📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc
?ጁመዐዬ?
ስሜት አልባ ቀናት በሀዘን የዋጁ፤
እረፍት አልባ ጊዜያት በድካም 'ሚያስረጁ፤
አለፉ በትላንት ልቤን እንዳጃጁ።
ዛሬ ግን...
ልዩ ነው ድባቡ፣
የጁምአን ማለዳ ማብሰር በሰለዋት፤
እነብዩ ዘንዳ 'እገሌ የእገሌ ልጅ' ተብሎ መጠራት፤
እኚያ ውብ ነብይ ዘንድ ከነአባት መወሳት!
አልፎም
.
.
ጀሊልን ማወደስ፣
ሱራ ካህፍን መቅራት በሰዋብ ማሸብረቅ፤
በሰደቃ ብዛት ጀሊሉ ዘንድ ጎልተን በኸይር ማብረቅረቅ፤
ይሄ ነው ጁምዓ...
ከጌታው የሸሸ ተውባ የሚሻበት፤
ለሱ የቀረበ በእጥፍ ሚሰጥበት፤
በሰለዋት ተምኪን፣
የሚያፈነድቀን፤
የሳምንቱ ውብ ቀን ጁምአ ኢዳችን!
አላሁመሰሊ አላ ሰይዲና ሙሀመድ ወአላ አሊ ሰይዲና ሙሀመድ?
@AlAminAlHadraJemea
@AlAminAlHadraJemea
?بسم. الله الرحمان الرحم?
?አሰላሙዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ?
ኢስላማዊ ግጥም
telegram.me/allahYetNewYalew
?
?ግ ?ጥ?ም?
?የልቤ መሸፈት?
?
?ወደ ሴቶች ማየት ያመጣል መዘዝ?
?መጣስም ነውና የነቢን ትዕዛዝ?
?
?እያሉኝ ነቢዩ ሴትን አትመልከት?
?አምራቸውን ጣስኩት ወደሷ በማየት?
?አመጣብኝ መዘዝ ከዚያም መመልከቴ?
?ልቤም ተረበሸ ተዛባ ህይወቴ??
?ጡማዕኒና አጣው በፈርድ ሰላቴ?
?ከዛሬስ በኋላ ለኔ የሚጠቅመው?
?ተገንዝቤዋለው አንገቴን መድፋት ነው?
?ወደ ሴት ማየቱን ሳየው እንደ ዋዛ?
?ከግዚያት በኋላ ልቤ ቀረች ፈዛ?
?እኔ ላይ አጣሁት የ ኢባዳን ለዛ?
?በኢሞ በታንጎ እንዲሁም በቫይበር?
?ሴትን አንመልከት አላህን እንፈር?
?እባክሽ እህቴ ስምኝ ልምከርሽ?
?ክብርሽ ነውና ላንቺ ሂጃብሽ?
?ላንቺ ሂጃብሽ ነውና ውበትሽ?
?መልቀቅ የሌብሽም በሁሉም ጊዜሽ?
?ይህን ውድ ገላ ማንም እንዳያይሽ?
?ለሌላው ተይና ተዋቢ ለባልሽ?
?ወንድን አትፈትኚ እየ ተገላለጥሽ?
?አላህን ያስቆጣል ይህኛው ስራሽ?
?
?ዋነኛው መንስኤ የልቤ መሸፈት?
?ጠንቅቀሽ እወቂ መሆንሽኝ እህት?
?
?ከላይ እስከ ታቿ ገላዋ ቢሸፈን?
?ልቤም አይሸፍትም እኔም አልፈተን?
?የሷም መገላለጥ አይሆነኝም ዑዝር?
?ስምንት ቁጥሩንም ለብሳ ብትዞር?
?ዱንያ አኼራዬ ሳይወድም ሳይከስር?
?አሁን ቶሎ ብዬ አንገቴን ላቀርቅር☘
☘ሴቶችን እያየው ስሄድም ስመለስ☘
☘ኢማኔ ጎደለ ሲወጣ ቀስ በቀስ?
?ሁል ግዜ መመልከት መዘዝን ያመጣል?
?ወደ አስቀያሚው "ዝሙት" ያደርሳል?
?በጣም ከባድ ነው የዝሙት መንጀል?
?አላህም ነግሮናል እንዳትቀርቡት ሲል?
?
?
?
?አይኖች ያዩትን ልቦች ይመኛሉ?
?ከዚያም ወደ ዝሙት ያቃርባል እያሉ?
?ረሱል አድርሰዋል ለህዝቡ በሙሉ?
?እናንተም ብትሉ እንዴት ያደርሰናል ?
?እኔም ልንገራችሁ ከዚህ በመቀጠል?
?
?እሷም ታየዋለች እሱም ያያታል?
?ከዚያም ረጋ ብሎ ይተዋወቃል?
?ለሀራም ሰላምታ እጁን ይሰጣታል?
?............................ይከታተላታል?
?ቀስ በቀስ እንደዚህ እያለ ይደርሳል?
?ወንድም ልብህ ይሁን ዝሆን የማይጥሰው?
?ለባለ ጉርዳሙ ቦታን እንዳትሰጠው?
?ማግባትም ከፈለክ ኒቃብ ከለበሱት?
?ካንዷ ኒካህ አስረህ ውሰዳት በ ፍጥነት ?
?ኒከውንም ሳታስር አትበል ሞትኩልሻ?
?ይህም ይሆናል የ ዝሙት መድረሻ?
?
?
?ባገኘሃት ቁጥር ሴትን አትመልከት?
?ኢማንህ ይወጣል ሳታየው በፍጥነት➊??______________________________
➊ኢማን ማለት ፦በምላስ ሚነገር
"በልብ የሚቋጠር
"ሚሰራ በተግባር
"በፍጥነት ሚቀንስ ወንጀል ስትዳፈር
"አላህን ስትታዘዝ ካለበት ሚጨምር
________________________________
ሴትን መመልከት መንጀል ነው ፡፡ስለዚህ ወንጀልን በሰራህ ቁጥር (ሴትን በተመለከትክ ቁጥር ኢማን ይደክማል)
---------------------------------
?
?
?በአብዱል ፈታህ(አቡ ያሲር)?
?
?
telegram.me/allahYetNewYalew
ኧረ ማንን ላግባ?
ቴሌ ግራም ቻናል ዋትስ አፕ ፌስ ቡኬ
ጌታዬን ለመንኩት ቆሜ ተንበርክኬ
ጥፋት አታምጡብኝ ያለፈ ከልኬ።
ትገረሙ ይሆን በዚች በርዕሴ
ደካማነት ገፍቶኝ እንዲህ መተንፈሴ
ያስከፋችሁ ይሆን ስጠይቅ ለራሴ?
አስፈለገው ይሆን ግን አቡ ሐኒፋ
ትዳር ላጤ ሆኖ ብቻውን ሲከፋ
በሸይጧን ጉትጎታ በስሜት ሲገፋ
ብሎ ለጠየቀም ምንም አልከፋ
ይህ ባለመሆኑ ብእሬን ደም ያስተፋ
አልቻልኩም ከፍቶኛል እህት ስትገፋ
በአረመኔ ወንዶች ያውም በቀርፋፋ
ብዕሬም ታካፍላቸው ታሪኬን ጨልፋ
ምክር ቢሆናቸው ልናገር በይፋ
ዐቂዳው ብልሹ እውቀቱም ቢሰፋ
ሰለፎችን ጠልቶ ወደደ ፈላስፋ
ስለሱ ልናገር ይድረሰኝ ወረፋ።
ስራዬም አናሳ በዛና ወንጀሌ
ጥሩ ሰው አልቀርብም መጥፎንም በግሌ
መወዳጀት አልችል ይቅር አልባሌ
ብቻዬን ከአላህ ጋር ዘንግቸው መዋሌ
ቢያስከፋኝም ይሁን ይሙላልኝ በቃሌ
ፍፁም ላገልግለው ባሪያው ልሁን ሁሌ።
በዚህ ጥያቄዬ እስኪ አትገረሙ
በውስጣዊ ትኩረት በግል ደጋግሙ
ድጋሜ ጠይቁ ዙሪያውን ገምግሙ
ሌላውን ከመውቀስ ቅድሚያ ተጠቀሙ
ትዳር ቁም ነገር ነው በከንቱ አትድከሙ
ህሌናም ይወቅሳል ጊዜን ተጠቀሙ
ሙከራ አታድርጉት አላህ ፊት ስትቆሙ
ጥያቄው አይቀርም ፍፁም መገምገሙ።
ከሰለፎች መንሐጅ ከሱናው ሳትርቁ
ያለምንም ሐፍረት ሐቅን ሳትደብቁ
ለመሆኑ እናንተ ለትዳር ልትበቁ
ዘንድ እስኪ በአላህ ራስን ጠይቁ
ለራስ ከራሳችሁ መልሱንም እወቁ።
ግራ የገባቸው የኔ አምሳያወቼ
ከራስ ሳይስማሙ ከሰው መች ተመቼ
እኔው ከራሴ ጋር ቅድሚያ ተጣልቼ
ከአላህ ርቄ እስልምናን ትቼ
አኼራን ዘንግቼ ዱኒያን ተጠግቼ
የኔው ጠላት ሆኜ እኔኑ ቀጥቼ
ከኔው ሳልታረቅ ማንንስ አግብቼ
ለኔው ፍቅር ሳልሰጥ ተውሒድ ላይ በርትቼ
ባጠቃላይ ቅድሚያ ከኔው ተጣልቼ
ከማን ጋር ልኖር ነው በትዳር ኮርቼ
ላልለያይ ሁሌም ፍፁም ተስማምቼ?
መልሱ እባካችሁ ይቅር ይህ ዝምታ
እሮሮና ለቅሶ በራስ ላይ ጨዋታ
በዛ በሙስሊሙ ምነው ይህ ቸልታ
ትውልድ መተኪያ በአላህ ችሮታ
ትዳር አልነበር ወይ የሐላል አለኝታ?
ወንዶች እባካችሁ ያዙ ከኔነቴ
ለኔ አትጨነቁ ልማር በጥፋቴ
ትምህርት ውሰዱበት ካለፈ ሂወቴ
ላልጠቅምሽ ቸኩዬ ጎዳሁሽ እህቴ
ለወደፊት ፈራሁ በወንድምነቴ
ማንን ላግባ እያለ ጠየቀ አንደበቴ
አላዋቂ ሳሚ... በዛና ከፊቴ
ከኋላ ቀረሁኝ ባስተዋይነቴ
ልቅደም በዝግታ በዚቹ ትዕግስቴ
አላህ ይረዳኛል ይሳካል ምኞቴ
እቀድማቸዋለሁ በመረጋጋቴ
ጠብቄ ሳቆያት ይችን ውድ ሂወቴ።
ድን ያለው ወራፊ
ጃሂሉም አስከፊ
ትልቁ አንቀላፊ
ዱርዬው ገፋፊ
ትንሹም ጠላፊ
በሆነበት ዘመን ሁሉም ሳይሆን ገፊ
አለፍ አለፍ ብሎ አንዳንዱ ተገፊ
.
.
.
እንደምንም ብለሽ ይህን ቀን እለፊ
ነፍሴ አደራ ባመፅ ጌታን አታስከፊ
በሸይጧን መረብ ውስጥ ከንቱ አትጠለፊ
ጎርፍ ነው በጤና ለቆየው አላፊ
ሐላልን ምረጭ እስኪ አትልከፍከፊ
ዱኒያ ላይ ባይሆንም በጀነት ዝረፊ
ድልቡን ተጋበዥ በእልፍ አሳላፊ።
በመጨረሻም ለወንድሞቼ?፦
ያች ውድ እህትህ አንተን ስታገባ
ከእናት ከወንድሟ ርቃ ካባባ
ሁሉን ተለይታ ከቤትህ ስትገባ
እንባ እየፈሰሳት ሆዷም እየባባ
ፍቅርህ ከሷ ርቆ ልብህ ጥፋት ቀርባ
ሳሎን ግድግዳውን በጥል ስትቀባ
አንዷን አልችል ብለህ ስትሆን ደርባባ
ሰማኋት እህቴን በሱጁድ ላይ ቀርባ
አላህን ስትጠይቅ ኧረ ማንን ላግባ?
አቡ ሐኒፋ ዐብዱልከሪም (ከገጠር)
ሱሴ
ዋትስአፕ ፌስቡኬ ቴሌግራም ቫይበር
ጓደኞቼ ናቸው ትዊተርም ሳይቀር
ስበላ ስጠጣ ካላደረኩኝ ቻት
ምንም ደስ አይለኝ ያስጠላኛል ህይወት
በቴሌግራሙ join አድርጌ likeን እጫንና
በኢሞ እዞራለሁ በዚህም ልዝናና
የፌስቡኬን መልእክት በደንብ እያነበብኩ
ቀኑን እገፋለሁ እንዲህ እያደረኩ
ረባሽም ካለ ቻት ሳደርግ በፌስቡክ
አባርረዋለሁ በቀይ ካርድ በብሎክ
በcomment likeዎቼ እየተደነኩኝ
timeን control ማድረግ ስላቃተኝ
የካርድ እማወጣው ሲበልጥ ከአስቤዛየ
ራሴን ጠየኩኝ ምን ይሻላል ብየ
connection ሲጠፋ እሚያቅበዘብዘኝ
ልለምደው ነው መሰል መተውን መረጥኩኝ
connection ጠፍቷል ፈጣሪ ይመስገን
እባክህ አምላኬ ቴሌንም አጥፋልን
ገጣሚ ሳራ መሀመድ ታህሳስ18/2010ዓ.ል
poetess Sara Mohammed December27/2017
አፍቃሪ ልብ
ይህልቤ አፈቀረ ደጋግሞ ደጋግሞ
በፍቅር ሆስፒታል እስከዛሬ ታሞ
ሊናገር ወስኗል ስሜቱን ሊያስረዳ
እሚሰማ ካለ ፍቅር የሚረዳ
አሁንስ ቆረጠ መብሰልሰል አስጠላው
በፍቅር ምክንያት ሰላም ጤና የለው
እስሁንስ ኑሯል እደው በፀጥታ
ፍቅሩን ሳይነረገር አንድጊዜ ላፍታ
ዝም ብሎ ኖረ እዳው በዝምታ
ፍቅር የሚሉት ነገር በጣም ከባድ እዳ
በጣም ያዳግታል አይገኝ ከሜዳ
✍✍✍ By Aman
ያሻል ብቸኝነት
ከሠው ጋር ከመሆን ያሻል ብቸኝነት
በአንድ ላይ ሆናችሁ ሰውንም ከማማት
እባካችሁ ሠወች ያሻል ብቸኝነት
ላያዋጣ ወሬ አጉል ከመሠብ
እባካችሁ ሰወች መፅሀፍ እናንብብ
✍✍✍ By Aman
??? ?
?♦️የምትወደውን ሰዉ ስታይ
?ፈገግ በል እንደምትወደው ይረዳል
?
?♦️ጠላትህንም ስታገኝ ፈገግ
?በል ጥንካሬህን ይመለከታል
? ???
?♦️ጥሎህ የሄደን ሰዉ ስታገኝም
?ፈገግ በል ፀፀት ይሰማዋል
?
?♦️የማታቀዉንም ሰዉ ስታገኝ
?ፈገግ በል ሰላም ያስገኝሀል
❤️ @sitriiiyelbe ❤️
???????????
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc