት ወስኖ አንዲት በእድሜ በሰል ያለች ግን ስራዋ ገና የሀያቤቶች መጀመርያ ላይ ያለች ልጃገረድ የምትመስል ሴት አመጣ ... መጀመርያ ያየቻት ቀን ሳራ ደስ አላላትም ቢሆንም ግን አባቷን ስለምታከብር በይሁንታ ተቀበለች...
ወራቶች አለፉ የስምንተኛ ክፍል ሩብ አመት ፈተና ደርሶ ሳራ ለሊት ተነስታ ለማጥናት ከመተኛ ክፍሏ ወደሳሎን አመራችና መብራቱን አበራች ይሄኔ ያየችውን ማመን አልቻለችም አባቷ በደም ተነክሮ መሃል ወለሉ ላይ ተዘርሯል የእንጀራ እናቷ ማርታ አፏ ታፍኖ ከበሩ ስር ካለው አግዳሚ ላይ ታስራለች ... ሳራ መጮህ ጠፋባት ድንጋጤ ጭር ካለው ለሊት ጋር ተደምሮ በፍርሃት ራደች አባ ብላ ልትቀሰቅሰው ሞከረች ግን ያለናት ያሳደጋት አባቷ ላይመለስ እስከወዲያኛው አሸልቧል ...
ሳራ የአባቷ ገዳዮች ሌቦች እንደሆኑ ፖሊስ መረመርኩ ሲል አሳወቃት ውስጧ ግን አንድ ነገር ይላታል የእንጀራ እናትሽ ማርታ እንዴት ተረፈች ስለምንስ ይህ ሁሉ ሲፈፀም ድምፅ አልሰማሁም ቤት ውስጥም የጠፋ አንድም ንብረት የለም ይህ ሁሉ ፈች አልባ እንቆቅልሽ በሳራ አይምሮ ውስጥ ይመላለሳል የአባቷ አርባ አልፎ ትምህርቷን ቀጠለች የእንጀራ እናቷ ማርታም እንደእናት ሆኜ አስተምራለው ስትል ቃል ገብታ ኑሮ ቀጠለ... ሳራ ህልሟ አንድ ሆነ ተምራ ስትጨርስ የተበዳዮች ጠበቃ መሆን ህግ አጥንቶ ወንጀለኛን ፈልፍሎ ለህግ ማቅረብ!!!
ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ሀሙስ ቀን እሷና ቆንጂዬዋ ጓደኛዋ ቤቲ ወደቤት እያመሩ ሳለ የግቢው ቆንጆና ቀለሜ ተማሪ ቤቲን ለመጀንጀን ወደነሱ ተጠግቶ ሰላምታ ሰጣቸውና ተቀላቀለ ... ሶስቱም ስለትምህርት ሲያነሱ ና ስለወደፊት እቅዳቸው ሲነጋገሩ በመሀልም ቀልድ ቢጤ ጣል ሲያደርጉ ሰፈራቸው ደርሰው መለያየት ግድ ሆነና ወደየቤታቸው ሄዱ ... በሁለተኛውም ቀን አንድላይ ሄዱ ከዛማ ሶስቱም ጥሩ ጓደኛሞች ለመሆን በቁ...
ይህ በዚ ብቻ አላበቃም ልኡል በቤቲ ውጫዊ ውበት ተማርኮ የነበር ቢሆንም ሳያስበው ለካ ሳራን ወዷታል ሳራ ስትስቅ ስታወራ ስታኮርፍ ... ብቻ ምንም ስትሆን ለሱ ስሜት ይሰጠዋል ካላገኛት ይከፋዋል ይህን ስሜቱን ግን ሸሽጎ መዝለቅ አልቻለም ለሳራ ፊት ለፊት ከምነግራት ብሎ ለቤቲ እንድትነግርለት ነገራት ይሄኔ ቤቲ በጓደኛዋ መበለጧ ውስጧን ቅናት አናወፀው እሷ ቆንጆ ሆና በልኡል ሳትፈቀር ሳራ መፈቀሯ አበሳጫት ... ሳራንም ከዚ ልጅ ጋር መሄድ እናቁም ስትል ስለሱ መጥፎ ነገር አልፎም በመልኳ እንደሚቀልድ ነገረቻት ሳራም ቤቲና ታምናትና ትወዳት ስለነበር ልኡልን አይንህን ላፈር አለችው ልኡልም ቤቲን ምን ሆና ነው ብሎ ሲጠይቅ እንዴት የፍቅር ጥያቄ ይጠይቀኛል ብላ ነው ስትል አራራቀቻቸው ... በትምህርቱ ጎበዝ የነበረ ልጅ ፈዘዘ ሳራም ልኡልን እንደወደደችው የገባት ሲራራቁ ኖሮ መልኳን የፈጠረውንና አባቷን ያሳጣትን አምላክ እያማረረችና የማታውቃትን እናቷ ፎቶ ላይ አፍጥጣ ማደር ጀመረች...
አንድ እለት ሳራ ትምህርት ቤት ሄዳ ራሷን በጣም ሲያማት ግማሽ ቀን ላይ አስፈቅዳ ወደቤት አመራች የውጪው በር በሰራተኛ ተከፍቶላት ገብታ በረንዳ ላይ ጫማዋን ስታወልቅ ቤት ውስጥ ብዙ ሰው እንዳለ ተረዳች ይሄኔ ድንገት አንድ አረፍተ ነገር ጆሮዋ ውስጥ ጥልቅ አለ "እሷንም እንዳባቷ ቀብረን በነፃነት እንኖራለን!!" ካካካካ( እረጅም ሳቅ)
ክፍል 2⃣እንዲቀጥል Share and Like አይርሱ????
ကြော်ငြာများထည့်သွင်းလိုပါက ဒီအကောင့်ကိုဆက်သွယ်ပေးပါ👇👇
@sithuaung2006
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ကြော်ငြာထည့်သွင်းလိုပါက
@sithuaung2006 တခြားအကောင့်လုံးဝမသုံးပါ
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ကြော်ငြာများထည့်သွင်းလိုပါက ဒီအကောင့်ကိုဆက်သွယ်ပေးပါ👇👇
@sithuaung2006
Last updated 6 days ago