የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc
ሀሊማ
??????
ክፍል 12
፡
፡
...ሰሚራ የከድርን አፍ አፍ እያየች የሚለውን እየጠበቀች ነው ከድር
ግን አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳይል ወደ መኝታ ቤት ሄደ ሰሚራ
በጣም ከፋት ዝም ከማለት ውጪ አማራጭ የላትም ጭለማው
አልፎ በብርሀን ተተካ ሀሊማ እህትና ወንድሟን ለትምህርት ቤት
አዘጋጅታ እሷም ተዘጋጅታ ሁሉም በአንድ ላይ ቁርስ በልተው
ሀሊማ እህትና ወንድሟን ይዛ ወጣች ሰሚራ በድጋሚ ልጠይቀው
ፈልጋ ነበር ግን ሊመልስልኝ ይችላል ብላ ዝም አለች ከአሁን
አሁን ምን ተናገረ እያለች ስትጠብቅ እሱም ልብሱን ቀያይሮ ደና
ዋይ ብሏት ወጣ ምንም ሳትመልስለት በዝምታ በአይኗ ሸኘችው
............
እነ ሀሊማ ከትምህርት ቤት መምጫቸው ደርሷል ሰሚራ አንድ
ነገር አስባለች ........ እነ ሀሊማ አስኪመለሱ ያላትን ሞያ
ተጠቅማ ቆንጆ ምግብ ሰርታ ጠበቀቻቸው እነ ሀሊማ ሲመለሱ
በሞቀ ፈገግታ ተቀበለቻቸው ሀሊማ ግን ፈገግታውን
አሎደደችውም ያለመደባትን ብላ ግራ ገባት በውስጧ ምን ተገኘ
እያለች አሰበች በሰአቱ ሀሊማ የ 10 ክፍል ማትሪክ ፈተና ልቶስድ
2 ወር ብቻ ነበር የቀራት ሰሚራ የሚበሉትን አቀረበችላቸው::
ሀሊማ.....እኔ አቀርበው ነበር እኮ ለምን ተቸገርሽ......ስለደከመሽ ብዬ ነው ምን ነው ችግር አለው?......ኧረ የለውም ብላ መመገብ ጀመረች:: በጣም ይጣፍጣል
አለቻት ሀሊማ ሰሚራ በአድናቆቱ ተደሰተች መሀመድ እና ሀያት
በልተው ወደ ቁርአን ቤት ለመሄድ ወጡ ሀሊማም እነሱን ተከትላ
ለመውጣት ስትነሳ አንዴ ሀሊማ የአንድ የማናግርሽ ነገር አለ
እነሱ ይሂዱ አለቻት ሀሊማም እሺ ብላ እንዲሄዱ ነግራቸው እሷ
ተቀመጠች......ምንድን ነው ንገሪኝ እየሰማሁሽ ነው....እሺ እነግርሻለሁ ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ካቀረቀረችበት ቀና
ብላ እኔ እና አባትሽ አንድ ላይ መኖር ከጀመርን ረጅም ጊዜ
ሆኖናል እና.... ብላ ዝም አለች......እና ምን እናእማ ለእኔ ልጅ ለእናንተ ደግሞ ታናሽ ወንድም
ያስፈልጋችኃል.......ታዲያ እኔ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልጊው.... ከእኔ ይልቅ አባትሽ አንቺን ስለሚሰማሽ እንድትጠይቂው ነው...ምን ብዬ....ልጅ ወለዱ በይው...ምን እንዴት ነው እንደዚህ የምለው ብላ አፈጠጠችባት ሀሊማ
እናቷ እንደሞተች እንደማታውቅ ለማስመሰል እየሞከረች... እናቴስ እሷ እያለች እንዴት ነው ከአንቺ እንዲወልድ
የምጠይቀው ደግሞ ምን ያህል ሀራም እንደሆነ አታውቂም እንዴ
ብላ በንዴት ተናገረቻት ስሚኝ ድጋሚ እንደዚህ አይነት ነገር
እንዳትጠይቂኝ ብላት ወጣች ፡፡
ሰሚራ ያሰበችው ባለመሳካቱ ተበሳጨች እንጂ የሀሊማ ንግግር
ምንም አልመሰላትም ተስፋ ሳትቆርጥ የመጨረሻ እድሏን
ለመመኮር ወሰነችከድር ሌላ ቀን ከሚመጣበት ሰአት አርፎዶዋል
ሀሊማ እና ሰሚራ ሲቀሩ ሌሎቹ ተኝተዋል ሀሊማም መጠበቅ
እያቃታት ነው ወደ ክፍሏ ገባች ለሰሚራ ከአሰበችው በላይ እቅዷ
እየተሳካ ነው ሀሊማ መተኛቷን ካረጋገጠች በኃላ መጀመሪያውኑም
ሳሎን ቤቱንም መኝታ ቤቱንም ከሌላ ግዜ በተለየ አሳምራዋለች
በተለይ መኝታ ቤቱን አልጋውን ቆንጆ አድርጋ አስተካክላዋለች
ፍዝዝ ያለ አንፖል ብቻ ለመኝታ ቤቱ ውበት ይሰጠዋል ያለችውን
ነገር ሁሉ አድርጋለች ሀሊማ እንደተኛች ሰሚራ አሪፍ የምትለውን
ቀሚስ ለብሳ መልኳን ይበልጥ ጎላ ብሎ እንዲታይ የተወሰነ
ሜካፕ ተቀብታለች በጣም አምሮባታል ጨራርሳ ከድርን መጠበቅ
ጀመረች..... ብዙም ሳይቆይ ከድር በሩን ከፍቶ ገባ........ከምንመ ግዜውም በላይ በፈገግታ ተቀበለችው ከድርም ሲያያት
በጣም ደሰ አለው የሰራችውን አሪፍ እራት አቀረበችለት ደስ
እያለው በላ ሰሚራ ያሰበችወ ለማሳካት ግማሽ መንገድ ሄዳለች
ሌላው ቢቀር ዛሬ ፊት አነሳትም የተቀባችው ሽቶ ከ እሩቁ ይስባል
ከድር በልቶ ሲጨርስ እቃውን አነሳስታ አጠገቡ ተቀመጠች
ሁለቱም ዝም ተባባሉ ሰሚራ ወሬ ለመፍጠር ያህል...ስራ እንዴት ነበር ብላ ጠየቀችው.....አሪፍ ነበር.....በሰላም ነው የቆየኃው....አው ያልጨረስኩት ስራ ነበር አላት
ሌላ የምታወራውን ነገር ማሠብ ጀመረች......ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንዲህ ያማረብሽ ከድር ነበር ያለው
ሰሚራም ትንሽ ሰአት ዝም ካለች በኃላ አው ሁሉም ነገር እንደ
ድሮ እንዲሆን ፈልጌ ነው ብላ የተወሰነ ወደ ከድር ጠጋ አለች
እሱም ወደ እሷ ጠጋ ብሎ ጥሩ ሀሳብ ነው አላት ሰሚራ በመልሱ
በጣም ተደሰተች ከድር እኔም ተስማምቻለሁ ብሎ አቀፋት ሰሚራ
ከከድር እቅፍ ውስጥ ሳቶጣ እሱም እንዳቀፋት ለ እረጅም ሰአት
ቆዮ ዛሬ አተኛም እንዴ ኧረ እተኛለሁ ቡሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ
ወደ መኝታ ቤት ለመሄድ አንድ እግሩን ሲያነሳ ሰሚራ እጁን ጎትታ
አስቀመጠችወ ደንግጦ ተቀምጦ ወደ ሰሚራ ሲዞር ሳያስበው
ሰሚራ ግጥም አድርጋ ሳመችው ከድር የተደበላለቀ ስሜት
ተሰማው ደንግጦ ስለ ነበር የሚላት ነገር ጠፋው እንደመጣለት
ተናገራት
...... ምን ማድረግሽ ነው እንደ ድሮ እንሁን ማለት በእንደዚህ
አይነት ሁኔታ ከሆነ እንደመጀመሪያችን ብንሆን ነው የሚሻለን
ብሏት እንደተቀመጠች ትቷት ወደ መኝታ ቤት ገባ እንደዛ ለፍታ
ያስተካከለችውን መኝታ ቤት በአትኩሮት እንኳ ሳይመለከተው
ልብሱን ቀያይሮ ሳሎን ቤት ተኛ ሰሚራ የመጨረሻ እድሏን
ሞክራለች ቅስሟ ተሰባበረ መኝታ ቤት ገብታ ከልቧ አለቀሰች
ሰሚራ እንደዛ ቀን ከፍቷት አያውቅም........
ሰሚራ ተስፋ ቆርጣ መኖር ጀምራለች ሀሊማ ለሰሚራም
ለከድርም ከመጀመሪያው በላይ ጥሩ እየሆነች ነው ከድር እና
ሰሚራም እንደ በፊቱ ናቸው ሀሊማ 10 እና11 ክፍልን በጥሩ
ወጤት አልፍለች ሀያትና መሀመድም እንደዛው ሀሊማ በአሁኑ
ሰአት የ 12 ክፍልማትሪክ ፈተና ተፈትና ወጤት እየጠበቀች
ነው..........
.......... ይቀጥላል........
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
ኸሚስ ምሽት
Usman የኸሚሱ ወዳጄ?
ቡናዉን ባልጠጣም
እንቅልፌ አይመጣም
እኔ 'ምፈልገዉ
ኸሚስ ምሽቱን
ካንቺ ጋር ማጣጣም
ሚስቴ??
ሰላምህ ይብዛ ብለናን ሰሚር አሚ?
ለይለተል ጁሙዓ ?
ምርጥ ምርጥ ኢስላማዊ ጵሮፋይ &
ዌልጴጰር ከፈለጉ join በሉ
ISLAMIC WALLPAPER
ISLAMIC PHOTOS
ISLAMIC PERILS
FOR THIS CHANNEL
?????????
ሀሊማ
??????
ክፍል 11
፡
፡
ሀሊማ ድንገት ወደ ፈጡማ ስትዞር የፋጡማ አይን
ፈጦዋል ሀሊማ ደንግጣ ባባ አክስቴን ተመልከታት ብላ ጮኃችበት
ከድር በጣም ደንግጦ ፋጡማ .....እህት ፋጡማ እያለ ጮኃ
ፋጡማ ግን እስከመጨረሻ አሸልባለች ከድር አይኗን ገርበብ
አደረገላት ሀሊማ ባባ ምን እያደረክ ነው ልጄ አይዞሽ እኔ ከጎንሽ
አለሁ ምን እያልከኝ ነው አክስትሽን ድጋሚ አናገኛትም ሞታለች
አላት ሀሊማ የሰማችውን መቋቋም አቅቷት እራሷን ስታ ወደቀች
ከድር የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው ባንድ በኩል የፋጡማ ሬሳ
አለ በሌላ በኩል ልጁ እራሷን ስታ ወድቃለች ሰሚራ ጋር ደውሎ
እንድትረዳው ጠየቃት ግን እንደ እድል ሆኖ ሰሚራ የፋጡማን ቤት
አታውቀውም በምልክት እንድትመጣ ነገራት ሰሚራም ታክሲ
ተኮናትራ ከከድር ጋር እየተደዋወለች በምልክት ደረሰች ከድር ከ
እቤት ወጥቶ ተቀበሏት አንድ ላይ ወደ ቤቱ ገቡ ሀሊማ ልትነቃ
ስላልቻለች ከድር አቅፎ ወደ ሀኪም ቤት ይዟት ሄደ፡፡
ሰሚራ ከፋጡማ ጋር ብቻዋን ነች በጣም ፈርታታለች ልትቀርባት
አልቻለችም ፋጡማ የቀረ ዘመድ የላትም ሰሚራ ለጥቂት ግዜ
ተረጋግታ አስባ አንድ ሀሳብ መጣላት የፋጡማ ጎረቤቶች ጋር
ሄዶ መናገር ወዲያው ከ ቤቱ ወጥታ ለተወሰነ ሰው ተናገረች
የሰፈሩ ሰው ተባብሮ ድንኳን ተደኮነ ሬሳውንም እንዲከፈን
ተደርገ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታ እየያዘ ነው በዚህ መሀል ግን
ሰሚራ እንደዛ በብጣሽ ጨርቅ ጠቅልላ የጣለችው ሬሳ ትዝ
አላት ስራዋ ለእራሷ ቀፈፋት አሁን ቢቀፋትም ባይቀፋትም ከ
አለፈ ወዲያ ምን ያደርጋል ......
ሀሊማ ከተወሰነ ሰአት በኃላ ነቃች ከድር ትንሽ ሰላም ተሰማው
ወዲያውኑ ዶክተሩን ጠራው ዶክተሩም የተወሰነ ነገር ቼክ
ካደረገ በኃላ ከድርን 1 ውጪ ላናግርህ ብሎ አብረው ከክፍሉ
ወጡ በሩን ጠጋ አድርጎላት መነጋገር ጀመሩ ያን ያህል አደጋ
ላይ ሊጥላት የሚችል ነገር የለም አንዳንድ ሰው ከመጠን ያለፈ
ደስታ እና ሀዘን ሲያጋጥመው መቋቋም ያቅተውና እንደዚህ
አይነት ችግር ሊፈጠር ይችላል ብሎ ዶክተሩ ለ ከድር ይነግረዋል
የተወሰነ ሰአት እረፍት ታድርግና ትወጣለች ብሎ ዶክተሩ ከድርን
ተሰናብቶ ይሄዳል ከድር የሀሊማን ጉዳይ ከሰማ በኃላ ወደ
ሰሚራ ጋር ይደውላል ሰሚራ ከሰፈር ሰዎች ጋር አንዳንድ
ነገሮችነ ነው 6፡00 ይላል ሰአቱ የዝሁር ሰላት ሰአት እየደረሰ
ነው ከድር ከሀኪም ቤቱ አሁን ካሎጣ ሰአቱ ይሄዳል ሀሊማንም
ጥሎ መሄድ አይችልም ከድር ወዲያውኑ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ሄዶ
ለዶክተሩ ሁኔታውን አሰረዳው ዶክተሩም ሀሊማን ይዟት እንዲሄድ
ፈቀደለት ከድር ዶክተሩን አመስግኖ ያለበትን ሂሳብ ከፍሎ
ሀሊማን ይዞ ወደ ፋጡማ ቤት መሄድ ጀመሩ የሰሚራን ጩኃት
እያሰበ ነው እስከ አሁን ብቻዋን እንደሆነች ነው የሚያውቀው
ወደ ፋጡማ ቤት የሚወስደው ቅያስ ጋር ሲደርስ ሀሊማ
በድጋሚ እራሷን እንዳትስት ፈራ ሰአቱ 6፡25 ይላል ወደ እቤት
ላድርሷት ቢል እንኳ ሰአቱ አይበቃውም አማራጭ ስለሌለው
ሀሊማን ወደ ፋጡማ ቤትይዟት መሄዱን ቀጠለ ቤት ሲደርሱ
ድንኳን ተደኩኖ ያያል ማን እንዲህ እንዳደረገ ለማወቅ በፍጥነት
ወደ ውስጥ ገባ ጭራሽ ያልጠበቀው ነገር ነበር ሀሊማ አካሏ
ነው እንጂ የለችም ማለት ይቻላል ወደ ወስጥ ሲገባ
የሚያለቅስ ሰው ምግብ የሚሰራ ሰው ብቻ ግቢው በሰው
ተሞልቶ ከድር በጣም በተገረመ ሁኔታ ያያል የሰውን ሁኔታ ሲያይ
እሱም ሚስቱ ትዝ አለችው አንገቱን ደፍቶ ወደ ውስጥ ገባ
ሰሚራን በአይኑ መፈለግ ጀመረ ሰሚራ አይታው ስለነበር ወደ
ከድር መጣች ከድር ሰሚራን እንዳገኛት በቅድሚያ የጠየቃት
ስለ ፋጡማ ሬሳ ነበር ሁሉንም ነገር ነገረችው እና ሬሳውም
መስጅድ ወስጥ እንዳለ ነገረችው ሀሊማን ወደ መስጅድ ይዟት
ሄዶ እንድትሰናበታት አደረገ ከዝሁር ሰላት በኃላ ተሰግዶባት
ተቀበረች...........
ሰው ትንሽ ቀዝቀዝ ብሏል ከድር ሀለቱን ለጆቹን ይዞ መጣ
ሁሉም አንድ ላይ ናቸው ሀሊማን ከፋጡማ ሞት ይልቅ የእናቷ
አሟሟት ነው ይበልጥ የጎዳት በስርአቱ እንኳን
አልተለቀሰላትም.....
በዛ ላይ አንድ አለችኝ የምትላት ፋጡማን መጣቷ ጓደኛዋ እናቷ
አክስቷ በቃ ሀሉ ነገሯ ነበረች ሀሊማ አሁን ከምንም ጊዜውም
በላይ ብቸኝነት ተሰማት.....
፡
፡
፡
ዛሬ ፋጡማ ከሞተች ሶስተኛ ቀኗ ነው እንደመጀመሪያው ቀን
የሰፈሩ ሰው በጋራ ሆነው ድንኳኑን አፈረሱት ሀሊማ ሀዘኑን
ለመርሳት እየሞከረችነው ጠንካራ ለመሆን እየጣረች ነው የ
አክስቷን አላማ ለማሳካት ወስናለች ከ ሳምንት በኃላ እነ ከድር
ወደ እቤታቸው ተመለሱ ሀሊማ ሀዘኑ አለቀቃትም ለ እህትና
ለወንድሟ ብላ ጠንካራ መሆን አለባት እሱን እያሰበች ጠንካራ
ለመሆን እየሞከረች ነው ክረምት አልፎ በጋ እየመጣ ነው
ሀሊማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታለች እህትና
ወንድሞቿም ትምህርት ጀምረዋል ሀሊማ በመጀመሪያ
ሴሜስተር የትምህርት ቤቱ የመጀመሪያው ነጥብ የእሷ ነበር
አባቷ በሀሊማ ውጤት በጣም ተደሰተ የሀሊማ ወንድም እና
እህትም ሀያትና መሀመድ 1ኛ እና 2ኛ ወጡ ይህ ውጤት
የሀሊማ የልፍት ውጤት ነው ሁለቱም ሀሊማን እንደ እናትም
እንደ እህትም ነው የሚያዮዋት እሷም ቢሆን የእናትነቱም
የእህትነቱን ሀላፊነት በሚገባ ትወጣዋለች ሀሊማ ለሰሚራ
ከምንም ግዜ በላይ ጥሩ እየሆነችላት ነው እናቷ የምታደርጋቸው
ነገሮችን ሀሊማም እያደረገች ነው፡፡ ሰሚራ በስራዋ እንድትፀፀት
እያደረገቻት , በይበልጥ ደግሞ ህሊነዋ እንዲወቅሳት
እያደረገቻት ነው ለከድርንም ቢሆን አንድ አይነት ነገር
እያደረችው ነው ሰሚራ በከድር ልጆች የቀናች ይመስላል ከድር
ከስራ እስኪመለስ ጠብቃ እራት በልተው ጨርሰው ሁሉም ተኙ
ከድር እና ሰሚራ ብቻ ሲቀሩ ከድር ከድር አለችው ለዘብ ባለ
ድምፅ አቤት አንድ ጥያቄ ለጠይቅህ ነበር ምንድ ነው ጠይቂኛ
እኔ ለ አንተ ምንህ ነኝ?
ዝም አላት ብትጠብቅ መልስ የለም እሺ አትመልስለኝ ግን ልጅ
መውለድ እፈልጋለሁ ቢያንስ ይሄን መልስልኝ......
.......... ይቀጥላል........
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
እንዲቀልህ 18
??ለሚሉት አትሸበር ከቁም ነገሩ ተጠጋ ዝምታ አይስበርህ <ወንድ ልጅ ጀግና ነው> ብለው አያድክሙህ <በሆዱ ነው> ብለው አያስንፉህ ሳይገባህ መዳኛህን እንዲያርቁ አትፍቀድላቸው!! ወንድ ልጅም ሰው ነው ያለቅሳል እኮ! አልቅስ... ህመምህን አውራ.... ችግርህን ተናገር... አንተ ዘንድ ያጣኸውን መፍትሄ ሌሎች ዘንድም ፈልግ... ዝምታም ሲበዛ ገዳይ ነው... እንባህ ላይ ጠንክርልኝ።
Ami
??ውዶቼ ተመልሻለው በልብ ከልቤ ለተዋወሳችሁኝ ሁሉ አመሰግናለው??... ከዛሬ ጀምሮ በአብሮነት የምንቀጥል ይሆናል #እንዲቀልሽ 18ን ከደቂቃዎች ቡሀላ አስነብባችዃለው።
Semir ami
ሀሊማ
??????
ክፍል 10
፡
፡
....ሀሊማ ቀጥታ ወደ ትምህርት ቤት ነበር የሄደችው ትምህርት
ቤት እንደደረሰች መምህራኖቹ አልመጡም ነበር ሁሉም ተማሪ
ተሰብስቦ እየጠበቃቸው ነው፡፡ ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ መምህራን
መምጣት ጀመሩ ሁሉም ተማሪ በየ ክፍሉ እንዲገባ ተደረገ
ሀሊማ እንደ ወትሮዋ ብቻዋን ናት እሷም ወደ ክፍልገባች
ትምህርት ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውጤት ታመጣለች ተብላ
የምትጠበቀው ሀናን የምትባል ልጅ ብቻ ነች ከ አባቷ ጋር
የመጣችው ሀናን የነ ሀሊማ ክፍል ተማሪ ነች ውጤት መሰጠት
ተጀምሮዋል እንደተጠበቀውም ሀናን 91.9 ነጥብ አመጣች
ሁሉም አጨበጨቡ እነ ሀሊማ ክፍል ለሁሉም ተሰጥቶ አለቀ ከ
ሀሊማ ውጪ አስተማሪው ሀሊማን በደንብ አያውቃትም ሁሉም
ካለቀ በኃላ የ እኔስ ወጤት ብላ አስተማሪውን ጠየቀችው
አልደረሰኝም ለወደቁ ተማሪዎች አዳራሽ ነው የሚሠጠው አላት
ሀሊማ በጣም ደነገጠች የ አክስቷን ምክር አስታወሰች
እየደበራት ወደ አዳራሽ ሄደች ሁሉም ክፍል ተሰጥቶ ካለቀ በኃላ
ሀሉም ተማሪ ወደ አዳራሽ እንዲገባ ተደረገ ከትንሽ ደቂቃዎች
ቆይታ በኃላ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ንግግር ማድረግ ጀመረ
በዛሬው ቀን የልፋታቹን ውጤት ያገኛችሁበት ቀን ነው
አብዛኞቻቹ እንዳለፋቹ ይታወቃል ለሚቀጥለው ከዚህ የተሻለ
እንደምታመጡ ተስፋ እናደርጋለን የወደቃቹ ተማሪዎች በዚህ
ውጤት ተምራቹ ለሚቀጥለው አመት በቁረጠኝነት ሰርታቹ አሪፍ
ወጤት ለማምጣት ሞክሩ ዛሬ እዚህ አንድትሰበሰቡ ያደረግናቹ
በጣም የገረመን የሚገርም ነገር ስላጋጠመን ነው አስተማሪዎች
አናውቃትም ስላሉ በግሏ ክፍል ውስጥ እንዲሰጣት ስላልፈለግን
እና እኛም ቢሆን ተማሪዋን ማወቅ ስለፈለግን እዚህ መድረክ
ላይ መጥታ ውጤቷን እንድትቀበል ብለን ነው ፡፡....ብለው የተማሪዋን ስም ለመናገር ጎሮሮአቸውን ሲጠራርጉ
መብራት ሄደ የተወሰነ ሰአት ጠብቀው ጄኔኔተር ተገጥሞ
በድጋሚ ለመናገር ጎሮሮውን ጠራርጎ መናገር ጀመረ እሺ
እባካችሁን አንዴ ጆሮአቹን ስጡኝ አዳራሹ በዝምታ ተዋጠ
ሀሊማ ማን ትሁን እያለች በጉጉት እየጠበቀች ነው እሷ ብቻ
ሳትሆን ተማሪው በሙሉ እየጠበቀ ነው እሺ ብሎ መናገሩን
ቀጠለ ተማሪ ሀሊማ ከድር ብሎ ተናገረ፡፡ ተማሪው ማንሾካሸክ
ጀመረ ማን ናት እያለ እባክሽ ሀሊማ ወደ መድረኩ ተማሪው
ማጨብጨብ ጀመረ ሀሊማ ግን ደንግጣ ከተቀመጠችበት
አልተነሳችም እባክሽን ሀሊማ በድጋሚ ሲናገር ሀሊማ
ከተቀመጠችበት ወንበር ተነስታ ወደ መድረኩ ሄጀች ሁሉም
ያልጠበቁት ነገር ነው ትምህርት ቤታችን እስከ ዛሬዋ እለት
እንደዚህ አይነት ወጤት አስመዝግቦ አያውቅም ሀሊማ
የመጀመሪያዋ ናት ያመጣችው ነጥብ 99.9 ሁሉም ተማሪ
ተነስቶ አጨበጨበላት ከ ሀናን ውጪ ሁሉም ተደስቷል
ትምህርት ቤቱ ያዘጋጀላትን ሽልማት ተቀብላ ከመድረክ ላይ
ወረደች
አስተማሪዎቿ እየመጡ ይስሟታል ሀሊማ ከትምህርት ቤቱ
ወጥታ ፋጡማ ጋር እስክትሄድ በጣም ቸኩላለች ሁሉም ተማሪ
ወደ እቤቱ ሲሄድ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሀሊማን ወደ ቢሮ
እንድትመጣ አድርጎ አድንቆቱን ገለፀላት ከቢሮ ወጥታ ቀጥታ
ወደ ፋጡማ ቤት ሄደች እንደደረሰችም በሩን ለረጅም ሰአት
አንኳኳች ግን አልተከፈተም ልትሄድ ስትል ፍጡማ ያላትን
ጉልበት ተጠቅማ በሩን ከፈተችላት ሀሊማ ፍልቅልቅ እያለች
ሳመቻትና ወደ ውስጥ ገባች ምነው አክስቴ በጣም አመመሽ
እንዴ አንገቷን እየነቀነቀች መታመሟን ነገረቻት
ዛ..ሬ...ም...ን..ድ..ነ...ው..እ..ን..ዲ.ያ...ስ..ደ..ተ..ሽ ልጄ
ብላ ጠየቀቻት የሆነውን ነገረቻት ፍጡማ ወደ እራሷ ሳብ አድርጋ
አቅፋ ሳመቻት ፋጡማ ከድርን ጥሪው አለቻት አይሆንም ብላ
ተከራከረቻት ስትለምናት እሺ ብላ ደወለችለት ባባ አክስቴ
ትፈልግሀለች እሺ መጣሁ ብሎ ስልኩ ተዘጋ ከድር ብዙም
ሳይቆይ መጣ ሰላም ብሏቸው ተቀመጠ ሀሊማን ሱቅ ላከቻት
ከከድር ጋር ለማውራት እና ሁሉንም ነገር ልትነግረው አስባ ነበር
ግን አንዳሰበችው አልሆነም ሀሊማ ከተላከችበት ቦታ በፍጥነት
ተመለሰች የፈጡማ እግር ጋር ተቀመጠች፡፡ ፋጡማ በድጋሚ
ተነሺ ማለት ከበዳት ትንፋሿ እየተቆራረጠ ነው ሀሊማም ሆነ
ከድርም አልተረዷትም ነበር ልትሞት እንደሆነ ታውቋታል ለከድር
ለመንገር የፈለገችው ለዚህም ነው ግን መናገር አልቻለችም
ፋጡማ እጃን ዘርግታ ሀሊማ ወደ እራሷ እንድትመጣ አድርጋ
ሳመቻት የሀሊማን እጅ ለ ከድር አስጨበጠችው ብቻዋን
እንዳትተዋት አደራ አለችው አክስቴ ለምንድ ነው እንደዚህ
የምትይው የተነጋገርነውስ ነገርስ አክስቴ ከድር የሀሊማን እጅ
ይዞ እንዲህ አይባልም ልጄ እያለ እያወራት ሳለ ፋጡማ ወደ
ማይቀርበት አለም አለም ወደ አሄራ ሄደች ሀሊማና ከድር
ፋጡማ እንደሞተች አላወቁም ከድር ከሀሊማ ጋር እያወራ ነው
.......... ይቀጥላል........
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
people don't have to love you
people don't have to like you
they don't even have to respect you
but when you look on the mirror you better love what you see?
@miracule_quote_and_pic
አንዳንድ ጊዜ…
ደህና መሆናቸውን ማወቃችን ብቻ በቂ ነው
@miracule_quote_and_pic
–አዲስ ቻናል ከፍታቹሁ
በአጭር ጊዜ ተከታዮቻችሁን ማብዛት የምትፈልጉ
–እንዲሁም ምርትና አገልግሎታችሁን በዚህ ቻናል ላይ ?
ማስተዋወቅ ለምትፈልጉ
በታላቅ ቅናሽ መጥተናል ??
:-per time ?
⌚️1 hour .................25birr
⌚️6 hour................50Birr
⌚️2 Days..................100 Birr
⌚️1 Week.................250 Birr
በ View??
1k view ? 100 birr
2K view ? 150 birr
3k view ? 200 birr
?በmember??
50 member 80 birr
200 Member 150 birr
400 member 300 birr
500 member 600 birr
?ቻናላችን በመከራየት (አድሚን በመሆን ምርትዎን ለማስተዋወቅ)
በቀን ለመከራየት (24 hr)? 100 birr
ለሳምንት ቀን ለመከራየት ? 300 birr
የፈለጉትን መርጠዉ ያናግሩን ??
Channel
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc